Sunday, July 8, 2012

የጉጂ ቦረና ሐገረ ስብከት ችግር መንስዔው እና አሁን ያለበት ሁኔታ

gugi borena: Click here to read in PDF
የጉጂ ቦረና ሊባን ዞኖች ሀገረ ስብከት በማኅበረ ቅዱሳን አማካኝነት የተቀሰቀሰው ችግር እስካሁን አልተፈታም። ችግሩ አሁንም የማኅበሩ አባልና የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነው ሲያምር ተ/ማርያም በተባለ ግለሰብ መሪነት በማኅበሩ ጭፍሮች አቀናባሪነት እየሄደ ያለበት መንገድ የህዝቡን ትዕግስት ያስጨረሰ ሲሆን ከብዙ የገንዘብ ጉድለቶች ጋር ተያይዞ ስሙ የሚነሳው ይህ ግለሰብ አሁንም በቦታው ተመልሼ ካልተመደብኩ በማለት ችግር እየፈጠረ ይገኛል።
ችግሩ ሲቀሰቀስ መነሻ የሆነው ዋነኛ ጉዳይ ሁሉን ልምራ ሁሉን ልቆጣጠር የሚለው ማኅበረ ቅዱሳንን የወቅቱ የጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳዊሮስ በኔ ሀገረ ስብከት ይህን ማድረግ አትችልም አቅምህን አውቀህ ኑር ብለው በማዘዛቸው ነው። በወቅቱ ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል አቅም ስላልነበረው ውስጥ ውስጡን አድፍጦ ከቆየ በኋላ አቡነ ሳዊሮስ አካባቢውን ለቀው ወደ ወሊሶ ከመጡ በኋላ ማኅበሩ የአመጽ ስራውን በግላጭ ጀመረ።
ችግሩ የተጠነሰሰው የአካባቢው ባለ ሀብቶች ለሻኪሾ ማርያም ቤተክርስቲያንን መንበር እኛ እናሰራ በማለት ጥያቄ ባቀረቡ ጊዜ ማን ይስራው የሚል ጥያቄ በተነሳበት ወቅት ነው። የአካባቢው ባለሀብቶችና የቤተክርስቲያንዋ ሰበካ ጉባኤዎች ጨረታ ወጥቶ ይሰራ ሲሉ እነ ሲያምር ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ይስራው በሚል ይሞግታሉ። ይህ ነገር እየከረረ ሄዶ መጨረሻ ላይ በጨረታ ይሰራ የሚል ውሳኔ ላይ ሲደረስ እነ ሲያምርም ነገሩን የተቀበሉ በመምሰል ጨረታው እንዲወጣ ታዞ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው መጋቢ ጥበባት ጸጋ ዘአብ አሸነፉ። መጋቢ ጥበባት ጸጋ ዘአብ በመንበር ሥራ ታዋቂ ግለሰብ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡  የገንዘብ ነገር የማይሆንለት ማቅም በዚህ ነግር ጥርሱን ነክሶ አቡነ ሳዊሮስን ለመዋጋት ተነሳ። ህዝብ ሁሉ ሰለሚደግፋቸው ግን አቡነ ሳዊሮስ በቦታው ላይ እያሉ ምንም ማድረግ አልቻሉም፡፡ ሲያምርም በሁሉ ነገር ታዛዣ መስሎ በውስጡ ግን ነገር እየበላ ከማኅበሩ ጋር እየሰራ ቆየ፡፡ አቡነ ሳዊሮስም ከፍተኛ የሳይነስ ህመም ስላለባቸው በግንቦት 2002 ሲኖዶስ ዝውውር እንዲደረግላቸው ጠየቁ፡፡ 

ይህን ነገር አስመልክቶ እውነት በዞረበት አልፎ የማያዋውቀው የማህበረ ቅዱሳኑ ብሎግ አንድ አድርግን በወተርታራ ብዕሩ የዘገበው ዘገባ ፍጹም ሐሰት እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ እነ መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ነገሌ ቦረና በቀንደኛው የማቅ አቀንቃኝ በሆነው አለም ቀር አማካኝነት  መጋቢ ሐይማኖት ተስፋዬ መቆያ የሰባኪያንና የዘማሪያንን ወጪ በመቻል እነ አለምቀር ደግሞ ምግብና መጠለያ በማዘጋጀት ለሀገረ ስብከቱ ቢሮ ማሟያ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ከማገልገልና ከመታዘዝ በቀር የፈጸሙት አንዳች ጉድለት ሳይኖር ጭፍኑ የማቅ ብሎግ አንድ አድርገን ስማቸውን ሊያጠፋ የፈለገበት መንገድ ሀሰት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ አቡነ ሳዊሮስም ቢሆኑ አካባቢውን የለቀቁት ችግር ተፈጥሮ ሳይሆን  በጤና ችግር መሆኑ እሙን ነው፡፡
 አቡነ ሳዊሮስ የጠየቁት ዝወውር ተፈቅዶላቸው ወደ ወሊሶ ከሄዱ በኃላ ሲያምር በማኅበሩ ቀጭን ትዕዛዝ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ጀመረ፡፡ በመጀመሪያ የስም ማጥፋት ዘመቻውን የጀመረው 30000 ብር ከሻኪሾ ማርያም ቤተክርስያን አሁነ ሳዊሮስ ወሰዱ በማለት ነበር፡፡ ይህ 30000 ብር ግን የወጣው ለመንበር ማሰሪ እንደሆነና ራሱ ሲያምርን ጨምሮ በወቅቱ በነበሩ እማኝ አቡነ ሉቃስ ፊርማ  ለመንበር ማሰሪያው ቀብድ የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ህዝቡም እውነታውን ስለሚያውቅ በነገሩ ማዘን ጀመረ። ብጹዕነታቸውም እንዲህ ያለውን ክስ ለእሳቸው እንግዳ ነበርና በፈጠራ የተጀመረው ክስ በመስማታቸው በነገሩ ከማዘን ያለፈ ያደረጉት ነግር አልነበረም። በዚህ ጊዜ የብጹዕነታቸውን  ቅድስና የሚያውቁና በነገሩ ያዘኑ የህዝብ ወገኖች ይህን የስም ማጥፋት ወንጀል በዝምታ አናይም በማለት ማኅበሩን ፊት ለፊት ተጋፈጡ።
ለዓመታት የካበተ የክስ እና የወንጀል ልምድ ያለውን ማኅበር ነገሩን በምን መንገድ ማስኬድ እንዳለበት ስለሚያውቅ አባላቱ ጥቂትም ቢሆኑ ለሁከቱ ግን አላነሱም ነበር። ፊት ለፊት በሚታይ የትኛውም መድረክ ማቅ 50 ሰው ቢያቆም ከሱ በተቃራኒ ደግሞ 1000 እና 2000 ሰው መቆም ቢችልም ጨዋታውን በደብዳቤ በማድረግ ሀገረ ስብከቱን ማመስ ቀጠለ፡፡
ችግሩ የመልካሙ አባት የብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ ስም ያላግባብ የጠፋበት ስለነበር ህዝቡን ይበልጥ እልህ ውስጥ ከቶት ተወካዮች እየመደበ የቤተክህነትን ቢሮክራሲና የማኅበረ ቅዱሳንን ተንኮል በመቋቋም ነገሩን በመከታተል እና ቀጣዩን አባት  በትዕግስት  በመጠባበቅ ቆየ። በቦታው ላይ አቡነ ገብርዔል ከአዋሳ ጋራ በሞግዚትንት ደርበው እንዲይዙ ተሾሙ፡፡ እሳቸውም አዋሳ ላይ የፈጠሩት ችግር አልበቃ ብሏቸው ችግሩን ወደ ጉጂ ቦረናም ለማስፋፋት ከጠቅላይ ቤተክህነት ስልጠና ይሰጣችሁዋል ብለው የየደብር አስተዳዳሪዎችን የወረዳ ሊቀካህናቶችን አበልና የትራንስፖርት ወጪያቸውን ከደብራቸው ችለው ወደ አዋሳ እንዲመጡ አዘዙ። በተነገራቸው መሰረት በጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞች አማካኝነት ስልጠናው በገብርኤል ቤተክርስቲያን ይካሄዳል ብለው ሲጠብቁ ሰዎችን በመላክ ስብሰባው ሴንተራል ሆቴል ነው ተባሉ። ሴንተራል ሆቴልም ተሰብሳቢዎቹ ከጠቅላይ ቤተክህነት ይመጣሉ የተባሉ ልኡካኖችን ሲጠብቁ አቡነ ገብርኤል እና ከአዲስ አበባ የመጡ የማኅበረ ቅዱሳንን የበላይ አመራሮች ስለ ማኅበሩና የወደፊት ራዕይና ለተሰበሰበው ምዕመን ማስተማርና መግለጽ ጀመሩ፡፡
ተሰብሳቢዎቹም እኛ የመጣነው ከጠቅላይ ቤተክህነት በመጡ ልኡካን ሴሚናር ይሰጣችኋልተብለን ነው እንጂ ስለማህበረ ቅዱሳን አላማና እቅድ ወይም ደግሞ አደረጃጀት ሴሚናር ሊሰጠን አይደለም በማለት የተቃውሞ ድምጽ ለአቡነ ገብርኤል አሰሙ። አቡነ ገብርኤልም ማንኛውም ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳንን የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡ በማለት በቁጣ ተናገሩዋቸው። ከዚህጊዜም ጀምሮ በተለያየ አካባቢ የተቃውሞ ድምጽ ከምእመኑ እየተሰማ በመምጣቱ ምዕመኑም በተደጋጋሚ ለቅዱስነታቸው አቤቱታ በማቅረብ በርካታ ምዕመናን ከተለያየ አካባቢ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት በመምጣት አቤቱታቸውን ስላሰሙ አቡነ ገብርኤል ደርበው ከያዙት የጉጂ ቦረና ሃገረ ስብከት እንዲነሱ ተወሰነ። ከዚህም ጋር ተያይዞ አለአግባብ ሥልጣንን ተጠቅመው በፈጸሙት ወንጀል እነ ሲያምር ሊቀ ስዩማን ልሳነ ወርቅ ሁንዴ እነ መሪጌታ ሰለሞን ጨምሮ ሰባት ግለሰቦች እገዳ ተጣለባቸው፡፡
ከዚህም በኃላ በስራ አስኪያጅነት ሌላ አባት በጊዜያዊነት ተሹመው ከአጣሪ ኮሚቴ ጋር መጥተው የነበረ ሲሆን በሲያምር ቦታ ተመድበው እንዲሰሩ መሾማው ሲሰማ  ሲያምርና ማኅበረ ቅዱሳን በአንድ ሌሊት ዱርዬ ገዝተው በጩቤ በማስፈራራት አባረዋቸዋል፡፡ አስከ ግንቦት ሃያ አምስት 2003 ሃገረ ስብከቱ ያለስራ አስኪያጅ የቀጠለ ሲሆን ግንቦት 25 2003 ዓም አ.ም. ሲያምር እገዳው ተነስቶለት ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚቤት ተመድቦ እንዲሰራ ሲታዘዝ ሊቀ ትጉሀን ተሾመ ኀ/ማርያም በቦታው ተሾሙ፡፡
ኀገረ ስብከቱ ያለ ሊቀ ጳጳስ መቆየቱ አግባብ ስላልሆነ በግንቦት 2003 ዓ.ም.ሀ/ስብከቱን ደርበው እንዲይዙ አቡነ ዮሴፍ ተሾሙ፡፡ የአቡነ ዮሴፍን ሹመት የሰሙት የማቅ ሰዎችም ባሌ ድረስ በመሄድ በትክክለኛው መንገድ በሻሸመኔ መሄድ ሲገባቸው እነርሱ ግን ህዝብ እንዳያገኛቸው ሲሉ በበረሐው ነገሌ እንዲገቡ አደረጉዋቸው፡፡ ነገሌ ከገቡ በኃላ በሀገረ ስብከቱ ቢሮ በመሰብሰብ ሊቀ ጳጳሱን የማኅበረ ቅዱሳን አባለት ብቻ እንዲቀበሉዋቸው አድርገዋል፡፡ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረው ግን የወረዳ ሊቀ ካህኖችና የደብር አስተዳዳሪዎች ከሰበካ ጉባኤ የተወጣጡ ምእመናን ያሉበት አቀባበል ነበር፡፡  በአቀባበሉ ላይም ሆነ ከዛ በኃላ የማቅ ሰዎች በዚህ በዛ ብለው አዋክበው ህዝቡ ከኛ ጋር ስለሆነ እኛን ይስሙ በማለት ያሳምኑዋቸዋል። አቡነ ዮሴፍም የማኅበረ ቅዱሳንን አባለት በመያዝ የወረዳ ሊቀ ካኅናትን ሲያግዱ የደብር አስጸዳዳሪዎችን ከስልጣናቸው ሲያነሱ ሰባኬ ወንጌሎቸን ሲያግዱ ከቆየ በኋላ በማያውቁት ጉዳይ ከማኅበረ ቅዱሳን በታዘዙት መሰረት በሲያምር የፍርድ ቀን ፍርድ ቤት በመግባት ይግባኝ በማለት ለሲያምር ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱም ችሎት ደፍረዋል  በማለት  ለጊዜው በማረሚያ ቤት ሊያቆያቸው ሲል በወቅቱ የነበሩት ስነስርዓት አስከባሪ ፖሊሶችና ከዳኛው ጋር የነበሩ ሌሎች ዳኞች በመለመናቸው ሳይታሰሩ ወጥተዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡነ ዮሴፍ ችግሩን ለዘለቄታው ለመፍታት በሚል ማኅበረ ቅዱሳን ባጠናላቸው መሰረት ቅዳሜ የገበያ ቀን በመሆኑ ምዕመኑ በማይገኝበት ቀንና ሰዓት ወደ ክብረ መንግስት እንዲመጡ ተደረገ፡፡ ምዕመኑም ቀድሞ ስላወቀ ተወካይ ልኮ መድሃኒዓለም ቤተክርሰቲያን መጥታችሁ አነጋግሩን በማለት ከሶስት አጥቢያ የተወጣጣ ሕዝብ ደብደቤ ይዞ በሚሄድበት ሰዓት በክብረ መንግስት የማቅ ተጠሪ የሆነውና የመድሀኒዓለም ደብር አስተዳዳሪ፣ የወረዳው ቤተክህነት ጸሀፊ፣ የወረዳው ስብከተ ወንጌል ሃላፊ፣ የዘንባባ ማርያም አስተዳዳሪ፣ የጨንቢ ሚካኤል አስተዳዳሪ፣ የመሊካ ገብርኤል አስተዳዳሪ፣ የገጠር ቤተክርሰቲያኖች ተጠሪ የሆነው ባለስምንት ስልጣኑ ቀሲስ መኮንን ጉተማ የህዝብ ተወካዮች አቡነ ዮሴፍን እንዳያገኙ በህግ አምላክ እያለ ማይክራፎን ይዞ ቢጮህም በአካባቢው የነበሩ የመንግስት ባለስልጣኖች ወረቀቱን አቡነ ዮሴፍ እንዲቀበሉና በማግስቱም ህዝቡን እንዲያነጋግሩ ይጠይቁዋቸዋል፡፡ አቡነ ዮሴፍ የማቅ ሰዎችን ወሬ አምነው ስለነበር ህዝቡ ቢሮ ከሰማሁት ውጭ አያወራም በማለት በማግስቱ ህዝቡን ለማነጋገር በሚካኤል ቤተክርስቲያን ቀጠሮ ይይዛሉ።በዚህም መሰረት በማግስቱ በ28 01 2004 ዓ.ም. ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲን ላይ የአምስቱም ደብር ህዝብ በተገኘበት የተመለከቱት ነገር እነርሱ ሲዋሹዋቸው የነበረውን ግልባጭ ነው፡፡
በሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ የጠበቃቸው ነገር ከጠበቁት እና ካሰቡት ነገር እጅግ የተለየ ስለነበር ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ ወርሷቸው የሚናገሩት ሁሉ ጠፍቷቸው እንዲያውም በቦታው የነበሩትን የወረዳውን መስተዳዳር ሃላፊዎች  ልታስገድሉኝ አመጣችሁኝ? እያሉ ጭንቅ ጥብብ እያላቸው የህዝቡን ምሬትና ሮሮ የማቅንም ክፉ መንገድ ሰምተው ሲያበቁ  መፍትሔ ማፈላለጉ የግድ መሆኑ ሲገባቸው ከአምስቱም ደብሮች ሁለት ሁለት ሽማግሌዎች ተመርጠው በወረዳ ቤተክህነት ላይ ያለውን ችግር አጣርተው ለጠቅላይ ቤተክነትና ለመንግስት ለሀገረ ስብከቱ እንዲያቀርቡ አዝዘው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አካባቢውን ለቅቀው መጡ፡፡
እሳቸው አካባቢውን ቢለቁም የሚሆነው አይታወቅም እና ከሻኪሶ፣ ከክብረ መንግስት፣ ከነገሌ ቦረና፣ ከቀርጫ፣ ከገርባ፣ ከሓገረ ማርያም፣ የተወጣጡ ምዕመናን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ተከትለዋቸው መጥተው አቤቱታ በማቅረባቸው አቡነ ዮሴፍ ወደ ሀ/ስብከቱ ተመልሰው ላይመጡ በወጡበት ቀርተዋል፡፡
በስተመጨረሻም የነገሩ አካሄድ ግራ እያጋባ ስለሄደ እና ነገሩ ከቤተክኅነት አቅም በላይ መሆኑ ስለተደረሰበት ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መግትሔ እንዲፈልግለት የሚጠይቅ ደብዳቤ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፊርማ ተጽፎዋል።
የደብዳቤው ሙሉ ቃል እንዲህ የሚል ነው።
ለክቡር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት
አዲስ አበባ
       ጉዳዩ፡   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጉጂ ቦረና ሊበን ዞን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ላይ የደረሰው ወቅታዊ ችግር መፍትሔ እንዲሰጠው የቀረበ ጥያቄ ነው
የዚሁ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ችግር ያሳሰበው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በተደጋጋሚ ለመ/ቤትዎ ያመለከተ መሆኑን ጠቅሶ ትኩረት እንዲሰጠው በቁጥር 2ዐ85/14430/04 በቀን 24/04/2004 ዓ.ም ከተጻፈው 3 ገጽ አባሪ ጋር ያቀረበልንን ስንመለከተው በሕግ የበላይነት ተረጋግጦ ውሳኔ ባገኘውና የሥራ ውላቸውን ካቋረጡ መጋቤ ጥበባት ሳያምር ተ/ማርያም ከሚባሉት ግለሰብ ጎን በመሠለፍ በቁጥር ከ12 የማይበልጡ እነ አቶ ፍቃዱ ታምሩ የሚባሉት ግለሰቦች ጠልቃ በመግባት የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት የበላይነት ሥራ አስኪያጁን ወደ ሀገረ ስብከት እርሱን አናስገባም በማለታቸው መንፈሳዊውና ማኅበራዊ አገልግሎት መቋረጡን በማስመልከት ይህ ከቤተ ክርስቲያኒቷ ማዕከላዊ አስተዳደር አቅም በላይ የሆነው ችግር በክልሉ መስተዳድር በኩል እንዲፈታ የሚያስችል ማሳሰቢያ እንድንጽፍለት የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በተደጋጋሚ አመልክቷል፡፡
ስለዚህ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ በቤተ ክርስቲያኒቱ መልካም አስተዳደር ላይ ሆን ብለው ሕዝብን ለሕገ ወይ ብጥብጥ የሚያነሣሡ ግለሰቦች እንዳሉ በሀገረ ስብከቱ ሪፖርት የተገለፀ ስለሆነ፣ ይህ ሕገ ወጥ ድርጊት ሀገሪቱ ለምትከተለው የዕድገት ጎዳና ጠንቅ ሊሆን እንደሚችል ከክቡርነትዎ ግንዛቤ ስለማይሰወር ጉዳዩ ትኩረት አግኝቶ ከአካባቢው መልክዐ ምድር አቀማመጥ ጠራፋማነት አንጻር ታይቶ የማያዳግም አስተዳደራዊ መፍትሔ እንዲሰጠው እያሳሰብን ለአፈጻጸም ይረዳ ዘንድ የቀረበውን ማሳሰቢያ 3 ገጽ ፎቶ ኮፒ ጽሑፍ ከዚህ ጋር አቅርበናል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
የችግሩን መቋጫ እየጠበቀ ያለው የአካባቢው ህብረተሰብ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ እየታገለ ይገኛል።

የአቡነ ሳዊሮስ ጉዳይ
ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ በግልጽ የሚታወቀው ሰብዕናቸው ቅን መልካም ተግባቢ የሆኑና የእግዚአብሔር ቃልና ሀሳቡ የሚስፋፋበትን መንገድ በማመቻቸት የሚተጉ ሰው በመሆናቸው ነው። ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው ማኅበር ሥራ የሚለው በሀገረ ስብከቱ የማህበሩ መንገስ እንጂ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ስላልሆነ እሱ የሌለበት የማንኛውም መልካም እንቅስቃሴ ሁሉ ጠላት ነው። ማህበሩ ሳይኖር 10000 ሺህ ሰው ክርስትና ከሚነሳ ማኅበሩ ባለበት 1000 ሺህ ሰው ቢሰልም ደስ ይለዋል። የሚያቀርበውም ሪፖርት እኛ በአካባቢው በመኖራችን 1000ሺህ ሰው ብቻ ሰልሟል ባንኖር ኖሮ ግን ቁጥሩ ከዛ ያልፍ ነበር የሚል ነው። በብዙ ቦታዎች ላይ ማኅበሩ ስለመኖሩ የሚያቀርበው ሪፖርት ኖረን ይሄን ለውጥ አመጣን ሳይሆን ባንኖር ኖሮ እንዲህ ይሆን ነበር የሚል ሽብር አዘል ነው።
በዚህ እይታም እነርሱ ሳይሳተፉበት ወንጌል ሀይል ማግኘትዋ የህዝቡ ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ የማያምኑት ወደ እምነት መምጣት እንቅልፍ ነስቷቸው የወንጌሉን እንቅስቃሴ ለማዳፈንና ቦታውን ለመቆጣጠር ውስጥ ውስጡን እንቅስቃሴ ጀመሩ። በዚህ እንቅስቃሴያቸው በብዙ ነውርና ገንዘብ ዘረፋ የሚታወቁትን አነ ቀሲስ መኮንንን እነ ሲያምርንና ሊቀ ስየማን ልሳነወርቅን እና መሪጌታ ሰለሞንን ከጎናቸው ለማሰለፍ ቻሉ። ከሚያገኙት ደሞዝ ጎን ለጎንም የማኅበሩ ተከፋይ የሆኑት እነዚህ ሰዎች በሙሉ ልባቸው በማኅበሩ በመስራት ህጋዊ መዋቅሮችን በማፍረስ ነገሮችን ሁሉን ነገር በማኅበሩ ቁጥጥር ስር ለማድረግ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመሩ። አዲስ አበባ ቤተክህነት አካባቢ በማኅበሩ ሰዎች የሚደረግላቸውን ከለላ በመጠቀምም አቡነ ሳዊሮስን ውስጥ ውስጡን መቃወም ጀመሩ። ይህንን አካሄዳቸውን የሚቃወሙትን የአካባቢው ተወላጆች ዲያቆናትና ሰባኬ ወንጌሎችን እያሳደዱ መምታች ጀመሩ፡፡ ለእውነት በመቆማቸው እና ቤተክርስቲንን እንጂ ማህበረ ቅዱሳንን አናገለግልም በማለታቸው ታግደው ከነበሩት ሰዎች መካከል መጋቢ ሓይማኖት ተስፋዬ መቆያ ዲያቆን ስንታዩ ዲያቆን ሀይማኖት ዲ/ን ብሩክ ዲ/ን አብርሃም ዲ/ን ግርማ ዲ/ን ብሩክ ዲ/ን ቢኒያም ….እና ሌሎችንም ዲቆናትና ካህናት ከስራ አግደው ነበር፡፡
ይህንንም አድርገውም ቢሆን የተቃውሞው አካሄድ ስር አልሰድ ብሎ ሲያስቸግራቸውም ሌላ የጀርባ ቁስል ቢፈልጉ ሰላጡባቸው እና አቡነ ሳዊሮስን በቁጥጥራቸው ስር ማድረግ የሚችሉበት መንገድ ሲጠፋባቸው ገንዘብ በልተዋል ለማለት የሚመስል ምክንያት ማፈላለግ ጀመሩ።
በሉ ብለው የሚያስወሩባቸው እና እነ አንድአድርገን እና አጫፋሪዋ ሎሚ የጻፉት ገንዘብ 30000 ብሩ የመንበሩ ማሰሪ ሲሆን 15000 ብሩ ደግሞ ከሀገረ ማርያምቅድስት ማርም ቤተክርስቲያን ሲያምር ተክለ ማርም እና አሁን አጣሪ ሆኖ ተሹሞ የነበረው አለም እሸት መውሰዳቸው የሰነድ ማስረጃ የተገኘባቸው ናቸው፡፡ ሌባ ሌብነቱ ሲታወቅ ሌባ ሌባ እያለ እንደሚሮጥ እነ ሲያምርም ሌብነታቸው ተደርሶበት ከህዝብ ዘንድ ጥያቄ ሲነሳ አቡነ ሳዊሮስ አካባቢውን ከለቀቁ በኋላ በእሳቸው ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ።
ብጹዕነታቸውን አሁንም ቢሆን የአካባቢው ህዝብ በመልካም ስራቸው የሚወዳቸው ሲሆን ከነዚህም መልካም ሥራዎቻቸው ጥቂቶቹ በደርግ ተወስዶ የነበረው የሀገረ ስብከቱ መሬቶችን ለቤተክርስቲን ጥቅም ማስመለሳቸው በቦሬ ወረዳ ላይ የጥምቀተ ባህር ቦታን ፕሮቴስታንቶች በጉልበት ለመውሰድ ሲሞክሩ ጨፌ ኦሮሚያ ድረስ በመሄድ ማስመላሳቸው በየገጠሩ ቤተክርስቲያን በማሰራት የምዕመን ቁጥር እንዲያድግ በማድረግ ጉባኤዎች እንዲዘጋጁና ህዝቡ በወንጌል ቃል እንዲጽናና በማድረግ ህዝቡን አስተባብሮ በመምራት የተመሰከረላቸው አባት ናቸው።
የሲያምር ነገር
ሲያምር የአዳሜ ቱሉ ልጅ ሲሆን በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሰው ነው። በቅልስልስነቱ የሚታወቀው ሲያምር የገጠመውን ሰው ሁሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባል እንዳልሆነ እና ለእውነት እንደሚሰራ ይናገራል። ቀርቦ ላደመጠው ሰው ከቅልስልስነቱ ጀምሮ የአነጋገር መንገዱ ሰዎችን ልብ የሚያስገዛ ሲሆን አብረውት የሚሰሩ አንዳንድ የማኅበሩ አባል ያልሆኑ ሰዎች እንኳ ስለእሱ ማኅበረ ቅዱሳን አለመሆን ደፍረው የሚናገሩ ናቸው። ሲያምር ግን አዲስ አበባ ሲመጣ በማኅበሩ ዋና ማዕከል መመሪያ እየተቀበለና የአሰራር ሂደቱን በተመለከተ ሪፖርት የሚያቀርብ ሲሆን። ወደ ነገሌ ቦረና ሲመለስ ደግሞ ምን ማድረግ እንዳለበት ከማንያዘዋል መመሪያ የሚቀበልና የሰራቸውን ማኅበሩን የሚመለከት ስራዎች ለማንያዘዋል ሪፖርት የሚያቀርብ ሰው ነው።
የሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅነቱ በሰጠው ክፍተት ከፍተኛ ገንዘብ በመዝረፍ ወንጀል የሚጠረጠር ሰው ሲሆን በአንዳንድ የዝርፊያ ወንጀሎችም የኦዲት ሪፖርት ጭምር የቀረረበት ሰው ነው። የማኅበሩ አባል በመሆኑ ግን ማኅበሩ ከለላ እየሰጠውእስካሁን በዝርፊያ ወንጀል  ሳይከሰስ ቀርቷል።
በጉጂ ቦረና ሊባን ዞኖች ሀገረ ስብከት ለተፈጠረው ችግር ዋነኛው ተጠያቂ እሱ ሲሆን በክብረ መንግስት ከተማ ህዝብ አይንህ ላፈር የተባለ ሰው ነው። ሰውየው በህዝብ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠላ ቢሆንም የማኅበሩ ተከፋይ መጽሔቶች መካከል አንድዋ የሆነችው ሎሚ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው በማለት የጎደፈ ስሙን በሀሰት ቅባት ለማስዋብ ሞክራለች። በዚህ አጋጣሚ እውነቱ ወዴት ነው ብለው ሳይመረምሩ ለማኅበሩ የሚሰሩ ጋዜጦችና መጽሔቶች በታሪክና በህሊና ፊት ተጠያቂ ከመሆን ስለማያመልጡ ስራቸውን ለእውነት ለማስገዛት እንዲሞክሩ እናሳስባለን።
የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ፣ የሐገረ ማርያም የግሎባል ፈንድ ኃላፊ፣ የሀገረስብከቱ የHIV ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና የማቅ አባል የሆነው ሲያምር የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት ውስጥ የችግሩ ምንጭ መሆኑ ስለተደረሰበት በ25 9 2003 በአቡነ ፊሊጶስ የተጻፈ እና
“የጉጂ ቦረና ሊበን ዞኖች ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነው እየሰሩ መሆንዎን እያስታወስን ከግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ተዛውረው የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት አስተዳደር ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ የተፈቀደለዎ ስለሆነ በሀ/ስብከቱ እስካአሁን ይሰሩበት የነበረውን ቢሮና ዶክሜንት ሀ/ስብከቱ በሚመድበው አረካካቢነት ለቦታው ለተመደቡት ለሊቀ ትጉሃን ተሾመ ኃ/ማርያም አስረክበው በተመደቡበት ሥራ ቦታ ተገኝተው የተመደቡበትን ሥራ በትጋት እንዲሰሩ እናስታውቃለን፡፡” የሚል ደብዳቤ ደረሰው። ከሀገረ ስብከቱ የሚያገኘው ጥቅማ ጥቅም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚቋረጥበት የተረዳው ሲያምርም በጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ፊርማ የታዘዘውን ትእዛዝ ወደ ጎን ትቶ ርክክብም አላካሂድም ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤትም አልሰራም በማለት ማህተምና የሀገረ ስብከቱን መኪና ይዞ ተሰወረ።
በዚህ ጊዜ የፈጸመው ብልግና የተሞላበት የድፈረት ወንጀል ያሳዘናቸው አቡነ ፊሊጶስ እንዲህ ሲሉ ለጉጂ ቦረና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በ30 10 2003 ዓ.ም.ደብዳቤ ጻፉ
“መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተ/ማርያም ቀደም ሲል የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ጊዜ ይጠቀሙበት የነበረውን ቢሮና ልዩ ልዩ ንብረት እንዲያስረክቡ ከበላይ መ/ቤት በተደጋጋሚ በተጻፈ ቢታዘዙም ለሕግ ለመታዘዝ ፈቃደኛ ሆነው ሊቀርቡ ካለመቻላቸውም በላይ ይባስ ብለው ለሀገረ ስብከቱ አገልግሎት እንዲውል ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተሰጠውን ኮድ 5 የሰሌዳ ቁጥር ዐዐ639 አ/አ የሆነውን ቶዮታ ፒክ አፕ መኪና ይዘው የተሠወሩ መሆኑን በመ/ቁጥር 6/2ዐዐ3 በ22/1ዐ/2ዐዐ3 ሀገረ ስብከቱ ከጻፈልን መረዳት ተችሏል፡፡
ስለዚህ የሀገረ ስብከቱን መገልገያ መኪና ይዞና ለሕዝበ ክርስቲያኑ ያላሰለሰ አገልግሎት የሚሰጥበትን ቢሮ ሳያስረክቡ ዘግቶ መጥፋት የህግ አግባብነት ካለው ሰው የማይጠበቅ ከመሆኑም አልፎ ቤተ ክርስቲያንን እጅግ ለጉዳት የሚዳርግ ወንጀል ስለሆነ የከፋ ችግር ከመድረሱ አስቀድሞ የሀገረ ስብከቱ ነገረ ፈጅ ሊቀ ትጉሃን ዘነበ አለማየሁ በጉጂ ሊበን ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሰርቱና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተክለ ማርያም ይዘውት የተሰወሩትን መኪናና ያላስረከቡትን ቢሮ ቀርበው በህግ አስገዳጅነት እንዲያስረክቡ ታደርጉ ዘንድ በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡”
በዚህ ትእዛዝ መሰረትም የጉጂ ቦረና ሊበን ዞኖች ሀገረስብከትም ክስ መስርቶ ለነገሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በቀን 8 11 2003 ዓ.ም. የትብብት ደብዳቤ ያስገባል።
ለነገሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት
ነገሌ

ጉዳዩ፡  የሕግ ድጋፍ እንዲደረግልን ስለመጠየቅ ሆኖ
በርዕሱ ለተጠቀሰው የጉጂ ቦረናሊባን ዞኖች ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የበሩት መጋቤ ጥበብ ሲያምር ተ/ማርያም ከግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የዛውረው የትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት አስተዳደር ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ሆኖ በእጃቸው የሚኘውን ንብረት በቦታው ለተመደቡት ለሊቀ ትጉሃን ተሾመ ኃ/ማርያም እንዲያስረክቡ በቁጥር 1/1710/2003 በ25/9/2003 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ የታዘዙ ቢሆኑም ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆን በተመደቡበት ቦታም ባለመገኘታቸው፡-
1ኛ.  በቁጥር 1/1837/2ዐዐ3 በ16/1ዐ/2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ የጥሪ ማታወቂያ
2ኛ. በቁጥር 1/1917/2ዐዐ3 በ3ዐ/1ዐ/2ዐዐ3 ዓ.ም ለ2ኛ ጊዜ በማስታወቂያ ቢጠሩም እምቢተኛ መሆናቸውን አረጋግጠው ሊገኙልን ባለመቻላቸው በቁጥር 1/1992/2ዐዐ3 በ3ዐ/1ዐ/2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በሀገረ ስብከቱ ነገረ ፈጅ አማካኝነት በሊበን ወረዳ ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶባቸው ይዘው የተሰወሩትን መኪናና ያላስረከቡትን ቢሮ በሕግ አስገዳጅነት ቀርበው እንዲያስረክቡ ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ኃላፊነት ከመሰጠቱም ሌላ ዝውውሩ ያለአግባብ ነው ይነሳልኝ በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ በቁጥር ½ዐ27፣2ዐዐ3 በቀን 6/11/2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ በፋክስ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን ባለመቀበላቸው ምክንያት ርክክቡ ያለመፈጸሙን አሁን በቦታው ከተመደቡት ሥራ አስኪያጅ በመ/ቁ 1ዐ/2ዐዐ3 በ7/11/2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጾልናል፡፡
በመሆኑም ተጠቃሹ አንድ ሠራተኛ ተዛውሮ መሥራት በኢት/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሠራተኛ አስተዳደር ደንብ አንቀጽ 4 ንኡስ ቁጥር አንቀጽ 1 መሠረት ያለና ወደፊትም የሚቀጥል መሆኑን በመዘንጋት ቢሮውንም ሆነ በእጃቸው የሚገኘው ኅብረት ለማስረዘብ ፈቃደኛ ባለመሆን የተበላይ መሥሪያ ቤቱን ትእዛዝ አልቀበልም በማለት ሠራተኛን በማሳደም በሰላምና በፍቅር ያሉትን ምዕመናን እርስ በእርስ እንዲለያዩ በየአብያተ ክርስቲያናቱ በጸብ በመቀስቀስ ወደ አልሆነ አቅጣጫ እየመሩ ይገኛሉ፡፡
ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በጉልበት በግድ በሥልጣን ላይ እኖራለሁ ባይ ግለሰብን ለመዳኘት የራሷ የሆነ ፖሊስና ፍ/ቤት እንደሌላትና ከመንግሥት በኩል ፍትህ የማግኘት መብት እንዳላት የሕግ የበላይነት ተረጋግጦ ተጠቃሹ በእጃቸው የሚገኘውን ንብረትና ቢሮ እንዲያስረክቡ የሕግ ድጋፍ እንዲደረግልን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

የነገሌ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት  ጉዳዩን  እየተከታተለው ቢቆይም ሊያምር ሊገኝ ስላልቻለ ነገሩ በእንጥልጥል ይቆያል። ሲያምር ከአካባቢው ይሰወር እንጂ ከአራት ኪሎ አካባቢ ግን አልጠፋም ነበር። ከማህበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል ከለላ ስለሚሰጠው ሕግ እንደሚፈለገው ቢያውቅም በመተማመን ለትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት በተመደደበበት ቦታ አልሰራም ሲል ያስታውቃል።
በስራ ገበታው ላይ አለመገኘቱ ትክክል ስላልሆነም በተደጋጋሚ ሰራ እንዲጀምር በውስጥ ማስታወቂያ ቢነገረውም እምቢ በማለቱ ማተሚያ ቤቱ ለጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ባሳወቀው መሰረት በስተመጨረሻ በ11 /12 2003 ዓ.ም. የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቡነ ፊሊጶስ የስራ ስንብት ደብዳቤ ይጽፋሉ።
ለመጋቤ ጥበባት ሲያምር ተ/ማርያም
ባሉበት
የሥራ ስንብት ማስታወቂያ
ከጉጂ ቦረና ሌበን ዞኖች ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪየጅነት ተነሥተው ከግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ተዛውረው የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት አስተዳደር ኃላፊ ሆነው እንዲሠሩ በቁጥር 1/1710/2003 ዓ.ም በ23/9/2003 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ መሠረት በተመደበቡት ተገኝተው ሥራውን ባለማከናወንዎ ምክንያት የሠራተኛ መተዳደሪያ ደንቡ በሚፈቅደው መሠረት፡-
1.      በቁጥ 1/1837/2ዐዐ3 በቀን 16/1ዐ/2ዐዐ3 ዓ.ም
2.     በቁጥ 1/1837/2ዐዐ3 በቀን 16/1ዐ/2ዐዐ3 ዓ.ም
በተፃፈ ደብዳቤ የጥሪ ማስታወቂያ መሠረት ከሥራ የቀሩበትን ማስረጃዎን ይዘው ቀርቦ በምድብ ሥራዎ ላይ ባለመገኘትዎ ሥራው እየተበደለ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ስለዚህ ሥራውን በገዛ ፈቃድዎ ስለለቀቁ ከሥራው ከቀሩበት ጊዜ ጀምሮ የተሰናበቱ መሆኑን እያስታወቅን የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት በእጅዎ ይገኝ የነበረውንና ሲጠቀመበት የቆየውን ንብረት በሕግ ተከታትሎ እንዲያስመልስ በዚህ ደብዳቤ ግልባጭ የታዘዘ መሆኑን እየተለጽን የዞኑ መተዳደሪያም ሆነ የሚመለከታቸው መ/ቤቶች ሁሉ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ለሀገረ ስብከቱ እንዲያደርጉልን በቤተ ክርስቲያንዋ ስም እንጠይቃለን፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
እንግዲህ ይህ ህግ አያዘኝም ብሎ ህግ እየጣሰ በሚያስቸግረው በማኅበረ ቅዱሳን ጉያ ተከልሎ የሚፋንነው ግለሰብ ህገ ወጥነቱ ታውቆ ከስራ የተሰናበተና ሲሆን በጠቅላይ ቤተክህነቱ እውቀት ምንም አይነት ስራ በቤተክህነት አካባቢ የሌለው ሰው ነው።
የሲያምር ህገ ወጥነት ልክ አጥቶ ችግሩ ሳይፈታ የሀገረ ስብከቱ ንብረትም ሳይመለስ እንዲሁ በእንጥልጥል ሳለ የከተራ እለትእዚህ አዲስ አበባ ከተማ ታቦት ሲሸኝ ያየው የአካባቢው ተወላጅ የሆነ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ለፖሊስ ጠቁሞ አስያዘው። በጥር ወር 2004 ዓ.ም. ተከሶ በነገሌ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ጥፋተኛ መሆኑ ተወስኖበት በእጁ ላይ ያለውን ንብረት እንዲያስረክብ ቢታዘዝም እስካዛሬ ድረስ ማህተሙንና ጽ/ቤቱን አላስረከበም። እንዲያውም እጁ ላይ ባለው ማኅተም ወንጀል እየፈጸመበት ይገኛል።
እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ተደርጎ የማያውቀውን እንዲህ ያለውን ወንጀል የፈጸመን ግለሰብ ሎሚ መጽሄት አንቆለጳጵፃ መጻፍዋ ያስገርማል። ፕሬሱ ኃላፊነት የማይሰማቸው ለእውነት ሳይሆን ለገንዘብ እና ለማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ አስፈጻሚነት ራሳቸውን የሾሙ ሰዎች ስብስብ እየሆነ መምጣቱ ያሳዝናል። ከብዕራቸው በቀር በልባቸው ያልተገዙለትን ፍትህ አነሰ ጉደለ ብለው መጮሀቸው ትርጉም አልባ ያደርግባቸዋል። እነርሱ ባለቻቸው ትንሽ እድል ፍትህን እየረገጡና እውነትን እየካዱ ህዝብ የምንለውን ሰለሚሰማ ችግር የለም በሚል መንፈስ እውነትን ለመጨፍለቅ መወሰናቸውን ስናይ ስልጣን ቢኖራቸውምማ የሚያደርሱት በደል ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግተንም። የሁሉንም ወገን ሀሳብ ግራ ቀኝ አቅርቦ ህዝብ እንደፈርድ ከማድረግ ይልቅ የምንሰራው ለማኅበረ ቅዱሳን ነው በሚል መንፋስ እይናቸውን በጨው አጥበው ከማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ደጀ ሰላም ላይ እየወሰዱ የውንጀላ እና የክስ ጽሁፎችን ማውጣታቸውን ስናይ በሀገራችን ፕሬስ ወገናዊነትና በጋዜጠኞቹ የሙያ ስነ ምግባር ማጣት እጅግ እናዝናለን።
 የሎሚ መጽሔት ቅባት የልብ ልብ የሰጠው ሲያምር ሰሞኑን ወደ ሀገረ ስብከቱ ለመመለስ በቤተክነቱ አካባቢ ባሉ የማኅበሩ ሰዎች አማካኝነት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ቤተ ክህነት አካባቢ ወደ ስራ ለመመለስ እየተቅለሰለሰ ወደ ጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት በመመላለስ ህግ በህገ ወጥነቱ የሚያውቀው ሲያምር እጁ ላይ ያለውን ህገ ወጥ ማኅተም ተጠቅሞ በማን አለብኝነት መንፈስ ያለስልጣኑ ለራሱ ስልጣን ሰጥቶ የበተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችን ከስራ በማባረር የሰበካ ጉባኤ በማፍረስና አዲስ በማስመረጥ ስራ ተጠምዶ ይገኛል። የቤተክህነት መቅለስለሱ ምክንያትም ህገ ወጥ ስራውን ሕጋዊ ልባስ ለማልበስ ነው።
አስካሁን ደረስ ባለው ሂደት የሚሰሩትን የማያውቁትን ለጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከት ሹመታቸው ያልጸደቀላቸው አቡነ ገብርኤል ሲያምርን መልሰው በቦታው ለመሾም ደብዳቤ ቢጽፉም በጠቅላይ ቤተክህነቱ በምን ስልጣን ተብለው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ይህም ቢሆን ግን የሰውየውን ህገ ወጥ አካሄድ ሊያግደው አልቻለም። በገጠሪቱ የሃገሪቱ ክልል ያሉ ካህናት ያላቸውን የህግ እውቀት ክፍተትና የማቅን ከለላ በመጠቀም ሀገረ ስብከቱን በህገ ወጡ ማኅተም ማመሱን አልተወም።
ይህ ግለሰብ በስልጣን ላይ ሳለ ተደጋጋሚ ወንጀሎችን የፈጸመ ሲሆን ከነዚህም ጥቂቶቹ
1.     በ2000 ዓ.ም. የታተመው የሚሊኒየሙ መጽሐፍ መሸጫ ዋጋው 100 ብር ሆኖ ሳለ በ600 ብር በመሸጥ ከመጽሀፉ የዋጋ ልዩነት 30000 ብር ለግል ጥቅሙ አውሏል። ይህም በበቂ የሰው ማስረጃ የተረጋገጠ ነው።
2.    የመጽሐፉን ዋና ገንዘብም አስካሁን ለጠቅላይ ቤተክህነት አላስረከበም።
3.    ከሃገረ ማርያም ት/ቤት ተቀብሎ የነበረው ገንዘብ 360000 ብር ጉድለት እንዳሳየ በኦዲተር ተረጋግጦዋል። ይህ 360000 ብርም የት እንዳደረሰው አይታወቅም።
4.    ከአለምእሸት ጋር በመሆን 15000 ሺህ ብር ከሀገረ ማርያም ወስዷል።
በነዚህ በተገለጹ እና በሌሎችም እሱ እንዳጎደላቸው በሚታወቁ ነገር ግን ማስረጃ ባልተገኘባቸው ወንጀሎች የሚጠረጠረው ሲያምር በሕግ መጠየቅ ሲገባው በቦታው እንዲመለስ ለማድረግ መሞከር ሊያስከትለው የሚችለው ችግር ግልጽ ነው። እንዲያውም ለጠቅላይ ቤተክህነት አልታዘዝ በማለት ከሰራ መሰናበቱ መሸፋፈን የማይቻል እውነት ስለሆነ የሱ ጉዳይ እዛው ጠቅላይ ቤተክህነት ሊታይ የሚገባው መሆኑ ግልጽ ነው።
እንደ እነ ሲያምር እና አለምሸት ያሉትን ወንጀለኞች አቅፎ የሚንቀሳቀሰው አፋኙ ማኅበረ ቅዱሳን ለእውነት ባይገዛ እንኳ አንዳንዴ ለራሱ ሲል እንዲህ ያሉ ወንጀለኞችን ከፊቱ ቢያርቅ ሊጠቅመው ይችላል እንላለን። ለነገሩ ማኅበሩ የወንጀለኞች ማጠራቀሚያ ስለሆነ ነፍሰ ገዳዮችን ለማቀፍ ያላመነታ ድርጅት ገንዘብ የሰረቁ ሰዎችን ማስጠለሉ ብዙም ላይደንቅ ይችላል።
ባለፈው ሳምንት ገልጸንላችሁ እንደነበረው አጣሪ ኮሚቴ ወደ ቦታው እንዲሄድ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም አሁን እንደሰማነው ደግሞ ውሳኔው ተሽሯል። ውሳኔው እንዲሻር ምክንያት የሆነው ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተሉ ያሉት ቅዱስነታቸው ሳያውቁት በጎን የተወሰነ ውሳኔ በመሆኑና በአጣሪ ኮሚቴው ውስጥ አንደ አለምሸት ያለ ቀንደኛ የማኅበረ ቅዱሳን አባል እና ተላላኪ በመገኘቱ ማጣራቱ ፍትሀዊነት ሊጎለው ይችላል ተብሎ በመገመቱ ነው።
ጉጂ ቦረና ሊበን ዞን ሀገረ ስብከት እና ቡሊ ሆራ ነዋሪ ህዝብ አሁንም እየተሰቃየ ይገኛል። ቤተክርስቲያን የፍትህ ምሳሌ መሆን ሲገባት ፍትህ ነጣቂዎች እንዲህ የሚፏንኑባት መድረክ ሆናለች። ለግል ጥቅም እንጂ ለእውነት የማያደሉ ሰዎች ስብስብ የሆኑ ማኅበራትን በጉያዋ ይዛም ተገቢውን ፍትህ የማስፈን እድልዋን መጠቀም አትችልም። ስለዚህ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ማኅበራትን ስርዓት ማስያዝ ግዴታዋ ነው። የህዝብ እንባ ወደ ላይ ወደ ቅዱሱ ጌታ ደርሷል። በፍቅር ያልታዘዙ ሁሉ በልምጭ የሚታዘዙት ቀን ከዕለት ወደ ዕለት እየቀረበ ይገኛል። ቤተክርስቲያን የልጆችዋን ጩኸት ትስማ። የሰማይ አምላክን አክብራና ፈርታም ለልጆችዋ ችግር በቶሎ ትድረስ።

13 comments:

  1. werae bicha!!! tera nachihu!

    ReplyDelete
    Replies
    1. trawema ante nehe. gefachu segeletese kemesetekakel sedeb new yemikenachu.

      Delete
    2. ቤተክርስቲያን የልጆችዋን ጩኸት ትስማ። የሰማይ አምላክን አክብራና ፈርታም ለልጆችዋ ችግር በቶሎ ትድረስ።

      leba atasemesele!!!!

      yebetekirstiyane chigere menafeqanena leboche enji mk ayedelem

      Delete
  2. አንዳንዶች ስለማኅበረ ቅዱሳን ሽፍታነት ስንናገር ከሜዳ አንሰተን የጥላቻ ስም የምንለጥፍበት አድርገው ይቆጥሩናል። ነገር ግን አጣፍቶ ከሚለብሰው ነጠላ ጀርባ የሽፍታነት መገለጫ ያለበት የመሠሪ አባላት ስብስብ መሆኑን የሚያሳያቸው ግብራት ከምንም በላይ ማረጋገጫዎች ናቸው። /ይህንን ስንል ግን በቅንነትና በየውሃት መንፈስ ያሉትን አባላቱን ሳንጨምር ነው/ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ እስካሁን ያልበረደው የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ሀገረ ስብከቶች እየታመሱ ከቆዩ ሁለት ዓመት ያለፋቸው መሆኑ ነው። የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ አገልጋይ የሆነው ሲያምር ተ/ማርያም በመንበረ ፓትርያርክ ውሳኔና በሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ ወደ ትንሣዔ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት መዛወሩን ከአንዴም ሦስቴ ደብዳቤ ተጽፎለት ሳለ እሱ ጫንቃውን ያሳበጠውን ማኅበር ተተግኖ ሽፍትነቱን በማጠናከር በእምቢታው ከጸና ሁለት ዓመት አልፎታል። ቤተክርስቲያን ስታዘው ያልተቀበለ ሽፍታ፤ ሃዋሳ ሆኖ የማንን ቤተክርስቲያን ሊመራ ይፈልጋል? ብለን ብንጠይቅ ያልጨረሰው የማኅበረ ቅዱሳን ስራ ስላለ ያንን ሳይፈጽም እንዳይመለስ ኅሊናውን ስላሳመነ እንደሆነ ግልጽ ይሆንልናል። የሀገረ ስብከቱን መኪና ይዞ ጠፋ፤ ማኅተምና የጽ/ቤት ንብረቶችን አላስረክብም አለ፣ በህግ ተጠየቀ፤ ከዚህ ሁሉ ሽፍትነቱ ይባስ ብሎ ከደጅ ሆኖ በማኅተሙ እየጻፈ ሰው ያግድ ጀመር። እንግዲህ እነዚህ የሽፍቶች አባላት ስብስብ ናቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት! አሸባሪ ማለት ከዚህ ውጪ ምን ሊመጣ ነው? እንኳን በበላይ አካል ተዛውረሃል የተባለ ግለሰብ ይቅርና ጠንካራ ሠራተኛ የሆነ ሰው እንኳን አታስፈልግም ከተባለ ጥያቄውን በሕግና በሕግ ብቻ ለማስፈጸም ይፈልጋል እንጂ ቀሚስ ለብሶ ይሸፍታል እንዴ? ሽፍትነት የተፈጥሮው የሆነው ማቅ አንድ አባሉን «ግብረ ጥፉን በስም ይደግፉ» እንድንል ሆኖ ለክፋት የጥበብ መግቦቱ፤ «መጋቤ ጥበብ»፤ ለክፋት ስማዊ ግብሩ «ሲያምር» የተሰኘው «መጋቤ ጥበብ ሲያምር ተ/ ማርያም» ያደረሰው ግፍና ዐመጻ አሳዛኝ ነው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. thank you brother. good explanation.

      Delete
    2. በእርስዎ አስተያየት እስማማለሁ፡፡

      Delete
  3. this is really sad. we are very sorry to know about this. the church must give solution for such kind of problem. mk is truly the enemy of the church.

    ReplyDelete
  4. ይህ ማኅበር 20 ዓመት ሙሉ ቤተክርሰቲያንዋን ቀለደባት። እግዚአብሔር ፈረድበት

    ReplyDelete
  5. አውደ ምህረቶች ስላልጻፋችሁት የሰባችሁት አልሰማኝም እና እኔም በአቅሜ የማኅበሩን ግፍ ለአንባቢዎቻችሁ ላሰማ።
    ማህበረ ቅዱሳን በነገሌ ገብርኤል ቤተክርስቲያኝ ያለውን ሰንበት ትምህርት ቤትንም ከ3 ቀን በፊት አሳሽጓል። አረ የፍትህ ያለህ። የዚህ ማኅበር ግፍ እኮ አንገላታን።

    ReplyDelete
  6. mk yebetekerestiyan tela new.

    ReplyDelete
  7. ማህበረ ቅዱሳን እንዲዘጋ የቤተክርስቲያን ልጆች በአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ፡፡
    እባካችሁን እንተባበር

    ReplyDelete
  8. በጭፍን ማኅበሩን አንደግፍ እውነትን እውነት እንበል ማደናገሪያ መጻፈባልቴት ይቅር የቤተክርስቲያን አባቶችን እንጠይቅ አለበለዚያ የኔቢጤዎቹ አስተያየት ከመስጠታችን በፊት ለግምገማ ከመቅረባችን በፊት መማር አለበለዚያ ዝም ብሎ አባቶችን ማዳመጥ እንጂ መዘባ… ይቅር

    ReplyDelete
  9. ምነው አቡነ ግብርኤል ለሰላም የመጡ መስሎን ነበር ሀገርዎ ሲገቡ ለካ ለአመጽ ነው የቆሙት ያባት ስራ ስሩ እባክዎ ስለ እማምላክ ብለው የጸልዩላት አንድነትዋን እንድታገኝ ለዚች ቤተክርስቲያን መልካሙን አስቡላት ፈተናዋን አታብዙት መከራ ነው የወረደብን ችግሩን መስማት በጣም ነው ተስፋ እያስቆረጠን ያለው ምን ልንሆን ነው ቤተክርስቲያን ነበረች ለህዝቡ መጽናኛ አሁን ግን የምንሰማው ሁሉ አንድ የነገር እሳት ጠፋ ሲባል በሌላው ይቆሰቆሳል እንቅል አጡ ምን የትቢት መንፈስ ተረጨባቸው ተው ሁላችንም ሰላምን እንፈልጋለን የያዘችሁት መንገድ ግን ልታፈርሱዋት ህዝቡን አታምሱት

    ReplyDelete