Monday, July 30, 2012

"ኢሳት"ና እውቀት ማዶ ለማዶ ተያዩ!

Esat andKnowledge:Click here to read in PDF
(ከጸሐፊው ግላዊ ገጸ መጽሐፍ(face book) የተገኘ)
በሙሉጌታ ወ/ገብርኤል
(ሐምሌ 23 2004 ዓ.ም.፣ ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com) (ባለፈው ሳምንት ኢሳት: በማቅ የአፍዝ አደንግዝ ፖለቲካ የተለከፈ የጽንፈኞች መናገሻ?” በሚል ርዕስ መቀመጫውን አምስተርዳም ያደረገ የዜና ማሰራጫ ማዕከል የሕዝብ ዓይንና ጆሮ፣ ሃብትና ንብረት መሆኑ እየቀረ ሕዝብንና ሀገርን ለመበታተን እንዲሁም ለማውደም ቆርጠው ከተነሱ የበግ ለምድ የለበሱ አደጋ ጣዮች ሥመ መንፈሳውያን በማበርና ድምጽ በመሆን በሰሚ ጆሮ ላይ እየፈጠርው ያለውን ሃላፊነት የጎደለበት ልቅ ውዥንብርና ብዥታ በመታቀብ ተቋሙ በዋናነት ለተቋቋመበትና ለተሰለፈበት ዓላማ ራሱን ያስገዛ ዘንድ በጥቂቱ ለማሳሰብ ያክል ተወያይተን ነበር በይደር የተለያየነው። ለዛሬ ታሪካዊ ስህተቶችን ብቻ በማተኮር ተፋለሶቹን አንድ በአንድ ነቅሰን አንጥረንና አበጥረን በሰፊው እንመለከታለን።
ጽሑፉ ምንም እንኳን "የዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ታጋዮች" የሆኑ ድረ ገጾች በመላ የተላከ
ቢሆንም ድረ ገጾቹ በተላከላቸው ጽሑፍ ይዘት ምንም ዓይነት ተቃውሞ እንደሌላቸውና በጽሑፉ እውነትነት ቢስማሙም በይፋ ለማስነበብ ግን ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። በቋሚነት ሀገራዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበረሰባዊ አመለካከቴንና አስተሳሰቤን ከማካፍልበት ግዙፍ ኢትዮጵያዊ ድረ ገጽ ሕዝብ እንዳያነበውና እንዳያየውም ተቋሙ በፈጠረው ጫና 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከስፍራው እንዲነቀል ተደርገዋል። ድርጊቱም - ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ ሐዘን ተሰምቶኛል። በዚህ አጋጣሚ የዳያስፖራ "ነፃ ፕሬስ/ሚድያ" ነጻ ይውጣ! እያልኩ ለጊዜው ሥራዎቼን በመጽሐፈ ገጽ (face book) በኩል ለማስነበብ ተገድጃለሁ። ይህም እስኪታፈን ድረስ መሆኑ ነው እንግዲህ።
የጽሑፉ መልክ - ተንጋዶ የተጻፈውን ወይንም ደግሞ በኢታሊክ የሰፈረውን ከተናጋሪው ጋዜጠኛ ቃል
በቃል የሰፈረ ሲሆን መስመር የተሰመረባቸው ቃላት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቃላት ለመሆናቸው ለማስታወስ ነው።መልካም ንባብ!)

የጋዜጠኛው ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ስህተት÷
"ፋይናሊ ሊያሸንፉዋቸው ስላልቻሉ ምን ብለው ገቡ ክርስቲያኖቹን እኛም አመንን ብለው በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ገቡ። በሃይል ማሸነፍ ሲያቅታቸው ምን ውስጥ ገቡ ክርስቲያኖች ነን ብለው፤ ሳይሆኑ ክርስቲያን ነን ብለው ሃይማኖት ተቋምን መቆጣጠር ያዙ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ነው የእምነት ተቋማት ቤተ-ክርስቲያን በገዢዎች ስር መዳፍ ስር እየወደቀችው ያለችውኢህአዴግ እያደረገው ያለው ከቄሳሮች የተለየ ነገር አይደለም በመስጊድም በቤተ-ክርስቲያን በኩልም ሁሉ ሊያደርግ የሚፈልገው እነዚህን ተቋማት ለእምነቱ ለእሱ ለአገዛዙ እንዲመቹት የማድረግ ነው:: ገብቶባቸዋል። በህገ መንግስቱ ላይ የነፃነቶች አለ ተብለዋል ኢህአዴግ ግን እንደፈለገ ገብቶ የራሱ አመራር አስቀምጠዋል
የኢሳት ጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተ ወልድ

መሰረታዊ ስህተቶች
ü  በተጠቀሰው ዘመን (በቄሳር ዘመን) የሮም ህግ ኃይማኖትን በማስመልከት አንድም ስፍራ የሚለው አለመኖሩ ለበረጠ መረጃ "Lex" ሕግ የሚለውን ይመልከቱ።
ü ነገሥታት/የፖለቲካ ባለሥልጣናት በቤተ-ክርስቲያን ላይ ዓይናቸውን የጣሉ በተጠቀሰው ዘመን ላለመሆኑ።
ü ይህም ብቻ ሳይሆን በተለይ ክርስቲያኖች ነን ብለው ገቡ የሚለውን አገላላጽከስህተት ሁሉ ትልቁ ስህተት ለመሆኑ!
ü  "ኢህአዴግ እያደረገው ያለው ከቄሳሮች የተለየ ነገር አይደለም" የሚለውን አባባል ፍጹም ጥንተ ታሪክን ያላማከል ደመ ነፍሳዊ አባባል ለመሆኑ በበቂ ታሪካዊ ማስረጃዎችና ጭብጦች የተመረኮዘ ሐተታ እንደሚከተለው ቀርበዋል
ዝርዝር ሐተታ
በአንደኛው ክፍለ ዘመን አከባቢ የሮም መንግሥት ይከተለው የነበረው ፖሊሲ "ዩኒቨርሳሊዝም" (universalism) በማለት ይታወቃል። ይህ ማለት ሥርዓቱ ለዜጎቹ የወደዱትንና የፈለጉትን የመከተልና የማምለክ የሃይማኖት ነጻነት ከማቀዳጀቱ በላይ ሁሉም ሃይማኖቶች ማለት አይጡንም ድንቢጡንም የሚያመልክ ወንዙም ነፋሱንም የሚከተል ሁሉ እኩል የሆነ መብት የሚሰጥም ነበር። የዚህ ሥርዓት ማዕከሉ አንድ ዜጋ በሕገ- መንግስቱ የተደነገገውን ሥርዓት ጠብቆና አክብሮ እስከኖረ ድረስ አምልኮ/ሃይማኖት በተመልከተ ለዜጋው ለግሉ የሚተው ነው የሚል ነው። በምንም ነገር የአለማመንም መብት ያጠቃልላል። የቄሳር የበላይነት ተቀብለው እስከኖሩ ድረስ ከግል የእምነት ልምምድዎ የተነሳ የሚገላምጦትም ሆነ በጎሪጥ የሚያዮት አንድም የመንግሥት አካል/ባለሥልጣን የለም።
"ዩኒቨርሳሊዝም" መልክና አሰራር ለማወቅና በቀላሉም ለመረዳት ያደጉ የምዕራባውያን ሀገራት መንግሥታት ፖለቲካዊ አደረጃጀትና መንግሥታዊ መዋቅር እንዲሁም አሰራር ማየት ነው። "ዩኒቨርሳሊዝም" በንጽጽራዊ መልኩ ለማስቀምጥ ያክል ከጥንቱ መልኩና አሰራር የሚለየው ቄሳር አምልኮ ሲቀበል የአሁኖቹ ክቡራን ፕሬዝዳንቶች ይህን ቀርቶባቸዋል። በተረፈ ግን ሃይማኖቴን አይፈቅድልኝም በማለት የመንግሥት ትዕዛዝ ሳይፈጽሙ፣ በሕገ መንግሥቱም ላይ ያመጹ፣ ያፈነገጡ፣ የተላለፉ እንደሆነ የሃይማኖትዎ አለቃ እስኪታደግዎ ድረስ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ወደ ገነባባቸው ዘብጥያዎች/ማረሚያ ቤቶች ለመውረዳቸው አያጠያይቅም። በሌላ አገለጽ መንግሥት የበላይ ነው! የሚል አንድምታ ነው ያለው። መጽሐፍ ልጆትን ቆንጥጠው ቀጥተው እንዲያሳድጉ ያዝዎት ይሆናል።
ሃይማኖቴ ያዘኛል በማለትም በልጅዎ ላይ እጅዎትን የሰደዱ እንደሆነ ልጆትም 911 ጨቁኖ ያደረሱበት ያስረዳ እንደሆነ ለአደጋ መጋለጥዎ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ "ቄሳር" የሚለውን መጠሪያ ራሱ ሁሉቱንም የሥልጣን እርከኖች ያጣመረ በመሆኑ
አንድ ዜጋ አንደ ንጉስ የላቀ ክብር የሁሉም የበላይ ሹም እንደ መሆኑም መጠን ደግሞ አምልኮ መስጠት ንጉሡን ደብሎ ማምለክ ይጠበቅበታል። እንግዲህ ከክርስትና እምነት ተከታዮች በስተቀር ሌሎች የተቀሩ ቤተ እምነቶች ቄሳርን ደብሎ የማምለክ ነገር ብዙም ችግር አልነበራቸውም። እዚህ ላይ የክርስትና እምነት ተከታዮች የጎላ ልዩነት ለማሳየት የተገደዱበት ምክያትም የእምነታቸው ምንጭ የሆነ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ) ለስጋ ለባሽ አምልኮ አለመፍቀድ ብቻ ሳይሆን በጽኑ የሚቃወምም ነውና ከተለያዩ እምነቶች ወደ ክርስትና ካምፕ የሚቀላቀሉትን ዜጎች ቁጥር እየጨመረ በምጣቱም ቅራኔዎችን ሊፈጠሩ ችለዋል። ከዚህም የተነሳ በቄሳርና በክርስቲያኖች መካከል ችግር ሊፈጠር ችሏል ክርስቲያኖችም ለስደትና ለእንግልት ተደርገዋል።
ከሕዝቡ ጋር ለተነሳው ግጭት ዋና ምክንያት ክርስቲያኖቹ በሚሰባሰቡበት ጊዜ የተለያዩ ሥርዓቶቹን ይፈጽሙ ነበርና እነዚህ ሥርዓቶቹም በሩቅ ተመልካች ለሆኑት ዜጎች አእምሮ ላይ የፈጠሩትና የሳሉት የተሳሳተ ምስል የተነሳ ነበር። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከልም ክርስቲያኖቹ የቁርባን እንዲሁም በጉባኤው መጨረሻ ይለዋወጡት የነበሩትን ክርስቲያናዊና የወንድማማች ሰላምታ/መሳሳስም ተጠቃሾች ናቸው። -አማኒያኖቹ ክርስቲያኖቹ ቁርባን ሲወስዱ በሩቁ ባያዩ ጊዜ "የህጻናት ስጋ ይበላሉ" በማለት ሲወነጅሎዋቸው እንዲሁም ሲሳሳሙ/ሰላምታ ሲለዋወጡ በተመለከቱ ጊዜም ባል ከሚስቱ ሚስትም ከባልዋ ውጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር ግብረ ስጋ ይፈጽማሉ በሚል የተሳሳተ ግምታዊ እልባት ነበር ከክርስቲያኖች ጋር ዓይንህ ላፈር ማለት የጀመሩ።
ታድያ ከመቼ ወዲህ ነው መንግሥት/ነገስታት በቤተ-ክርስቲያን ላይ ፍላጎት ማሳየት የጀመሩ? ለሚለው
ጥያቄ ከመነሻው በአጭሩ ላስረዳ። ነገስታት ተቆርቋሪነት በሚመስል አጉል ፈሊጥ በቤተ-ክርስቲያን ላይ ፍላጎት ማሳየት የጀመሩ በታሪክ በግልጽ እንደሰፈረውና እንደሚታወቀው ቁስጠንጢንዮስ ወደ ሥልጣን ከወጣ ዘመን ጀምሮ ነበር። ይኸውም "ራዕይ ከሰማይ አየሁ" ከማለት ጀምሮ ሲሆን በዋናነት ይህ 320 በኒቅያ ከተማ አርዮስ የተባለ የእስክንድሪያ ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ (ካህን) ለማውገዝ የተዘረጋው ጉባኤ ንጉሡ ባወረደው ቀጭን ትዕዛዝ ነበር።
ንጉሡም በጉባኤው የተገኘ ሲሆን የአርዮስ ሙግት ጭብጥና አስተምህሮ ከዳመጣ በሃላ አርዮስ ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት እንዲወገዝ ተደርጓል።
ይህን ተከትሎም ከዚህ ቀደም ፍጹም የሆነ ልዩነትና የተናጠል አስተዳደር ሲለማመዱ የመጡትን እነኚህ
ሁለት ተቋማት የቀድሞ የተናጠል አሰራራቸውን ደብዛ የሚያጠፋ በአንጻሩ ደግሞ አንዱ በሌላው የሚሰለጥንበትና የበላይ ወደ ሚሆኑበት አሰራር ውስጥ ለመግባት በተለይ ከወደ ቤተ መንግሥት አከባቢ ፍላጎቱ እየጨመረ በመምጣቱ ተቆርቋሪነት በሚመስል አጉል ፈሊጥ ነገሥታት በቤተ-ክርስቲያን ላይ የበላይ የመሆን አባዜ እየተጸናወታቸው መጣ። 451 ኬልቄዶን ከተማ የተካሄደው የኬልቄዶን ጉባኤም ለዚህ ሁሉ የነገሥታት በቤተ-ክርስቲያን ላይ የበላይ የመሆን ፍላጎት ሲብላላ የመጣውን ትኩሳት የፈነዳበት ሁነኛ ምሳሌና አጋጣሚ ነበር።
ይህ በኬልቄዶን ከተማ የተደረገው ጉባኤ ቤተ- ክርስቲያን ዛሬ ለምትገኝበት የመከፋፈልና አንድ ያለ መሆን
በሽታ ያበረከተው አስተዋጽኦ የላቀ ነው። ጉባኤው ብዙ ጠባሳዎች ጥሎ ያለፈበት፣ ከፈተኛ ውጣ ውረድና እሰጥ አገባ ያስተናገደበት ምክንያትም የነገሥታቱ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ለመሆኑ የማይካድ ሐቅ ነው። ይህን ለማረጋግጥ ከድህረ ኬልቄዶን ጉባኤ በሃላ የሮማ ዙፋን ለመጠበቅ የተሰባሰበውን የሊቃነ ጳጳሳት ጉጅለ (የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን) እምነትዋን በማይጋሩ የእምነት መሪዎችና አማኞት ያደረሰችው ግፍ ማየት ከመሰረቱ ፖለቲካዊ አካሄድና አሰራር ለመኖሩ ለመረዳት አያዳግትም።
ሌላው ኢህዴግን ከቄሳር ጋር በማመሳሰል "ኢህዴግ እያደረገው ያለው ከቄሳሮች የተለየ ነገር አይደለም" የሚለውን ጥንተ ታሪክን መሰረት ያላደረገ ደመ ነፍሳዊ አባባል ከወዴት እንደተገኘ ባላውቅም "በተንታኞቻችን" አዲስ ግኝት በመገረም "ኢሳትና እውቀት ማዶ ለማዶ ተያዩ!” ከማለት ውጭ ብዙ ማለትም አልታየኝም። በተረፈ ግን ጊዜን ለመቆጠብ ያክል ለተናጋሪው የምለው ቁም ነገር ቢኖር ኢህአዴግ ከቄሳር ጋር በማመሳሰል ያልተጻፈ ከማንበብና ከዚህ ቀደም ያልተሰማ ያልተነገረም ታሪክ መናገር አይበጅም፡፡
በመጨረሻ ለወደፊቱም ቢሆን እንዲህ ባሉ ርዕሰ ጉዳዮችን ላይ ተናጋሪዎች የመናገር ዕድሉ ስለገጠማቸው
ብቻ ሳይሆን ከተናጋሪዎቹ የላቀ እውቀት ያላቸው ሰሚዎች እንዳሉ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚደረጉ ውይይቶች ሁሉ በቂ የሆነ ጥናትና እንዲሁም የባለሞያዎች ምክርና አስተያየት ታክሎባቸው ቢቀርቡ ባይ ነኝ። በተቀሩት ህጸጾችና ተፋለሶች ሳምንት እንገናኝ።
/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
e-mail yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America
July 29,__2012

No comments:

Post a Comment