Thursday, July 5, 2012

የ"ማኅበረ ቅዱሳን" የሰሞኑ የገጽታ ማሻሻያ (Facelift) ሙከራ

getseta mukera: Click her to read in PDF
ምንጭ፡-ደጀ ሰላም(dejeselaam.blogspot.com)
ሰሞኑን (ሰኔ 25 ቀን 2004 .) የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን "አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት" በሚል ርዕስ ዶኩሜንታሪ ፊልም አቅርቦ ነበር፡፡ በዚህ ፊልም ኢቴቪ ሊያስጨብጥ የፈለገው እውነት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖቶች መቻቻል ጥንት የነበረና ያለ፣ ለወደፊቱም መቀጠል ያለበት መሆኑን ነው፡፡ በዚሁ ዘገባው አንዳንድ ሃይማኖቶችንና ተቋማቸውን የማይወክሉ የጽንፈኝነት አዝማሚያዎች በየጊዜው መታየታቸውን በማሳየት አፍራሽ ጎናቸውን ለማንጸባረቅ ሞክሯል፡፡ መልዕክቱ ከሞላ ጎደል የተዋጣለትና ጥሩ አቀራረብ ነበረው፡፡
አስተያየታችን ያነጣጠረው ስለዘገባው ይዘትና በሃይማኖቶች መካከል ስላለው መቻቻልና የጽንፈኝነት አዝማሚያዎች ለመተቸት ሳይሆን፣ አንዳንድ በየመንግሥት ተቋሙ የሚገኙ "ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለማኅበራቸው ገጽታ ግንባታና ማኅበሩ ለሚያደርሰው የጥቃት ሽፋን ለመስጠት ምን ያል እንደሚፍጨረጨሩ ለማሳየት ነው፡፡

"ማኅበሩ" ከሚገመተው በላይ ሥር ሰዶ ምን ያህል የመንግሥት መዋቅርን እንደተቆጣጠረ ማወቅ የሚቻለው ችግር ሲያጋጥም ብቻ ነው፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥር ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ ዘወትር ግጭት በመከሰት ላይ ያለ ሲሆን፣ በዚህ ችግር የሚጎዱ ምዕመናንና ካህናት ቤተክህነት ፍትሕ መስጠት ስላልቻለች ወደ መንግሥት ተቋማት ለአቤቱታ መሄዳቸው የማይቀር ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ የቀረቡ አቤቱታዎች ተዳፍነው፣ ተቀልብሰው ወይም በተበዳይ ላይ ፍርደ ገምድል ፍርድ ተሰጥቶ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡
ዛሬ በሠለጠነው ዓለምና ዘመን፣ መንግሥት ለሕዝብ ፍትሕና እኩልነትን አሰፍናለሁ ብሎ በሚታገልበት በአሁኑ ወቅት፣ በግብር ከፋዩ ገንዘብ ደመወዝ እየተከፈላቸው በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ተቀጥረው የተሰገሰጉ "ማኅበሩ" አባላት ለማኅበራቸው ኅልውና ሲሉ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ እንዳሻቸው ሲቆለሙሙ ኅሊና የሚባል ነገር የተፈጠረባቸው አይመስልም፡፡ ይህንን የሚረዳው የደረሰበት ብቻ ነው፡፡
"ማኅበሩ" ጋር በሚደረግ ግጭት የሚቆስሉ፣ የሚደሙ፣ የሚሻሩ፣ የሚባረሩ፣ የሚታገዱ ምዕመናንና ካህናት ጉዳያቸውን ለፖሊስ ሲያቀርቡ ተጣርቶ ለፍትሕና ለፍርድ ቤት አይቀርብላቸውም፤ ዐቃቤ ሕግ የተልፈሰፈሰና በሕግ አንቀፅ ያልተደገፈ ሃሳብ ይዞ ይቀርብና ሆን ብሎ ውድቅ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይግባኝ ሲጠየቅ የይግባኝ ሰሚ አካላት በር አስቀድሞ እንዲዘጋ ይደረጋል፡፡ መዝገብ ቤቶች ፋይሉን በመቅበር ወይም በዳተኝነት ጉዳዩን እንዲያጓትቱት ይደረጋል፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ያለው ሰንሰለት ተጠፍንጎ ይያዛል፡፡
ይህ ብቻም አይደለም በየነፃ ፕሬሱ የተሰገሰጉ አባላትም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስና የማኅበሩን አካሄድ በማይደግፉ ሊቃነጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ መምህራንና ምዕመናን ላይ የስድብና የማንቋሸሽ ዘመቻ ይከፍታሉ፡፡ ከነፃ ፕሬሶቹ እንደ ዕንቁ፣ ሎሚ፣ ቆንጆ፣ ማራኪና የመሳሰሉት መጽሔቶች በአመዛኙ በወሲብ ላይ የሚያተኩሩ መጽሔቶች ሲሆኑ ከቤተክርስቲያን ሕይወት ጋር የሚያያይዛቸው ጉዳይ የለም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ መጽሔቶች ሆን ብለው በከፈቱት ዘመቻ ብፁዓን አባቶች፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና ካህናት እንዲሁም ምዕመናን ተሰድበዋል፤ እየተሰደቡም ነው፡፡ ይህ በጠራራ ፀሐይ በገሃድ ተፈጽሞ ያየነው ነው፡፡
ነፃ ፕሬሶች "ማኅበረ ቅዱሳን" የሚጫወቱት ሚና በሁለት መንገድ ይገለጻል፡፡ ይኸውም፣ ፕሬሶቹ ለሚያወጧቸው ጽሑፎች ለዐምዶቻቸው ደጎስ ያለ ክፍያን ይቀበላሉ፡፡ ወይም በሌላ መልኩ "ማኅበሩ" በስውር ያቋቋሟቸው ፕሬሶችም አሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አፍቃሬ ማቅ የሆኑ የፕሬስ አዘጋጆችም የበኩላቸውን ለመወርወር ወደ ኋላ አላሉም (አዲስ አድማስ ጋዜጣን ለምሳሌ መጥቀስ ይቻላል)፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ እንደ ዕንባ ጠባቂ ኮሚሽንና ደህንነት ባሉ መሥሪያ ቤቶችም የተሰገሰጉ አፍቃሬ ማቅ ግለሰቦች የተሰጣቸውን ሥልጣን እንዴት አንሻፈው እንደተጠቀሙበት ማስተዋል ይቻላል፡፡ ይህንን እውነት የሚጠራጠር ቢኖር እስከ ዛሬ በፖሊስ፣ በፍርድ ቤትና በፕሬስ የተያዙ ጉዳዮችን ውጤት ማጥናት በቂው ነው፡፡
ወደ ጽሑፋችን መነሻ ስንመለስ፣ የሰሞኑ የኢቴቪ ዘገባም የሚያሳየን ሐቅ ከላይ የገለጽነውን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አስመልክተው የሚሰጡ ቃለ መጠይቆችና መግለጫዎች ሆን ተብሎ "ማኅበረ ቅዱሳን" አባላትና አመራሮች መሆኑ "ማኅበረ ቅዱሳን" ስውር እንቅስቃሴ አንዱ አካል ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፡፡ እንደ ሌሎቹ የመንግሥት ተቋማት ሁሉ "ማኅበሩ አባላት" በኢቴቪ ተሰግስገው "ማኅበረ ቅዱሳን መልካም ገጽታ ግንባታ እየሠሩ መሆኑ መጠራጠር ይቻላል፡፡ ዳንኤል ክብረት፣ ዘሪሁን ሙላቱ የቀረቡባቸው ፕሮግራሞችን እዚህ ላይ ያስታውሷል፡፡
ሰሞኑን "አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት" በሚል ርዕስ በተሠራጨው ዘገባም "ማኅበረ ቅዱሳን" ቀንደኛ መሪ የሆነው ዓባይነህ ካሤ፣ ብርሃን አድማስ እና የማኅበሩ ደጋፊ የሆኑት / አባ /ማርያም ስለ ሃይማኖቶች መቻቻል አስተያየት ሲሰጡ ተመልክተናል፡፡ የአባ /ማርያም መቅረብ ካላቸው የሥራ ኃላፊነት ጋር ተያይዞ ነው የሚል ሰበብ ሊሰጥ ቢችልም፣ ዓባይነህና ብርሃን ከሌሎች የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ለይቶ ሊያስቀርባቸው የሚችል ክራይቴሪያ የለም፡፡
ሁኔታውን ስናየው ኢቴቪ ውስጥ ያሉ አፍቃሬ "ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራተኞች በአሁኑ ወቅት "ማኅበሩ" ላይ እየደረሰ ያለውን ዝቅጠትና መፍረክረክ ለመታደግ በያዙት አጋጣሚ የገጽታ ማሻሻያ (Facelift) ሥራ ለመሥራት የተቻላቸውን በማድረግ ላይ መሆናቸውን ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን "ማኅበረ ቅዱሳን" ስለ ሃይማኖቶች መቻቻል ሊሰብክና ሊያስተምር የሚችልበት ሞራልም ሆነ ብቃቱ የለውም፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው የሠላም ዕጦትና ግጭት መባባስ የማን ሥራ ሆነና ነው?

3 comments:

  1. እባካችሁ ከቻላችሁ "አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት" በሚል ርዕስ የቀረበውን ዶኩሜንታሪ ፊልም ልታቀርቡልን ትችላላችሁ

    ReplyDelete
  2. እርግጥ ነው ከራሱ ወንድሞች ጋር ተቻችሎ አንዲቷን ቤተ ክርስቲያን የማገልገል ፍላጎት የሌለው ማቅ አገራዊ በሆነው አጀንዳ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት፤ ዜጎች ሁላችን በምንከፍልበት የቲቪ ፕግራም ብቅ ማለቱ በአንድበኩል ሲያሳፍረኝ በሌላ በኩል የቀረበውን ዝግጅት በጥርጣሬ እንድመለከተው አድጎኛል፡፡በዚህ ዝግጅት በኢቲቪ አዘጋጆች ሊነግረን የተፈለገው መልዕክት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማለት ማቅ፣ማቅ ማለትም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ነው፡፡ዲ.ብርሃኑ አድማሴ፣ዲ.ዓባይነህ ጣሴ፣አባ ኃ/ማርያም(ዶ/ር)፣ሊቀ ኅሩያን ዮሐንስ መዝገቡ እነዚህሁሉ በየተመደቡበት ሥፍራ ላይ የማቅ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነው እየሰሩ ያሉ ናቸው፡፡በጣም ያስገረመኝ ደግሞ የሐረሩ ሊቀ ኅሩያን ዮሐንስ መዝገቡ ነው፡፡ ማቅ በገፅታ ግንባታው ረገድ የራሴ የሚላቸውን ግን ሰው አያውቃቸውም ብሎ የሚያስባቸውን ወደ ሚዲያው ለማውጣት እየተጠቀመ ያለውንም ስልት ጭምር ለማየት ችያለሁ፡፡ዮሐንስ መዝገቡ በሐረር ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤ/ክ በድጓ መምህርነት በደሞዝ ተቀጥሮ የሚሠራ፣በማቅ ጉዳይ አስፈፃሚነት በማኅበሯ ተመልምለው በውስጥ አሠራር በምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ ሆነው የሚሰጣቸውን የማቅ ትእዛዝ በታማኝነት በመፈፀም ለውለታቸውም ሆን ተብሎ ሁለት ደሞዝ እንዲበሉ የተደረጉ(ለዛውም በደሞዝ እጥረት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት በሞሉባት ቤት) ፣ያስተማረቻቸውንና ያሳደገቻቸውን እናት ቤ.ክ ትተው ማቅን ለማገልገል ቆርጠው የተነሱና በተለይም በሐረር ለሚታየው ስብከተ ወንጌልን የማደናቀፍ ዘመቻ በፊታውራሪነት በመምራት በምዕመናን ዘንድ የሚታወቁ ናቸው፡፡በተጨማሪም የእነ ዲ.በጋሻው፣ዲ.አሰግድ፣ዲ.ትዝታው፣መ/ር ተረፈ ወዘተሐረር ላይ መጥተው ማገልገላቸውን በመቃወም አንድ ጊዜ የደህንነት መ/ቤት ሌላ ጊዜ ደግሞ ለኦሮሚያ ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጽ/ቤት እንዲሁም ለሐረሪ ፖሊስ ኮምሽን ከሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ በማፃፍና በግንባር በመቅረብ “ተጠቃሾቹ የሚያስተምሩ ከሆነ የሃይማኖት ግጭት ይነሳል” በማለት ባለስልጣናትን በማሳሳት በቁጥጥር ስር ውለው እንዲታሠሩ እንዲያደርጉ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ያለምንም ማመንታት በተደጋጋ ሚቢጥሩም ባለስልጣናቱ እግዚአባሔር በቸራቸው ማስተዋል አንድም ጊዜ ሳይሳካ አገልግሎታቸውን በስኬት ሲያጠናቅቁ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡
    ለማንኛውም መንግስት ቤቱን በደንብ ቢፈትሸው መልካም ነው ምክንያቱም ችግሩ ያለው እዚያው አልጋው ሥር ነውና፡፡
    ይሥሐቅ ነኝ ሐረር አደሬ ጢቆ ሰፈር

    ReplyDelete
  3. Qdame mata Yidegemal eza metebeq yichalal.

    ReplyDelete