Thursday, July 12, 2012

አቡነ አብርሃም ከሐረር ሰንበት ተማሪዎች ተቃውሞ ገጠማቸው።

aba abreham tqawemo harer: Click here to read in PDF
(ሐምሌ 5 2004 ዓ.ም. ፣አውደ ምህረት/www.awdemihret.blogspot.com) ቤተክርስቲያን የሁሉም ልጆችዋ ነች። አባትም ሁሉን እንዲወድ ሁሉን እንዲጠብቅና ሁሉን እንዲመራ የሰማይ ትእዛዝ አለበት። ወገንተኝነት አባታዊ ባኅሪ አይደለም። ለሚሻለው ለወደዱት ታጥፎ ሰግዶ የጠሉትን ደግሞ አይንህን አያሳየኝ ማለት እንኳን ለጳጳስ ለአንድ የቀበሌ ሹምም ተገቢ ጸባይ አይደለም። ሸክሙን ማን እንደሰጠ ማስተዋል ከተቻለ ትከሻን አስፍቶ መጠበቅ ይገባል። በስማ  በለውና አንድን ወገን ለማስደሰት ተብሎ የሚሰራም ስራ ኋላ ላይ ማጣፊያ እንደሚያጥር ግልጽ ነው።
 ለማኅበረ ቅዱሳን ካደሩ የሰነበቱት አቡነ አብርሃም ሀረር ከተማ ውስጥ ያሉትን የሰንበት ተማሪ ተወካዮች ሰብስበው “የካሴት መዝሙሮችን ማዳመጥና መዘመር አቁማችሁ የማኅበረ ቅዱሳንን መዝሙሮች እየገዛችሁ ስሙ በጉባኤም አነርሱን ዘምሩ።” ብለው ለማዘዝ በመሞከራቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። 

አባ አብርሃም “ቤተክርስቲያን 2000 ዓመት የቆየችው ኢየሱስ ኢየሱስ ብላ አይደለም።” በማለት ኢየሱስ ኢየሱስ የሚሉ ዝማሬዎች ስህተት እንደሆኑ ለማስረዳት ቢሞክሩም የሰንበት ተማሪ ተዋካዮች ግን በአጸፋው “…እርስዎ እስካሁን የቤተክርስቲያን አባት ይመስሉን ነበረ። ለማን እንዳደሩና ከማን ጋር እንደሚሰሩ አሁን አወቅናል። ለማኅበረ ቅዱሳን ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ማዘጋጀት ይችላሉ እንጂ አልሸጥ ያለ ዝማሬዎቻቸውን እየገዛን ገቢዎቻቸውን እንድናሳድግ አይምከሩን። እኛ እርሰዎ ይቁሙ የሚሏቸው ዝማሬዎች ላይ ምንም ችግር አላየንም እርስዎም ችግሩን አላሳዩንም ዝም ብሎ ጌታ ከበረ በማለት ግን መቃመም ለምን በዝማሬዎቹ ህይወታችሁ ለመለመች የሚል ምቀኝነት ይመስልብዎታል። ዝማሬዎቹን መዘመር አናቆምም ከህይወታችን ጋር ተዋህደዋል። የእርሰዎ አባትነት ግን ሊቀር ይችላል። በእኛ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ልዩነት በማድረግም አባትነት የለም። ካገለገሉ ቤተክርስቲያንን ያገልግሉ አለበለዚያ ግን በሰላም ሀገራችንን ለቅቀው ይውጡ።…” በማለት ጠንካራ ተቃውሞ አሰምተዋቸዋል። ፕሮግራሙም በተቃውሞ ተቋርጧል።
በተቃውሞው ጥንካሬ የተደናገጡት አባ አብርሃምም የተወሰነ የአላማ ተጋሪዎቻቸውንና የቅርብ ወዳጆቻቸውን ሰብስበው  ተቃውሞውን ለማብረድ የሚችሉበትን ነገር ሲመክሩ “…ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የሐረር ሕዝብ ቅዱስ አባታችን ሀረር እንዲመጡ ጠይቆ  ነበር አልመጡም እኔ አስመጣቸዋለሁ። በዚህም ተቃውሞውን ማብረድ ይቻላል” ማለታቸው ተሰምቷል። ቅዱስነታቸውን አስመጥቶም አሳቸው የሀሳቤ ተጋሪ ናቸው እኔን መቃመም እሳቸውን መቃወም ነው የሚል አንድምታ ያለው መልዕክት ለማስተላለፍ ፍላጎታቸው እንደሆነ ታውቋል።  ለቅዱስነታቸው በዓለ ሲመት አዲስ አበባ የመጡት አባ አብርሃም ቅዱስነታቸውን ወደ ሀረር እንዲመጡ እንደጠየቁዋቸው ተሰምቷል። አባ አብርሃም ቅዱስነታቸው ወደ ሀረር እንዲመጡ የፈለጉበትም ዋነኛ ምክንያትም ሀረር እየተነሳባቸው ያለውን ተቃውሞ ለማብረድ ነው።
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ “ቅዱስነታቸው መናፍቅ ናቸው” እያሉ ይናገሩ እንደነበር ሲታወቅ በቅርቡ ግን አንድ አገልጋይ “ቅዱስነታቸውን መናፍቅ ካሉ በእርሳቸው የተሾሙት እርስዎም መናፍቅ ኖት” ብሎ ስለተናገራቸው እንዲህ ያለውን ንግግር ጋብ አድርገዋል።
አባ አብርሃም አሁን እያስጨነቃቸው ያለው በሀረር በህዝብ ተቀባይነት ማግኘት የሚችሉበትን ነገር ማመቻቸት ነው። ለዚህም ደግሞ ቅዱስነታቸውን ዋነኛ መሳሪያ አድርገው ለመጠቀም ፈልገዋል። ለቅዱስነታቸው የተለየ ፍቅር ያለው የሐረር ከተማ ህዝብ በከተማው ቢያገኛቸው የሚሰማውን ደስታ የተገነዘቡት አባ አብርሃም ለራሳቸው ገጽታ ግንባታ ሲሉ አንተ ሲሉ የሰደቡዋቸውን አባት ይቅርታ ሳይጠይቁ ሐረር ካልመጡልኝ እያሉ መለመናቸው አስገርሟል። የሲኖዶሱ ስብሰባ በመጣ ቁጥር ከማኅበሩ የቤት ስራ እየተቀበሉ ሲኖዶሱን የሚበጠብጡት እኚሁ አባት የሲኖዶሱ ስብሰባ ሲያልቅ ደግሞ እየተቅለሰሱ አቡነ ጳውለስ ስር ስር ማለታቸው ያስገርማል። ለማኅበረ ቅዱሳን ብለው የማያሸንፉትን ህሊናቸውን ከሚዋጉ ለምን በራሳቸው አቋም እንደማይራመዱ ጥያቄ ሆኗል። ምናልባት ወዲህና ወዲያ የሚያላትማቸው ማቅ ይደብቅልኛል ብለው ያመኑበት ጉዳቸው እያስጨነቃቸው ሊሆን እንደሚችልም ያስገምታል።
በተያያዘ ዜና በአቡነ አብርሃም ላይ የጉድ ሙዳይ የሚል መጽሐፍ የጻፈው ሲገለጽ በጊዜው በኢሜል በላከልን መልዕክት የመጽሐፉን ዝግጅት ሙሉ በሙሉ  መጨረሱን እና ለማሳተም እየጠበቀ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ስለ እሳቸው የገጽታ ግንባታ መጽሐፍ ይሁን መጽሔት ነገር ለማሳተም ተፍ ተፍ እያለ መሆኑን ስለሰማ ቀድመው እንዲያሳትሙ ጊዜ ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል። እንዲህ ያሉ ጽሁፎች ለጽሁፉ ተጨማሪ ግብዓት ስለሚሆኑ መጠበቁ አስፈላጊ ነው ብሏል። ዳንኤል ክብረት እጁን በልቶት የሀሰት ታሪክ ስለ አቡነ አብርሃም ባይጽፍ ኖሮ የጉድ ሙዳይ እንደማትጻፍ የገለጸው ሲገለጽ ማኅበሯ ያዘጋጀችውን ጽኁፍ እስክትበትን መጠበቁ አስፈላጊ መሆኑን አስምሮበታል። በተለይ ቀሲስ ደጀኔ ስለትህትናቸው የተናገራት ነገር መኖርዋ አዲስ ሀሳብ እንዳጫረበትና መጽፉን ለመጠበቅ እንዳስገደደው ገልጾልናል። ለደጀኔም አንድ ቀን እኔና አንተም ስለጅማ እንነጋገር ይሆናል። መጽኀፉ የማይታወቅ የተከደነ ምንም የለም ይል የለ!! በሉልኝ ብሏል።
ማህበረ ቅዱሳን እንቅልፍ አጥቶ በቀን በማታ መጽሐፉ ሊታተም ይችላል ብሎ የሚያምንባቸውን ማተሚያ ቤቶች እያካለለ እንዲሚውል ወሬው የደረሰው ሲገለጽ ይልቅስ አርፋችሁ ተቀመጡ እየነካካችሁ መዘዝ አታምጡ በሉልኝ ብሎናል።
አባ አብርሃምም በዚህ ጉዳይ ሰሞኑን ሀረር ላይ የተናገሩትን እንደሰማና ከእሳቸው ጋር ከመጽሀፉ ህትመት በኃላ ወይ በግንባር አሊያም በስልክ ሊያናግራቸው ሀሳብ እንዳለው ገልጿል። ለአቡነ አብርሃምም አይዞት እንደማውቀው ሚስጢር ሁሉን አልጽፈውም ከፍቼ የማሳያቸው ብቻ ሳይሆን ከድኜ የማበስላቸውም ብዙ ጉዶች አሉ። ብሏል።
አትሁኑት ወገን ላይጠቅማችሁ ሀሰት
ይልቅስ ታዘዙ ተረቱ ለእውነት
ሲል ግጥም ነገር የሞካከረው ሲገለጥ ስለማኅበረ ቅዱሳን ሞኝ አንጋሽ ሞኝ ቀስቃሽ ጉዞ በቅርቡ አንድ ዘገባ እንደሚልክልን ቃል ገብቶልናል።

4 comments:

  1. እኝህ አባት ሀረርን አላወቁትም መሰለኝ? እኛ መጨናነቅም መዘባረቅም አንፈልግም። ያው የአቡነ ያሬድ እጣ እንዳይገጥሞት ቢያስቡበት ይሻለል።

    ReplyDelete
  2. የሚገርመኝ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበሉትን አደራ ከመወጣት ይልቅ ሰዎቹ ድራማ እየሰሩ መሆናቸው ነው፡፡ሐረር የሚገኙ የሰንበት ት/ቤት ላይ በመዝሙር ጉዳይ ጫና ሲፈጠር ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡እድሜ ለማቅ ተላላኪዎች፡፡በተለይ አሁን በመላው የኦርቶዶክስ አማኙ ዘንድ እየተደመጡ ያሉትን ዝማሬዎች ከአገልግሎት መስጫ ክልል ዉጭ ለማድረግ የማየፈነቀል ድንጋይ የለም፡፡ቀድሞ የጥምቀት ጊዜ ነበር፡፡አሁን ደግሞ የአቡኑን መኖር እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር ጭራሽኑ ከቤ/ክ ለማጥፋት በሀገረ ስብከቱ(የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ማለት ነው) የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ኃላፊ የሆኑት መላከ ሰላም ታደለ ፊጣ በቅርብ ከሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ በማህበሯ የተሰጣቸውን 300 ዝማሬዎችን ብቻ እንዲዘምሩ በግድ ለማስፈረም ቢሞክሩም የማቅ መፈልፈያ ከሆኑት የቅዱስ ገብርኤልና የካቴድራል ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ዉጭ የቅዱስ ሚካኤልና የደብረ ገነት መድኃኔዓለም ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች ሀሳቡን ሙሉ በሙሉ ዉድቅ በማድረግ ጥለዉ ለመውጣት ተገደዋል፡፡እዚህ ደረጃ የተደረሰው አቡኑ ራሳቸው በአደባባይ አሁን ያሉትን ዝማሬዎች ሲያሻቸው ከዘፈን ጋር ሲያሻቸው ደግሞ ከሉተራውያኑ ጋር ለማመሳሰል በመሞከር ምዕመኑ “ዝማሬው የቤ/ክ አይደለም”ብሎ እንዲተወው የማድረግ ጥረታቸውን በመመልከት የልብ ልብ ስለተሰማቸው ነው፡፡ይህ ድፍረት ቀጥሎም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከሁለት ሳምንት በፊት ዘማርያን እንደ በፊቱ በቀትታ በአጥቢያ ስብከተ ወንጌል ኮሚቴ እየተጋበዙ የሚያገለግሉበት አሠራር መቅረቱንና እንደ ሰባኪያኑ ሁሉ በሀገረ ስብከቱ በኩል መጋበዝ እንዳለባቸው በደብዳቤ ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡ግልባጩን ለመንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት እንዲሁም ለአቡነ አብርሃም እንደሆነ የሚገልፀው ይህ ደብዳቤ ከበስተጀርባው የአቡነ አብርሃም ቀጥተኛ ትእዛዝ ለሆን እንደሚችል በብዙዎች ዘንድ ይታመናል፡፡ምክንያቱም ሥራ አስኪያጁ በሌላ ጉዳይ ስህተት በሠሩም በዝማሬ ጉዳይ ጣልቃ ይገባሉ ተብሎ አይታሰቡም እስከ አሁንም ድረስ ምንም ዓይነት ሀሳብም ሲያራምዱ ተደምጠው አያውቁም ፡፡ ነገር ግን በስማቸው እንዲወጣ ተገደው ሊሆን እደሚችል እንገምታለን፡፡ለዚህ ደግሞ ሁለት ነገሮችን በምክንያትነት እንጠረጥራለን ፡-
    1. ኛዉ-ከተሳካ ዘማርያኑንና ዝማሬውን ከአገልግሎት ማስጫ ክልል ዉጭ በማድረግ የማቅን ጉዳይ ለማስፈፀም ሲሆን
    2. ኛው- ደግሞ ደብዳቤው የተጻፈው በሥራ አስኪያጁ በመሆኑ በግለሰቡ ላይ ከአቡነ ያሬድ ጊዜ ጀምሮ በምዕመናን እና በአጥቢያ አገልጋዮች ዘንድ ያለውን ቅሬታ እንደመልካም አጋጣሚ በመውሰድ ፤በደብዳቤው ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ አቡኑ ራሳቸውን እንደ ቅሬታ አስውጋጅ ወይም ደግሞ ልክ እንደ ችግር ፈቺ ግለሰቡን ደግሞ እንደችግር ፈጣሪ አድረጎ በማቅረብ ተቀባይነት ለማግኘት የተጠቀሙት ዘዴ ሊሆን ይችላል፡፡
    ለማንኛውም አቡነ አብርሃም ሰሞኑን በርካታ ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በአብዛኛው ተቀባይነት ለማግኘት አልመው የሚጠሯቸው ስብሰባዎች ናቸው ፤አንዱም ሳይሳካ ቢቀር፡፡ለማንኛውም ለወደፊት ለርሳቸው የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖረኝም ለአሁን ግን የዲ.ትዝታውን “አናቋርጥም ዉዳሴ አናቋርጥም ምስጋና” የሚለው ዝማሬ የማጠቃለያ መልዕክቴም ጭምር ነው፡፡እግዚአብሔር ሁላችንንም ያስበን፡፡
    ይሥሐቅ ነኝ ሐረር አደሬ ጢቆ ሠፈር

    ReplyDelete
  3. አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ዘበነ የሚባለው የማቅን መንፈስ ተሞልቶ የነዘርፌና የነትዝታው መዝሙር ኢንዳይዘመር የከለከለ ታላቅ ወራዳ አገርጋይ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ መግለጽ እዎዳለሁ

    ReplyDelete