Sunday, July 1, 2012

የጉጂ ቦረና ሐገረ ስብከት ችግር አሁንም አልተፈታም

Click here to read in PDF
  •         አጣሪ ኮሚቴ በድጋሚ ተመድቧል።
  •       ችግሩ ያለው ክብረ መንግሰት ሃገረ ማርምያና ሻኪሶ አጣሪዎቹ የሚሄዱት ነጌሌ ቦረና ነው።
በጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት እስካሁን ድረስ የቆየውንና በማቅ አማካኝነት የተፈጠረውን ችግር የሚያጣራ አጣሪ ኮሚቴ ተመደበ። አጣሪ ኮሚቴው አራት አባላት ያሉት ሲሆን እነርሱም ፋንታሁን ሙጬ፣  የጠቅላይ ቤተክህነቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ፣ ፍስሀና ቀንደኛው ማቅ አለምሸት መሆናቸው ታውቋል፡፡ አጣሪ ኮሚቴው የሚሄደው ነጌሌ ቦረና መሆኑ ሲታወቅ ችግሩ ያለው ክብረ መንግሰት ሃገረ ማርያምና ሻኪሶ ሆኖ ሳለ አጣሪ ኮሚቴዎቹ ነጌሌ ቦረና መሄዳቸው ግራ ሆኗል። ነጌሌ ቦረና ደርሰው ወደ እነዚህ አካባቢዎች የማይሄዱ ከሆነ የችግሩን እውነተኛ ስዕል ማግኘት እንደሚያዳግታቸው ታውቋል።

የጠቅላይ ቤተክህነቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ በአጣሪ ኮሚቴ ውስጥ መካተቱ ጥሩ ሲሆን ወገኑ ከየት እንደሆነ የሚለይበትም ሰዓት ደርሷል እየተባለ ነው፡፡´ጠቅላይ ቤተክህነት አካባቢ ለማኅበሩ እንደሚሰራ ቢታመንበትም እሱ ግን በፍጹም ማኅበሩን አላውቀውም አልደግፈውምም እያለ እንደሚናገር ይሰማል፡፡ አንዳንዶች ሀሳብህን የተቀበለ መስሎ ረዥም ርቀት ከሸኘህ በኃላ ውሳኔ ላይ ሲደርስ ወደ ማኅበሩ እጥፍ የማለት አባዜ አለው የሚሉት ሰው ነው፡፡ ለእውነተኛነቱና ለምክንያታዊነቱ ፈጽመው የሚከራከሩለት ሰዎችም አሉ። አሁን ለርሱም ቢሆን ለእውነት የሚቆምበት ወይም በእውነት ላይ የሚቆምበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡
አጣሪ ኮሚቴ ውስጥ እንዲካተት የተደረገው አለምሸት የአዋሳ ሀ/ስብከት ስራ አስኪያጅ እንደ ነበረ ሲታወቅ በአዋሳ ከተማ ለማኅበረ ቅዱሳን ባሳየው ግልጽ አድልኦ በህዝብ ተቃውሞ የተነሳ ግለሰብ ነው፡፡አሁንም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳን ወይም ሞት የሚለው ይኸው ግለሰብ አጣሪ ኮሚቴ ውስጥ መካተቱ ችግሩ መፍትሔ አልባ እንዳያደርገው ያሰጋል፡፡
(የጉጂ ቦረና አገረስብከትን ችግር በተመለከተ ሰፋ ያለ ሪፖርታዥ ይኖረናል)

No comments:

Post a Comment