Tuesday, July 17, 2012

የዳላሱ አቡነ አረጋዊ የማቅ ወኪል ቄስ ከግንድ ላይ ተገንጥሎ በኪራይ ቤት ውስጥ ተተከለ!

Dalas : Click here to read in PDF
ምንጭ ደጀ ብርሃን
(እራሱን በሚመለከት ሥርዓተ ቤተክርስቲያን መጣስ ስህተት የማይመስለው፣ እውነትን ለሲዖል አውራሽ ራዕዩ የሰዋው አሸባሪው ማኅበረ ቅዱሳን ባልበላው አንኳ ጭሬ ልድፋው በሚለው አስተምሕሮው የአሜሪካኑን ሓገረ ስብከት እየበጠበጠ ይገኛል፡፡ መንፋሰዊ አገልግሎት ምንነት ያልገባቸውን አባ ኤውስጣጤዎስን ይዞ የመበጥበጥ ሥራውን ይፋዊ ያደረገው ማኅበር ተረት ሰፈር ተወልዶ ተረት ሰፈር ያደገውን ሊቀ ተረታት ወድርቅናታት የሰውን ስራ ገልብጦ በማሳተም ጉዳዮችተመራማሪ የሆነውን ወይ ጸጋ አሊያም የንግግር ውበት የሌለው እና እንጨት ነክሶ የሚጮኸውን ዳንአል ክብረት አዝማች አድርጎ ሶስተኛ ሲኖዶስ ለማቋቋም እየጣረ ይገኛል፡፡ 

ዳንኤል በሀገር ቤቱ ማቅ ፊት ስለነሳው የአሜሪካውን ማው ሙጥኝ ካለ ሰነባብቷል፡፡ ሁከት እንጂ ሰላም በማይስማማው መንፈሱም አሜሪካንን ለመበጥበጥ ታጥቆ ተነስቷል፡፡ ማቅ የአገር ሰው ሢሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ እንደሚለው ሀሳቡ በሚፈጠምበት ቦታ ላይ የሀገር ውስጥ ሲኖዶሱ የኔ ነው እያለ ሀሳቡ ከልካይ ባጣበት ቦታ ላይ ደግሞ ከሀገር ውስጥ ሲኖዶስ ውጭ ነኝ በማለት መበጥበጡ ይህ ማህበር እውነት ባይኖረው ይሉኝታ የለውም ወይ ያሰኛል? ዳላስ ከተማ ላይ ማኅበሩ እየሰራው የሚገኘውን ስራ በዝርዝር የሚያስነብብ ዘገባ ደጀ ብርሃን ሰርታለች፡፡ መልካም ንባብ ይሁንላችሁ፡፡)
በመሠረቱ ቤተክርስቲያንን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ማቋቋም ቀና ሃሳብ መሆኑ አይካድም። ጥፋት የሚሆነው አንዲቱን ቤተክርስቲያን ለማዳከምና ምእመናን በቡድን ለመከፋፈል ሲባል ከሆነ የመንፈሳዊ ተግባርን እሳቤ በማደብዘዝ ስውር ዓላማን ለመፈጸም መንፈሳዊ ካባን የደረቡ ወረበሎች የሚጠቀሙበት ስልት መሆኑ እየታየ ነው። እናም ቄስ መሥፍን የተባለው የዳላስ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል የነበረው ግለሰብእ የተሰጠውን የማቅን ተልእኰ አንግቦ በኅቡእ የቆየ ቢሆንም ሰዓቱ ሲደርስ ከዛሬ ጀምሮ ተገንጥያለሁ ማለቱ ተሰምቷል።
በኢትዮጵያ ሀገር ውስጥ  ያለ ዋና ሲኖዶስ ፤ በስደት ያለ ዋና ሲኖዶስ እና  አሁን ደግሞ በፓትርያርክ ማኅበረ ቅዱሳን የሚመራ አዲስ ሲኖዶስ በምድረ አሜሪካ እየተገነጠለና ራሱን እያራባ ወደ ሦስትነት እያደገ ይገኛል።
በዳላስ አቡነ አረጋዊ ወተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል የሆነው የማኅበረ ቅዱሳኑ ታማኝ ሎሌ ለመገንጠልና በይፋ አውጆ በ5000 ዶላር ቤት ተከራይቶ የወጣ ሲሆን  መነሻ ምክንያት  የሆነው ነገር ሲቃኝ እንዲህ መሆኑን ምንጮቻን አረጋግጠዋል።

በታህሳስ ወር ገደማ በአዝማሪ መዘምራን ሴቶች የታጀበና በገበሬ አስደንግጥ ስብከቱ ስሙዓ ዜና  በሆነው ዳንኤል ክብረት የተመራው ከፍተኛ የማኅበረ ቅዱሳን የልዑካን ቡድን ጥቂት መርዝ ነስንሶ፤ ብዙ ምርት ማፈስ በሚል መርህ በሄዱበት የ3 ቀናት ዘመቻ ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ወቅት ከዳህጸ ልሳን በዘለለ የተነገረው ዲስኩር ለችግሩ መነሻ ምክንያት ሆኗል። ይኼው ቄስ መሥፍን የተባለው የማኅበረ ቅዱሳን አባል የደብሩ ስብከተ ወንጌል ኃላፊ እንደመሆኑ መጠን አዝማሪ መዘምራኖቹና ገበሬ አስደንግጥ ሰባኪያኑ ከደብሩ እንዲገኙ ሁኔታዎቹን በማመቻቸት ግንባር ቀደሙ ሰው ነበር።
በስብከቱ መድረክ ራሱን የሰየመው ዳንኤል ክብረት ወንጌልን እንዳያስተምር ያልዋለበት በመሆኑ በወግ ጥረቃና በምሳሌያዊ ተረት ዘመኑን የጨረሰ በመሆኑ የሚናገረው  ቢጠፋበት የተቆጣጠረውን መድረክ በመጠቀም  ሀገር ቤት አፍኖ የቆየውን የፖለቲካ  ትኩሳት አሜሪካ ሲደርስ እስኪበቃው ድረስ ሲተነፍስበት መታየቱ በምእመናኑና በደብሩ ካህናት በኩል ተቀባይነት ሳያስገኝለት  ከመቅረቱም በላይ የስብከት መድረክ የእግዚአብሔር መንግሥት የሚነገርበት እንጂ የግል ስውር ዓላማንና የፖለቲካን ትኩሳት ማስተላለፊያ መንገድ እንዳልሆነ በደብሩ አስተዳዳሪ ቀሲስ ታደሰ አርአያ በሀዘኔታ መገለጹን ተሰምቷል።
ዳንኤል ክብረት በወቅቱ ወዴት እንሂድ? ኢትዮጵያ ውስጥ ታፍነን ተሰቃየን እኰ? ዝምታው እስከመቼ ነው? ወዘተ የሚሉ ቅስቀሳዎችን ሲያስተላልፍ የደብሩ አስተዳዳሪም የዳንኤልን  «ሁሉም ነገር ወደጦር ግንባር» ዓይነት ስብከቱን በመቃወም አሁን ይሄ ስብከት ነው? በባእድ ሀገር ለሚገኝ ምእመንና ምእመናት ከአንድ ሰባኪ የሚሰጥ የሕይወት   ቃል ይሄ ነው? ዓላማን ለይቶ ወደ ፖለቲካው መግባት አለበለዚያም ምእመናንን የሚያጽናና ትምህርት መስጠት ሲገባ ይህን ሁሉ ሀገር አቋርጣችሁ ከመጣችሁ በኋላ ህዝብን መቀስቀስ ተገቢ አይደለም ሲሉ ሀዘኔታቸውን ገልጸዋል።  ቤተክርስቲያን የሚመጣ ደጋፊም፤ ተቃዋሚም እንደመሆኑ መጠን ቤተክርስቲያን ማስተማር የሚገባት ሁሉንም የሚያንጽ እንጂ የአንድ አቅጣጫን ዓላማ ማስተጋቢያ መሆን የለበትም የተባለ ሲሆን የገበሬ አስደንግጡ ስብከት ውድቅ ተደርጓል። ማቅና ገበሬ አስደንግጥ ሰባኪያኑ ዳግመኛ እንዳይመጡ በመነገሩ ይህ ለማቅ ትልቅ ኪሳራ ሆኖ  ነበር።
የማቅ ታማኝ አገልጋያቸው የደብሩ ስብከተ ወንጌል ቄስ መስፍን ገበሬ አስደንግጦችን በማሰባሰብና በማስጮህ ብዙ የለፋበት የማቅ አገልግሎት ዋጋ በማጣቱና ተቀባይነት ባለማግኘቱ ውስጥ ውስጡን ሲቆስል ቆይቶ ከነፍስ አባቱ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ከመከረ በኋላ የደብሩን አስተዳዳሪ፤ ካህናትንና ማኅበረ ምእመናንን ቆይ ሳንሰራላችሁ ብንቀር በሚል ብቀላ አዲስ ቤት በአምስት ሺህ ዶላር ገደማ ተከራይተው እዚያው በቅርብ ርቀት የተተከለ ሲሆን ይህም በፓትርያርክ ማኅበረ ቅዱሳን የሚመራው ሦስተኛው ሲኖዶስ መሆኑ ነው።
ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ ሀገረ ስብከቱ በአቡነ ፋኑኤል የሚመራ መሆኑ እየታወቀ የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ ከድተው ማኅበረ ቅዱሳን ቤት ተከራይቶ ሲያትል በሚያኖራቸው የሶስተኛው ሲኖዶስ ቋሚ አባል በሆኑት በአቡነ ኤዎስጣቴዎስ በኩል የቄስ መሥፍን ቤት ተመርቆ መከፈቱ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል። በእርግጥ ሦስተኛውን ሲኖዶስ በምድረ አሜሪካ ቤቶችን በመክፈት ላይ የተጠመደው ማቅ ምንም ሀገረ ስብከት የሌላቸውን አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ቤት ተከራይቶ ማስቀመጡ ምናልባት የአሜሪካ ፓትርያርክ አደርግዎታለሁ የሚል ተስፋ ሰጥቷቸው ይሆናል። በዚያ ላይም ለማቅ  አልገዛም፤ አልታዘዝም ያሉትን አቡነ ፋኑኤልን ለማናደድ ጭምር የተጠቀመበት የግንጠላ ስልት ሲሆን  ካከራየበት ቤት ጎትቶ በማምጣት ጳጳሱ ታዛዥነታቸውን ማሳየታቸው  ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል። አቡነ ኤዎስጣቴዎስም የጵጵስና ማእረግ ወንድማቸውን ለማቅ ደስታ ሲሉ መጥላታቸውና ሕገ ቤተክርስቲያንን ማፍረሳቸውን ስንመለከት እንዲህ ብለንለመጠየቅ እንገደዳለን።  እሳቸው ከጣሱት የትኛውን ህገ ቤተክርስቲያን  ተግባራዊ ለማድረግ ነው የጰጰሱት እንላቸዋለን?
 ጎረምሳው ቡድን የራሱ ዓላማ ያለው ሲሆን ጳጳሱ ደግሞ  የራሳቸውን የሲኖዶስ ዓላማ ጥለው ለማቅ ዓላማ ስኬት መዞራቸው ያሳዝናል። ዘወትር የአቡነ ፋኑኤልን ስም በየድረ ገጾቹ  እያነሳ የሚያጨልማቸው አልበቃ ብሎት፤ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ወስዶ በአቡነ ፋኑኤል ሀገረ ስብከት ላይ ቤት እንዲመርቁ ያደረገው እርር ድብን ላድርጋቸው ብሎ እንጂ  ሕገ ቤተክርስቲያን ያንን እንዲያደርግ የሚፈቅድ ሆኖ አልበረም። ነገሩ ባልበላውም ልድፋው ነው! 

የዳላስ አቡነ አረጋዊ  ወተ/ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ካህናትም  እንዳሻኝ የምናኝበትን መድረክ ከከለከሉኝ እነሱንም ላዳክማቸው፤ አባ ፋኑኤልንም ላቃጥላቸው ብሎ መገመቱ ነበር።  ይህንንም በ7/ 11/ 2004 ዓ/ም የሥላሴ ዕለት በስመ ሥላሴ ተገንጥለናል በማለት አውጆ ለማስመረቅ ችሏል።
ቤተክርስቲያንን  መመስረት ምክንያት፤ ዓላማና፤ ግብ አለው። መገንጠል ግን ብቀላን፤ ቁጭትንና እልክን መሰረት ያደረገ ስለሚሆን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። እናም ደብረ አቡነ አረጋዊን ለማዳከም እልከኛው ማቅ በታማኝ አገልጋዩ የቀድሞው ሰባኬ ወንጌል የአሁኑ አስተዳዳሪ ተገንጥሏል። ከሲኖዶስ ሁለት ቦታ መገንጠል ቤተክርስቲያን ምን አተረፈች? ምንስ አጎደለች? የማቅም ይሁን  የግለሰቦች ግንጠላስ ምን ይጠቅማል? እንዴትስ ያዳክማል? እንደምናውቀው በገንዘብ ጉዳይ የሚናጩ ቦርዶች ወይም ካህናት እንደሚገጥሉ እንሰማለን። ይህ ግን ቤተክርስቲያንን ለማዳከምና የግልን ኪስ ለማድለብ ካልሆነ ሌላ እውነትን የተከተለ አይደለም። አሁንም የምናየው ያንን ስህተት ነው።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚነሳው በምድረ አሜሪካ ማቅ በየቦታው የቤተክርስቲያን ጦርነት መጀመሩ ነው።  በኒቫዳ፤ ላስ ቬጋስ ከተማ  ሐመረ ኖኅ ቤተክርስቲያን የተጀመረው ዘመቻ ሌላው ማሳያ ሆኗል። ከእነ ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ ያልተስማማ መሆኑ የሚነገርለት ጢም አልባው መነኩሴ ከማኅበረ ቅዱሳን ጉያ በመሸሸግ ድክመቱን ለማካካስ እየሞከረ መሆኑም ታውቋል። በአቡነ ፋኑኤል ላይ ወዶ ዘማች ሆኖ የተቃውሞ ደብዳቤ በደጀ ሰላም ብሎግ ላይ ማስነበቡ የሚያሳየው ፤ እኔ ይህንን ያህል ከዘመትኩላችሁ እናንተ ደግሞ ለእኔ የሚበጀውን ሁሉ ለማድረግ ከጎኔ ቁሙ በማለት ለማቅ የአቤቱታ መልእክት ለማስተላለፍ ፈልጎ መሆኑም እየተነገረ ነው።
በአጭር ቃል አቡነ ፋኑኤልን በዘመቻ እናባራቸው የሚለውን የማቅን ተልእኮ ለመፈጸም የተጎነጎነ ነው።
በሌላ ቦታም ማቅ የረጋውን ወተት እየናጠ እንደሆነ ይነገራል። በሲያትል ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያንም  እየበጠበጠ መሆኑም የተሰማ ሲሆን በዚያው በሲያትል አማኑኤል ቤተክርስቲያንም በማቅ የተነሳውን ሁከት በማረጋጋት መንፈሳዊ ትምህርት ለመስጠት አቡነ ፋኑኤል ወደዚያው ማቅናታቸውን ለማወቅ ችለናል።
ማቅ በምድረ አሜሪካ ሁለት ነገር እየተገበረ ስለመገኘቱ ማሳያዎች አሉ።
አንደኛው በየአድባራቱ በተላላኪዎቹ በኩል ሁከትና መከፋፈል በመፍጠር አቡነ ፋኑኤልን በብቃት ማነስ አሳብቦ ማስነሳትና ቢቻል ታዛዥ የሆኑትን አቡነ ኤዎስጣቴዎስን እዚው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አስደርጎ ማስመቀመጥ ሲሆን ካልቻለ የጉድ ሙዳዩን አገልጋይ ማስመለስ ነው።
ሁለተኛው ደግሞ በየቦታው ተገንጣይ አዳራሾችን በመከራየት በተገንጣይ ጳጳሳቶቹ በኩል ሦስተኛ ሲኖዶስን ማቋቋም ናቸው።
በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙም ሊወደድ ባለመቻሉና መንግሥትም ቀን እየጠበቀልኝ ነው ከሚል ፍርሃት የተነሳ በምድረ አሜሪካ ተገንጣይ ተቋሞቹን የማስፋፋት ሂደት እንደአማራጭ እየተጠቀመ እንደሆ ነ ይገመታል። ምክንያቱም ሀገረ ስብከቱን የሚመሩ አባት እያሉ በሌላ ሀገረ ስብከት ውስጥ ተገንጣይ ቤተክርስቲያን አይተክልም ነበር። ከዚያም የባሰው ደግሞ በአንዲቱ ቤተክርስቲያን ዓላማዬን የማስፈጽምበት መድረክ ከተከለከልኩ ከፋፍዬ አዳክማችኋለሁ በሚል ስሌት በቅርብ ርቀት አዲስ ቤተክርስቲያን በመክፈት የሚጠቀምበት የብቀላ ስልት ነው። ቄስ መሥፍንም በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ብቻ እየተገኘ ለተወሰነች ሰዓት አገልግሎት በወር አንድ ሺህ ሁለት መቶ ዶላር/ በኢትዮጵያ 21,000 ብር/ ገደማ ቤተክርስቲያኒቱ እየከፈለችውና ቀሪውን ቀናቶች ሁሉ የራሱን የግል ሥራ እንዲሰራ እድል ሰጥታው ሳለ  ለማቅ ተልእኮ ሲል ግንጠላን በመፈጸም ገበታውን መርገጡ  ምእመናንና ካህናቱ በከባድ ሀዘን እየተናገሩ ነው። በእርግጥም ያልበደለችው ቤተክርስቲያን ላይ ላደረሰው  በደል የእጁን ማግኘቱ አይቀርም።  እግዚአብሔር ልቡና ይስጠው!

10 comments:

  1. newete kelebu mk kemsdeferse bekere lela min sera alew?

    ReplyDelete
  2. YEGIZABHERIN SIM BEKENTU ATITRA: EGIZABHER LENANITE LIBUNA YISTACHU:

    ReplyDelete
  3. እነን የሚገርመኝ?

    እኔን የሚገርመኝ ማቅ በታሪክ እንዳየናቸው ገዥዎቻችን 'ሁሉ ነገር ያለ እኔ አይቻልም' በማለት እጁን እዚህም እዚያም መንከሩ ሳይሆን በሄደበት ቦታ ሁሉ መሳሪያ አድርጎ የሚጠቀምባቸው ኅሊና አልቦ ሎሌዎች መኖራቸው ነው::

    ለእነዚህ የማቅ ጀሌዎች በማስተዋል የሚሰሙኝ ከሆነ እንዲህ ልበላቸው:

    1)እግዚአብሔር አምላክ የራሳችሁ ፈቃድ እንዲኖራችሁ አድርጎ የፈጠራችሁና
    በምሳሌው የሠራችሁ ውብ ፍጥረት እንጂ የሠው እጅ የሠራው ሮሆቦት
    አለመሆናችሁ ገብቷችሁ እራሳችሁን ለመሆን ብትሞክሩ?

    2)ይህ ሳይማርና ብልቶ ሳይጠግብ ግብር እየከፈለ ያስትማረን ሕዝብ መከራ
    ችግርና የደም እንባ ምናለ ግድ ቢላችሁና ለእውነት ብትነሱ?

    3)ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም በእውነተኛ መረጃና እውቀት ላይ
    በመደገፍ እንጂ በቲፎዞና በአሉባልታ ባንደግፍ ወይም ባንቃወም?

    4)በምድራችን ላለው ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሄ የሚመጣው ሁላችንም ተግባብተን በአንድነት ስንሠራ እንጂ አንዳችን የሌላውን በጎ ዓላማ ሁሉ ስንቃወም አለመሆኑን ብንረዳ?

    5)ታሪካችን የተሞላው በመናናቅ በመጠላልፍ በምቀኝነት በትእቢት ሁሉንም እኔ ለእኔ በእኔ በሚለው ዝንባሌ ላይ በመሆኑ ተመካክሮ ለሁላችንም የሚሆን በጎ ነገር መሥራት ያቃተን መሆናችን አያሳዝናችሁም?

    6)ምንም እንኳ ባለውለታችን የሚያደርጓት በጎ ጎኖች ቢኖሩባትም ለጠቅላላ ችግራችን (ለፓለቲካው ለኢኮኖሚው ለማኅበራዊው ለሃይማኖታችን ለድህነታችንና ለተመጽዋችነታችን ... ወዘተ ሁሉ) ዋና ተጠያቂዋ ይች ዓይናማ ሊቃውንቶቻችንን እንደ ዛሪው ማቅ ያሳደደች ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች ከፍሬምናጦስ እስከ አሁን ያለውን ያገሪቱ ታሪክ በማጥናት ለማየትና ለማወቅ ብትሞክሩ?

    7)በአጠቃላይ ማ? ማነው? ዓላማው? የሚሉትን ጥያቄዎች በጥልቀት ዓይተን ተገቢ መልስ ካገኘን በኋላ ለአገር የሚጠቅመውን በመደገፍ ለችግራችን አብረን ሁነን መፍትሔ ማምጣት ይኖርብናል:: ለስውር የግል ዓላማ አባላትን አሰባስቦ በአገርና በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሱትን ደግሞ አያዋጣም ልንላቸው ይገባልና እባካችሁ ሁላችንም የነጻው ህሊናችን ባለቤት ብንሆን??

    የሰላም አምላክ ማስተዋልን ይስጠን!!!

    ሰላም ነኝ

    ReplyDelete
  4. You got it:this is the hidden agenda of "Mak". People start to notice the erruption of the dormant force in almost all the churches I know.
    What wonders me is that if "Mak"'s preachers really understand the gospel, why do the need to mix politics with the holy Bilble?

    If "Mak" has an interest or a vision in politics, it is easy to prepare a program and form a political organization. However, playing with God's word only for a political purpose or gain and becoming an obstacle to the christians has a consequence. One day, the soul will be separated from its body and face the judgement.

    So, "Mak"s preachers should think with whom they are dealing!

    ReplyDelete
  5. WHO IS KESIS MESFIN ?
    He was in new york he fight with priests and aba gbrselassie and then he went to Nashvilleand he fight with mergeta nebeyu and he went to dallas and he isolated and went to tekelhimanot and isolated ................for ever

    ReplyDelete
  6. በጣም ያዛናል ። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ራሳቸው ጳጳሳት በነዋይ ጥቅም የሚከፍቱት ነገር ያሳዝናል።በሰው ሀገረ ስብከት ውስጥ ተቀምጦና እንደገና ማን አለብኝ በማለት ቤተ ክርስቲያን መባረክ እጅግ አሳፋር ነው። የአንድ ማህበር ቡድን ለማስደሰት ተብሎ ሐይማኖት በገንዘብ መሸጥ ይችላልን? በአሜሪካ ሀገረ አንደዚህ የሚያደርጉት ካህናት በእውነት እምነቱን በቁም ገድለውታል። አማኙንም ስለ ወንጌልና ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንደማያዊቅ ደመ ነፍሱን እንደምሄድ ቆጥረውታል። እባካችሁ በስህተት ሐይማኖታችንን አታስነቅፉዋት።

    ReplyDelete
  7. Aye gude....gude ayesemayele yehegaw degmo completely different form what we usally here and listen. we now have Ethiopian Senodose, sedetew, geleltegw and Ye maherebere kidusane church ( rulde, managed, supervised by thier own gebraberoch}
    ኧረ በፈጠረን ታሪክ አናበላሸ በራስ ሲመጣ ህግ ማክበር ሃጢያት መስሎ የታየው ማ/ቅ በ dallas ደቀ መዝሙሮች ታሪክ አበላሸ የሆነ ስራ ሲሰራ አየታየ ዝም ጭጭ ለምን ይባላል የ አክባቢዉ ሊቀ ጳጳስ ተጠሉና ቅ/ቤ/ክ መገነጣጠል አለባት ፍርዱን ለህሊናችን

    ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።

    2 ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።

    3 ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤

    4 ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።

    5 ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።

    ሮሜ 13:1-5

    ReplyDelete
  8. በጣም የሚያሳዝነው ነገር ማህበረ ቅዱሳንን እንደ ሃይማኖት አስራት እየከፈሉለት የምታገሉት አንዳንድ የሰንበት ት/ቤት አባለት ነው። ሐይማኖትና ማህበርን ለይተው ካላወቁት በጣም አስቸጋር ነው። ቅዱስ ስኖዶስ የመደበውን ሊቀ ጳጳስ አለውቀውም ብሎ ሰልፍ መውጣት ምን አይነት አማኝ ነው? ስኖዶስን አላውቀውም ብሎ እነ እራሰ ስኖዶስ ነኝ ብሎ መጓዝ ከየት የመጣ አድስ ሐይማኖት ነው? ለዚህ አይነት ጥያቀዎች ማቅ ተከታዩች ለእውነተኛ የተዋህዶ ተከታዮች መልስ ልሰጡ ይገባል።
    1. ቅዱስ ስኖዶስ የመደበውን ሊቀ ጳጳስ አልቀበልብ ብሎ መከልከል ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን አይፈቅድም። ይህ በራሱ ሀይማኖትን ማደስ ማለት ነው። ወይም ተሐድሶ ማለት አንዱ ስርአተ ቤተ ክርስቲያን በራስ ፍላጎት መለወጥና ማፍርስ ነውና።
    2. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁከት መፍጠር ለማን ይጠቅማል ወይንም ማንን ያስደስታል? ዲያብሎስና ተከታዮቹ ብቻ ናቸው። ሰላም ፍቅር አንድነት ህብረት በእግዚአብሐር ቤት ክርስቲያን ሰላም እንዳይኖር የምያደርገው የሰጣን ስራዎች ናቸው።የኢትዮጵያ ቅዱስ ስኖዶስ አንቀበልም ማለት አድስ ሃይማኖትን እየተፈጠረ ነው ማለት ነው። በምድረ አሜሪካ በዓሉት የማቅ ቤተ ክርስቲያንና ተከታዮቹ ዘንድ ።
    3. ወገኖቸ በእውነት ቆም ብለን እናስብ። የማቅ አባላት ሐይማኖቱዋን እያረከሱ ነው። በነዋይ ጥቅም የደከሙት አንዳንድ ካህናት መቅደሱን እያረከሱ ናቸው። ወደ እግዚአብሔር ሁላችንም እንጩህ መጨረሻው ቀርቦአልና።

    2.

    ReplyDelete
  9. የእግዚአብሄርን ህግና ትዕዛዙን ብናከብር ኖሮ ይሄሁሉ መለያየትና መከፋፈል አይኖርም ነበር:: ለሁላችንም እግዚአብሄር ማስተዋሉን ያድለን::አሜን!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  10. He personally try to talk to me to move out with him to new church when i ask why he and his followers blamed others. I think even if difference in each other it should not be a big deal. Our religion fathers give up them live to christionity. i belived he is doing business not been an example father to be follow.

    ReplyDelete