Thursday, June 28, 2012

የሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ ሹመት ለመላው ሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት የስቴት ቤተክህነቶች ተላለፈ

Click here to read in PDF
ሰሞኑን ጉባኤ አርድዕትን ለማቋቋም እየሰራ ነው በሚል የማኅበረ ቅዱሳን የነገር በኩር ብሎግ ደጀ ሰላም ከፍተኛ የስም ማጥፋት ውንጀላ ያደረገችበት ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ የመላው አሜሪካ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ሹመት ለመላው የሰሜን አሜሪካ አህጉረ  ስብከት ተላለፈ። በመንፈሰ ጠንካራነቱ እና ቤተክርስቲያንን በቅንነት ለማገልግል ባለው ተነሳሽነትና ጥረት የሚታወቀው ሊቀስዩማን በተሰጠው ሹመት ተገቢውንና ቤተክርስቲያንን የሚጠቅም ስራ ይሰራበታል ተብሎ ይታመናል።
ኃይለጊየርጊስ በተሾመበት ሥልጣን ላይ የነበሩት በቅርቡ የክብር ክህነቱ የተሻረው ዶክተር መስፍንን ጨምሮ በሙሉ የማቅ አባላት ሲሆኑ አቡነ አብርሃም ለማኅበሩ ያላቸውን ታማኝነት ያረጋገጡበት ሹመት እንደነበር ይታወቃል። እነ ክህነት በጉልበቱ መስፍንም የስራ ድርሻቸው እስኪጠፋቸው ድረስ የእውር ድንብር መውተርተራቸው ያስከተለው ችግር ይስተካከል ዘንድ እንደ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊድ ያሉ ሰዎች መሾማቸው ተገቢ ነው።
ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ እስከአሁን ድረስ በቤተክርስቲያን ውስጥ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ የሚያውቁ ሰዎች በአህጉረ ስብከቱ የተለየና ጠንካራ ስራ የመስራት አቅሙን በአግባቡ የሚያሳይበት ዕድል አግኝቷል ይላሉ። 

ሃያ አመት ሙሉ ባልተቀየረው የማኅበረ ቅዱሳን የክስ አንቀጽ  በጾም በላ የፕሮቴስታንቱን አዳራሽ ያዘወትራል እና መሰል ውንጀላዎችን ያቀረበችበት ደጀ ሰላም ከተለመደው ስድብና ማጣጣል የነገር ክስ አንቀጽ ወደ መምዘዝ የተሻገረችው የሊቀ ስዩማኑ እንቅስቃሴ ስለአስደነገጣቸው መሆኑ ታውቋል።
ማኅበረ አርድዕት በቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ስልጣን ባላቸው እና በጠንካራ አገልጋዮች የተዋቀረ መሆኑ “እውነተኛ ሠራተኛ ሲገለጽ ሰራሁ ብዬ የምመጻደቅበት ሥራዬ ሁሉ ባዶ መሆኑ ይገለጻል። ሥራ ፕሮፓጋንዳ መሆኑ ቀርቶ ተግባር ይሆናል” በሚል ሥጋት የተዋጠው የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ጉባኤውን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለመምታት እንዲህ እንቅልፍ አጥቶ መታየቱ ጉባኤው ሥራ ሳይጀምር እንዲህ የሆኑ ሥራ መስራት ቢጀመርማ ምን ሊሆኑ ነው አስብሏል።
ሥር በሰደደ ጎጠኝነት የሚታወቁት የማኅበሩ አመራሮች ኃይለጊዮርጊስን ጉጠኛ ሲሉ ስማችንን እንካ ውሰድ ብለውታል። በአንድ ወቅት የማኅበሩ አመራር የነበረ ሰው የማኅበሩን አመራሮች ምሳ ይጋብዛል። እነርሱም ደስ ብሏቸው ቤቱ ምሳ ሊበሉ ይሄዳሉ። የልጁ ቤትም ሲደርሱ የልጁ እናት በማኅበሩ አመራርነት ደረጃ ባልተገባ ቋንቋ ሲናገሩ ይሰማሉ ያልጠበቁት ነገር ነበርና ድንጋጤ ሲገባቸው ልጁም ቋንቋውን ከእናቱ ተቀብሎ ያስነካው ጀመር ረዘም ያለ ጊዜ ይወስዳል የተባለው ምሳ በአጭሩ ተቋጭቶ በነጋታው ሰርጎ ገብ ተገኘ በሚል አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ ልጁ ከአመራርነት እንዲወገድ እና በሳምንቱ እንዲነገረው ይደረጋል።
ልጁም ነገሩ ስለገባው በጣም በማዘን “በእውነት ቤተክርስቲያንን ለማገልገል አድል አገኘን ብለን ብንመጣም የማኅበሩ አላማ ለካ ሌላ ኖሯል” ሲል ተደምጧል። እንዲህ ባለ ዘረኝነት የተያዘው ማኅበር “ጉባኤ አርድእት የዘረኝበት ውጤት ነው” ሊለን ሲሞክር ጥቂትም ለማፈር አልፈቀደም።
ማኅበረ ቅዱሳንን በደንብ የሚያውቀው ኃይለጊዮርጊስ፥ በሚያወጣቸው እቅዶችና በእቅድ አፈጻጸሙ የሚደነቅ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት የዶክትሬት ዲግሪውን እየሰራ ይገኛል። ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ በአሜሪካ ምድር ታዋቂ ከሆኑ የቤተክርስቲያናችን ሰባኪዎች አንዱ ሲሆን በተሳካ ራዕይ ቤተክርስቲያንን ለማገልግል እየጣረ ያለ የቤተክርስቲያን ውድ ልጅ ነው።


2 comments:

  1. ዐውደ ምህረቶች፦መልካም ዜና ነው የአማሪካን እስተቶች አብያተ ክርስቲያናትን በጠንካራ በሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አሰራር ለማስፈን የሚደረገው የሥራ እንቅስቃሴው ደስ ያሰኛል። ምነው ማቆች በሰውም ሀገር ኦርቶዶክሳዊያን ምዕማንና ምዕመናት በሰላም እየሱሩ እግዚአብሔርን ብያመልኩትበት። የግድ ክርስቲና በሰው ስም ማጥፋት የሚገኝ ወይንም የሚጓዝ አይደለም። ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት ሀሰተኛች ወሬ መስማት ሰልችቶታል ። ለዚህም የዋልድባ ሰልፍ ዉጠት ምስከር ነው።ሰወን መዋሸት የሚቻል ልመስል ይችላል ግን ችግር የሚነዋሸው ሰው ቅድስት ሀገራችን እየሄደ እውነቱን አይኑ እያየ ነው። የድህረ ገጽ ላይ ጦርነት የትም አያደረስም ውጠቱን በገሃድ አለም አቀፍ ዋልድባ ሰልፍ ኦርቶዶክሳዊያን እውነተኛ ልጆ አለመደገፋቸው ታየ። ስለዚህ ማቆች በእውነት በንስሃ ተመለሱ የማታዩት የሰማይ አምላክ ያያችሗል። ለሃይማኖቱም አይበጅም እየጎዳት ነው።

    ReplyDelete
  2. Hi Awudemihret,

    Thanks for posting this message. I know him very well for the last nearly twenty years. He is a good listener and all the MK Senor members know his capacity to coordinate and mobilize laties and clergies for common goal. L.S.Hailegiorgis is committed and genuine preacher of gospel and an excellent leader in EOTC. We know him while he used to work for the the church as head of departments in EOC for 6 years. As same time he used to serve us as a preacher in the university. Oh my God!! He has a wonderful words of GOD to challenge our Christianity and convince us to be good christian. He teach us why we should respect our EOTC church fathers, preachers as well as the laties. As we all heard, Hailegiorgis has changed the EOTC USA portfolio based on the KALAWADI after the church appointed him as CEO of EOTC in USA. And, so, this is good opportunity for all clergies, preachers and laties in USA to bring the EOTC followers together and alleviate the problem there.

    Agelgay wondimachihu

    ReplyDelete