Tuesday, July 3, 2012

‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ባይሄድ እግዚአብሔርነቱ እኮ ቀረ›› ዘሪሁን ሙላቱ

Eyesuse kirestos: Click here to Read in PDF
በዲያቆን ፈታሂ በጽድቅ
የፈለገውን እንዳመጣለት በመናገር የሚታወቀውና ከኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ውጭ ለራሱ አዲስ የሆነ አስተምህሮ የፈጠረው ዘሪሁን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ በፊት እና ከመጣ በኋላ በሚለው ሀሳብ ላይ  ብዥታ ያለበት ይመስላል ይህ ካልሆነ ደግሞ አድማጮቹን የሌለ የስህተት ሕይወት ውስጥ ለመክተት ቆርጦ ተነስቷል፡፡ ይህን ያልኩት እንዲሁ አለመሆኑን ለማረጋገጥ ከፈለጋችሁ ዘሪሁን አምኖበትና በስቱድዮ በሚገባ አስተካክሎ ያወጣውን የቪሲዲ መልእክት 37 ደቂቃ 32 ሰከንድ ላይ ወስዳችሁ እንድትመለከቱት አበረታታችኋለሁ፡፡
ይህን ስራ የገዛችሁት ሁላችሁም በእጃችሁ ስላለእኔ ለማለት የፈለኩት እንዲህ አልነበረም እነሱ አጣመውብኝ ነውሊል ምንም ምክንያት ባይኖረውም ሰውየው ግን ምን ዓይነት ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን ሁላችሁ እንድታስተውሉና ከዚህ በፊት እንዳልኩት እሱም ለመታረም ፍቃደኛ ከሆነ እንዲታረም ካልሆነም ደግሞ አባቶች አባታዊ ተግሳጻቸውን እንዲያስተላልፉ ይረዳቸዋል ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ስፍራ ላይ ዘሪሁን እንዲህ ሲል ትሰማላችሁ፡-
‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ባይሄድ እግዚአብሔርነቱ እኮ ቀረ እንደማንኛውም ሰው ሞቶ ፈርሶ በስብሶ ሊቀር ነው››፡፡
ይህ የኦርቶዶክስ ትምህርት ነው የሚል ሰው ካለ እሱ ኦርቶዶክስን የማያውቃት ሰው ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱም በፊት ከመጣም በኋላ እንዲሁም ተመልሶ ሲሄድም እግዚአብሔር መሆኑን ታምናለች እንዲሁም ታስተምራለችና፡፡
ዘሪሁን ግን ኢየሱስ በዚህ ምድር ሳለ እግዚአብሔር እንዳልነበረ በሚያስመሰል ሁኔታ ተመልሶ ባይሄድ ማለትም በዚህ ምድር ቢቀር እግዚአብሔርነቱ ቀረ ማለት ነው ብሎ አውጇል፡፡ ስለዚህ ይህን ሰው ኦርቶዶክሳዊ ነው ለማለት ያስችላል? ይህን ትምህርት ያስተላለፈበትስ መድረክ የኦርቶዶክስ መሆኑ አልቀረምን? አሁንስ ይህን ቪሲዲ ለመሸጥ እያስተዋወቁ ያሉቱ ኦርቶዶክሳዊያን ናቸው ለማለት ይቻላል?


በሙሉ አፉ በታላቅ ድፍረት በኦርቶዶክሳዊቷ መድረክ ላይ ቆሞ እንዲህ እንዲናገር እድሉን ለሰጠው መናፍቅና ለተናጋሪው ወዮላቸው፡፡
እንደ ዲያቆን አሸናፊ ያሉትን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ለሕዝብ ሁሉ መጽናናት የሆነ እነ ይቅርታን የኑሮ መድህንን የእግዚአብሔር ትዕግስት የመሳሳሉ ድንቅ መጽሐፈትን ያበረከተልንን ወንድም በቤተክርሰቲያን ታሪክ ተደርጎ በማይታወቅ የምንፍቅና ህግ ከቶውንም ሀይማኖታዊ ባልሆነ ውንጀላ መከርክ ገሰጽክ በማለት ከሌሎች ቤተክርቲያኒቱን ከተዉ 10 አመት ካለፋቸው ሰዎች ጋር ቀላቅሎ ያወገዘ ሲኖዶስ ምነው እንዲህ ያለውን ክህደት በቸልታ አየው? ቤተክርቲያን የቆመችው ለሰዎች ስሜት ወይስ ለእግዚአብሔር እውነት ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጠኝ ልባም ሰው ባገኝ ደስ ይለኛል።
አሊያ እንዲህ ያለውን የስህተት ትምህርት ጆሮዋን ሳይኮረኩራት የምታዳምጥ ቤተክርሰቲያን በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ የምትሆንበትን ወፈ ግዝት ለማስተላለፍ ሞራሉን ከምን እንዳገኘቸው ማወቅ አልቻልኩም። ለአባቶቻችን ጥላቻና የቡድን ስሜት ቁም ነገር ካልሆነላቸው በቀር እንዲህ ያለ ስህተት ውስጥ በቀላሉ ይዘፈቁ ነበር ተብሎ አይታሰብም። ማንም ሰው ከሀዲም ቢሆን የእምነት  ክህደት ቃሉን ለቤተክርሰቲያን እንዲሰጣት ተጠርቶ መጠየቁ መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ፍትሐ ነገስቱ ያዛሉ። የተወገዙት ሰዎች ነገሩ አስወጋዥ መሆኑ ቢታመንበት እንኳ ተጠርተው ለመምከር ለመገሰጽ ወደ እናት ቤተክርስቲያን እንዲቀላቀሉ ለማድረግ መሞከር ለአባቶች የግዴታቸው ግዴታ ነው።
ተጠርተው አልመጣም ካሉ ወይም ደግሞ መክረው አልመለስ ከተባሉ ያኔ ነገሩ ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር ተቀባይነት ያገኝላቸው ነበር። እንደ ዲያቆንነቴ በቤተክርሰቲያኒቱ ባለኝ የአገልግሎት ድርሻ እኮራለሁ እደሰታለሁ። ቤተክርቲያን ፊት አይታ ሳታደላ ሁሉን ልጆችዋን በእኩል አይታ መምራት ማቆምዋን ሳስብ ደግሞ አዝናለሁ። ዘሪሁን እንዲወገዝ ሀሳቤም ምኞቴም አይደለም ነገር ግን የስህተት ትምህርት ከመስጠት እንዲቆጠብና ንስሀ እንዲገባ ማድረግ ግን የቤተክርስቲያን ግዴታዋ ነው ብዬ አምናለሁ።
ባለፈው ጽሁፌ ላይ ለዘሪሁን ወገባችሁ እስኪከነጠስ የተከረከራችሁ እና አርቶዶክዊ መሆኑን ልታሳምኑኝ የደከማችሁ አስተያየት ሰጪዎች እንዳለችሁ አስታውሳለሁ። ዘሪሁን አሁን ተወልዷል ነገ ደግሞ ያልፋል። ቤተክርስቲያን ግን በሙሽራዋ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለዘላለም ትኖራለች። እንደ ዘሪሁን ላለ ለእንጀራው አዳሪ ከመከራከር ይልቅ ለእግዚአብሔር እውነት ጥብቅና ቁሙ። ለሁላችንም ቢሆን የሚበጀን እሱ ነው። በበኩሌ የረቡዕ ዕለት የዘሪሁን ጉባዔ ከአንድ ቀን በቀር አላመለጠኝም። ሁሌም ግን በቤተክርሰቲያን መድረክ ላይ በደፋር ሰባኪ ነኝ ባይ በምሰማቸው ክህደቶች እያዘንኩ ነው የምመለሰው። ይቺ ቤተክርሰቲያን መቼ ነው ከእንዲህ ያለ እበላ ባይ ምንደኛ ነጻ የምትወጣው? ከማለት ተቆጥቤ አላውቅም። ጴንጤ ስለሰደበ ብቻ በቤተክርስቲያን መድረክ ላይ የክህደት ትምህርት ያስተምር ብሎ መፍቀድ ሁሉን መርምሩ ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ የሚለውን አምላካዊ ትእዛዝ ያዛባብናልና እንጠንቀቅ።

10 comments:

  1. እግዚአብሔር ይባርክህ

    ReplyDelete
  2. Wey gude joro aysemawe yele? yasazenal becha.

    ReplyDelete
  3. hhahhhahhaha now, you want to twist the words which he did not want to say and finaly to make doubts at him by the people.unfourtunatly people are wise enough to identify the wolf from the sheep.this strategy also does not take you 1 step ahead.

    ReplyDelete
    Replies
    1. ለዚህ ነበር የሲዲውን ደቂቃና ሰከንድ ለመጻፍ የተገደድኩት እሱን ተመለክትህ አስተያየት ለመስጠት ብትሞክር ጥሩ ነበር አንተ ግን የቸኮልክ ይመስላል፡፡ እባክህ እንደገና ሲዲውን ተመለከትና አስተያየት ጻፍልኝ አክባሪህ ዲያቆን ፈታሂ በጽድቅለዚህ ነበር የሲዲውን ደቂቃና ሰከንድ ለመጻፍ የተገደድኩት እሱን ተመለክትህ አስተያየት ለመስጠት ብትሞክር ጥሩ ነበር አንተ ግን የቸኮልክ ይመስላል፡፡ እባክህ እንደገና ሲዲውን ተመለከትና አስተያየት ጻፍልኝ አክባሪህ ዲያቆን ፈታሂ በጽድቅ

      Delete
  4. እይ የሙሉ ወንጀል ውሾች የቤተ ክርስቲያንን አስተምሮን ሰለማታውቁ ነው

    ReplyDelete
    Replies
    1. በሀገራችን ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል። ይባለል እንዲህ ያለው ተረት የሚሰራው እንዳንተ ላለው ጨዋ ነው። ስለማታውቃት ቤተክርስቲያን አስተምሮ አታውራ። የቤተክርስቲያን አስተምሮ እንዲህ ያለውን ስህተት አይቀበልም። ምናለ እውነትን እውነት ማለት ብንለምድ!!

      Delete
    2. ውሾች በለህ ለተሳደብከው ሰው፡፡ በስድብህ እግዚእሔርን እያገለገልክ ያለህ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል፡፡ አሁን አንተ ያቀረብከው ስድብ ለማን ይጠቅማል ብለህ ነው? ስድብ ከሰይጣን የሚወጣ መሆኑን አላወክ ይሆን? ስለስድብህ ንስሐ ግባ፡፡
      ደቂቀ አቡዬ ነኝ

      Delete
  5. eyesus amalaj kemitilut ke'enante mechem yishalal.

    ReplyDelete
    Replies
    1. አዚህ ብሎግ ላይ ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚል ጽሁፍ አንብበሀል? ዝም ብለህ የመሰለህን አታውራ። ማቅን አለመውደድ ሌላ ትምህርት ማስተማር ነው ከሚል ጭፍንነት ውጣ። በዛ ላይ ከመቼ ጀምሮ ነው የክህደት ውድድር የመጣው? ዘሪሁን ክዷል ስለዚህ ንስሀ ይግባ በቃ። ሌላ ምንም አይነት የሽንገላ ቃል አያስፈልገውም።

      Delete
    2. እርስ በርሳችሁ ስትበላሉ መናፍቁና ሙስሊሙ በትዝብት እየተመለከተ ይሳለቅበቀችኋል!! የስድብ አባትና የአባቶች አሳዳጅ የሆነው ማ/ቅድሳንም ሆነ እናንተ የዚህ ብሎግ አምደኞች ክስና ውንጀላ እንጂ የመንግስቱን ወንጌል ለማስተማር ስትተጉ አላየናችሁ

      Delete