Friday, July 13, 2012

“ኢሳት”: በማቅ የአፍዝ አደንግዝ ፖለቲካ የተለከፈ የጽንፈኞች መናገሻ!

esat :Click here to read in PDF
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

(ሐምሌ 6 2004 ዓ.ም. ፣አውደ ምህረት/www.awdemihret.blogspot.com)(ይህ ጽሑፍ የተወሰደው / ሙሉጌታ ወልደገብርኤል ለረጅም ጊዜያት ፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበረሰባዊ አመለካከታቸውን በቋሚነት ከሚገልጹበትና ከሚጽፉበት ታዋቂ ከሆነው "ከኢትዮጵያ ሪቪውድረ ገጽ ሲሆን በአሁን ሰዓት ግን ጽሑፉ ከስፍሯው ተነስቷል። መልካም ንባብ )
 
አሁን አሁን “ኢሳቶች ምን ነው ያለጸባያቸው?” ተብሎ ዜናዎቹ፣ ዘገባዎቹና ሐተታዎቹ በቸልተኝነት የማለፉ ነገር ወደ መሟጠጡ ተደርሷል።[1] ጉልህ የአደባባይ ሞያዊ ህጸጾቹንና ሥነ- ምግባራዊ ችግሮቹንም በፈቃደኝነት ለመነጋገርና በመተማመን ላይ የተመሰረተ የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ራሱን ካላዘጋጀና ችግሮቹንም ለመፍታትም ዝግጁ ካልሆነ ማዕከሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በተመልከተ ለሚሰራቸው ዜናዎች፣ ለሚያቀርባቸው ዘገባዎችና እንዲሁም ቁንጽል ሐተታዎች የሄደበትን ርቀት ያክል በመጓዝ ከስር ከስር ተገቢ ምላሽ መሰጠቱ የማይቀር ነው።
ይህም በመሆኑ ችግር ያለበት ችግር ፈጣሪ ወከበኛ ካልሆነ በስተቀር እውነትን በማድበስበስና በማዳፈን በአንጻሩ ነጭ ሐሰትንና ቅጥፈትን በመዝራት፣ ውዥንበርም በመፍጠር ለጥቂት ግለሰቦናችና ልሂቃን የሥልጣን ጥም ማርኪያ ተብሎ በሕዝብ ደካማ ጎን በመግባት ንጹሐን ዜጎች በኃይማኖት ስም በመቀስቀስም አላስፈላጊ መስዋዕት እንዲከፍሉ የማድረጉ የ“ማህበረ ቅዱሳን” የመተላለቂያ ስልት መኆን መቀበል የማይቻል ነገር ነው፡

ከዚህም አልፎ ዜናው ደም በተጠሙ፣ በሕግ ፊት፣ ኃላፊነት በማይወስድ አካል እየተዘጋጀ የሚቀርብ ተራና በሬ ወለደ ወሬ መሆኑን እየታወቀ ሆን ተብሎ የማህበሩን የሁከት ድምጽ በማስተጋባት የሚገኙትን ማናቸውንም የመገናኛ ብዙሐን ጋር በሚካሄድው ግልጽ ፍልምያ የኢትዮጵያ ምድር ሰላም፣ የሕዝቦችዋንም አንድነት ለውጥ ለማየት የሚናፍቅ ንጹሕ ዜጋ በጽሑፉም ሆነ በጽሑፉ አዘጋጅ ግለሰብ “ለምን እንዲህ አልክ?፣ ለምንስ ኢሳት ነካህ?” በማለት ፊቱን የሚያዞርበት አልያም የሚያኮርፍበት አንዳች ምክንያት አይኖረውም። በተረፈ “ኢሳት” ማለት “ታቦተ ጽዮን” አይደለም የማይነካው! ሰይጣንም ቢሆን ስሙና እኩይ ምግባሩ በቅድሳት መጻህፍት የሰፈረው በቁልምጫ “ሲጡ! የእኔ አባት!” እያልን እንድናመልከው ሳይሆን ማንነቱ አውቀን ራሳችንን ከወጥመድ እንድንጠብቅ ነው

ከጥቂት ቀናቶች በፊት ሁለት እግር አለኝ በማለት በአንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት የሚንጠራራውና የሚውተረተረው ይህ ራሱን የቅዱሳን ማህበር በማለት የሚጠራ ሕጋዊ ሽፍታ በስውር በሕዝብ መካከል ሁከት የሚቀሰቅስባቸው  የቀውስ መድረኮች መካከል አንድ በሆነው “ደጀ ሰላም” በማለት የሚታወቀው የጡመራ መድረክ ሰኔ 27/2004 ዓ.ም (ላይ 4/ 2012) የሚጮክ ርዕስ ያለው ዳሩ ግን ውስጡ ገለባ የሆነውን እንዲህ በሚል ርዕስ ለንባብ አብቅቶ ነበር “የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት በነዋሪው ተቃውሞ ለተቃጠለው የፕሮጀክቱ ዶዘር እና ለተጎዱት ሠራተኞች ሓላፊነት እንዲወሰዱ እየተገደዱ ነው” ሲል። “ማህበረ ቅዱሳን” በግላጭ (በስምዓ “ጽድቅ” ጋዜጣውና በሐመር መጽሔት)  የማይዘግበውና የማይለው ነገር በስውር በከፈተው የሁከት መድረኩ ከዚህም የባሰ ሌላ የፈለገውን ቢለፍፍ ምንም ባላሳሰበ ታድያ ወሬው ሳይውል ሳያድር ህጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ለዛውም መቀመጫው በምዕራቡ ዓለም የሆነ አንድን ዜና በመዘገብ ረገድ ሊወሰዱ የሚገባቸው ጥንቃቄዎችን ወደ ጎን በመተው እንዴት ነው በተደጋጋሚ ጉልህ የሆነው ተጥያቂነት የጎደለበት ስራ ሊሰራ የሚችለው? “ደጀ- ሰላም  ከስፍራው የሚገኙ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው … ፣ ድረ- ገጹ እንዳለው…” እየተባለ በፈጠራ የተሰራውን ዜና ሳይውል ሳያድር ቃል በቃል ማስተጋባትስ አያሳፍርም?[2]


ቅምሻ:
የጽሑፉ ዓላማም ሆነ የጽሑፉ አዘጋጅ ግብ “ኢሳት” በአሁን ሰዓት እያሳየው ያለው ዕድገትና ከየአቅጣጫው እያገኘው ያለውን ተቀባይነት እንዲሁም እያስመዘገበው የሚገኝ አመርቂ ውጤት ጠብቆ አማራጭ ድምጽ ይሆን ዘንድ ስለሚፈለግ ሲሆን ሌላው ነጥብ ደግሞ “ኢሳት” ለሕዝብ የቆምኩ የሕዝብ ሀብትና ንብረት ነኝ እስካለ ድረስ የጽንፈኞችና የአጥፍቶ ጠፊዎች መናገሻ አይሁን! በማለት የተጻፈ ነውየጽሑፉ ይዘት (በከፊልም ሆነ በመላ) ከፍ ሲል በተገለጸው ዓላማና ግብ ውጭ በመመንዘር የተለየ ትርጉም በመስጠት፣ እንዲይዝም በማድረግ ለሚሰማ ማንኛውም ዓይነት የማጉረምረም ድምጽ ጸሐፊው ኃላፊነት አይወስዱም
ራሱን የቅዱሳን ማህበር ሲል የሚጠራ ጽንፈኛ ግብረ እኩይ ድርጅት በሀገር ውስጥ ኃይማኖታዊ ሽፋን ሰጥቶ ከሚዘራው ፖለቲካዊ እንክርዳዱ በተጨማሪ በውጭው ዓለምም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ተጠሎ የዘረጋውን የጥፋት ወጥመድ ለረጅም ዘመናት አንድነቱን ጠብቆ የመጣውን ሕዝብ በጎሳበኃይማኖትበኑሮና በትምህርት ደረጃ በመከፋፈል፤ ቤተ- ክርስቲያንን በማተረማመስና ሀገርን በመበታተን ሊያገኘው የሚችለውን ትርፍና በእንቅልፍ ልቡ/በምናቡ በሳለው ዙፋን (የሥልጣን ማማ) ላይ ተቀምጦ/ወጥቶ ሰባና ሰማኒያ ሚልዮን ሕዝብ በግንባሩ ድፍት ብሎ “ሰጊድ ላንተ!” እያለ ሲሰገድለት እየታየው የምድሪቱ ሀብትና ንብረትም ጎተራው መልቶ ሲፈስ እያየ፣ ወጪ የሌለበት ገቢውንም እያሰላና እያለመ የሚባክነው ሕልሙንም እውን ለማድረግ መልኩንና ምስሉን እንደ እስስት እየለዋወጠና እንደ እባብም እየተቅለሰለሰ ስቶ ያላሳሳተው አካልና ሰርጎ ያልገባበት ስፍራ ፈልገህ ለማግኘት አዳጋች እየሆነ መጥተዋል። የትም ስፍራ ቢሄዱ በተለይ በሚድያው በኩል በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው በአንድም በሌላም በግልጽም በስውርም የሞት ጥላው ያላጠላበት፣ ራሱን (የአካሉ ክፍል) ያላስገባበት/ያልሰወረበት፣ እርሾውን ያልቀረቀረበት ቦታና ምግቡ የሆነውን የመቃብር አፈር ያልነሰነሰበት የለም። ይህንንም ያደረገበት (ሚድያዎችን መቆጣጠር እንደ ስልት ስራዬ ብሎ የተያያዘው ማለት ነው) ዋና ምስጥር:
አንደኛ- በየሚድያውና የህትመት ውጤቶች በሆኑ መገናኛ ብዙሐን ባስቀመጣቸው ወኪሎቹ አማካኝነት በግልጽም ሆነ በስውር የነፍስ ግድያ ጨምሮ የሚፈጽማቸው አሰቃቂ ወንጀሎች፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ሊያስገኙለት የሚችሉትን ንብረትነታቸው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የሆኑትን ንዋያተ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሳ ቅርሶች ከሀገር ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭው ዓለም በመሸጥ የሚያካሂደውን ከፍተኛ የሆነ የዘረፋ ወንጀሉን ለማዳፈን፣ በተለይ በሀገሪቱ ገጠራማ ክፍሎች የሚገኙትን ገዳማትና አድባራት አገልጋዮች የሆኑትን ካህናት ቀሳውስት የሚያደርሰውን ግፍና በደል በይፋ ለህዝብ ጆሮ እንዳይደርሱ ለማፈን፤ በተጨማሪም እውነተኛ ገዳይ ማንነቱ፣ አሳዳጅ ድርጊቱና የአመጽ መንገዱን ለማድበስበስ ብሎም ደብዛውን ለማጥፋት ሲሆን:
ሁለተኛ- ደግሞ የሌላውንና ያልሆነውን በፈጠራ ዜና እየሰራና እያሰራ የራሱን መልካምነት እንዲያውጅ፣ እንዲነገርለትና ብሎም ብዥታ ለመፍጠር ይህን አደረገ።
ከሞላጎደል “ማህበረ ቅዱሳን” በማስመልከት ሌላው ቢቀር በሀገር ውስጥ “በነጻ ፕሬስ” ስም የተቋቋሙት የግል ጋዜጦችና መጽሔቶች ለመጻፍም ሆነ እንደ አንድ ዜጋ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ተጠቅመው አስተያየት መስጠትም ሆነ ጽሑፎችን ለንባብ ማብቃት ጨርሶ የማይታለም ነው። እንደው የግል ፕሬሶቹ ስለ “ማህበረ ቅዱሳን” ስውር ፖለቲካዊ አጀንዳም ሆነ ኃይማኖታዊ ሕጸጾች ለንባብ ማብቃት በሕግ ያስቀጣል የሚል የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ያላቸው ነው የሚመስሉት። እዚህ ላይ የማይታለፍና መታወቅ ያለበት ተጨማሪ እውነት ቢኖር ማህበሩ በአካፋ ዝቆ ሲያበቃ በስኳር ማንኪያ የሚጥላትን ዕጣን ለቤተ- ክርስቲያን ሰጠ ተብሎ ለመዘገብ ግን ዝሩው አካል ነፋስ አይቀድማቸውም።
በተመሳሳይ “በዲያስፖራው” ማህበረሰብ ማካከል የሚገኙ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሐን በምስል የተደገፉ የዜና ማሰራጫ ማዕከሎች ሳይቀሩ በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ የሆነ እውቀት ያላቸው የቅድስት ቤተ- ክርስቲያን ልጆች የ“ማኅበረ ቅዱሳን” አደገኝነትና ነገ በአዲሱ በትውልድ ላይ ጥሎት የሚያልፈውን ጠባሳ ከወዲሁ ለማስወገድ ሕዝብ በስሙ እንዲሁም በአከባቢው እየሆነ ያለውን አዙሪት ያውቅ ዘንድ አውቆም በንቃት ራሱን ከበላተኛ አውሬ እንዲከላከል ግንዛቤ ለማስጨበት በሚደረገው እንቅስቃሴ ዕድሉ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ እንደማሽሎክ ሲበዛ ክፉኛ ጠባብ ነው።    
ይህ ማህበር አጣብቂኝ በገባ ቁጥር ያልተንጠላጠለበትና ያልተጠጋው የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ ያልተሻሸው የሚድያ ተቋም ለምስክር አለመገኘቱ ይበልጥኑ ትኩረት የሚሻ ነገሩም በቸልታ የማይታለፍ አድርጎታል። ታድያ በለመደው የቅጥፈት ስልቱ ሩቅ ሊጓዝ ያልቻለውና ገመዱን እያጠበበ የሚገኘውን ማህበር ገና በሚገባ እንኳን በሁለት እግሩ ያልቆመው በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ብዙ መስራት የሚጠበቅበት ኢሳት ማህጸን ውስጥ “ማህበረ ቅዱሳን” አካል ዘርቶ ጎልቶ መታየቱ እንዴት አያስጽፍም? የመጣ በልቶና ዝቆ “ውሃ ጠጭ!” ብሏት የሚፈረጥጠው ምድሪቱስ አይታዘንላትም? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ቢሆን ምን ያደረገ ሕዝብ ነው? ወይስ … ?
ሳምንት
መቀመጫው አምስተርዳም ያደረገውን የዜና ማዕከል  የእርስ በርስ  “እንወያይ” በሚል ርዕስ እ.አ.አ 05/08/2012 በባልደረቦቹ መካከል በከፊል በሃይማኖት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን ውይይት “ማህበረ ቅዱሳንን” በማስመልከት ለረጅም ደቂቃዎች የዘለቀው የአንደበት ፍሬና ተፋለሶቹ ያስነብባል። በተጨማሪም በውይይቱ የተፈጸሙትን ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ስህተቶች፣  አንድምታዊ ግድፈትኢ-ፍትሐዊ እይታሞያዊ የስነ ምግባር ጉድለትና ጥሰት እንዲሁም ስነ መለኮታዊ ህጸጽ ይገኙበታል[3] ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ርዕሰ ጉዳዮችም በተከታታይ ለንባብ ይቀርባሉ።
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
United States of America



[1] ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በተመለከተ ቤተ- ክርስቲያኒቱንና የሥርዓተ እምነትዋ ተከታዮችን የሆኑትን ምእመናን የማፈራረስና ውዥንብር የመፍጠር አጀንዳ አንግቦ ሌተቀን መሰሪነቱ የማይተው ራሱን የቅዱሳን ማህበር በማለት የሚጠራ የአራት ኪሎ ጎበዝ በሽፋን የሚሰራብቸው መካነ ድሮችና የጡመራ መድረኮች መካከል አንዱ የሆነውን “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀውን ልክፍት አንደ አንድ የመረጃ ምንጭ በመጠቀም “ኢሳት” በተደጋጋሚ የተያያዘው የማን አለብኝነት አስተሳሰብ ብቻ ያነጣጠረ ነው። በድጋሚ ጽሑፉ ሌሎች የተቋሙ ስራዎችን አይመለከትም።
[2] አሁንም ኢሳት “ማህበረ- ቅዱሳን” እንደዘገበው በማለት አይዘግብ አልተባለም። በሕግ ተጣያቂ አካል የሌለው የተቋሙን ስም የሚያጎድፍ ከተራ አሳፋሪ ሕብረት መፍጠርም ሆነ ቁርኝነት ከማድረግ ይታቀብ ነው።
[3] በምስል የተደገፈው ሙሉውን ውይይት ለመመልከት/ለማዳመጥ ቀጥሎ የተቀመጠውን “ሊንክ” ይጫኑ   http://www.youtube.com/watch?v=uKjZ9xlnmGA&feature=BFa&list=UU2AvdK6_3mGgyky6T82QBMQ


9 comments:

  1. Arif new ketayun begugut entebekalen

    ReplyDelete
  2. የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እባካችሁን ይህን ማህበረ ቅዱሳን የተባለ ኮርማ ለማሰር እንተባበር፤ ምክንያቱም ኮርማው አባት፤ እናት ፤አህት፤ ወንድም አይልም ሁልኑም በመውጋት እያባረረ ነው፡፡ እባካችሁን ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ፡፡ እንተባበር፡፡

    ReplyDelete
  3. bualitegna!!!!.eina min yitebesilihi!!!!

    ReplyDelete
  4. you guys what doyou taking about?

    ReplyDelete
  5. ለኢትዮጵያ ሪቪው
    የኢትዮጵያ መንግስትን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ያፍናል ብሎ የሚከሰው ኢትዮጵያ ሪቪው እሱም የነጻነት ተሟጋችነቱን የሚገልጽበት አንዱ መንገድ የማይቀበለውን ሀሳብ በማፈን መሆኑን እየገለጸልን ነው። የእናንተ ዲሚክራሲያዊነት የሚሰራው መንግስትን ሰድቦ ለሚጽፍ ብቻ መሆኑን ስላሳያችሁን እናመሰግናችሁኋለን። ልታስከብሩትና ልታከብሩት ያልቆረጣችሁለትን ዲሞክራሲ አትከራከሩለት እንላችኋለን። እንዲህ ያለው ለማኅበረ ቅዱሳን ወግኖ የመቆም አሰራር ማኅበሩ ምን ያህል በፖለቲካ እንደተጠላለፈ ያሳየናል።

    ReplyDelete
  6. Thank you Ethiopian Review! He should listen majority, not you. Alubaltegna!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ስለ ዲሞክራሲ እና ሰብዓዊ መብት ሁለመናዬን እሰጣለው እያለ የሰውን የመናገር መብት ሲያፍን እያየህ እንዴት ታመሰግናለህ? ጭፍንና ጠባብ በመሆንህ ታሳዝናለህ? የሚያስፈራው እንዲሁ እንዳለህ ጭፍንና ጠባብ ሆነህ ከሞትክ ነው።

      Delete
  7. በርታ ሙሌ ስለነዚህ እሾኮች ከመጸፍ ወደ ኃላ አትበል። በርታ በርታ በርታ

    ReplyDelete