Wednesday, June 27, 2012

ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ከቀረበባቸው የስም ማጥፋት ክስ ነጻ መሆናቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ!


ምንጭ፤ የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ

መምህር አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል (ቆሞስ) ከሳሹ በአግባቡ በማይታወቅ መልኩ የቀረበባቸውን የስም ማጥፋት ክስ በጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስለቀረበ ቅዱስ ሲኖዶስም በወቅቱ የክሱን እውነተኝነት ለማጣራት ኮሚቴ እንዲቋቋም መወሰኑ ይታወቃል።

የተቋቋመው ኮሚቴም የተባለው ነገር እውነት ወይም ውሸት እንደሆነ በአግባቡ አጣርቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ በተደጋጋሚ የክሱ ባለቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ጥሪ ቢያቀርብም የዚህ ክስ ባለቤት እኔ ነኝ ባይ ስለጠፋ የቀረበውን የሐሰት ክስ ወደ ሊቃውንት ተልኮ ሊቃውንቱ ነገሩን አጣርተውና ቃላቸውን ተቀብለው (በአካል ጠይቀው) የደረሱበትን እውነት ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ በታዘዙት መሠረት ጽሑፉን በሚገባ አጣርተው አለ የተባለውን መረጃና ማስረጃ አገናዝበው በተከሰሱበት ሁኔታ አቋማቸውን ጠይቀው ካጠናቀቁ በኋላ ከቀረበባቸው የሐሰት ውንጀላ ነጻ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርበው እልባት አግኝቷል።


በመሆኑም ከጉባኤው ፍጻሜ ማግስት ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በጥቅምት ወር 2004 . ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቀረበብኝ የስም ማጥፋት ክስ አጣሪ ኮሚቴ ተሰይሞ በማጣራት ነጻ ስላደረገኝ የማስረጃ ወረቀት እንዲሰጠኝ ብለው ለቅዱስ ፓትርያርኩ አመልክተው ስለተፈቀደላቸው የቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት ነጻ እንደሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ መስጠቱን ይፋ አድርጎአል፡፡ ይህንን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣቸው ማስረጃ ከዚህ ቀጥለን አቅርበነዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት ነጻ እንደሆኑ የሚገልጽ ማስረጃእዚህ ይጫኑ ]

መምህር አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል (ቆሞስ)አቋማቸውን ተጠይቀው የሰጡት መልስ[እዚህ ይጫኑ]

 

3 comments:

  1. እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋልና እናንተም ዝም ትላላችሁ፡ ዘፀዓ ም 14 ቁ 14 ። የእውነት አምላክ ስሙ ይመስገን። እግዚአብሔር ታላቅ ነው። ይህ ሁሉ ክስ ያመጣው የማቅ ገንዘብ ኦዲት ይደረግ በማለታቸው ነበር መናፍቅ ያሰኛቸው። ወየጉደ እንድህ ብሎ ማቅ ጉደኛ ማህበር እውነት ዉጦ ሀሰትን የምተፋ ማህበር ነው። ገና ብዙ ጉደ አለ። የእግዚአብሐር ሀይል አሁን ያሸንፋል።ዐውደ ምህረቶች በረቱ ተበራቱ እውነቱን ከማውጣት ዝም አትበሉ።

    ReplyDelete
  2. ድሮም የጨለማ ሥራ ብርሃን ሲበራበት ድራሹ ነው የሚጠፋውና ገናና ምኑ ታይቶ ታሪክ ይፈጠራል::ምነው እንደ አባ ቆሞስ ሰረቀ ብርሃን ዓይነት አንድ ሁለት ሶስት ሰዎች ቢኖሩ እዚያ መንበረፓትርያርክ አካባቢ?አባ ሰረቀን እንኳን ደስ ያለዎት በሉልን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ስለሰማ እናመሰግናዋለን!እናንተም ዐውደ ምህረቶችም በርቱ ቸር ወሬ አሰሙን!ወዮላቸው ማቆች!!
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  3. aye yezeh midir Ewnet Ewnetes amlakena fetari hulun seri getachen amlakachen medhanitachhen Eyesus christos new, yihema ye wushet mender new, gedelachehum sekoy segebachehu min eyetesera endehone yigebachewal bicha amlakachen haymanotachenen, betechristyanachenen ena agerachen Ethiopianena Hizbuan Yitebeklen, hulachenenem Lib yisten

    ReplyDelete