Wednesday, July 11, 2012

ቤተክርስቲያንህን እወቅ የሚለው መጽሐፍ የማኅበረ ቅዱሳን የመጽሐፍ ምንተፋ (plagiarism) ውጤት ነው።

Teru minche Vs Betekerestiyanihene eweke. Read in PDF
ማኅበረ ቅዱሳን ከሚታወቅበት የክፋት ሥራዎቹ መካከል አንዱ የሰውን ጽሑፍ በመስረቅ እና የራሡ ሀሳብና እቅድ አድርጐ በሚያሳትማቸው መጽሔቶቹ፣ ጋዜጦቹ መጽሐፍቶቹ ላይ በማውጣት ነው፡፡ አንባቢ ከኔ ወዲህ ላሳር ብሎ የሚያምነው ይህ ማኅበር አይታወቅብኝም ብሎ የሰው ሥራ እየመነተፈ ከሳተማቸው መጽሐፍት መሀል ለዛሬ አንዱን እናያለን።
ይህ ሊቅ የማያስወድድ ባህሪው እያንደረደረ እና እያንቀዠቀዠ ወስዶ ይወገዙልኝ ካላቸው በርካታ ግለሠቦች መካከል የሀገራችንን የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ እድገት እዚህ ደረጃ ያደረሡ፣ 42 የሚደርሡ መጽሐፍቶችን የዳሰሱ ይልቁንም እንደነ ጎህ-ጽባሕ እና አዲስ ዓለም የተሠኙ መጻሕፍቶችን የደረሱ እና ባለ ትልቅ ራዕዩና ከዘመናቸው ቀድመው የተፈጠሩት ታላቅ ሰው ይጠቀሳሉ። እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊና ኦርቶዶክሳዊ (በማ.ቅ. አጠራር ፕሮቴስታንታዊ ተሀድሶ ተብለው የተፈረጁ) ክቡር ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ይባላሉ፡፡ እኚህ ታላቅ አባት ከነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ከነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ከነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም እና ከነ ፕሮፌስር ጌታቸው ኃይሌ ጋር ፕሮቴስታንታዊ ተሀድሶ ተብለው የተፈረጁ ሲሆን ማኅበሩ ይህን  ስም የሰጣቸው ስራዎቻቸውን ሁሉ ካስወገዘ በኃላ በስሙ ለማሳተም ፈልጎ ነው ወይ የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

ማኅበሩ በ1988 ዓ.ም ከእርሳቸው ገልብጦ ባሣተመው “ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ” የሚለው መጽሐፍ በተለይ የቅ/ጳውሎስንና የቅ/ጴጥሮስን ታሪክ ከእነሙሉ ሥራቸው ብላቴን ጌታ ኅሩይ“ነቅ ንፁህ ዜና ሐዋርያት” ብለው በ1923 ዓ.ም ካሣተሙት ወስዶ ተጠቀሞበታል። ለማሳያ ያህል የሚከተሉትን ታሪኮች እናቀርብላችኋለን፡-
1.     ዜና ሐዋርያት ገፅ 324 (1923)
Ø ቅዱስ ጴጥሮስ ፊቱ ሰፊ ሆኖ ሪዛም ነበር፣ ቁመቱም ካጭር የረዘመ ከረዥም ያጠረ መካከለኛ ነበር፡፡
v ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ ገፅ 65 (1988)
Ø ቅዱስ ጴጥሮስ ፊቱ ሰፉ ያለ ሲሆን ረዥምና መካከለኛ ቁመት የነበረው ራሰ በራ ሰው ነው፡፡
2.    ጥሩ ምንጭ ገፅ 330
Ø ቅዱስ ጳውሎስ መልኩና ሠውነቱ የምሥራቅ ሊቃውንት ቃል ለቃል ተያይዞ እንደመጣላቸው ከጻፉት መጻሕፍት ያገኘነውን ከዚህ ቀጥለን እንጽፋለን፡- ጭንቅላቱ ትልቅ ሆኖ ራሡ በራ ነበር፡፡ የሁለቱም ሽፋሉ ጠጉር የተጋጠመ ያውም የረዛዘመ ነበር፡፡ ዓይኖዋ ሰማያዊ ቀለም የመሠሉ ብሩሀን ነበሩ፡፡ አፍንጫውም ትልቅና ቀጥ ብሎ የወረደ ጉንጭና ጉንጩ የሮማን ፍሬ የመሠሉ ነበር፡፡ ጽሕሙና ሪዙም ረጃጅም ነበር፡፡ ጽሕም ማለት ከአገጭ ላይ በቅሎ ወደ ታች የሚወርደው ነው፡፡ ሪዝ ማለት ግን ከላይ ከራስ ጠጉር ተያይዞ የበቀለና ወደ ታች በጉንጭ ላይ ወርዶ ከጽሕም ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ አንገቱ አጠር ያለው ሆኖ ትከሻው ክብና ጎባጣ ነበር፡፡ እግሮቹ ከጉልበቱ ላይ የተቃረቡ ሆነው ከቅልጥሙ በታች የተራራቁ ነበሩ (ወርኃ ነበር ማለት ነው)፡፡ ቁመቱ ግን ከረዥም አጠር ያለ ከድንክ ረዘም ያለ ለአኃን አሳቻ ነበር፡፡
v ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ ገፅ 125
Ø የምሥራቅ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲተላለፍ የኖረውን ትውፊት በማሠባሠብ ስለ ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ተክለ ሰውነት እንዲህ ይላሉ፡-
ጭንቅላቱ ትልቅ ሲሆን ራሰ በራ ነበር፡፡ የሁለቱም ቅንድቦች ጠጉር የተጋጠመ አይኖቹ ሰማያዊ ቀለም ያላቸው ሲሆኑ ዘወትር ብሩሃን ነበሩ፡፡ አፍንጫው ትልቅና ቀጥ ብሎ የወረደ ጽሕሙና ሪዙም ረጃጅም ናቸው፡፡ አንገቱ አጠር ያለ ሆኖ ትከሻው ክብና ግብብ እግሮቹ ደግሞ ከጉልበቱ ላይ የተቃረቡ ናቸው፡፡ ቁመቱ አጠር ያለ እና ደንዳና ሰው (ከድንክ የረዘመ) እንደነበረ ይነገርለታል፡፡
3.    ጥሩ ምንጭ ገፅ 117
Ø ተሰለንቄ በቀድሞ ዘመን የመቆዶንያ ዋና የወደብ ከተማ ነበረች። ዛሬ ግን የግሪክ መንግስት ሆናለች። ስሟም ቴርማ ይባል ነበር። ቴርማ ማለት ፍልውሃ ማለት ነውና አጠገብዋ ፍልውሃ ስለመኖሩ ነበር።…በኃላም ካሳንድር የተባለ ጌታ የትልቁን እስክንድር እህት ሳሎኒቃ የምትባለውን አግብቶ የቴርማ ገዢ ሆኖ ነበርና ሚስቱን ሳሎኒቃን ደስ ለማሰኘት ሲል ቴርማ መባሏን አስቀርቶ ተሰሎንቄ ብሎ ስለሰየማት ከዚያ ዘመን ጀምሮ አስካሁን ተሰሎንቄ እየተባለች ትጠራለች።
ተሰሎንቄ ከአውሮፓ ወደ እስያ ለሚተላለፍ ንግድና ሰው ሁሉ ዋና የባሕት በር ስለሆነች ከአድርያቲክ ባህር ጀምሮ እስከ ተሰሎንቄ የሰረገላ መንገድ ተሰርቶ ንግዱም ሰውም ያለችግር ይመላለስ ነበር።
v ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ ገፅ 118
ቀድሞ የመቆዶንያ ዋና ወደብ ነበረች። ዛሬ ግን በግሪክ ሥር ናት። ስሟ ቀድሞ ቴርማ ይባል ነበር። ትርጉሙም ፍል ውሃ ማለት ነው።ይህ ስም ከአጠገብዋ ከነበረው የፍል ውሃ የተወሰደ ነበር። በኃላ ግን ካሳንደር የተባለ ገዢ የታላቁን እስክንድር እህት ሰሎኒቃን ስላገባ ከተማዋን በሚስቱ ሰየማት።
ከአውሮፓ ወደ እስያ በሚያልፈው ዋና መስመር ላይ ስለምትገኝ ከተማዋ ዋና የንግድ ማዕከል ነበረች።

የሀሳብ አወራረዱን ተመለከቱ፤ የታሪኩን አወቃቀር ተመልከቱ፤ ሁለቱ መጽሐፍት በአጋጣሚ ታሪኮቻቸው ሁሉ በሀሳብ አወራረድና በታሪክ አወቃቀር አንድ አይነት ሊሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር አይችልም። አንዱ የአንዱ ቅጂ ካልሆነ በቀር። ምንተፋ(plagiarism) የሚባለው ይኸው ነው።
በአጠቃላይ ሁለቱን መጽሀፍት ጎን ለጎን አስቀምጦ ያየ አስተዋይ አንባቢ ቤተክርሰቲያንህን እወቅ የጥሩ ምንጭ ግልባጭ መሆኑን በቀላሉ ይገነዘባል። መጽሀፉን አይተነዋል ለማለት ቤተክርስቲያንህን እወቅ ላይ በአንዳንድ ቦታ በምንጭነት የተጠቀሰ ቢሆንም ባነሳናቸው ነጥቦችና ላይ በሌሎችም የመጽሐፉ ክፍሎች ጥሩ ምንጭ በምንጭነት አልተጠቀሰም። ጥሩ ምንጭ የተጻፈበትን የቀድሞ አማርኛ በዘመናዊው አማርኛ አቃንቶ መጻፍ የመጽሀፉ ባለቤት አያሰኝምም አያስደርግምም። ማኅበረ ቅዱሳን ሕሊና ቢኖረው ኖሮ ቤተክርስቲያንህን አወቅ የብላቴን ጌታ ኅሩይ መጽሀፍን በዘመኑ አማርኛ አስተካክዬ ሀሳቡን ለማብራራት የታከሉ ምሳሌዎችን ቀንሼ አና የሌሎች ሐዋርያትን ታሪክ አክዬበት ያሳተምኩት መጽሐፍ ነው ማለት ነበረበት።
እነ መጋቢ ሐዲስ በጋሻውን “የጻፋከው መጽሐፍ ርዕስ ከአንድ የጴንጤ ሰባኪ ስብከት ርዕስ ጋር ተመሳሳይ ነው ስለዚህ መናፍቅ ነህ” እያለ እያዋከባቸው ያለው ማኅበር ለራሱ ጊዜ ከሞቱ ከ80 ዓመት በኋላ መናፍቅ ናቸው ይወገዙልኝ ሲል የጅምላ ይወገዙልኝ ጩኸት ካሰማባቸው ኢትዮያዊያን ምሁራን መካከል አንዱ የሆኑት ስመ ጥሩው ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴን መጽሐፍ መንትፎ በስሙ ማሳተሙ የሚያስገርምም የሚያሳዝንም ነው።
እንግዲህ “ቤተ ክርስቲያንህን እወቅ” ብሎ ማኅበሩ ያዘጋጀው መጽሐፍ ውስጥ የሁለቱን ሐዋርያት ታሪክ፣ ሥራ፣ እራሱ የደከመበት የተመራመረበት አሥመስሎ አሳትሞታል፡፡ ይህ ማኅበር ሊቃውንት እንዳይታወቁ ብሎም ከእነ ሥራቸው እንዲረሡ፣ እንዲጠፉ እየጣረ የሚገኘው ዛሬ ሳይሆን ከመነሻው ጀምሮ ነው፡፡ የእኝህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጽሑፍ መሥረቅ ሳያንሳቸው አሁን ደግሞ ይወገዙልኝ ከሚላቸው ውስጥ ደምሮአቸዋል፡፡
በአንድ ወቅት መ/ር ሃይለማርያም ላቀው የተባለ በስምአ ፅድቅ ኃዜጣ ላይ “ቤተ አብርሃም” አምድ አዘጋጅ የብላቴን ጌታ ህሩይን ታሪክ በጋዜጣው ላይ ጽፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ ይኸው ግለሰብ የእሳቸውን የሕይወት ታሪክና ሥራ በመጽሐፍ መልክ እያዘጋጀ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ለመሆኑ “ጉህ ጽባሕ” እና “አዲስ አለም” የተሠኙ መጻሕፍቶቻቸውን ምን ይላቸው ይሆን? በጉጉት እንጠብቃለን፡፡
ማህበሩ በነካ እጁ የሌሎችን ሥማቸውን ያጠፋቸው ሊቃውንት አስወግዞና አስረግጦ መጽሀፎቻቸውን በስሙ ያሳትም ይሆናል ብለንም እንጠብቃለን። ሃሳብን አሳጥሮ እና ከርክሞ ማቅረብ ደራሲ እንደማያደርግ ከሁሉ በላይ ምናልባት በውስጣችሁ  ካለ ህሊናችሁ ይነግራችሁ ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በስነ ጽሁፍ ህግ ምንተፋ በእንግሊዘኛ ስሙ plagiarism  የሚባለው እንዲህ አይነቱ ወንጀል ነው። ይህ ወንጀል በጽሁፍ ስራ ከሚፈጸሙ  ወንጀሎች ሁሉ ትልቁ እና ዋነኛው ነው።
ይሔ ሁሉን እነክስ ሲል ጊዜ የጣለው ማኅበር አባላቱ  በተለይ በጽሑፍ ሥራ ላይ የተሠማሩት ከፕሮቴስታንት መጽሐፍቶች ላይ ሳይቀር እንደወረደ በመገልበጥ ለአደባባይ ያበቁ እና ደራሲ የተሰኙ የስምአ ጽድቅ አምደኞችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ይህን በተመለከተ ወደፊት በበቂ ሁኔታ የተዘጋጀ ሥራ ስላለ ማን ከማን ወሠደ የሚለውን አሳፋሪ ሥራ እንገልጣለን፡፡ የጽሁፍ ሥራ ጸጋ ሲሆን ከላይ ይሰጣል። ምንጩም የማይቋረጥ ይሆናል። የጽሁፍ ስራ እልህ ሲሆን እንዲህ ሰው አያውቅም እያሰኘ የሰው ሥራ ያስገለብጣል። መጽሐፍ ካላሳተምኩ የሚል እልህ የትም አያደርስም እና የሰው ሥራ ከመመንተፍ ልባችሁንም፣ ህሊናችሁንም፣ እጃችሁንም  እግዚአብሔር ይፈውስላችሁ።
                            

21 comments:

  1. nothing wrong, you keshim

    ReplyDelete
    Replies
    1. REALLY? BESAK ALE YAGERE SEW!!

      Delete
  2. ke ETV basachihu chekakoch

    ReplyDelete
  3. Mikegna. Melkam negere eskehone dires bibazam mim aydelem. Enante mikegnoch. Bemeseretu enante yetsafachihutin blog manbebu new newir! Stupid

    ReplyDelete
    Replies
    1. denkoro kalhonke bekere yesew sera serko besem masatem belgena endehone tawekalhe? aemerohe seletemereze gin ewneten tegafalhe maferiya. dedeb honehe sale chegerehene yemiyasayehene dedebe ateble. lebenet lebent new. aleke lela tergum atesetewe.
      BERCHI AWDE MIHRET. endizehe aynet tera sewochen kekum neger atseafuwachew.

      Delete
    2. ብላቴን ጌታ ኅሩይ ተሃድሶና መናፍቅ ተብለው ከተከሰሱ፤ ከሳቸው መጽሐፍ መገለበጥ በራሱ የተሃድሶና የመናፍቅ ወዳጅ መሆኑ ያሳያል። ሊሆን የሚችለው ኦርቶዶክሳዊ መምህር መሆናቸውን አምኖ እንደማጣቀሻ መጠቀም፤ አለበለዚያም መናፍቅ ከሆኑ በአንድም ነገር ማስረጃ አድርጎ የሳቸውን መጽሐፍ ባለመጠቀም መጽናት ብቻ ነው ሊኖር የሚችለው ምርጫ!! ያለበለዚያ «ከመረቁ አውጡልኝ ከሥጋው ጾመኛ ነኝ» ማለት ጿሚ መሆኑን አያሳይም።

      Delete
  4. ena min yitebeselehe? MUTICHA!!!!!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. SEW HULGIZE TIKEKEL AIDELEHIM SIBAL KSIHITEU IMARAL ENJI YESEW FITUREN BAMLAKE MISALE YETAFETEN SW KELAI YALWN MESDEM SILAYHUTEM IKER IBELEN MIN ISALAL TEMARU EBY TARMU EBY ATSADEBU EBY SW MASDED BICHA ENANETEN MAMEN ALTECHALEM SIYAMNUWACHU ZHON YAKELE SIHITET IZCHU BIQ TILALACHU

      MASTEWALEN ISTEN EGZIYABHEREN IBAREKEN SELAMUN YASASIBEN AMEN!!!

      Delete
  5. wey mk leka endihe aynet seram teseriyaleseh? betam yazazenal.

    ReplyDelete
  6. abet abet abet ybuna were nw!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  7. Yesim matifat zemechaw altesakam,Wulude seytan nachihu

    ReplyDelete
  8. ማህበረ ቅዱሳን በየመስሪያ ቤቱ ተሰግስገው ቀስ ብለው በሽኩሹክታ ስለፖለቲካ ሲያወሩ መስማት የተለመደ ነው፡፡ እኔን የሚገርመኝ ስልጣን ከፈለጉ ህጋዊ ዕውቅና አውጥተው በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ትግል ማካሄድ ይችላሉ፡፡ የትጥቅ ትግል ከፈለጉም ኢትዮጵያ ውስጥ በረሀ ሞልቷል፤ ኢሳያስ አፈወርቂ እስካለ ድረስ የጦር መሳሪያ እርዳታ እንደልብ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ግን እንደ ሴት ቢሮ ውስጥ ፤ ቤተ ክርስቲያንና በየጓዳው ተደብቀው ማንሾካሾክ ምን ይባላል?? ማቅ ደንባራ ፈረስ

    ReplyDelete
    Replies
    1. Lehagerachewe hiwotachewen yesetue bezue setewoche alue mk besete letera ayecheleme sete eko enate ehete meste mekarie astemare nate

      Delete
  9. TADYA MIN YITEBES?

    ReplyDelete
  10. YOU GUYS DO YOU KNOW WHAT YOU TAKING ABOUT. POLITICA, ESAYS,FIER ARM,SO WHAT HOW YOU RELATE TO MK?

    ReplyDelete
  11. EGZIABHER LESRW ENA LETEREGETEW WONGEL YENESA!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  12. ታዲያ ስህተቱ የት ነው? ታሪክ አንድ ነው። ጸሐፊው የጻፉትም ማህበሩ ያሳተመውም አንድን እውነት ነው። ስለዚህ ማሳተሙ ነው ክፋቱ፣ ወይስ ጽሐፊው ብቻ ናቸው ያንን እውቀትና ታሪክ ማሳተም የሚችሉት ነው የምትሉት? እንኳንስ የአንድን ቤተ ከርስቲያን ፣ ቅዱስ... ታሪክ ቀርቶ ሳይንሳዊ የሆኑ ጽሑፎች እንኳን ያለማጣቀሻ አይጻፉም። ስለዚህ ማህበሩ ይህን መጽሐፍ በአጭሩም ቢሆን ከርሳቸው መጽሐፍ ላይ ተመርኩዞም ይሁን በራሱ ይጻፈው፣ የጻፈው ስለ አንድ እንውነት፣ ታርክ ነው። ይህ ደግሞ የፕላጃሪዝም ወንጀል አይደለም። ምናልባት የፕላጃሪዝምን ትርጉም አታውቁት ይሆን? መሰለኝ። ስለዚህ ዝም ብላችሁ አታጭበርብሩን።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ወንድም በሕይወቴ ደስ የማይለኝ ሰው ስለማያውቀው ነገር የሚዘባርቅ ሰው ነው። አይንህን ጨፍነህ ለስህተት ትክክለኛነት መከራከርህ ያሳዝናል። ፕላጃሪዝም ወንጀል ነው። ስለማታውቀው የፕላጃሪዝም ትርጉም በድፍረት መናገርህ ያሳዝናል። ምናልባት አንተ ትሆን እንዴ የብላቴን ጌታን መጽሐፍ ለማሕበረ ቅዱሳን ጥቅም ገልብጠህ የጻፍከው? ጠረጠርኩህ ለምን ታወቀብን ብሎ ድርቅና አያዋጣም ይልቅስ ልብ ካላችሁ ተሳስተናል ብላችሁ ይቅርታ ጠይቁ። ለማንኛውም ፕላጃሪዝም ወንጀል መሆኑን የሚያሳይ የቃሉን ትርጓሜ ምናልባት መሳሳትህን ለማወቅ ከረዳህ ይኸው አንብብ www.plagiarism.org ነው የወሰድኩት።

      What is Plagiarism?

      Many people think of plagiarism as copying another's work, or borrowing someone else's original ideas. But terms like "copying" and "borrowing" can disguise the seriousness of the offense:
      According to the Merriam-Webster Online Dictionary, to "plagiarize" means

      to steal and pass off (the ideas or words of another) as one's own
      to use (another's production) without crediting the source
      to commit literary theft
      to present as new and original an idea or product derived from an existing source.

      In other words, plagiarism is an act of fraud. It involves both stealing someone else's work and lying about it afterward.
      But can words and ideas really be stolen?

      According to U.S. law, the answer is yes. The expression of original ideas is considered intellectual property, and is protected by copyright laws, just like original inventions. Almost all forms of expression fall under copyright protection as long as they are recorded in some way (such as a book or a computer file).
      All of the following are considered plagiarism:

      turning in someone else's work as your own
      copying words or ideas from someone else without giving credit
      failing to put a quotation in quotation marks
      giving incorrect information about the source of a quotation
      changing words but copying the sentence structure of a source without giving credit
      copying so many words or ideas from a source that it makes up the majority of your work, whether you give credit or not (see our section on "fair use" rules)
      አሁንስ ምን ትል ይሆን?

      Delete
  13. Thanks awedemhret for the great job your doing! I was a member of MK for a really long time, not really an active member but just still a member. I love what they did to teach us since high school n in college but i didnt agree with what they where doing and where they want to take EOTC! Egziabher belogn ke teleq atfe group temeleshiyalew! Enesum endemeletu etseleyalew!
    Chelemaw hulem beberhan yeshenefal ena bertu! Egziabher Ethiopian yetebek!

    ReplyDelete