Thursday, July 19, 2012

«ደጀሰላም» ብሎግ እንዴት እንደሚያጭበረብር ተመልከቱ!

(ደጀ ብርሃን ብሎግ ስለ ዳላሱ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ከዘገበች በኋላ መቀደሟ አበሳጭቷትና ከኔ የተረፈ ነው ለማለት ደጀ ሰላም ቀን አሳስታ ታሪኩን ለመዘገብ ሞክራለች፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን የተንኮል ማቆሪያ ጣቢያ የሆነችው ደጀ ሰላም የምትተጋለትን የሐሰት ሥራዋን ምክንያታዊ ለማድረግ መሞከርዋ ለተፈጥሮዋ የሚስማማ ነው፡፡ ግን ጎግል ለማንም ስለማያደላ እና እንደ አንዳንድ ጳጳሳት ለማህበረ ቅዱሳን ስለማይሰራ የደጀ ሰላም የማጭበርበር ሙከራ ምን እንደሚመስል አሳይቶናል፡፡ ደጀ ሰላሞች ለምን አንዲህ እንዳደረጉ ደጀ ብርሃን በቂ ማብራሪያ ሰጥታበታለች፡፡መልካም ንባብ)
ምንጭ፡- ደጀ ብርሃን
        የማቅ አፈቀላጤ ስለሆነውና ከዳላሱ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ራሱን ስለገነጠለው ቄስ መሥፍን ማሞ አዲስ የሥራ ፈጠራ ጉዳይ በ10/11/2004 ወይም በ(17/7/2012) ዓ/ም  ዝርዝር ሀተታ ደጀብርሃን ብሎግ ማስነበቧ ይታወሳል። ከዚያም  ስለ ላስቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ጢም አልባው መነኩሴ ጥቂት ዳሰሳ አድርገን ወደምእራቡ ክፍለ አሜሪካ ተጉዘን፤ በመምህር ወ/ሰማዕት ስለሚመራው ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን የማቅ ሰርጎ ገቦች እያደረሱ ስላለው የሁከት አገልግሎትና የረጋውን ወተት የመበጥበጥ ተልእኰ ከጠቃቀስን በኋላ የካሊፎርኒያና የዲሲ አካባቢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ አባታዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሲያትል ደ/ም  ቅ/ አማኑኤል ቤተክርስቲያን  እንደሚያመሩ ዘግበን እንደነበር ይታወሳል።

አስቀድመን እንደዘገብነው የማቅ ሰርጎ ገብ በጥባጮች፤ በሀገር ቤቱ እንቅስቃሴ እየተዳከሙ ሲመጡ የውጪውን ሀገረ ስብከት የመጠብጠጥ እቅድ ነድፈው፤ የቆየ  ዐመላቸውን እየተገበሩ ይገኛሉ። በቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ጉብኝት ያደርጋሉን የሰማው መምህረ ሁከት ማቅ አንድም ቀን ተኝቶላቸው እንደማያውቀው ሁሉ አስቀድሞ ጆሮውን አቅንቶ የብጥብጥ አጁን በመዘርጋት እንቅፋት መፍጠሩን ቅንጣት ሳያፍር «ደጀ ሰላም» የተባለው የማቅ ማእከላዊ ኰሚቴ ቃል አቀባይ ብሎግ  ዘግቦ አስነብቦናል።  ወደ ሁከትና ዐመጻ እንዲገቡ የሚቀሰቅሳቸውና የስህተት መንገድን አሰማምሮ ስለቅድስና እንደመታገል አድርጎ በኅሊናቸው በመሳል የሚያነሳሳቸው ከሌለ በስተቀር ምእመናን የዋሃን ናቸው። ገንዘባቸውን፤ ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ለአገልግሎት የሚያበረክቱትን እነዚህን የዋሃን የእግዚአብሔር ቤተሰቦችን ማቅ እንዴት መጠምዘዝና ለተፈለገው ዓላማ ማዋል እንደሚቻል ብዙ የሥራ ልምድ ስላለው ይህንኑ ጥበበ ዐመፃውን በሲያትል አማኑኤል ቤተክርስቲያን  ተግባራዊ አድርጎ ብጹእ አቡነ ፋኑኤልን የመቃወም ህውከት ለመፍጠር ሞክሯል። 

እንኳን እምነት፤ ኅሊና ያለው ማንም ሰው የሚፈርደውና ጥያቄ ሊያነሳበት የሚገባው ነገር፤  ብጹእ  አቡነ ፋኑኤል በሀገረ ስብከታቸው ባሉ አድባራት ተዘዋውረው እንዳያስተምሩ የሚከለክላቸው ምንድነው? ቅዳሴ ቀድሰው፤ ቡራኬ ሰጥተው ከመመለስ በስተቀር በደብሩ የውስጥ ሥራ ምን አድርገው ያውቃሉ? እያንዳንዱ ደብር የየራሱ አስተዳደር ያለውና በምእመናን የተቋቋመ እንጂ በብጹእ አቡነ ፋኑኤል  አይፈርስ፤ አይቋቋም!!  ሲኖዶስ የሰጣቸውን ተልእኰ ከመወጣት ውጪ አድባራቱን ምን በድለዋል? ምእመናንስ ቤተክርስቲያናቸው የምትሰጣቸውን መንፈሳዊ አገልግሎት ከማግኘት ውጪ ከዐመጻና ከብጥብጥ ምን ያተርፋሉ? እነዚህንና እነዚህን መሰል ጥያቄዎች ብናቀርብ መልሱ ምንም ይሆናል! ከብጥብጥና ከዐመጻ ምእመናን ምንም አያተርፉም። ይልቁንም ከኋላ ሆኖ ድብቅ አጀንዳውን እንደ ወፍ ጉንፋን/bird flu/ የሚረጨውና የሚበክለው ማቅ፤
1/  የአድባራቱ ተቆርቋሪ ሆኖ ራሱን በመሰየም መድረክ ከተቆጣጠረ በኋላ ገንዘብ መዝረፍ፤ አላስቀርብ ካሉት ደግሞ በጥቅም የሚደልላቸውን መሥፍኖች በመፍጠር መገንጠል፤
2/ አባ ፋኑኤልን በሄዱበት ሁሉ እየተከታተለ ማሳደድ የመጨረሻው ዓላማና ግቡ ስለሆነ ይህንኑ አሽክላ ሥራውን እስከእለተ ሞቱ መተግበር፤
3/ የፖለቲካ ሥራው ከሀገር ቤት ብዙም እያወላዳው ባለመሆኑ ወደውጪው ዓለም ፊቱን በማዞር በየቦታው ማመስ፤ መበጥበጥና ጉንፋኑን ማራባት ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል። የሲያትሉ ቅ/ አማኑኤል ቤተክርስቲያንም ህውከት የዚያ ተግባሩ አንዱ ማሳያ ነው። 

በዚሁ አጋጣሚ በምድረ አሜሪካ የምትገኙ አድባራት ሁሉ የብጥብጡ የጽዋ ማኅበር  «ሙሴ» የሆነው ማቅ «ማነሽ ባለሳምንት? ያስጠምድሽ በዐሥራ ስምንት»  ይላችኋልና «እኔ ነኝ የማቅ አገልጋይ» እያላችሁ እጃችሁን በማውጣት የብጥብጡን ጠላ ጥመቁ! አለበለዚያም በራችሁን ከብጥብጥና ከሁከት ዘግታችሁ መንፈሳዊ ሥራችሁን የማጠናከር ሁለት ምርጫ ከፊታችሁ ቀርቧል።
ማቅ ሲጀምር በውስጥ ደጋፊዎቹ በኩል የቅድሚያውን የቤት ሥራ ይጀምራልና ጥንቃቄ ማድረጉ አይከፋም ምክራችን ነው።
ደጀ ብርሃን ብሎግ ስለአማኑኤል ቤተክርስቲያን መረጃ በ17/7/2012  ካወጣች በኋላ የማቅ ቃል አቀባይ «ደጀ ሰላም» ደግሞ በ18/7/2012 ከአንድ ቀን በኋላ ብጥብጡን መዘገቧን አይተናል። የሚገርመው ግን የደጀ ሰላም ማጭበርበር ሲሆን  /blogger.com/ በብሎጉ ላይ ካሳየው ከ 18/7/2012  እለት  ቀን አንድ ቀን ቀድሞ  በ17/12/2012  የተዘገበ በማስመሰል ጣት እንደሚጠባ ህጻን ልታታልለን ትሞክራለች። ይህ የሚጠቁመው በቅ/ አማኑኤል ቤተክርስቲያን የተነገረ ወይም የተጻፈ መረጃ ከመኖሩ በፊት ብጥብጥ እንደሚኖር የደረስንበት ሲሆን  ከእኛ መረጃ  ይፋ መሆን በኋላ የሚመጡ መረጃዎች ሁሉ ስም ለማጥፋት የተዘጋጁ ናቸው ለማለት የታቀደ ይመስላል። ያለበለዚያማ ደጀ ብርሃን ብሎግ  ማቅ በሲያትል ቅ/ አማኑኤል ቤተክርስቲያን እየበጠበጠ ነው በማለት በ17/7/2012 ያወጣውን ዘገባ ተከትሎ ደጀ ሰላም በ18/7/ 2012 ብጥብጡን ጽፎ ሳለ በጽሁፉ ውስጥ ባስቀመጠው ቀን በ17/7/ 2012 በማለት አንድ ቀን ወደኋላ በመቀነስ ማጭበርበር ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ነው?
እስኪ ይህንን የደጀ ሰላምን የቀን አቆጣጠር ተመልከቱና ማጭበርበሩን እናንተም ፍቱት!! እንዴት ሆኖ እንደዚህ ይቆጠራል?
July 18, 2012
የሲያትል ምእመናን አቡነ ፋኑኤልን በይፋ ተቃወሙ፤ እንዳይመጡም ተስማሙ
Email ThisBlogThis!Share to TwitterShare to Facebook
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 10/2004 .ም፤ ጁላይ 17/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF) በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ በዋሺንግተን ሲያትል በሚገኙት  በደብረ ሰላም /ሚካኤል እና በደብረ መድኃኒት /አማኑኤል አብያተ ክርስቲያናት በድብቅ ሊመጡ ያሸመቁትን አቡነ ፋኑኤልን ሕዝቡ በይፋ ተቃወመ፡፡ እሑድ ከቅዳሴ በኋላ ምእመናን በይፋ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሕገ ወጡ ሊቀ ጳጳስ አባ ፋኑኤል ወደ አብያተ ክርስቲያናቱ እንዳይመጡ በብርቱ ተቃውሞ ቀርቧል። በሌሎች አካባቢዎች የተጀመረውቤተ ክርስቲያንን ከነአባ ፋኑኤል እና ከፕሮቴስታንቱ አጋራቸው ከኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የመታደግእንቅስቃሴ በሲያትልም ተጀምሯል።ምንም አያውቅምእየተባለ የሚናቀው ምእመን ለቤተ ክርስቲያኑ የክፉ ቀን ደራሽ መሆኑን እና በሐዋሳ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንባውና በተጋድሎው /ሲኖዶስ ኡኡታውን ሰምቶ ያገኘውን ድል በአሜሪካ የሚገኘውም ምእመን እንደሚደግመው አረጋግጧል።
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
10 comments: Posted by ደጀ ሰላም
ማውጫ፦ ዜና ወዲህ የሚጠቁሙ ገጾች

ከአውደ ምሕረት
እንደ አለፉት ስድስት አመታት የውሸት ቀለብን በማጭበርበሪያ ዘፈኖቻችሁ እያጀባችሁ ህዘቡን እንዳሳሳታችሁት አትቀጥሉም፡፡ በመንፈሳዊ ስም ብሎግ ከፍታችሁ ከአባታችሁ ከዲያቢሎስ የሆነውን ሀሰት ለየዋሁ ሕዝብ እና እጸድቅ ብሎ ለተከተላችሁ አባላችሁ ስትግቱት ከርማችሁዋል፡፡ ከአሁን በኃላ ግን በምንም መንገድ በዛ ሁኔታ አይቀጥልም፡፡ የእናንተንም ሆነ የአባታችሁን የሐሰት ሥራ በብርሃን ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አጋዥነት እናፈርሳለን፡፡ በማንኛውም ሁኔታ የሐሰት ሥራችሁን በዝምታ አናልፈውም፡፡ ለሕዛባችን እውነቱን ለመግለጽ አንታክትም፡፡ እንደ ከዚህ በፊቱ ብቻችንን ነን እኛ ያልነው ሁሌም ትክክል ነው እያላችሁ የነውጥ ዘርን የምትዘሩበት ጊዜ አብቅቷል፡፡ ቢያንስ ቢያንስ እንደዚህ  ካለ የጅል የጥበብ ራሳችሁን ለመጠበቅ ሞክሩ፡፡

6 comments:

  1. endihe yalew sera kemaheberu baheri yemimeneche new

    ReplyDelete
  2. ቅዱስ ስኖዶስ የመደበውን መንፈሳዊ አባት (ሊቀ ጳጳስ) አልቀበልም በማለት አመጽ ማካሄድ የአንድ ክርስቲያንና መንፈሳዊ ማህበር (አገልጋይ) ተግባር አየደለም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለማያውቋቸው የግብፃዊያን ጳጳሳት ስትታዘዝና ስታከብራቸው መቆየቷ የቤተ ክርስቲያናችን የቅርብ ግዜ ታርክ ነው። ለመሆኑ አንዳንድ የሰበት ት/ቤት መዘምራን ባለ ማወቅ የማቅ ደጋፍ መሆን መንግሰተ ሰማያት የሚገቡ የምመስላቸው ካሉ ተሳስተዋል። ይልቁን ፍቅር ትግስት የዋህነት ታጋሽነት በንስሐ ህይወት ከጥላቻ መንግድ መመላለስ ወደ እውነተኛ የእግዚአብሔር መንግስት ይመራናል።የክርስቲያና ተግባር ብጥብጥ፤ጥላቻ፤መለያየት ከሆነ ይህ የዲያብሎስ መንገድ ነው።

    ReplyDelete
  3. የማቅ ተከታዮች ለመሆኑ ከእግዚአብሔር ቃል ምን የማሩ ይሆን?
    ዳሩ በቅዱስ ቃሉ የማይመሩ የዘመኑ አመጸኞች ናቸው።

    2ኛ ጢሞ ም 3 ቁ 1
    በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።

    ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥3ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።

    ReplyDelete
  4. ማቆች በደጀ ሰላም ስለአባ አብርሃም ጥሩ ጥሩ ይዘግባሉ። ስለአባ ጳውሎስ ግን ዘወትር ጥላቻ ብቻ ነው። ለምንድነው?

    ReplyDelete
  5. Ene yemigermegn, Ewnet kasebachihu lemin sile"Deje Selam" taweralachihu. Yerasachihun sira siru beka. Hule yesew bett mames Ezza min tebale bilo mechenek. Yebetekirstianin ewnet eninageralen kalachihu erasachihu ketilubet, lela bota atasadu - Deje selam min biyawera enante tewut beka.

    ReplyDelete
  6. Las Vegas Abba Gebire Kidan ( Melake Salem ) Betebalu Menekuse Mesay Mahibere Kidusan Eyetebetsebetsech New Minew Abba Gebire Kidann Anid Bitilulun Welo Yeteweledew -Semen Shewa Yadegew - Wetader Yeneberew- Awash Yeneberew -Misitun Kedito Menekuse Neg Yalew -Melk Yelelew -Moya yegodelew-Mahibere Kidusan Amilake New Bilo Yemiyaminew -washington D C ye America Sinodos Kedash Hono Yenorew -Yemengisit Selay Hono Yemiyagelegilew Yihi Menekuse Mesay Las Vegasn Kefafelew Ahun Debiru Bemulu Mahibere Kidusan Endihon Teferedebet -Metedaderiya Denb endizegaj Tazeze Kale Awadi Ferese Abune Pawlosina &Abune Fanueil Tewegezu Sinodos Ayagebawim Alu Awde Mihiret Sefa Yale neger Lehizibu Akiribi Bertu

    ReplyDelete