Tuesday, June 26, 2012

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን የሰራተኛ ጉባኤ የተመሰረተበትን አራተኛ አመት በድምቀት አከበረ።

click here to read in PDF
የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን የሰራተኛ ጉባኤ የተመሰረተበትን አራተኛ አመት በኩክ የለሽ ማርያም ቤተክርስቲያን ባለፈው እሁድ አከበረ። ወደ ኩክ የለሽ ማርያም በተደረገው ጉዞ ምዕመናኑ የተለያዩ ዝማሬዎችን እየዘመሩ  የተጓዙ ሲሆን ለተጓዡ ህዝብ ደስታና በረከት የሚሆንም የእግዚአብሔር ቃል በጉዞው ወቅት ተሰብኳል። በዓሉ የሰራተኛ ጉባኤው ሲመሰረት ጀምሮ የነበሩ አገልጋዮችን ያካተተ ሲሆን በጉዞው ላይ ከነበሩት አገልጋዮች መካከልም ማክሰኞ ማክሰኞ ለረጅም ጊዜ ያገለገለው መጋቢ ሀዲስ በጋሻው ጉባኤው ሲጀመር ለረጅም ጊዜ ተከታታይ ትምህርት የሰጠው  መምህር አሰግድ ሳህሉ የደብሩ ሰባኪያነ ወንጌል መምህር ታሪኩ አበራ እና መምህር ናሁሰናይ መላከ ሰላም አስቻለው መሀሪ የደብሩ ካህናት እና ሌሎችም ሲሆኑ ከዘማሪያንም ዲ/ን ዕዝራ ኃ/ሚካኤልና ዲ/ን ታምራት ሃይሌ ተገኝተዋል።
ወደ ኩክ የለሽ ማርያም ጉዞ ለማድረግ 60 ሰው የሚጭኑ 12 መኪናዎችን ተዘጋጅተው የነበረ ሲሆን የተዘጋጁት መኪናዎች እነዚህ ብቻ በመሆናቸውም በርካታ ሰዎች አብረው መጓዝ እየፈለጉ መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል። ሌሎች ሰዎችም መኪኖቹ መሙላታቸውን ሲያረጋግጡ የራሳቸውን አማራጭ በመውሰድ በቤት መኪናና በትናናሽ ሚኒባሶች ጉዞውን የተቀላቀሉ ሲሆን የቤት መኪኖቹና የሚኒባሶቹ ብዛት ምዕመኑ ላመነበት ነገር ምን ያህል ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ መሆኑን ያሳየ ነበር።
ኩክ የለሽ ማርያም እንደደረሱም ጉዞው በደብሩ አስተዳደር ሸኒ ደብዳቤ ዕውቅናን ያገኘ ስለነበር ተጓዡ ህዝብ ኩክ የለሽ ማርያም በነበሩ ማኅበረ ካህናት መልካም አቀባበል ተደርጎለታል። በቤተክርስቲያንዋ ዓውደ ምሕረት መምህር አሰግድ ያስተማረ ሲሆን በመምህሩ ላይ ያደረ የእግዚአብሔር መንፈስ ምዕመኑን በከፍተኛ ደረጃ አጽናንቷል። 

መምህሩ የልቤ አምላክ ሆይ የዘላለም እድል ፈንታዬ አንተ ነህ በሚል ርዕስ ያስተማረ ሲሆን አገልጋይ በመሆኑ የሚከፍለውን ዋጋ ሚዛን ላይ ያወጣው አሳፍ የተባለ የእግዚአብሔር ሰው በቤተመቅደስ ውስጥ በቅድስና እያገለገለ ግን በውጭ ያሉት አመጸኞች እያማረባቸውና እየጎመሩ መሄዳቸው እየደነቀው እንደቆየና በኃላ ግን መልሱን ከእግዚአብሔር እንዳገኘ ፤ ህዝብ እንዳይሰናከል ግን ነገሩን ይጠብቀው እንደነበር፤ የገባው እና ያስተዋለውም ነገር አመጸኞች በመቃብራቸው ጉድጓድ ላይ እንደሚጓደዱ፤ ውድቀታቸውን በምቾቶቻቸውና በስኬታቸው ውስጥ ተሸክመው እንደሚዞሩ መሆኑን   የሱ መጨረሻ ግን የክብር እንደ ነበር እና የእግዚአብሔርን ሥራ በታማኝነት በሚሰሩ ሰዎች ላይ መከራና ችግር ቢበዛም ከዛ ቀጥሎ ደግሞ በከብር ከፍ ከፍ ማለት ስለሚከተል በሚሆነው ነገር ማጉረምረም እንደማይገባ ያስገነዘበ ነበር።
እንዲሁም መጋቢ ሀዲስ በጋሻውም ከመምህር አሰግድ በኋላ ያስተማረ ሲሆን እግዚአብሔርን ለመገናኘት ከሰፈር ወጥቶ በመገናኛው ድንኳን በደብተራ ኦሪት ዙሪያ የነበረውን የእስራኤል ህዝብ ታሪክ በማስታወስ ዛሬም ወንጌልን ፍለጋ ከቤቱ ከአካባቢው ወጣ ብሎ በኩክ የለሽ ማርያም ለተሰበሰበው ህዝብ በአካል ከስፍራ ስፍራ የመንቀሳቀሱን ያህል በመንፈስና በማስተዋልም እንደመንደርተኝነት ከሚቆጠር ከንቱ ሀሳብ ሀሜትና አሉባልታ ወጥቶ እግዚአብሔርን ለመገናኘት በመንፈስ መሆን እንደሚገባ አስገንዝቧል።
በትምህቱም ላይ ዛሬ በቤተክርስቲያናችን ያለው ችግር ከመንደር ከመውጣት ይልቅ መንፈሳዊውን አለም ወደ መንደር በመሳብ አባዜ ውርደቱን እንደ ክብር እንደምናይና ጉሰኝነቱን ማህበርተኝነቱን ከቤተክርስቲያን በላይ የማጉላት መንፈሳዊ ድቀት ውስጥ እንዳለን የሚያሳይ ነው። የእኛ አገልግሎት በዋናነት ሐዋሪያት የሰበሰቡዋት ቅድስት ቤተክርስቲያን የትኛውም ስብስብና ህብረት በላይ አክብሮና አግንኖ ማሳየት ሲሆን ግልጽ ባለ ቋልቋ ሳንሸፋፍን እውነቱን ስንነግራችሁ ማኅበረ ቅዱሳን በማለት ራሱን የሚጠራው ድርጅት በሀይማኖት ሽፋን እያደረገ ያለው ፖለቲካ የራሱን ስብስብ ከቤተክርስቲያን ልዕልና በላይ የማግዘፍ ስውር ደባ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል ብሏል።
 ተወደደም ተጠላም የወንጌል ማዕድ አይታጠፍም ለማንምም ተብሎ እግዚአብሔርን ያወቅንባትን ከክርስቶስ ጋር የታረቅንባትን ሌላው ቀርቶ እንጀራ እንኳ ቆርሰን የበለንባትን ቤተክርስቲያን እናታችን መሆንዋን የጠሉን እስኪገነዘቡ ድረስ እኛ የዚችኛዋ ቤተክርስቲያን ልጆች ነን። ለዘላለም ሟርታቸው አይሰራም ከቤታችን አንወጣም። በሚሉና ከዚሁ ጋር በተያያዙ ሀሳቦች አሁን ያለው ግራ መጋባት ለሚያደናግረው ችግሩ በግልጥ እንዲነገረው ለሚፈልገው ህዝብ ልብ የሚያሳርፈ መልዕክትን አስተላልፏል።
የሰራተኛ ጉባኤው ከመጀመሩ በፊት በቀብር ስፍራነት የሚታወቀው የዮሴፍ  ቤተክርስቲያን በወንጌል አገልግሎት ስሙና ታሪኩ ተቀይሮ መጠራት ከጀመረ አራት አመታት ሆኖታል። በነዚህ አራት አመታት ውስጥም ደብሩ  ከአዲስ አበባ አራቱም ማዕዘናት የሚመጡ ምዕመናን መጽናኛ ሆኗል። ከክፍለ ሀገርና ከተለያ ቦታዎች የሚመጡ ክርስቲያኖችም የወንጌል ረሀባቸውን የሚያስታግሱበት ነፍስን የሚያለመልም ዝማሬ የሚሰሙበት ጉባኤ የሆነው የሰራተኛው ጉባኤ በእውነትም የብዙዎች መጽናኛ ሆኗል። ብዙዎች  እንደጥሩ የነብስ ማረፊያ የሚያዩትና ወንጌል የጠማቸው ዝማሬ የናፈቃቸው የቤተክርስቲያን ልጆች የሚሰበሰቡበት የነፍስ ምግብ የሆነው የሰራተኛ ጉባኤ መካነ መቃብር የነበረው ቦታ መካነ ቅዱሳን አድርጎታል።
የሰራተኛው ጉባኤ ከተጀመረ ጀምሮ የነበሩ በርካታ አገልጋዮች በጉዞው ላይ መገኘታቸው በጉዞው ላይ ለነበሩ ምዕመናንና ምዕመናት የደብሩ ካህናት ደስታን የጨመረ ተጨማሪ ጉዳይ ሆኗል።

7 comments:

  1. teru zegeba new bertulen

    ReplyDelete
  2. askenachuge benor noro endet des yilege nebere

    ReplyDelete
  3. ማንም አይታለልም!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ብልጥ ሆነሀል በቤትህ

      Delete
  4. እንዴ መምህር አስግድና መምህር በጋሻው በቤ/ክ ውስጥ ይሰብካሉ እንዴ?የማቅ ቅንቅኖች ምነው ሆኑባቸው???ቤ/ክ ልጅ ወለደች ከተባለ በዚህ ዘመን እነዚህን ሁለት መምህራን ነውና በርቱ!እንደዚህ እየተከታተላችሁ ከነድረክ እንዳልወረዱ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አሰሙን እንጂ!እንዴት ልባችን ዓረፈ!ስበኩ የጨለማ ጊዜ ሳይመጣ እሺ!
    አሸናፊ

    ReplyDelete
  5. kikikikikikiki..........

    ReplyDelete
  6. wenegeln masetmar kbeletetem belay beletet new

    ReplyDelete