Wednesday, June 27, 2012

የዔደን ገነቱ እባብ “ማኅበረ ቅዱሳን”

click here to read in PDF
(ይህ ጽኁፍ አራት ኪሎ አካባቢ ሲበተን የተገኘ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እየተዘጋጀ ያለ ተከታታይ ጽሁፍ ዘጠነኛው ክፍል ነው። ከዚህ ጽሁፍ በፊት ያሉትን ጽሁፎችን ለማግኘት ሙከራ አድርገን የነበረ ቢሆንም የጽሁፉን አዘጋጅ ማወቅ ስለአልተቻለ ጽሁፎቹ አልተገኙም። በዚህ ጽሁፍ የማኅበረ ቅዱሳንን ምስረታ አስመልክቶ እስካሁን ድረስ ከሰማናቸው ሀሳቦች ለየት ያለሀሳብ ይዞ የቀረበ ነው። ማኅበረ  ቅዱሳን ከእውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር መግባባት ሲገባው እኔ ያልኩትን ተቀበል አሊያ አንተም አትኖርም በሚል ደካማ አስተሳሰብ የቤተክርስቲያን ልጆች እያሸማቀቀ ያለ ሲሆን ስጋ እንጂ መንፈስ  የሌለበት መሆኑም ታውቋል። የማኅበሩ ኃሳብ አላማና አካሄድ ከአመሰራረቱና ከስም አወጣጡ ጀምሮ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው መሆኑን የሚያስረዳው ይህ ጽኁፍ አቡነ ገብርኤል የማኅበሩን ስም ማኅበረ ቅዱሳን ያሉበትን ምክንያት የዋህ አባላቱና ሌሎች ሰዎች ከሚያስቡት እጅግ በተለየ መንገድ ያቀርባል። ማህበረ ቅዱሳን እንደ ኤደን ገነቱ እባብ ስቶ የሚያስት ወድቆ የሚጎትት ታውሮ ልምራ የሚል መሆኑን የሚያውቁ ሁሉ የኤደን ገነት እባብ መባሉን ተገቢነት ይስማማሉ። መልካም ንባብ) 

1.    የማኅበሩ ህቡዕ የፓለቲካ አደረጃጀት ከመሠረቱ ሲታይ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሐይማኖታዊ ስምና ግብር ራሱን ሰውሮ የሚገኘው ሐይማኖታዊ ፈቃድ የያዘ ግን ደግሞ ያልተመዘገበ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ የሚንቀሳቀሰው “ማኀበረ ቅዱሳን” ከጅማሬው በደርግ ዘመን በ1982 ዓ.ም በብላቴ አየር ወለድ ማሰልጠኛ ካምፕ ገብተው ከሰለጠኑ በኋላ ጋምቤላ መተከልና ፓዌ ዘምተው የነበሩት ወታደሮች ኋላም በዝዋይ ሃመረ ኖህ ላይ የተጠለሉት ሰዎች ተሰባስበው የመሰረቱት የወታደሮች ፓርቲ (“ማህበር”) ነው፡፡
ፊታውራሪ አመዴ ለማ የሕይወት ታሪካቸውን ባሳተሙበት መጽሐፍ ውስጥ ገጽ 217 ላይ በኤርትራ ውስጥ የጣሊያንንና የእግሊዞችን ቅኝ ግዛት ተቋውሞውን በሽምቅ ውጊያ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆኖ ዓላማውን ሲያራምድ የነበረ “ማኅበረ ቅዱሳን” የሚባል ህቡዕ ድርጅት እንደነበረና የድርጅቱ መሪ ደጃዝማች ሐረጎት አባይ እንደነበሩና በቅርበት እንደሚያውቁትም አመዴ ለማ ጠቁመዋል፡፡

እኚህ ደጃዝማች ሐረጎት አባይ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከኤርትራ ወደ አዲስ አበባ በመዛወር አሁንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ሀገረ ስብከት ውስጥ ሥራ ተመድበው በሚሰሩበት ወቅት ቤተክርስቲያኒቱ ለመኖሪያ ቤትነት የሰጠቻቸውን ከ4 ኪሎ ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን የምዕራብ በር ፊት ለፊት የሚገኘው ጊቢን በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አውጥቼ “ቤቱን ከሐረጎት አባይ ገዝቼዋለሁ” ብሎ የያዘው ሲሆን በይገባኛል ጥያቄ ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር በከፍተኛ ክስና ክርክር ከቆየ በኋላም ስለቅ ንብረቱ የቤተክርስቲያኒቱ ይሆናል ብሎ ፈርሞ ፎቅ እየሰራበት ይገኛል፡፡ ይህ ታሪካዊ ግጥምጥሞሽ ሳይሆን በዓላማ የተደረገ የህቡዕ ድርጅት የውርስ ሂደት ትስስር ነበር፡፡ የህቡዕ ድርጅቱ ማህበረ ቅዱሳን መስራች የሆኑትን የደጃዝማች ሀረጎት መኖሪያ ቤትን አሁን በግልጽ የሚንቀሳቀሰው ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳን ህንጻ እየሰራበት መሆኑ ከአላማ ውርስ ውጭ ምን ሊባል ይችላል?
እንዲሁም ለማህበሩ “ማኅበረ ቅዱሳን” የሚል ስያሜ እንዲይዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ሃሳቡን ከነምክንያቱ አቅርበው ያስጸደቁት ደግሞ ብጹዕ አቡነ ገብርኤል ናቸው፡፡ ይህንንም በ2ዐዐ1 ዓ.ም የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ተዘጋጅቶ ይፋ የሆነው ስለማህበሩ አመሰራረትና ስያሜ አሰጣጥ አስመልክቶ ባቀረበው መግለጫዊ ጽሑፍ ውስጥ “በዝዋይ ለተመሠረተው ማኅበር ስያሜ ለመስጠት አዲስ አበባ በብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቤት በዚሁ 1984 ዓ.ም በየካቲትና መጋቢት ወራት በተካኼደው ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “የማኅበራችሁ ስም ማህበረ ቅዱሳን ይባል” በማለት ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን ተመሠረተ” ብሏል፡፡ ይህ ደግሞ የተደረገው ታስቦበት እንጂ እንዲሁ አይደለም። ምክንያቱም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ኤርትራ ውስጥ በደጃዝማች ሐረጎት ዓባይ አማካኝነት በህቡዕ ሲሰራ በነበረው “የማህበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊ ድርጅት” ተሳታፊና አባል የነበሩ ሲሆኑ በወቅቱ የኤርትራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ነበሩ፡፡ ያንንም የሽምቅ ውጊያና ሐይማኖት ለባስ አካሄድ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ራዕዩን ለነዚህ የደርግ ምልምሎችና ርዝራዞች መስመር በማስያዝና ቅርጽ በመፍጠር የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትም ለዚሁ ነበር፡፡
ማህበሩ ከዚህ ቅርፅና አካሄድ ከያዘበትና በሲኖዶስ አባቶች ባለማወቅ በሰጡት ግልብና ቁጥጥር አልባ ደንብና ፈቃድ ተሸፍኖ አካሄዱን በፖለቲካዊ አወቃቀር አደራጅቶ የቤተ ክርስቲያኒቱንም አሥራት ከምዕመናን ወደ ራሱ ካዝና አዙሮ በሀገርና በውጭ ክፍለ ዓለማት አዋቅሮ ሀገርን ለባዕድ አሳልፎ በመስጠት እስከ ሲ.አይ.ኤ የተላላኪነት አገልግሎት በመስጠት ሲሠራ ቆይቷል፡፡ እየሰራም ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ የማኅበሩ ተራ አባላት ከጥቅም ተጋሪዎቹ በስተቀር ስለማህበሩ ስውር አካሄድና ዓላማ የማያውቁና ለቤተክርስቲያናችን እድገትና ደህንነት የሚሠራ የሚመስላቸው ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን የሚገብሩ ሲሆኑ በአንጻሩ ደግሞ ከመሥራች አመራር ከሆኑት እንደ አቶ ባያብል ሙላቱ አይነት የሲ.አይ.ኤ ተላላኪ ባንዳ አቅፎ የያዘ የገዘፈ የዓለቲካ ፓርቲ ነው፡፡
ማኅበሩ ይመራበት ዘንድ ቤተክርስቲያን የሰጠችውን ደንብ በአንቀጽ አምስት የማኅበሩ አቋም በሚል ርዕስ ሥር “ማኅበሩ በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ምንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት አይኖረውም” የሚለውንና  በአንቀጽ 6 የአባልነት መመዘኛ በሚል ርዕስ ሥር በተራ ቁጥር “ረ” ደግሞ “በማኅበሩ ስም ማንኛውንም የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማያራምዱ” አባላት መሆን እንደሚገባቸው የሚደነግገውን አንቀጽ በመጣስ ነው፡፡ በዚህ አንቀጽ ውስጥም “በማህበሩ ስም ማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ የማያራምዱ አባላት” ስለሚል የማህበሩ አባላትን በግላቸው ወይም በቡድን የሀገሪቱን ሰላም አንድነትና ልማት በሚያናጋ ተግባር ላይ እንዲሰማሩ ከፍተኛ የገንዘብና የሀሳብ ድጋፍ አድርጎ ሲያሰማራም ቆይቷል፡፡
አሁንም በማሰማራት ላይ ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ የጹሑፍ ችሎታ ያላቸውን አባላቶቹን ከሐመር መጽሔትና ከስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ አዘጋጅነት የተቃዋሚ ቃና ወዳላቸው ፖለቲካዊ ጋዜጦች ውስጥ ገብተው የሀገሪቱንና የመንገሥትን ገጽታ በሚያበላሽ ተግባር እንዲሰማሩ አዲስ ነገር ጋዜጣን በ3ዐሺ ብር በመደገፍ የተሳተፈ፣ የሀገሪቱን እድገትና ልማት በማይወዱ አካላትና ሚዲያዎች ውስጥ ሀሰተኛና እውነትን በማጥመም ቅስቀሳ ነክ ሀሳቦችን በማስተላለፍ፣ በሀገር ውጭም ያሉ አባላቶቹ በሀገሪቱ ማንኛውም ጉዳዮች ላይ በተቃውሞ በመንግሥትና በሕዝቡ ጥቅም ላይ ተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎችን እንዲያካሂዱ በማስተባበር፣ ሀገሪቱም በምታደርገው ፈጣን ልማት ህዝቡን በበዓል ስም ድንቁርናን በመስበክና ከተሳትፎ ይልቅ ነውጥ ላይ እንዲሳተፍ በማድረግ፣ ዜጎች ከመቻቻል ይልቅ መገጫጨት እንዲያስፋፉ በማድረግ፣ በምርጫ 97 ወቅትም ከፍተኛ ነውጥ እንዲነሳና መንግሥት በነውጥ እንዲወድቅ የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግና፡ በተለይ በአማራ ክልልና በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢህአዲግ ሽንፈት እንዲያገኝ፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ መድረክ በመሆንም በማገልገል፣ የመንግሥትን የህዝብ ቆጠራ ውጤት አሻፈረኝ በማለትና ምእመናን የአንድ ሃይማኖት የበላይነት እንዲይዙና እንዲሰብኩ በማድረግ፣ በቅርቡም በዋልድባ ገዳም ላይ በተነሳው ግጭት ሁለት ሚኒባስ ሙሉ ከዋናው ማዕከል ቡድን አዋቅሮ ወደ ሥፍራው በመላክ ጎንደር ሀገረ ስብከት ድረስ ሄደው ህዝቡን ሀገረ ሥብከቱ እንዲያነሳሳ የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ፣ ከዚያም የወልቃይትና የበለሳ የአርማጭሆ ሕዝብ ጦርነት እንዲከፍቱ በመቀስቀስ፣ በቤተክርስቲያኒቱም አንድነትና ሰላም ከመትጋት ይልቅ እርስ በርስ መከፋፈል እንዲኖርና ሀሰተኛ ሰነዶችን በየመጽሔቱ ህዝቡን በሚያስቆጣ መልኩ በማሰራጨት የቤተክህነት እዳ ሆኖ ሲሰራ የቆየናና እየሰራ የሚገኝ ቡድን ነው፡፡
ማኅበሩ አንድ ቀን በአመራር ደረጃ ካሉት ጀምሮ እስከ ታችኛው አባላቶቹ ድረስ በነውጥና በፖለቲካዊ ጉዞ ውስጥ ሲሳተፉ ካለኝና ከተቋቋምኩበት ዓላማ ውጭ ነው ብሎ ስልጠና የሰጠበትና ያቀናበት አንድም ጊዜ የለም፡፡ ይልቁንም ጠመንጃ መስጠትና ግልጽ ጦርነት የሚጀምርበትን መንገዶችን እንዲጠርጉለት ሲያስተባብር ይውላል ያድራል፡፡ ሰሞኑንም “ሰላማዊ ሰልፉን” ወደ “ሰላማዊ የእግር ጉዞ” በሚል ልባስ በመቀየር በአዲስ አበባ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ይታወቃል።  ዝንቦች በንብ ቀፎ ውስጥ ሲሰባሰቡ ማር ይሰጣሉ ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡
በአንድ ወቅት የማህበሩ ስራ አመራርና የመአሕድ የፖለቲካ ፓርቲ መሥራች የነበሩት ፕሮፌሰር አሥራት ወ/ኢየሱስ ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ ላይ ባደረጉት የማህበሩን ዓላማ ሲገልጹ “ጫካ እንዳንገባ ኢሕአዲግ መንጥሮታል ተነሥ የአማራ ህዝብ …” በማለት እንደቀሰቀሱ በወቅቱ የነበሩ ሚኒሊክና ጦቢያ መጽሔት ዘግበውት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የአሁንዋ የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መሶበወርቅ ቅጣውም ቀንደኛ ማኅበረ ቅዱሳን መሆናቸው ይታወቃል። በክብረ መንግስት ከተማ ባለፈው የካቲት 16 ቀን የማቅ አባለት ባስነሱት ብጥብጥ ሲታሰሩ መኢአድም ሳት ብሎት በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ አባላቶቼ ታስሩ ብሎ ኡኡ ማለቱ አይዘነጋም።  
እዚህ ላይ በአንድ ወቅት ስለራሱ ማኅበር ዳንኤል ክብረት ሲናገር “ከዚህ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ አስተሳሰቡ፣ አካሄዱ እና አሠራሩ ለውጥ አምጭ ሆኖ መቀጠል አይችልም ቆሟል/ስታክ አድርጓል” ብሏል፡፡ እንደገናም “ማኅበሩ ይዞት የተነሣውን መሠረታዊ አመለካከት ቀይሯል ሁለተኛ ደግሞ አመለካከቱን ሲቀይር አባላቱን ሳያማክር እና ይሁንታ ሳያገኝ በጥቂት ስውር የአመራር አካላት ፍላጎት ብቻ አስኪዶታል” በማለትም አክሏል፡፡
ማህበሩ በግልጽ የፖለቲካ ፓርቲነት ፈቃድ አግኝቶ ተመዝግቦ መንቀሳቀስ እንደሚችል ሀገሪቱ ያላት ሕገ መንግስት የሚፈቅድ ቢሆንም ለምን በሐይማኖታዊ ሽፋን ሽምቅነትን እንደመረጠ ለብዙዎች ግልጽ አይደለም የሚሉ በአሁኑ ጊዜ በዝተዋል፡፡

9 comments:

  1. werae bicha!!!.terawch!!!!!

    ReplyDelete
  2. ይሄ ማህበር ፈርዶበታል አንዴ ሌዋታን ሌላ ጊዜ ደግሞ የኤደን ገነት እባብ ትሉታላችሁ። ሌሎች አልቃይዳ ይሉታል ታሊባንም የሚሉት አሉ አሉ እኛ ደግሞ ለጠረፍ ቀረብ ያልነው አልሸባብ እያልነው ነው። ከዚህ ሁሉ ምናለ ልብ ቢገዛ?

    ReplyDelete
  3. ግራ የገባው የማቅ አመራር አሁን ደግሞ ያለውን መጻህፍትና በየጎዳናው እየቸበቸበ ነው፤ የሚመጣው አይታወቅም ብሎ ይሆናል፡፡ ነፍሱ እየወጣችም ቢሆን ገንዘብ መሰብሰቡን አያቆምም ማለት ነው፡፡
    ከየወሓን አባላቶቹ አብዛኘው ግን የአሥራት ክፍያቸውን አቁመዋል፡፡ በፊት ማቅ ፍጹም ጻድቅ ነው እያሉ የተከራከሩ ሳይቀሩ አሁን ማህበሩ አመራር የተዘፈቁበትን ሙስናና ፖለቲካ በመረዳታቸው ራሳቸውን ከማህበሩ ምርኮኝነት ነጻ አውጥተዋል፡
    አይን ያወጡት የቅርስ ጥበቃ መ/ቤት ሃላፊዎች ግን የመንግስት ንብረትን ለማህበሩ አሁንም እያዋሉት ይገኛሉ ለምሳሌ
    የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል የማኅበሩን 20ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ “ዝክረ አቡነ ጎርጎርዮስ” በሚል ርእስ የጥናትና የውይይት መድረክ ሰኔ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም አዲሱ አዳራሽ አዘጋጅቷል፡፡ ተብሏል ለመሆኑ ቅርስ ጥበቃ የማቅ ቢሮ ሆን እንዴ

    ReplyDelete
  4. tera wore selehone aydenkem, kinatem alebachehu meselegn, lelas yemitilut yelachehum? lib yistachehu

    ReplyDelete
  5. ድንቅ አደረጉ

    ReplyDelete
  6. የቤተክርስቲያን አልቃይዳው ማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑ ልጆቻችን እንኳን ለቤተሰብ አልታዘዝ ብለው የአባታቸውን የማቅን ለቤተክርስቲያን አልታዘዝ ባይነት እነርሱም በተግባር ለቤተሰባቸው በማሳየት ላይ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የመቅን ውድቀት ያፋጥንልን ለልጆቻችን ሳይቀር ጠንቁ እየተረፈን ስለሆነ ይህን የትውልድና የቤተክርስቲያን ጠንቅ የሆነ ማህበር ማጋለጥና እርቃኑን ማስቀረት ያስፈልጋል፡፡ አሁን ስለተነቃበት መግቢያና መውጫ አጥቷል፡፡

    ReplyDelete
  7. ማቅ አልቃይዳ፣ አልሻባብና ሰለፊ በተጨማሪም የኦሳማን ብላዲን ኮፒ በተግባር ወንድሞቹን የቤተክርስቲያን ልጆች አሳዳጅ

    ReplyDelete
  8. Lemindinew? Mk siwekes yaltemaru ablalatu lesidib yemichekulu?

    ReplyDelete
    Replies
    1. fake.........................................................................................................................all fake.

      Delete