Monday, June 25, 2012

የሰለፊያው ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ላይ ያሴረው ሴራ ተጋለጠ!!

Click here to read in PDF
በከላይነው ትዕዛዙ
ሰሞኑን ጉባኤ አርድዕት የሚባል ማኅበር ተቋቋመ ከሚለው ዜና ከተሰማ ጀምሮ ማኅበሯ ከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቃለች። ከዚህም የተነሳ ይህን ማኅበር አቋቁመዋል እና የማህበሩ ደጋፊ የመሆን ዕድል አላቸው የሚሉትን ሰው ሁሉ ከጠቅላይ ቤተክህነት የስልጣን መዋቅር ለማንሳት ቆርጠው ተነስዋል።
ለዚህም የተከተሉት እስትራቴጂ ለማኅበሯ ድጋፍ የሚሰጡ የቤተክህነት ሰራተኞችን ተጠቅሞ ዝውውር ማድረግና ሊፈጠር ይችላል ብለው የሚጠረጥሩትን አንድነት ማላላት ነው። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ የማኅበሩ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ብዙ ጊዜያቶችን የሚያጠፉት በእስክንድር ገብረክርስቶስና የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ በሆነው በአቶ ተስፋዬ ውብሸት ቢሮ ውስጥ እንደሆነ የቤተክህነት ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ተስፋዬ ጠንቃቃና ከማኅበሩ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲታወቅበት የማይፈልግ ሰው ሲሆን አስክንድር ግን ባለው ከፍተኛ የንዋይ ፍቅር ለማኅበሩ ያለ ይሉኝታ ሙሉ በሙሉ መገዛት የጀመረ ሰው ነው።
ማኅበሩ ከመታው ድንጋጤ ለመረጋጋትና ከገባበትም ማጥ ለመውጣት የተለያዩ ሥልቶችን  እያውጠነጠነ ቢሆንም ብዙዎቹ ዘዴዎቹ ፈር ሊይዙለት አልቻለም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በጠቅላይ ቤተክህነት እየታየ ያለውን ነገር ስንመለከት ማኅበሯ ከከበባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ነጻ ለመውጣት ካሳባቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን እንረዳለን። ጤናማ አእምሮ ሊያስብ የሚገባውን ነገር ከማሰብ ይልቅ የተለያዩ ተንኮሎችንን የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን በሽብር ብሎጎቹ እየከፈተ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ገና ለገና ጠንካራ ማኅበር ተቋቁሞ ቤተክርስቲያኒቱን ለብቻችን የማስተዳደር ፍላጎታችንን ይጋፋብናል። እየተቆጣጠርነው የመጣነውን የቤተክሀነቱን አስተዳደር ከቁጥትራችን ውጭ ያደርግብናል። በሚል ከወዲሁ በጉባኤ አርድዕትና በመስራች አባላቱ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቷል። 

ከማኅበረ ቅዱሳን በተለየ መንገድ ቤተክርስቲያን በሰጠቻቸው የስራ ኃላፊነት በታማኝነትና በቅንነት እያገለገሉ ያሉትን እነ ሊቀስዩማን ኃይለጊዮርጊስና መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤልን የመሳሰሉ የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች ቀድሞ መጮህ በሚል መርህ አንዲህ እና እንዲያ ናቸው በማለት ስማቸውን በማጥፋት ላይ ይገኛል። ቤተክርስቲያኒቱ ባሏት ሶስት መንፈሳዊ ኮሌጆች ትምህርቱን በብቃት ተከታትሎ የእውቀት ገንቦ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረው መምህር አእመረንም በስጋ እውቀት ከነሱ እንደማያንስ በመንፈሳዊ እውቀት ደግሞ ከእግሩ ጣት ጋር እንኳ መድረስ እንደማይችሉ እየገባቸውም ቢሆን በተለመደው እኔን ያልተቀበለ ሁሉ መናፍቅ ነው በሚል አሸባሪ መንፈሳቸው ተመርተው ስሙን ማብጠልጠል ይዘዋል። ቅዱስነታቸው አቡነ ጳውሎስን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ስማቸውን ማብጠልጠልን ሥራዬ ብለው የያዙት የማኅበረ ቅዱሳን የሽምቅ ውጊያ ብሎጎች ገና ለገና ጉባኤ አርድዕት እንዲቋቋም ፈቅደዋል በማለት ስማቸውን በክፉ በማንሳትና ተግባራቸውን በማኮሰስ የተቀናጀ ዘመቻ መክፈታቸውም አስገርሞዋል። እንዲያውም የጊዜው ማስፈራሪያ እርስዎን አንስተን አባ ህዝቅኤልን እንሾማለን የሚል ሆኗል።
እንደተለመደው በኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ እና በአቶ ማንያዘዋል አበበ አማካኝነት የሚመራ የስለላ ሥራዎች በቤተክህነት ውስጥ እያካሄደ ያለው ማቅ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ አቶ ሰሎሞን ቶልቻ በሚባል ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ለአቶ እስክንድር ገ/ክርስቶስ 30 ሺህ ብር በመክፈል በንቡረዕድ አባ ገብረማረያም ምትክ የገዳማት መምሪያ ኃላፊ ሆኖ በቤተክህነት የስልጣን ተዋረድ ላይ አለሁ ያለውን ግለሰብ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ እንደሚታወቀው የገዳማትን ጉዳይ መያዝ ያለበት በገዳም ኑሮ በሚያውቁ መነኮሳት ነው። በዚህም መሰረት በመነኩሴ ሲመራ የቆየውን መምሪያ በአሁኑ ሰዓት የአጥቢያ  ቤተክርስቲያን ሰባኪ ለሆነ ግለሰብ ያለምንም ውድድር መሰጠቱ ሁሉም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች ያዘኑበት ጉዳይ ሆኗል፡፡
ለአቶ ሰሎሞን ቶልቻ እዚህ መድረስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገለት ያለው ግለሰብ በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም በመባል የሚታወቀው አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ ነው፡፡ አቶ እስክንድር ከ12ኛ ክፍል በላይ ምንም ዓይነት የትምህርት ማስረጃ የሌለው፣ የቤተክህነት ትምህርትም ሆነ ክህነት የሌለው፣ አዲስ አበባ ተወልዶ አዲስ አበባ ያደገ በቤተክህነቱ ቋንቋ ጨዋ የሚባል ሰው ከመሆኑም በላይ ምንም ዓይነት ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር የሌለውና የአባቶችን ክብር እጠብቃለሁ በማለት ሥራውን በገንዘብ የሚለውጥ፣ እና  በፓለቲካው አለምም በትግል ህይወት የኖርሁ ታጋይና የኢህአዲግ መስራች ነኝ ለማለት የሚቃጣው ሰው ነው፡፡
 ይህ ሰው ከቀበሌ ሊቀመንበርነት በግምገማ ተባሮ መውጣቱን (በሙስና ቅሌትና አቅም ማነስ) ምንጮችቻችን ሲገልጡ ወደ ቤተክህነት በመምጣት ባለቤቴ ማኅሌት የቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ስለሆነች እኔም ከእርሷ የሪፖርተርነት ሙያ ሰልጥኛለሁ ብሎ ከባለቤቱ ማህሌት በተሰጠው ሰርተፍኬት የዜና ቤተክርስቲያን ሪፖርተር ሁኖ ተቀጠረ፡፡ ይህ ግለሰብ በዜና ቤተክርስቲያን የሚወጡ ጽሑፎችን ለመጻፍ የሚያስችል ዕውቀት እንደሌለው ከሊቃውንቱ በተደጋጋሚ ተገልጾለት “…በተቻለ መጠን የቤተክህነቱም ይሁን የዘመናዊ ትምህርት ስለሌለህ ወደ ቀበሌህ ብትመለስ ያለበለዚያም እንደአቅምህ በሆነ ሥራ ተቀጥረህ ቤተክህነት ብትሰራ ተብሎ ይመከራል፡፡…” እስክንድርም ወደ ፓትርያርኩ በአቡነ ፊሊጶስ አማካኝነት ከቀረበ በኋላ “…ከመንግስት ጋር ባለኝ ግንኙነት የዋልድባን ጉዳይ(ገጽታ) እኔ አስተካክለዋለሁ። ስለዚህ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለጊዜውም እንኳን ብሆን..” ብሎ በአማላጅ ያግባባል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም ይህ መምሪያ ሙያ ስለሚጠይቅ የመምሪያ ኃላፊው አቶ ስታሊን (በጋዜጠኝነት ሙያ የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው) ክትትልና ቁጥጥር ሳይለየው ተጠሪነቱ ለአቶ ስታሊን ሁኖ ለጊዜው ይመደብ ብለው ሲስማሙ በብፅዕ አቡነ ፊሊጶስ ፊርማ ተመደበ፡፡
አቶ እስክንድር በዋልድባ ጉዳይ እንኳን ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃ ሊሰጥ ቀርቶ በዋልድባ ምክንያት በማኅበሩና በቤተክህነት መካከል ትልቅ መቃቃር የፈጠረ ሥራ ሠርቶ በመመለሱ ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹ሙያ አልባ የቤተክርስቲያን ባለሥልጣኖች›› በማለት በነአቶ እስክንድር ላይ አስገራሚ ጽሁፍ አስነበበን፡፡
እንግዲህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በጊዜያዊነት የተሰጠውን የመምሪያ ኃላፊነት እንዳይነጠቅ ከፍተኛ ሩጫ ማድረግ የጀመረው፡፡ ሩጫው አቅጣጫ አልባ ቢመስልም ተንኮል ግን አላጣውም። ስለዚህ በቀጥተኛ መንገድ በችሎታው ስራውን መቀጠል ካልቻለ በማኅበሩ በኩል ሆና ስልጣኑ ላይ ለመቆየት የግድ ከማኅበሩ ጋር ተግባብቶ ለማኅበሩ ታዞ በዚህም ከማኅበሩ የሚገኘውን ጥቅማ ትቅም ተቋድሶ መኖርን መረጠ። በዚህም ምክንያት የተለያየ እኩይ ተግባራትን ማድረግ ቀጠለበት፡፡ ለምሳሌ፡-
1ኛ. በጠቅላይ ቤተክህነት የሚገኙ ሊቃውንትን የተለያየ ስም በመሥጠት በጡረታና በዝውውር እንዲዛወሩ አቡነ ፊሊጶስንና አቶ ተስፋዬን (ም/ሥራ አስኪያጅ) በማግባባት በርካታ ሰዎች ተዛዋውዋል ወይም ጡረታ ወጥተዋል፡፡
2ኛ ወደ ፓትርያርኩ እና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በመቅረብ ከፊታቸው የውሸት ስልክ በመነጋገር አሁን የደወለልኝ አቶ አባይ ፀኃዬ ነው፣ አቶ መረሳ ነው፣ አለቃ ፀጋዬ ነው፣ ዶ/ር ሸፈራው ነው በማለት በአባቶች ዋነኛ ታጋይ መስሎ በመታየት ስለኢህአዲግ አቅጣጫ በውሸት ለማስረዳት ይሞክራል፡፡ (ይህ ሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማኅበሩ ጋር በመሠረተው ግንኙነት አማካኝነት 250,000 ብር  ተቀብሎአል፡፡ ለወደፊት ከመረጃ ጋር ይቀርባል፡፡) ለማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችም መንግስት ምንም አያደርጋችሁም፣ ስለናንተ በሚገባ አስረድተነዋል፤ በማለት ቢናገርም በአሁኑ ሰዓት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አቶ እስክንድር የሚባል ሰው እንደማያውቁ፣ በመንግስት ስም መነገድ እንደማይችል እና ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ ለፓትርያርኩና ለአራት ሊቃነ ጳጳሳት እንደተገለጸላቸውም ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡
3ኛ. የዜና ቤተክርስቲያን መምሪያ ኃላፊ እኔ ነኝ፣ አቡነ ጳውሎስ መጋቢ ሚስጢር ወልደሩፋኤልንና መ/ር ካህሳይ (የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጆች) ተቆጣጠር ብለውኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ይህንን እድል በመጠቀም የማኅበሩን ገጽታ በዜና ቤተክርስቲን እናስተካክለዋለን እያለ ለማኅበሩ ሥራ አመራር ገልጿል፡፡ ከዚህም አልፎ እምቢ ቢል ግን ወልደሩፋኤልን እናባርረዋለን በማለት ከማኅበሩ ጋር እንደሚዶልት መረጃ ተገኝቷል፡፡ ይህንን በተመለከተም ስለአፈጻጸሙ ከሰሎሞን ቶልቻ ጋር ተነጋገሩበት እንዳላቸው ታውቋል፡፡
4ኛ.  እንዲሁም በዋነኛነት በአሁኑ ሰዓት ለማኅበሩ ህልውና አደጋ በመሆን ላይ ባለው በሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ አማካኝነት እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ማለትም ‹‹በሊቃውንቱ መካከል አንድነትን መፍጠር እንዲሁም በጳጳሳት መካከል ስለማኅበሩ በቂ ግንዛቤ እንዲኖር ማድረግ ›› የሚሉ ሥራዎች እንዳሉ የሚያውቀው የማኅበሯ አመራር የሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ አካሄድ የፈጠረበትን ሥጋት ለአቶ እስክንድር ያዋያል፡፡ አቶ እስክንድርም “…የኃይለጊዮርጊስንና የሊቃውንቱን እቅዶች አፈራርሳለሁ፡፡ እሱንም ከአባቶች ጋር እና ከሊቃውንቱ እንለያይዋለን ይህንን ደግሞ ከአቶ ተስፋዬ ውብሸት ጋር ተነጋግረናል…” በማለት ለማኅበሯ አመራሮች የማጽናኛ ቃል ከተናገረ በኋላ በማግስቱም፤
- ለፓትርያርኩና ለተለያዩ ጳጳሳት እየዞረ “…ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ  ከመንግስት ጋር ስር የሰደደ ግጭት ውስጥ ነው፣ መንግስት ይፈልገዋል፣ በዘረኝነት ከነአቡነ አብርሃም ጋር ይገናኛል፣ የማኅበሩ አመራርም ጓደኞቹ ናቸው በማለት ያሥወራል፡፡ አባቶችም አይ እስክንድር ይህ እኮ ‹‹የህዝብ ግንኙነት ሥራ ሳይሆን ህዝብ ማደናገር›› ነው በማለት ከመለሱለት በኋላ “…ሊቀሥዩማን በኛ በኩል ከ15 ዓመታት በላይ በተለያዩ ኃላፊነት አይተነዋል፣ ለኃይለጊዮርጊስ እንደ ሐዋርያት ዘር የለውም፣ ከማኅበሩ ጋርም ቢሆን ለ15 ዓመታት እንደታገለ ማኅበሩም በደጀሰላም ድህረ-ገጽ ገልጾታል፡፡ ሊቃውንቱም እጅግ የሚያከብሩትና የሚወዱት ወንድማቸው ነው፡፡ በሄደበት ሁሉ በጥንቃቄ ሥራ የሚሠራ ከማንም ጋር በአላማ ካልሆነ በቀር በግሉ የማይጣላ፣ የተናገረውን ለመሥራት ቀንና ማታ የማያግደው መሆኑን ሊቃውንቱ ሁሉ ይስማማሉ፡፡ በል ከዚህ በኋላ እንዲህ ያለ ሥራ አትስራ ከአሁን በኃላም  የምትሠጠንን መረጃ ዝም ብለን አንቀበልህም። ይህ ውንጀላህ የምትሰራውን ሥራ በጥንቃቄ እንድንከታተል ያደርገናል” በማለት የመለሱለት ሲሆን ከማኅበሩ የጎረሰው ገንዘብ ከጉሮሮው ሳይወርድ በሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ ላይ ያቀደው ሴራ ከሽፏል፡፡ በመቀጠል እስክንድር ለተዛወሩ እና ጡረታ ለወጡ ሠራተኞች እየዞረ ከፓትሪያርኩ እና ከአቡነ ፊሊጶስ ጋር ባለው ግንኙነት ይህንን ያደረገው ኃይለጊዮርጊስ ነው በማለት ለማሳደም ከፍተኛ ጥረት አድርጎ የነበረ ሲሆን ይህም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡
ባለ ብሩህ ልቦናው ኃይለጊዮርጊስም ይህንን ወሬ መበታተን የሚቻለው ሊቃውንቱን እና የሥራ ኃላፊዎችን ግንዛቤ በመስጠት ነው በማለት ሁላችንንም ከሠበሰበን በኋላ በቂ ውይይት ተደርጎ አሁን ማኅበሩን ገና በምስረታው እያንቀጠቀጠ ያለውን ‹‹ጉባዔ አርድዕት ዘኦርቶዶክስ›› ይመሠርታል፡፡ ሊቃውንቱም ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ ከአውሮፓና አሜሪካ አህጉረ ስብከት፣ ከአዲስ አበባና ሌሎች አህጉረ ስብከት፣ ከሦስቱ መንፈሳዊ ኮሌጆችና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከቤተክርስቲያኗ ልማት ተቋማት የተወጣጡ ናቸው፡፡ ማንንም ማኅበር ይሁን የግለሰብ ሀሳብ ሳንደግፍ እንደ 72ቱ አርድዕት የሲኖዶስ አባላትን (የሐዋርያትን ምትክ) የሆኑትን ብፁአን አባቶችን በማገዝ ለአንድ ቤተክርስቲያን መሥራት፣ ለገንዘብና ለሥልጣን እንዲሁም ለዘር አለመደለል በሚል ተዋቅረው መሥራታቸው ያሥደነገጠው ማቅ በእነ እስክንድር አማካኝነት  ጉባዔ አርድዕት ዘኦርቶዶክስን ለማፈራረሥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ለዚህ እንዲረዳው የተለያዩ ፕሮፓ ጋንዳዎችንም የጀመረ ሲሆን ፡፡ ለምሳሌም፡-
1.     “የአቡነ ጳውሎስ ደጋፊዎች ናቸው እየተባሉ ናቸው፡፡” በማለት ጉባኤውን ከአቡነ ጳውሎስ ለመለየት እየሞከረ ነበር፡፡ አርድዕቱም “…እኛን የሠበሰበን ይህችን ቤተክርስቲያን ከአባቶቻችን ጋር በመሆን ለመጠበቅ እንደአርድዕቱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አቡነ ጳውሎስ አይደሉም፡፡ ይሁን እንጂ ዓላማችን አርድዕቱ በእውነትና በመንፈስ አምላካቸውንና ሐዋርያትን እንዳገለገሉ እኛም ብፅአን አባቶቻችንን እና ቅዱስ ፓትርያርካችንን በፍቅር መታዘዝ እና ቅዱስ የሆነውን ጌታ እግዚአብሔርን ማገልገል ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሌላ ማኅበርም ይሁን በገንዘብ የሚገዛን አካል አንፈልግም…” ብለው በበዓለ ሃምሣ የመሠረታቸውን መንፈስ ቅዱስ አመስግነዋል፡፡
2.    ማቅና እስክንድር በተለመደው ወራዳ ባህሪያቸውና በሸረቡት ደባ የጉባኤውን መሥራች አባላት ዘረኛ፣ ተሃድሶ አራማጅ፣  የመንግሥት ተላላኪ በማለት የተለመደውን እና ከአመት አመት የማይቀየረውን የክስ ዘመቻ ቢከፍቱም ‹‹ሐዋርያትንና አርድእቱን ያጸና መንፈስ ቅዱስ ያጸናናል፡፡ ተሳስተንም ከሆነ ወደ ቀና መንገድ ይመራናል ነገር ግን ይህ ሥድብ አስቀድሞ ለደቀመዛሙርቱ የተሰጠ እኛም በዚህ ዘመን ለበረከት የተቀበልነው ስለሆነ በፍቅርና በአኮቴት እንለፈው..›› የሚል ውይይት በጠንካራ መንፈስ ማድረጋቸውንና ልበ ሙሉነታቸውን የሠሙ ሌሎች ሊቃውንት በብዛት እየተቀላቀሏቸው ይገኛሉ፡፡
3.    በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የሥልጣን ድልድል በመሥራት “ የማኅበሩን መስራች አባላት ዝውውር ለማድረግ ከአቡነ ፊሊጶስና ከፓትርያርኩ ጋር ጨርሰናል፡፡ ልናባርራችሁ ነው። በዚህ መንገድ አስደንግጠን የጉባኤውን አላማ እናኮላሻለን።…” በማለት  የየመምሪያው ኃላፊዎችን እየጠሩ ማኅበረ ቅዱሳን ያለውን ክንድ እንዲያውቁና ሀሳባቸውን ከጉባኤው እንዲለዩ በአቶ ተስፋዬና በእስክንድር አማካኝነት የተጠንቀቁ መልእክት እየተነገራቸው ይገኛል፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳንም እንዲህ ያለ ሥራ እየሰራን ነው ሥራችንን እስክንጨርስ ነገሩን በሚሥጢር ያዙት ለእናንተ የምንነግራችሁ እየሰራን ያለውን ሥራ እንድታውቁልንና ሥራችንን እስክንጨርስ በትእግስት እንድትጠብቁን ነው።…” በማለት በመልዕክት አድራሹ በአቶ ሰሎሞን ቶልቻ አማካኝነትና ተነግሯቸዋል፡፡ ለአርድእቱም የታቀደው ነገር ምን እንደሆነ በቀላሉ የሚያውቁበትን መንገድ ያመቻቸ እግዚአብሔር ይመስገንና የታቀደባቸውንና በሚሥጢር እንዲያዝ ተነግሮ የነበረው እውነት ደርሰውበታል።
ከሞላ ጎደል አስክንድርና ተስፋዬ ከማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ጋር በመሆን ጉባኤውን ለመበታተን ያወጡት እቅድ ይህን ይመስላል፡-
  • የንቡረዕድ ኤልያስ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሥራ አስኪያጅነት ለሊቀ-ማዕምራን ፋንታሁን ሙጨ እንደሚሰጥ
  • የሊቁ እና በመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ዘንድ ተንቀሳቃሽ መጽሐፍ ቤት ተብሎ የሚታወቀው የመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል የቅርስና የመዘክር መምሪያ ኃላፊነት ለሰሎሞን ቶልቻ እንደሚሰጥ
  • በቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት ይህ ቀረህ የማይባለው የልበ ሙሉው የመጋቢ ብሉይ አእመረ አሸብር የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊነት ለሳሙኤል ሮቶ እንደሚሰጥ
  • v የመ/ር እንቁባህሪይ የሰ/ት/ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ኃላፊነት  ለሃይሉ ጉተታ እንደሚሰጥ
  • v የገዳማት መምሪያም ለአባህሩይ (የቀድሞው ስ/ት/ቤት መምሪያ ኃላፊ) እንደሚሰጥ
  •  የአባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙኤል የትምህርትና ሥልጠና መምሪ ኃላፊነት ለመ/ር ደጉ የእኔ አለም (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር) እንደሚሰጥ
  •  የመጋቢ ሥርዓት ዳንኤል ወልደገሪማ ሥልጣን ለኃይለጊዮርጊስ ዳኜ (ቀንደኛው የማቅ ተላላኪ) እንደሚሰጥ
  • ንቡረዕድ ኤልያስ ወደ ቀድሞው የመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን እንደሚመለሱ
  • አባ ሠረቀብርሃን በአዲስ አበባ ሀገረ ሥብከት የካህናት አስተዳደር መምሪያ እንደሚሆኑ
  • መ/ር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ወደ ሰዋሰው ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ሄደው በአቋም የለሹና በማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪነት በሚታወቀው በሳሙኤል ሮቶ ቦታ እንደሚመደብ
  •  መጋቢ ብሉይ አእመረ አሸብር ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዶ/ር አባ ኃይለማርያም ቦታ እንደሚተኩ
  •  ንቡረዕድ ተስፋዬም ወደ አዲስ አበባ አድባራት አለቅነት እንደሚዛወሩ
  • መምህር ብርሃኔን ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ወደ መቀሌው ከሳቴ ብርሃን ኮሌጅ እንደሚዛወሩ እቅድ ወጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል፡፡
እንግዲህ ይህን መረጃ ከእነ እስክንድርና ከነ ተስፋዬ ጋር ተነጋግረንበታል፣ ማኅበረ ቅዱሳንም አዳር ፕሮግራም አድርጎ ተወያይቶበታል፣ ግንዛቤም ለጳጳሳት ተሰጥቷል፣ ተጠንቀቁ፣ ምን አገባን ይቅርብን የምን ‹‹ጉባዔ አርድእት›› ነው፡፡ በቃ!!! እስክንድርና ተስፋዬ መከተል ነው የሚሻለው፡፡ እያሉ እያስወሩ ያሉት ሰሎሞን ቶልቻ፣ ማንያዘዋል አበበ እና ኃይለጊዮርጊስ ዳኜ ናቸው፡፡
ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው እንደሚባለው እንዲህ ጉባኤውን የመሰረቱት ሊቃውንት እንዲሸበሩና ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ ለማድረግ ወሬው በየግላቸው እንዲደርሳቸው ሲደረግ ወሬውን አምኖ ከመሸበር ይልቅ ተገርመው ከተወያዩበት በኋላ “እኛ ለዚህ ክብር ያበቃንን እግዚአብሔርን እንጅ እናንተን አንሰማም ቅዱስነታቸውም ቢሆን ማን፣ ለምን፣ ምን ለማድረግ እንዳሰበ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ለሥልጣናችን ብለን የምናደርገው ምንም አይነት ትግል አይኖርም፡፡  እስክንድር በገንዘብ ተገዝቶ ይሆናል ያለው ሳይሆን እግዚአብሔር ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን ያለውን ብቻ እንደሚሆን ስለምናውቅ ምንም እንኳ በተለያዩ ብሎጎች ክብራችንን የሚነካ ጹሁፎች ቢጻፉም ከአላማችን ግን አንዳች ፍንክች አንልም ምክንያቱም ‹‹ያመንነውን እናውቃለንና››፡፡ ስለሆነም ለብፁአን አባቶቻችንና ለቅዱስ ፓትርያርካችን ያለን ክብርና መታዘዝ ይቀጥላል፡፡ የእስክንድርና የማኅበሩ ቅዠትም ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያበቃል፡፡”  በማለት አቋም ወስደዋል።
እንደ እስክንድር አባባል ከሆነ እሱም ቢሆን ተሯሩጦ ይሔን ነገር ለማሳካት ከተጋ በቅርቡ  የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ እንደሚሆን ተስፋዬ ጠቁሞታል፡፡ ተስፋዬም ቢሆን በዶ/ር አግደው ረዴ ቦታ ኮሚሽነር እንዲሆን ታስቦአል፡፡ በተደጋጋሚ “…ሹመት ለማግኘትና በያዙትም ስራ ለመቀጠል በአሁኑ ሰዓት በቤተክርስቲያናችን አስፈላጊው ነገር ትምህርት አይደለም ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ተግባብቶ መስራት ይበቃል፡፡” በማለት የሚታወቀው ተስፋዬ ለማኅበሩ በሚስጢር በሚሰራው ስራ ኮሚሽነርነቱን እንደማያጣው አምኗል። የእስክንድር ባለቤትም በባለቤቷ አማካኝነት በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ተመድባ በአሁኑ ሰዓት በመካኒሳ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ላይ ፈላጭ ቆራጭ ሁናለች፣ በአሁኑ ሰዓት ብዙ የአዲስ አበባ አድባራት አለቆችም ከ20,000 – 50,000 ብር ለአቶ እስክንድር የተሻለ ቦታ ፍለጋ ለድለላ እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡
እንግዲህ ጠቅላይ ቤተክህነትን ለማኅበሩ ለማስረከብ የተሰራው ደባ ሊቃውንቱን በማባረር በማኅበሩ አመራር አባላት መተካት ሲሆን በተጨማሪ ይህ ነው የማይባል ጉቦም እየተበላበት ይገኛል፡፡ ስለሆነም ይህ ሁሉ ደባ ከቤተክህነት አልፎ በአሁኑ ሰዓት ለፀረ-ሙስና ኮሚሽንና ለሚመለከታቸው አካላት ለግንዛቤ ተገልጿል፣ ስለሆነም ‹‹ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ክብር ይሆናል፡፡ ታሪክም ይገለበጣል፡፡ የማኅበሩም ህልም እልም ይላል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የመጣው ከላይ ነው። የእግዚአብሔር ቁጣ ሰዓቱን ጠብቆ የንፁሀን አገልጋዮቹን እንባ ሊያብስ ተገልጧልና፡፡››

12 comments:

  1. mignot aykelekelm.

    ReplyDelete
  2. weye girum mk meche new ktenkol sera yemiyarefew

    ReplyDelete
  3. ጉድ ጉድ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አምላክ ገና ብዙ ድንቅ ነግሮችን ያሳየናል። ሥራቅ ድንቅ ነው። ዐውደ ምህረቶች እግዚአብሔር አምላክ እርሱ ይጠብቃችሁ። ቅድስት ቤተ ክርስትያናችን በማቅ እጅግ ተጎድታ ነበር አሁን ግን ከዛ ከክፉ መንፈስ ልታገግም። አምላካችን ስሙ ይመስገን ቅድስት ድንግልም በጸሎቷ ትርዳን ። አሜን

    ReplyDelete
  4. Wodajochi egziabher kenante gar yihun. Yemahiberun propoganda hulum silemiawikew bertulin. Ewunet new hulun yazegaje egziabher new. Yihin yemitsifilachihu Ke mahibere kidusan office new. Betam azignalehu kelay yetegeletut ene eskindir gar mahiberu eyeseraw yalewin (Bible, mulugeta hailemariam and Samson Gebre) gar silayehu. By the way, enezih akahedoch menfesawi silalihonu hulachinim bekirib kemahiberu enilekalen kenanitem gar begara le'and betechristian eniseralen. Lesilitanachihu Aticheneku please please le ewunet siru.....Emamilak kenanite gar tihun!!

    ReplyDelete
  5. Enanite min agebachihu? You do not belong to our church!

    ReplyDelete
    Replies
    1. endeante aynetu cefenena mk new betekeresteyanachen bota yemayegebaw

      Delete
  6. endihe new berteto metagel bertulen abo endet endmetenafekun lenegerachu alchelem. enante ewnetega yebetekerestiya tekorkuwariwoche nachu

    ReplyDelete
  7. D Hayile Giyorgis Yetebale Sew Le Mahibere Kidusan Ras Mitat Honoal Ahun Degimo Gubae Ardiet yemibal keleloche ameste sewoche gar hone Meserete Yibalal. abalatu bekefetega fitnet eyadegu new. Ahun Kebad New Mihuran Alubet -Halafiwoch Alubet-Berkata Nachew Wey D Hayile Giyorgis berta eski

    ReplyDelete
  8. ለ አውደ ምህረት አዘጋጆች
    ጉባኤ አርድዕት ምን ማለት ነው ፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት ምን ዓይነት ነው፤ ጉባዔ አርድዕት ከተመሰረተ በኃላ ሌሎች ማህበራት ይፈርሳሉ ወይስ ባሉበት ሁኔታ ይቀጥላሉ፤ በአጠቃላይ እነዚህን እና ሌሎች መሰል ጥያቄዎች ሊመልስ የሚችል ጽሁፍ እንድታቀርቡልን በትህትና እንጠይቃለን፡፡ ስለ ማህበረ ቅዱሳን አባላት የሆነ እንደሆነ የሰው ልጆች ስለሆኑ አንጠላቸውም ነገር ግን እነርሱ በድብቅ የሚሰሩት መጥፎ ስራ እንደ ሰገራ አጸያፊ ስለሆነ እንሸሸዋለን፤ እንጠላዋለን፤ እንቃወመዋለን፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. yih tiyake yeEnem Tiyake new. awudemihretoch eski melisulin!!!

      yihin asiteyayet yetsafut tebareku!!!

      Delete
  9. እናንተ ጉደኞች እዚያው አብራችሁ የምትሰሩ ነው እኮ የሚመስለው! አቤት ኢንፎርሜሽን ጉደኛች ናችሁ???በርቱ ግን እኮ ሰው ለምን መውደቂያውን ሲቆፍር ትቃወማላችሁ? ሰው ለምን አርፎ የተኛውን እባብ ሲነካካው ትፈራላችሁ?እኛ እኮ የምንፈልገው ጽዋው እንዲሞላ ነው እናንተ ደግሞ ለምን ጽዋ ይሞላል ነው የምትሉት?እባካችሁ ጽዋው ይሙላልን ሌላም ነገር ይቀጥሉ!!እሺ እሰይ ጽዋው ሞልቶ ሊፈስ ነው እግዚአብሔር ሊገለጥ ነው በስሙ ሊነገድ አይችልምና!!!!
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete