Friday, August 3, 2012

የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን እና የማቅ ምልምሎችየእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን እና የማቅ ምልምሎች

Click here to read in PDF:
(ሐምሌ 27 2004 ዓ.ም.፣ ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com)ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ከሚነሱ ጥያቄዎች አንዱ  ለምን የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ሰዎች በአባልነት ይመለምላል? ከነተገለጠው የስነ ምግባር ጉድለታቸው ለተልዕኮ ያሰማራል? የሚል ነው። በየቤተክርስቲያኑ የሚመለምላቸው አባላቱ ያልተዉትና ሊተዉት የማይፈልጉት አንዲያውም ማኅበረ ቅዱሳን ሲገቡ እንደ መልካም ነገር በሚጸድቅላቸው ነውሮች የተሞሉ ናቸው። በተለይም ሁከትና ረብሻን በሚመለከት ረገድ በአስፈጻሚነት የሚመለመሉት ሰዎች ከሜዳ ተሰብስበው እዛው ሜዳ ላይ “መንፈሳዊ ሽብርን” መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ተገቢ የሚያደርግ  ትምህርት ተሰጥቷቸው ለኃይማኖታችሁ በስጋ አሰራር ተጋደሉ የሚለውን መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀውን የማቅ ወንጌል የተቀበሉ ናቸው።
እነዚህ ሰዎች ስለ ሃይማኖት ለመሞት ሳይሆን ለመግደል እና የቤተክርስቲያን ልጆችን ከየአጥቢያው ለማሳደድ ከየጫት ቤቱና ከየመሸታ ቤቱ ተሯሩጠው የሚመጡ መንፈሳዊነት መደባበደብ ሳይሆን ራስን በእግዚአብሔር ቃል መቀደስ መሆኑ ያልገባቸው ሰዎች ናቸው። አንደነዚህ ያሉ ሰዎች  ማኅበረ ቅድሳን ለአድማ ለረብሻ የሚመለምላቸው ምንም የወንጌል ግንዛቤ የሌላቸው፣ በግል ስነምግባራቸው ግን አሳፋሪ የሆኑ ሰዎችን በየቤተክርሰቲያኑ አሉ። እነርሱም ተለወጡ ሳይሆን አሳዱ ደብድቡ የሚል ለስጋ ጠባይ በሚመች “ማኅበረ ቅዱሳናዊ መንፈሳዊነት” ስለተያዙ ለማቅ  አላማ መጠቀሚያነት በቀላሉ ሰለባ ሆነዋል።  

ማህበረ ቅዱሳን  “ሃይማኖት እንጂ ስነምግባር ችግር የለውም” በሚል ሰበካው ከመለመላቸው ሰዎች መካከል በደብረ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው በስተርጅና እንደ ህጻን ልጅ ጣቱን እየጠባ ከሰንበት ትምህርት ቤት አልወጣም ያለው ዲያቆን ዮናስ መኮንን አንዱ ነው፡፡ ይህ ግለሰብ በአካባቢው ቅፅል መጠሪያ ስሙ “አስጭር” የሚል ሲሆን ከ6 ያላነሱ የሴት ጓደኞች እንደነበሩት ሲታወቅ በቃኝ ብሎ በዚሁ ደብር አሁን ኦነግ ሆነው አሜሪካ የኮበለሉት አቡነ ኤዎስጣጢዎስ ስርዓተ ተክሊል አድርገውለት ጋብቻውን የዛሬ 4 ዓመት ፈጽሞ ነበር፡፡
በቃኝ ስላለ የበቃው መስሏቸው ብዙ ምእመናን አምነውት የነበረ እና ተለወጠ የሚል ደስታ የተሰማቸው ቢሆንም እሱ ግን ከአሜሪካ መጥታ ሰው መስሏት ያገባችው ሚስቱ እግሯ አዲስ አበባን እንደለቀቀ እብድ ቢጨምት እኩል ቀን ነው እንደሚባለው ወደ ቀድሞ ግብሩ ተመለሰ፡፡ ምነው ቢሉ ሃይማኖት እንጂ ስነ ምግባር ችግር የለውም እና የሚል ምላሽ ይገኛል። ከመንፈሳዊነት መገለጫዎች አንዱ መልካም ስነ ምግባር መሆኑን የረሳው የማቅ ምልምል “ወታደር” የሆነው ዮናስ ለሀይማኖቴ ከኔ ወዲያ ለአሳር የሚል ሲሆን ሃይማኖት ኑሮ እንጂ ፕሮፓጋንዳ አለመሆኑ ያልገባው ሰው ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ለቅድስናቸው የሚጠነቀቁ ማስተዋል የሞላቸው አንዳንድ የዋህና ትሁታን አባላት እንዳሉ ሁሉ እንደእነዚህ አይነቶችም ጋጠወጦችም ሞልተዋል። የማቅ አመራሮች ማንን ለምን ተግባር እንደሚያሰልፉ ስለሚያውቁ ሁሉንም አንተ ባትኖር ቤተክርስቲያን ትጠፋ ነበር እያሉ ይይዙዋቸዋል።
እንደ ዮናስ ያሉ የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው ሰዎች ለአመጽ እንቅስቃሴ እንጂ ለመልካም ነገር አይታዘዙም። በገዛ ነፍሱ ላይ ያመጸ ሰው በሌላ ሰው ላይ አመጽ ቢፈጽም አይገርምም ዮናስም በዝሙት መንፈስ ተመቶ በራሱ ላይ አመጸኛ ስለሆነ ትዳሩን እስከማጣት የደረሰ ዋጋ ከፍሎበታል።
በቅርቡ ደግሞ ከዚህ ከገባበት የዝሙት አስር ነጻ እንዲወጣ አልመከር ብሎ ያስቸገረው ዮናስን በሚመለከት  የአካባቢውን (የአጥቢያውን) ሕዝብ ያወከ ወሬ ተሠማ። ይህም ሚስቱ ሰዶማዊት መሆኗ እና ከዲያቆን ዮናስ ጋር ፍቺ መፈጸሟ ነው፡፡ ይህንን ወሬ ያመጣው አሁን መኖሪያውን አሜሪካ ያደረገ አብሮ አደግ ጓደኛውና የማኅበረቅዱሳን አባል ቀሲስ ፍቅረኢየሱስ ጋረደው  ሲሆን በቅርቡ መጥቶ ይህንኑ እውነት ገልጿል።  ዲያቆን ዮናስ መኮንን ካገባ በኋላ ያልለቀቀው ሴሰኝነቱ ለዚህ ምስቅልቅል ለወጣ ሕይወት ዳርጎታል፡፡ አግብቶ አሜሪካ ለመሔድ የነበረው እቅዱ በዚህ መልክ ከሽፏል፡፡
ይህ ዲያቆን በወንጌል ሕይወት ኖሮ ንስሐ መግባት ሲገባው ፀረ ወንጌል አቋም በመያዝ በደብሩ ሰ/ት/ቤትና በደብሩ ስብከተ ወንጌል የሚካሄደውን አገልግሎት በማደናቀፍ በወንጌል ያረፈውን ሕዝብ በመበተን፣ የሠንበት ት/ቤት ወጣቶችን ተሃድሶ ናቸው በሚል ስም አጥፊነት ተሰልፎ የነበረ ግለሰብ ነው፡፡
እድሜው 40 ዓመት አልፎ እንኳ በእድሜ እጅግ ከሚያንሱት ምናልባትም ቢወልዳቸው ከሚያደርሳቸው ልጆች ጋር ግብግብ በመግጠም የማቅ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት ወንድሙን “የቀጨኔ ልጅ እንዴት ታገባለህ” በማለት ሰላም ነስቶት አላስቀምጥ ስላለው ወንድምየው በብስጭት የሞተ ሲሆን ይህም በነዋሪው ሕዝብ “ክርስትና እንደነ እገሌ ከሆነ በአፍንጫዬ ይውጣ” አስብሎ ነበር፡፡ ባህልን እንጂ የሚለውጥ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሰው ሰውን በአካባቢ ከመፈረጅ ነጻ አይወጣም እና ዮናስም ቀጨኔ እንደዚህ….. ከሚል የአስተሳሰብ እስር ነጻ አለመውጣቱ አያስገርምም።
በተመሳሳይ ሁኔታ የደብሩ ሰ/ት/ቤት ዋና ሰብሳቢና የማቅ አባል አቶ መንክር ግርማ የተባለ አባቱ በአካባቢው የታወቁ በጥንቆላ የሚተዳደሩ ሲሆን ይህ ግለሰብ ከዚህ ከዚህ በፊት ኮስትኔት በተባለ አታላይ “ቢዝነስ” ውስጥ በመዘፈቅ ከዛ በሰበሰበው ገንዘብ ትዳር የመሰረተ ሲሆን ይህንን ግለሰብ ማቅ የአላማው ማስፈጸሚያ በማድረግ ከቤተክርስቲያን አላማና ከመመሪያ ውጭ በመውጣት ደብሩን ሳያስፈቅድ የራሱ ማህተም አስቀርጾ ቡድን በማደራጀት በህገ ወጥ መንገድ የሰንበት ት/ቤቱን ስም ተተግኖ ማህበራትን በደብዳቤ ጠርቶ ረብሻ በማስነሳት ስራ ተደርሶበት በደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ለቅዱስ ፓትርያርኩ የገባ ደብዳቤ ተጽፎባቸዋል፡፡
እንግዲህ ዲያቆን ዮናስ ሚስቱ በአሳፋሪ ሁኔታ ውስጥ መግባት እና ትዳሩን ማጣት የአቶ መንክር ግርማ በማቅ  ፖለቲካዊ አጀንዳ ተጠምዶ የሚታይ ስጋዊ አድልዎ ማድረግ እና በኩዌስት ብር ትዳር መመስረት አብሮ አመራር የሆነው ጓደኛው አቶ ሔኖክ በተመሳሳይ ሁኔታ ኩዌስት በቤተክርስቲያን ልጅነቱ የሚያምኑትን ሰዎች በማታለል ሕገወጥነቱ ወደ ተረጋገጠው ኩዌስት በማስገባት የግል ጥቅምን በማጋባስ ተግባር ላይ ተሰማርተው በርካታ ሰዎች በቤተ ክረስቲያን ልጆች ምክንያት በከሰሩት ገንዘብ እያዘኑ ሃይማኖታቸውን እስኪጠራጠሩ ድረስ ለመድረሳቸው አንዳንዶቹም ቤተክርስቲያን መምጣት ለማቆማቸው ምክንያት ሆነው ሳለ የሰበሩትን ለመጠገን እንደመሯሯጥ ሌሎችን ተሃድሶ ጴንጤ እያሉ ማሳደድን ቀጥለውበታል፡፡ አሁንም ለነዚህ ሰዎች የሚበጃቸው ራስን በንስሐ አድሶ ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን እና ለእግዚአብሔር መመቸት ነው፡፡  

2 comments:

  1. Yet Yalew Egiziabher New ? Kesis Fikire Eyesus Malet America KIntaki Gebreil Yalew New ?
    Kesis Fikire Eyesus Yetebale Kintaki St Gebreil Mahibere Kidusan Ale Lenegeru Abune Abirham Selay Adirgew Ohayo Kolomibos Kesis Yared G Medihin Gar Medibewit Nebere Kesis Yared G.Medihin Gin Yeteshale Kahin silemayifelg Abarerew Kisis Fikire Eyesus Malet Melk- Kumet-Moya Yelelew .Yemengisit Seratega Yenebere New

    ReplyDelete
  2. good job guys i know yonas when i was that church he loves females. He addicted in adultery but he oppose gospel.he looks like christian but fake

    ReplyDelete