Wednesday, July 18, 2012

መንግስት ለማኅበረ ቅዱሳን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

masetenqeqiya lemk: Clicl HEre to Read in PDF
(ሐምሌ 11 2004 ዓ.ም. ፣አውደ ምህረት/www.awdemihret.blogspot.com)የበቀለውን እየነቀለ የታጨደውን እየበተነ ቤተክርስቲያንን የሁከት መንደር ያደረገው ማኅበረ ቅዱሳን አሰራሩን እንዲያስተካክል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው።
ማስጠንቀቂያው የተሰጠው በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ሲሆን የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች  የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጠርተው ውስጣቸውን እንዲያጠሩ፣ ሃይማኖቱ ከሚፈቅድላችሁ ወሰን ወጥተው ከሚፈጽሙት ድርጊት እንዲቆጠቡ፣ ከየትኛውም የአመጽ ሥራ በስተጀርባ ጥላቸውን እያጠሉ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲገቱ፣ ከሌላ ጽንፈኛ ሐይል ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቆሙ፣ ቤተክርሰቲያኒቱን በመበጥበጥና ስራዋን ሁሉ እቆጣጠራለሁ በማለት የሚያደርጉትን ሩጫ እንዲገቱ አካሄዳቸውን የማያስተካክሉ ከሆነ ግንከዚህ በላይ ሊታገሳቸው እንደማይችል እና መንግስት የሰበሰባቸው መረጃዎች ማኅበሩን ለማፍረስ እና በወንጀልም ለመጠየቅ በቂ  እንደሆኑ ተነግሯቸዋል።
ከአመሰራረቱ ጀምሮ እጁን በደም ነክሮ የተነሳው ማኅበር በተለያዩ ወንጀሎች እየተጠላለፈ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ እነ እሸቱ ለዛር እያደነከሩ የ8 ሴቶች ክብረ ንጽህናን ገፈው የመሰረቱት ማኅበር በደም አበላ እየተነከረ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲፈጽማቸው የነበሩ የነብስ ግድያ የሙስና እና የተለያዩ ወንጀሎች በሙላት የሚታወቁ ሲሆን ያስጀመራቸው የዛር መንፈስ የደም ግብሩን በየአመቱ በተለያየ መንገድ እየተቀበለ ይገኛል፡፡ 

ሁከት ባለበት ቦታ ሁሉ ከሰሁ ሁሉ ቀድሞ አለሁ የሚለው ማኅበር የሰከነውን እየበጠበጠ ያማረው እሸት ላይ አረም እየዘራ ይኸው ቤተክርስቲያንን 20 ዓመት ሙሉ እያመሳት ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያካሂድ የነበረውን የአመጻ መንገድ አሁን ደግሞ ጡንቻዬን አፈረጠምኩ ብሎ ወደ መንግስት ላይም ያዛረው ሲሆን በተለይም በሰሜን አሜሪካ ከፖለቲከኞች የባሰ ፖለተከኞ ሆኖ ኢትዮጵያዊውን እያመሰው ይገኛል፡፡ ዳንኤል ክብረትም በስልታዊ መንገድ ሲሸሸው የነበረውን ፖለቲካ አሁን በይፋ “…የት ሄደን እንተንፍስ ተጨቆንን እኮ…” እያለ በአሜሪካ ባለችው ቤተክርስያቲን መድረክ ላይ መናገር ጀምሯል፡፡
ማኅበሩ ኢትዮጵያ ውስጥም በተለያየ መንገድ መንግስት የማዳከም ስራ እየሰራ ሲሆን በህዝብ ስሜት እየገባ ያልበላውን እያሳከከ ህዝቡን በተለያያ የአመጻ መንገዶች እየቀሰቀሰ ይገኛል፡፡ ለዚህም እንደ መሳሪያ በሕቡዕ  ብሎጎቹ እና በጆሮ ማስታወቂያ ይጠቀማል፡፡ እንደ ምሳሌ ማሳያ የሚሆነው የዝቋላ ገዳም ደን ቃጠሎ እና የዋልድባ ጉዳይ ነው፡፡ በዝቋላ ጉዳይ እሳት መነሳቱ እውነት ነው፡፡ በርካታ የቤተክርስቲያን ልጆች ሕይወታቸውን ሰውተው እሳቱን ለማጥፋት ያደረጉትም ርብርብ እጅግ የሚያኮራና በታሪክ ፊትም ስማቸውን የሚያስጠራ ነው፡፡
የእሳቱ መነሻ ግን የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች ይሉት እንደነበረው በመንግስት አሊያ ደግሞ በእስላሞች ምክንያት የተከሰተ አልነበረም፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ የበልግ ዝናብ በዘገየ ቁጥር እሳት መነሳቱ ተደጋጋሚ ክስተት ነው፡፡ ባለፉት በርካታ የበልግ ዝናብ በዘገየባቸው አመታት ሁሉ በጥቂት ምክንያት እሳት እየተነሳ የማይተኩ ደኖች ወድመዋል፡፡ ይህንንም እውነት እያወቁ ግን ይሆነኝ ብለው መንስኤውን ወደ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ለመውሰድ መሞከራቸው አሳዛኛም አሳፋሪም ድርጊት ነበር፡፡
መንግስት መሳሪያ ለማጓጓዣ የገዛቸውን ኢሊከፍተሮች በማጥፍት ሥራው ላይ ለምን አልተሰማሩም በማለት ኢሊኮፍተሮች በእሳት ማጥፋት ዘመቻ ሲሳተፉ በቴሌቪዝን ከማየት ባልዘለለ እውቀታቸው ሲተቹ አንብበናል፡፡ በኢሊኮፍተር እሳት በማጥፍት ሙያ የሰለጠነ ባለሙያ ሳይኖረን የእሳት ማጥፊው ኬሚካል ሳይገዛ ለእንደዚህ አይነት ዘመቻ መሰማራት የሚችሉ አሊኮፍተሮች በሌሉበት ሁኔታ አሳት አጠፋ ብሎ ኢሊኮፍተር ይዞ መውጣት የበለጠ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ የስም  ጥፍት ዘመቻው ግን ህዝቡ በመንግስት ላይ የሚያቄምበት ምክንያት ሆኖ አልፏል በዚህም ማኅበሩ ሊያሳካው የፈለገውን ግብ በከፊል መቷል፡፡
የዋልድባም ጉዳይ ተመሳሳይ ነው ማኅበሩ በሕጋዊ ዌብ ሳይቱ ስለዋልድባ ያጠናሁት ጥናት በማለት ፕሮጀክቱን ትክክለኛ አቀማመጥና ይዘት ከጎግል ርዝ በወሰዱት ካርታ አስደግፈው እያቀረቡ እና ችግር የለውም እያሉ በህቡዕ ብሎጎቻቸው ግን ገዳሙ እንደፈረሰ በመስመሰል ከፍተኛ ሁከት በመዘርጋት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሕጋዊው ሪፖርታቸው ፋብሪካው በአንዱ በኩል ከገዳሙ 36 ኪሎሜትር በሌላኛው በኩል ደግሞ በ50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ብሎ ሲያበቃ በእነ ደጀ ሰላምና አንድ አድርገን ግን የተነስ ታጠቅ ዝመት ቅስቀሳውን ሲያካሄድ ሰንብቷል፡፡ ሰሞኑን እንኳ ለ3 ሳምነት ያህል አርምሞ ላይ የነበችው ደጀ ሰላም አቡነ ጳውሎስ ጀርመን አገር በዋልድባ ጉዳይ ሰልፍ እንዳይደረግ አስደረጉ ሲል አስነብቦናል፡፡
ሰልፉ ሰላማዊ እስከሆነ ድረስ አንጀላ መርከል እንኳ መከልከል በማይችሉባት ጀርመንን በመሰለ  ሀገር አቡነ ጳውሎስ ሰልፍ አስከለከሉ ብሎ ማስወራት እራስን ከግምት ውስጥ ከመጣል ወጭ የሚያስገኘው ጥቅም የለም፡፡ የጭፍን ደጋፊ ልብና ስሜት ግን ጠርቆ ለመያዝ ይረዳ ይሆናል፡፡ ለንግስ ወደ ገዳሙ የሚሄዱ ክርስቲያኖችን ለአመጽ  እየሄዱ እንደሆነ በማስመሰል የተከተሉዋቸው ቅስቀሳ ማድረግንምም ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ ፓትርያርክነቱ እነደ ጭን ገረዶቻቸው በአይናቸው ላይ የሚመላለስባቸውን አቡነ ሳሚኤልን በመጠቀም የዋልድባ መነኮሳትን ለማነሳሳትና ወደ አመጽ ለመግፋትም ያልተሳካ ሙከራ አድርጓል፡፡
ገና ለገና መንግስት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች  ለማነጋገር ቀጠሮ መያዙን ስትሰማ በከፍተኛ ድንጋጤ ተመታ ኮማ ውስጥ ገብታ የነበረችው አንድአድረገንም ከ10 ቀናት ቆይታ በኃላ ሪከቨር አድርጋ ሰሞኑን ወደ አደባባይ ብቅ ብላለች።  ኮማ ውስጥ የገባ የሚናገረውን እውነት እውነቱን ብቻ እንደሆነ ሁሉ አንድ አድርገንም የመታታት የድንጋጤ ምች አስለፍልልፍ የሚባለውን ጋኔን አስነስቶባት ማኅበረ ቅዱሳን አይደለሁም እያለች ስትገዘት እንዳልነበር እወቁልኝ ማኅበረ ቅዱሳን ነኝ ወከባ ስለበዛብን የጭንቀት ጣሩ እስኪለቀን ኮማ ውስጥ ገብቻለሁ ብላ ተሰናብታን ነበር። እንደ ደጀ ሰላም በዝምታ ማሸለብ እየቻለች ኡኡ ብላ ማኅበረ ቅዱሳንነቷን ተናግራ ለማሸለብ መሞከርዋ ድሮስ የሕጻን ነገር እንዳልበሰለ ሽሮ በሁሉ ነገር ያንተከትካቸዋል አስብሎባቸዋል።
ማኅበሩ ሰው የለውም ወይ እያስባለ ያለው የአንድ አድርገን አካሔድ በርካታ የአካሄድ ስህተታቸውን እያጋለጠ ያለ ሲሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚነሳ ረብሻ እና ብጥብጥ ሁሉ አለሁላችሁ የሚለውን ማኅበረ ቅዱሳን ሀሳቦች እንደወረደ እየነገረን ማኅበሩን እስትራቴጂ አልባ አድርጎታል። ከእድሜ በቀር መንፈሳዊ አውቀት አልያም የስነጽሑፍ ዘዴን የማያውቁት ህጻነ አእምሮዎቹ አንድአድርገኖች ባልተገራ ብዕራቸው ያገኙትን እየጨረገዱ የማኅበሩን ውል አልባ እንቅስቃሴ እያሳዩን ይገኛሉ።
በዚህም ይሁን በዚያ ማኅበሩ የአመጻ ተቋም መሆኑ እየተደረሰበት መጥቷል፡፡ እግዚአብሔርን አማክሮ ሳይሆን በጥንቆላ እና በአመጻ የተቋቋመው ማኅበር  ተፈጥሮው እሺ ስለማይለው ከአመጽ አካሄድ መውጣት እየከበደው ይገኛል፡፡ ለመካሪ ያልተመቸው ማኅበር በመንግስት እጅ ሊወሰድበት የሚችለው እርምጃ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ሲደርስ የምናየው ይሆናል፡፡

19 comments:

  1. meles zenawi is critically sick b/c he started to challenge MK( an association established by the help of god), god may give him his warnings. if the prime minister , with his dictator behavior, keeps on challenging or attempting to destroy Mk, FOR SURE, HE WILL DIE. AS TO THE SO CALLED PATRIARCH, HE IS NOT THE FOLLOWER OF THE CHURCH, RATHER HE IS MENAFIK, THAT IS WHY GOD IS GIVING HIM TIME FOR 'NESAHA'

    ReplyDelete
    Replies
    1. ትንሽ ጭንቅላት ያለው ሰው መጥፎ ነው፡፡ ሀሳቡ ከአንተ አይነት ሀሳብ አይለይምና ነው፡፡ መለስ ቢታመመም የሚታመመው እንዳንናተ አይነት ራስ ምታቶችን በቸልታ በማለፉ ነው እንጂ በመናገሩ አይደለም ያደረባችሁ መንፈስ አሰራሩ አደገኛ በመሆኑ ተደብቃችሁ ቆያችሁ እንጂ የእናንተ ግፍ እኮ ጽዋው ከሞላ ቆየ አሁን የታየው ሲፈስ እና አደባባዩን ሲያጥለቀልቅ ነው፡፡ ይልቅስ ንስሀ ገብተህ ከእግዚአብሔር ተዋወቅ ማቅ ወይም ሞት ብለህ የተመኘኸውን ሞት በነፍስህ እንዳታገኛት፡፡ መለስ ድኗል ስራውንም ይቀጥላል ጤንነቱ ሙሉ የሚሆነውም እናንተን ያፈረሰ ዕለት ነው፡፡ትንሽ ጭንቅላት ያለው ሰው መጥፎ ነው፡፡ ሀሳቡ ከአንተ አይነት ሀሳብ አይለይምና ነው፡፡ መለስ ቢታመመም የሚታመመው እንዳንናተ አይነት ራስ ምታቶችን በቸልታ በማለፉ ነው እንጂ በመናገሩ አይደለም ያደረባችሁ መንፈስ አሰራሩ አደገኛ በመሆኑ ተደብቃችሁ ቆያችሁ እንጂ የእናንተ ግፍ እኮ ጽዋው ከሞላ ቆየ አሁን የታየው ሲፈስ እና አደባባዩን ሲያጥለቀልቅ ነው፡፡ ይልቅስ ንስሀ ገብተህ ከእግዚአብሔር ተዋወቅ ማቅ ወይም ሞት ብለህ የተመኘኸውን ሞት በነፍስህ እንዳታገኛት፡፡ መለስ ድኗል ስራውንም ይቀጥላል ጤንነቱ ሙሉ የሚሆነውም እናንተን ያፈረሰ ዕለት ነው፡፡

      Delete
    2. ante chewa mk asebehe tenagere afeleley yemetawen atlefelefe. benante mikneyate Yetawekechew betekerestiyan beegziabehere erdata testrkakelaleche melesem yegemerewen sera yecheresal enanetenem yatefal.

      Delete
  2. ደጀ ሰላሞች ቸር ወሬ ያሰማችሁ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን (ኮርማው) የሚታሰርበት ቀን እየደረሰ ነው፡፡ ከእንግዲህ ማንንም እየወጋ አያስቸግርም፡፡

    ReplyDelete
  3. ha ha ha Lemehonu enante manachihu ena lelawn titechalachu meyaziya mechebecha yetefaw!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  4. ክፉው መንፈስ ግን መልሶ። ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። ሐዋ.19:15

    ReplyDelete
  5. Tiru hilm new. Keman ga eyetemuagetachihu endehone bitawku lerasachihu tasibu neber. Daru sim zirzirachewun bezih Thihuf yastewawokachihun menafist silemimeruachihu kezih yebelete enditasibum hone endititsifu metebek aychalim.
    Gin mengist enante endemitasibut balbesele aemero yemimera yimeslachihual? Keekee keee.Dinkem zede... Helicopter bilo metsaf yalchale sew mahiberu sew yelewum minamin bilo mezelabedin min ametaw. Wana sirachihun yihin mahiber matlalat kemitaderguna seyitanin kemitagelegilu (kemitasdesitu) deg sertachihu wodefetary bitmetu yishalal. This is what I advice you. May God Help You to Come Out of this Trajectory.

    ReplyDelete
    Replies
    1. sele hilekofter yawerawe eko wendem andaderegene new. zore belehe reportun anbebe. maheberu sew yelewem wey yeteblew degmo ende andeaderegen yale yechewana yedenkora alekase selasemara new. sew binorew andeaderegenene blog belo yekefe neber? aymeselegeme. seleze amdemihretehene tetehe yemaheberune guwade kage.

      ለሰይጣን አገልጋይነት ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን የፈጠነም የተሻለም ስለማይገኝ እንኳን የማይፈልገው ወደ እርሱ ሊሄድ ፈልገውት ለሚጠቀጉትም ማህበረቅዱሳን ከኔ ወዲያ ማን ሊጠራ ብሎ በር የሚዘጋ ይመስለኛል፡፡ ትክክለኘው የአጋንንት አገልጋይ ማቅ ነው፡፡ለሰይጣን አገልጋይነት ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን የፈጠነም የተሻለም ስለማይገኝ እንኳን የማይፈልገው ወደ እርሱ ሊሄድ ፈልገውት ለሚጠቀጉትም ማህበረቅዱሳን ከኔ ወዲያ ማን ሊጠራ ብሎ በር የሚዘጋ ይመስለኛል፡፡ ትክክለኘው የአጋንንት አገልጋይ ማቅ ነው፡፡

      Delete
  6. ምን ዓይነት ማስጠንቀቂያ ነው በቃል ነው ወይስ በጽሑፍ ነው ያስጠነቀቀው። በደብዳቤ ከሆነ ለምን አታሳዩንም። እውነት ከሆነ በጣም የሚገርም ነው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. እንደዘገባው ከሆነ የቃል ነው፡፡

      Delete
  7. Yehe mahebere meferese yalebet mahebere new hasebu hulu kediyabilos mengeste yetekeda new. yemiseraw sira betenkol yetemola ena miemenanen wedediyabilos mengest yemimera new. mastenkekiyaw tiru new. ermejwe degmo yiketal beya tesfa adergalhu.

    ReplyDelete
    Replies
    1. አስበህበት ነው የምተናገረው ይህ ማህበር ማን ነው ታውቀዋለህ እነ አርዮስ በተወገዙበት ዘመን ብትሆን ያወገዙትን ማህበራት ምን ትላቸው ነበር ይፍረሱ ነው የምትለው ግን እኔ እንደሚመስለኝ ሁለቱንም ምበራት አታውቅም ይህን አስተያየት ከመስጠትህ በፊት ብዙ ጊዜ ብታስብ ይሻል ነበር፡፡ ፈጣሪ የንባብ ባህል ጥበብ ያድልህ

      Delete
  8. ማሥጠንቀቂያው የተሰጠበት ቀን ሐምሌ 3 ነው፡፡ በማህበሩ አማራሮች በሚስጢር እንዲያዝ ታዞ ለተወሰነ ሶች ነበር የተነገረን ዜናውን ስለሰራችሁት ገርሞኛል፡፡ የሆኖ ሆኖ ዜናውን ማሳወቃችሁ ጥሩ ነው፡፡ ሌሎች ያላሰፈራችሁዋቸውም ዝርዝር ጉዳዮችም ነበሩበት አንድ ቀን እልክላችሁዋለሁ፡፡ የሚሰራው ስራ አሳዛኝ ነው፡፡ መንፈሳዊነት ያላቸው ሰዎች የሚመሩት ማኅበር መሽሎን ነበር ግን ተሳስተናል፡፡ ብዙ ችግሮች አሉ ያሳዝናል፡፡

    ReplyDelete
  9. http://ethiopianreporter.com/news/293-news/7112-2012-07-18-06-34-50.html

    ReplyDelete
  10. እጅግ የሚያሳዝነው የማህበሩ ደጋፊ ነን የሚሉት የተሰበሰቡት የሚበዙቱ ስለመንፈሳዊን ነገር ግንዛቤ የሌላቸው ናቸው፡፡አሁን የማቅ ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ መታመም ጋር ምን ያገናኘዋልና ነው ማቅን ስለተቃወም ብሎ አስተያየት የሚሰጠው‹ANONYMOUS>JULY 18,2012 8:58AM እባክህ?አንድ ነገር ላሳስበው መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ ካወቀ ወደ ሉቃስ 13 ሄዶያለውን የመድሃኒታችንን ትምህርት ቢያነበውና የጠቅላይ ሚንስቴሩ መታመም ለእርሱም የንስሐ ጥሪ መሆኑን ቢያውቅ መልካም ነው በዚህ በጻፈው ጽሑፍ የጻፈውን አያውቀውምና ይቅር ይበለው አምላካችን ሌላ ምን እንላለን!!
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  11. betam tasazinalachehu Enanitem lmengist asibachehu ayedelam lnufakaachu new enji

    ReplyDelete
  12. kikikikikikikikik

    ReplyDelete
  13. hate doesn't last you longer because you should know who dealing with, it is MK who stood with God will not like you guys who are martialist. MK is true believers God is with them matter what say still know what they are doing including government officials. so don't wast your time. instead do something good for your church if really care about your church! the more you guys talk about MK the more they grow keep hating. my God keep MK protected and bless their hard work amen!!!

    ReplyDelete