Thursday, June 14, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ሦስቱ የሴል መሪዎች

click here to read in PDF
ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሰው የፖለቲካ ድርጅት ዘርፈ ብዙ የአሰራር መንገዶች አሉት። አሰራሩ የማፊያነት ባህሪ ስላለው የሚሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ያደርጋል። አላማውን የሚያስፈጽምበት እስከመሰለው ድረስ አዋጭ ብሎ የሚያምንበትን መንገድ ይጠቀማል። መንፈሳዊ ባኅሪ ስለሌለው ልምድን ከመንፈስ ቅዱስ በጸሎት ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶችን አሠርር እየገመገመ ይጠቅመኛል የሚለውን መንገዶች ሁሉ ይጠቀማል።
ለዛሬ ስለሦስቱ ሴሎቹ እና ስለሴል መሪዎቹ እናቀርባለን።
አሉላ  ጥላሁን
            አሉላ ዋነኛ ስራው ግልጹንም ስውሩንም ሚዲያ መቆጣጠርና መምራት ነው። ቱሪስት የነበረውን ቡድን ይመራል። ኤፍሬም እሸቴ የከፈታትን ደጀ ሰላምን ይመራል ይቆጣጠራል። ሪፖርተሮችዋን በደንብ ያንቀሳቅሳል። እነ ሱራፌልን ጳውሎስ መረዋን ሌሎችንም ይመራል። ለጥንቃቄ እንዲረዳ በእነርሱ ስር የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን አይደለችም ብለው እንዲያምኑ የሚያደርግ የተለያየ ዘዴዎችን ይፈጥራል። ያስጠናል። አንዳንዴም ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይበዛ በልዝቡ ወረፍ ያደርጋል። ከዛም ዛሬስ እኛም አልቀረልንም ብለው እንዲያስወሩ ያደርጋል። በዚህም ተሳክቶለታል። አንዳንዶቹ ወሬ አቀባዮች ምለው ተገዝተው ደጀ ሰላም የማቅ አይደለም ብለው የሚያምኑ ናቸው። ሱራፌል ወደ አሜሪካ በሄደ ጊዜ እሱም ከማኅበሩ ዋና ጸሀፊ ከሙሉጌታ ጋር በመቃቃሩ ደጀ ሰላም ተቀዛቅዛ እንደነበር ይታወሳል።
        ከምርጫ 97 በኃላ ቅንጅት ለምን ተቀባይነት አገኘ ብላ ማኅበሯ ጥናት ስታደርግ ተቀባይነት ያገኘበት መንገድ ጠንካራ መሪዎች ስላሉት ወይም የተሻለ የፖለቲካ መስመር አሊያም ልብ የሚያደርስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስላለው ሳይሆን ጋዜጦችን በሙሉ ደጋፊ አድርጎ ማቆም በመቻሉ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመደረሱ ማኅበርዋም ሀሳብዋን ወደ ህዝቡ ለማድረስ የግል ሚዲያዎችን ከማቋቋም ጀምሮ አባላትዋን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ አምደኛ በማድረግ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ይመራል ይቆጣጠራል።
      አዲስ ነገር በማኅበሩ ፈንድ አድራጊነት በማኅበሩ ሰዎች በነመስፍንና ዓቢይ ሲቋቋም እሱ ኮፒ ኢዲተር ዳንኤል ክብረት አምደኛ ኤፍሬም ሪፖርተር ሆነው በአብዛኛው የማኅበሩ አባላት የሚገኙበትና እንቅስቃሴውን በሙላት የሚቆጣጠሩበት ጋዜጣ እንደነበረች አይዘነጋም። ግን እነ መስፍን እንኳን የሆነ የተጠረጠረ ነገር ሁሉ የሚያስደነግጣቸውና እንደ ልጆች ኩኩሉ ጨዋታ ገና ቁጥር ሳይጀመር መደበቂያ የሚፈልጉ በመሆናቸው ጋዜጣዋ መክና ቀርታለች። አሉላ ከእነርሱ የተሻለ ሰብዕናም ድፍረትም ያለው በመሆኑ ሁሉ ሲፈረጥጡ እሱ ግን ኢዚሁ ቀርቷል።
        ጋዜጣዋ በ2001 የቤተክህነት ግርግር የአባ ሳሙኤልን የሌለ ሰብዕና በመገንባትና የቅዱስነታቸው የአቡነ ጳውሎስን ገጽታ ደግሞ በማኮሰስ የተሰጣትን ተልዕኮ በሚገባ ተወጥታለች። ሚስጥር ቢሆን ከጉዳቱ ጥቅሙ የሚያመዝነውን የሲኖዶስ ስብሰባን ከአዲስ ነገር ጋዜጣ ጀምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች እንዲዘገብ በማድረክ የአባቶችን ገመናና መጠነኛ አለመግባባት በማስፋት እንዲዘገብ በማድረግ የአንበሳ ድርሻውን ይይዛል።
       አሁንም ቢሆን ባለው ቀረቤታ ምክንያት ለሚዲያው የተለያዩ ወሬዎችን በማቀበል እየሰራ ያለው እሱ ነው። አሁን እንኳ ሰፊ ገበያ ባላት ፍትህ ጋዜጣ የሚወጡትን ቤተክርስቲያን ጉዳዮች ወሬ ይኸው ብሎ የሚሰጠው እሱ ነው። አምና ጀምረውት በነበረው የሚዲያ ሰርክል የመፍጠር እንቅስቃሴ ዋና አስተባባሪው አሉላ ነበር። የሚድያ ሰርክሉ አላማ ቤተክርስቲያንን በሚመለከት የሃይማኖት ጉዳይ ነውና መረጃ ከኛ ብቻ ውሰዱ እኛን ብቻ እመኑ ከሌላ ከማንም ዜና አትቀበሉ በማለት የማሳመን ስራ ይሰራ የነበረው አሉላ ነው። ሚዲያ ውስጥ ስላለና ከዚህም የተነሳ ባህሪያቸውን ስለሚያውቅ ጨርሶ ያላነጋገራቸው ጋዜጠኞች አሉ። በዚህ አካሄድ ግን አብዛኛዎቹን ጋዜጠኞችና ጋዜጦች በማሳመን ተሳክቶለት ነበር። እንደባህሪያቸው በገንዘብም በማግባባትም የተያዙ ጋዜጠኞች አሉ። አሁን አሁን አንዳንዶቹ ጋዜጠኞች እያፈነገጡ ይገኛሉ።
         ባለፈው አመት ዳንኤል የጻፈው ጽሁፍ ደጀ ሰላም ላይ እንዲወጣ በማድረጉ ከሙሉጌታ ጋር ያለው ግንኙነት የተቀዛቀዘ ነው። የማኅበሩ ዋና ጸሀፊ ሙሉጌታም ከአሉላ ጋር ስር የሰደደ ጸብ ውስጥ መግባቱ የሚያስከትለውን ችግር ስለሚያውቅ በሱ ቦታ ላይ የሚተካ አስተማማኝ ሰው እስኪያዘጋጅ ቀን እየጠበቀለት ይገኛል።
      ገብርሄር እንድትጀመር በወዳጆቹ በኩል ሀሳቡን አስነስቶ ደጀ ሰላምን ለመተካት ጥረት ቢያደርግም አልተሳካለትም። አንድ አድርገንንም በግልገል ስሜታውያን አባለት ያስጀመረ ሲሆን ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እያየለ በመሄዱ ቁጥጥሩ ሙሉ በሙሉ በአሉላ እጅ ወድቋል። ለጊዜውም ከአንዳንድ ወሬዎች በቀር ሙሉ በሙሉ የደጀ ሳለምን ዘገባ ኮፒ እንድታደርግ ታዛለች።
ማንያዘዋል አበበ
      ማንያዘዋል ደግሞ የሚመራው የኮሌጅ ተማሪዎችንና ለማኅበሩ ያደሩ ጳጳሳትን ነው። የስላሴ ኮሌጅ ምሩቃን ኅብረት ሊቀመንበር በመሆኑ ተማሪዎችን በቅርብ የማግኘት ዕድል ስላለውና ከአቡነ ሳሙኤል ጋር ከፍተኛ ቅርርብ ስላለው ሁለቱንም ለመምራት ዕድል ሰጥቶታል።
    ማንያዘዋል መንፈሳዊነትንና መንፈሳዊ ባህሪያትን በአባቶቻችን የአርበኝበት መንገድ ለማሳካት የሚፈልግ ሰው ነው። በእጅጉ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብሎ ያምናል። እነዚህን የሚቃወሙትን ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን ሰዎች ከፊቱ ለማስወገድ እስከ መግደል ድረስ የሚደርስ ጭከና አለው። በደብረ ብርሃን ከተማ በሙሉ ወንጌል ቸርች ህዝቡን አስተባብሮ ያደረሰው ጭፍጨፋ ለዚህ አንዱ ማስረጃ ነው። ድቁና እንኳ የሌለው ማንያዘዋል ስላሴ ኮሌጅ የገባው በደብረ ብርሃን ከተማ በእሱ መሪነት በደረሰው ጭፍጨፋ በፖሊስ ስለሚፈለግ ከዓይን እንዲርቅ ለማድረግ ነበር።
      በአሁኑ ሰዓት ለእርሱ ትልቁ ግቡ አቡነ ጳውሎስን ከስልጣን ማውረድ ነው። ለእሳቸው ያለው ጥላቻ ወደር የሌለው ነው። ሳይደክምም ሳይታክትምም ይኼ ነገር እንዲሳካ ጥረት ያደርጋል። ላመነበት ነገር ጽኑ በመሆኑ የማኅበሩ አመራሮች ከሱ ጋር ያላቸው አቀራረብ ጥንቃቄ የተሞላ ነው። እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው እንደሚባለው ቀረብ አደርገው ኃላፊነት እየሰጡ ብዙ ሚስጢሮች እንዳያውቅ ደግሞም እንዳይገባው አድርገው ገፋ እያደረጉ በጥንቃቄ የያዙት ሰው ነው።
    የኮሌጅ ተማሪ እያለ ሁልጊዜ ፈተና ሲደርስ ይታመም ነበር ይባላል። የሚታመመው ግን እውነተኛ ህመም ሳይሆን አሞታል ተብሎ ፈተና ላይ እንደልቡ እንዲወራጭና ፈተና ላይ አድርጎት የሚገባው ጋቢ ላይ የሚሰፋትንን አጠሪራ በቀላሉ ለማንበብ እንዲረዳው ነው። እንዲህ እያደረገ አምስት አመት ማሳለፉን ተማሪ ሁሉ ያውቃል። እንዲያውም አንድ ተማሪ ማኔና ህመሙ የሚል ግጥም ጽፎ አጠሪራውን እንዴት እንደሚጠቀምበት በሚያስቅ መንገድ ገልጾ እንደነበር ይነገራል። ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ስለሆነ ማንያዘዋል ስለዚህች ግጥም ምንም ሳያውቅ ይኖራል።
      ጨካኝ ክፉና በአላማው ጽኑ ነው እንጂ አስተዋይ ስላልሆነ የሚያወራውን አያውቅም። ከአንድ ወር በፊት እንኳ የሥላሴ ኮሌጅ ተማሪዎችን ሰብስቦ “እኔ እኮ ለዚህ ግቢ የማልሆነው የለም ደጀ ሰላም ላይ ስለዚህ ጊቢ ተጽፎ በሁለት ሰዓት ውስጥ ያስጠፋሁ ሰው ነኝ” አለ አሉ። አይ ሞኞ እግረ መንገድህን ደጀ ሰላምን ማን እንደሚያዘጋጅ ጠቆምክ እኮ!! አሉላ ይኼን ሰምተሃል?
ዳንኤል ክብረት
    ዳንኤል ክብረት በጳውሎስና ትዝታው አለመግባባት ምክንያት ለሁለት የተከፈለው የሰባኪያን ህብረት አንዱን ይመራል። ልጁ ተንኮለኛ መሰሪና ምን ማድረግ እንዳለበት አርቆ የሚያስብ ነው። ከፖለቲካ ጋር የሚያነካካ በሚመስለው ነገር በሙላት አይሳተፍም። አዲስ ነገር ጋዜጣ ይጀመር ሲባል በመሰረታዊ ሀሳቡ ቢስማማም ከአምደኝነት የዘለለ ሚና እንዲኖረው አልፈለገም። ጋዜጣው ከተቋቋመበት አላማ አንጻር ጠልቆ መግባት ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ያውቃልና። ነገሮችን ቀለል አድርጎ የመጻፍ ችሎታው ቢያስመሰግነውም ለራሱ በሰጣቸው የወግ ጸሀፊነትና የቤተክርስቲያን ታሪክ ተመራማሪነትን ማዕረግ  ይወቀሳል። በቅርቡ አለማየሁ ገላጋይ የሚባል ሀያሲ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ወግና የወግ ጸሀፊዎችን በገመገመመበት ጽሁፉ ዳንኤል የወግ ጸሀፊነት ማዕረግ የማይገባው ወግ ምን እንደሆነ እንኳ ያልገባው ሁሌ ራሱን ትክክል ማድረግና ኢትዮጵያዊያንን መውቀስ ሙያው የሆነ ሰው ነው ብሎታል።
        በተንኮል ጉዳዮች ሊቀመንበር ተደርጎ ይታሰብ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከሱ በላይ ሙሉጌታ የሚባል መሰሪ መጥቶበት የልብ ወዳጁን ባያብልን ስለነጠቀው አዲስ አበባ ባሉ አመራር አካላት ላይ ያለውን ተጽዕኖና ተሰሚነት አሳጥቶታል። የአሜሪካኖቹ ላይ ግን አሁንም በቂ የሚባል ሀሳቡን መፈጸም የሚችልበት ተጽዕኖ እንዳለው ይነገራል።
       አራት ኪሎ አካባቢ በድራፍት ተጀምሮ በድራፍት እቅድ ወጥቶበት በድራፍት ያልቅ የነበረውን ስብሰባ ቅርጽ እንዲኖረው ያደረገው ዳንኤል ሲገባበት ነው። እንደነ ምህረተአብ ያሉ የራሳቸው ልዩ ዶግማ ያላቸው ሰባኪ ነን ባዩችን የአላማ አንድነት እንዲኖራቸውና ተግባብተው እንዲሰሩ በማድረግ ተሳክቶለታል። ዘመድኩን አርማጌዶን የተባለ ካሴቱን ሲሰራ የዳንኤል አስተዋጽኦ ታላቅ ነው። ሀሳባቸውንና አትኩረታቸውን ወደ ማቅ በማድረጉ በኩልም ተሳክቶለታል።
       ባለፈው አመት ከሙልጌታ ጋር የነበራቸው ጸብ እየከረረ በመሄዱ በማኅበሩ ላይ የነበረውን ተጽዕኖ ለመመለስ እንደ መልካም አማራጭ አይቶ በጻፈው ጽሁፍ የማኅበሩን አባላት መከፋፈል ቢችልም ነገሩ በፈለገው መንገድ ሊሄድ እንዳልቻለ ከተረዳ በኃላ ስልታዊ ይቅርታ ጠይቆ ነገሩን ካበረደ በኃላ የሙሉጌታ የበላይነት በአስተማማኝ ሁኔታ እየተረጋገጠ በመሄዱ ይህንን ቡድን መምራቱን ቸል ብሎታል።
    

14 comments:

  1. good job keep it up from Texas

    ReplyDelete
  2. you guys are funny!

    ReplyDelete
  3. you guys did good job. would you pleace keep gooing?

    ReplyDelete
  4. you guys did good job pleace keep going.

    ReplyDelete
  5. ወንድሞቼ ዕውነት ለመናገር ማህበረ ቅዱሳን በየመ/ቤቱ ሴል አለው በተለይም በፌድራል መ/ቤቶች በአሁን ሰዓት ጥረታቸው የራሳቸውን ሰው ለማስቀጠር እና ስልጣን ለማስያዝ ……. ወዘተ ነው ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ያልተገነዘበው አንድ ነገር በአሁኑ ሰዓት የሁሉም ብሄረሰብ ተወላጆች ስልጣን ምን ያህል ጣፋጭ ነገር መሆኑን እራሳቸውን በመምራት አረጋግጠዋል:: ተነቅቶብሻል ምኞትሽ ጠማማዋ ማቅ።

    ReplyDelete
  6. mk man yichalish. alitechalishim eko.
    megibiash beza

    ReplyDelete
  7. ato kassahun becha yebkashal koshasha becha.

    ReplyDelete
    Replies
    1. ምን አልክ ቆሻሻውስ አንተ የማቅ ቡችላና ድርጅትህ ማቅ!! ካሳሁን ቢሮ ምን እንደተባለ አልሰማህም እንዴ? አውደ ምህረቶች ለምንድንነው የማትዘግቡት ካሰሁን ቢሮ እኮ ስብሰባ ነበር ስለማቅ የተባለም ነገር አለ። አጣርታችሁ ዘግቡት። አላቃህ ካሳሁን ውሻ ይመስል መቅለስለስ ያበዛው ለምን ይመስልሃል እንኳን ሌላ ሊያጠቃ እራሱንም መሸሸግ አልቻለ።

      Delete
  8. Koshash, Koshash, Koshash, if you like or not Mk will live longer.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Besmeam Besmeam Men Honachu Hulachuem.

      Delete
  9. Besmam Besmam Besmam Men Aynet good new Ere Zem Belu Koshasha Koshasha men malet new ? Geta eko yeferdal Zem Belen Yegetan Sera benay yeshalal .

    ReplyDelete
  10. woiiiiiiiiiiiiiiiii erefu Sew atesadebu

    ReplyDelete
  11. are u really sure to say this things? your out off ur mind.

    ReplyDelete