Friday, July 20, 2012

የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ማኅበረ ቅዱሳን በስራዬ ጣልቃ እየገባ ስላስቸገረ አደብ ይያዝልኝ አለ

Addis abeba Hageresebket: Click Here to Read in PDF
(ሐምሌ 13 2004 ዓ.ም. ፣አውደ ምህረት/www.awdemihret.blogspot.com)ማኅበረ ቅዱሳን በማን አለብኝነት ወዋቅራዊ አሰራርን በመጣስ በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሥራ ላይ ጣልቃ በመግባት በስሩ የሚገኙ ገዳማትንና አድባራትን ሰበካ ጉባኤ ስብሰባ እየጠራ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ከሶስተኛ ወገን የሚገናኝበትን መመሪያ እየጣሰ ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀ፡፡ 


ይህ የመዋቅር ጥሰት አግባብ ያልሆነ ስለሆነ ሃገረ ስብከቱ “…ማኅበሩ በሃገረ ስብከታችን ጣልቃ እየገባ የሚያስተላልፋቸውን ጥሪዎችና የመዋቅር ጥሰቶች እንዲያቆም…”የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አካሄዱን የሚያተካክልበት መመሪያ እንዲሰጥልን እናሳስባለን ብሏል፡፡

ከፅንሰቱ ጀምሮ አመጽ በቀል የሆነው ማኅበር እኔ ያልጣድኩት ድስት አያስፈልግም እያለ በተለያየ ሥራዎች ላይ ጣልቃ በመግባት ለቤተክርስቲን የሚጠቅም ሥራ ከመስራት ይልቅ የማኅበሩን ገጽታ በመገንባት ሥራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡  ህዝብ ወደ እግዚአብሔር እውነት የሚደርስበትን መንገድ ከማመቻቸት ይልቅ ቤተክርስቲያን ያለህዝብም ቢሆን በማኅበሩ ቁጥጥር ሥር የምትውልበትን ስራ በመስራት ላይ ያለው ማኅበር ባልተፈቀደለት የስራ መስኮች እየገባ በማን አለብኝነት እየበጠበጠ ነው፡፡
ደፋሩ ማኅበር ለመምሪያዎች ከተለያዩ አካለት የሚመጡ በየስልጠና ጥሪዎችን መምሪያዎች ውስጥ ባሉ ሰዎቹ አማካኝነት ደብዳቤ እያስከፈተ መምሪያው ሳያውቅ በመምሪው ስም ስልጠናዎችን የማኅበሩ ሰዎች እንዲወስዱ እያስደረገ መሆኑ ሲታወቅ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲከሰት ከማዘን ያለፈ ተቃውሞ ሳይሰማ ቀርቶ ነበር፡፡ ይህም የልብ ልብ እየሰጠው በሃገረ ስብከቶችና በአጠቃላይ በቤተክኅነቱ ስራዎች ላይ ጣልቃ በመግባት ማኅበረ ቅዱሳን ወይም ሞት ፉከራን እያሰማ ይገኛል፡፡
እንደ አንድ አለሌ ሽፍታ የተወሰኑ እበላ ባይ ጳጳሳትን ማስገበሩ የልብ ልብ እየተሰማው ምንስ ባደርግ ምን እሆናለሁ ያሻኝን ሰርቼ ወጥቼ እገባለሁ እያለ በአንድ መጠምሻ ጎረምሳ ስሜት የሚንቀሳቀስ ማኅበር መሆኑ ለቤተክርሰቲኒቱ አደጋ እየሆነ መምጣቱን ያሳያል፡፡
የቤተክርሰቲያንን ክፍተት ለመሙላትና አደጋዋን ለመቅረፍ በሚል አባባይ ቃል የታገዘው የማኅበሩ አካሄድ ግቡ ቤተክርስቲኒቱን በማኅበሩ መተዳደሪ ደንብ እንድትመራ ማድረግ ሲሆን ዶግማዋም ቀኖናዋም ማኅበሩ እንዲሆን የሚያስገድድ አካሄድ እየተከተለ መሆኑ የአደባባይ ሚሥጢር ሆኗል፡፡
የአንድ ተቋም ትክክለኛነት ከሚለካበት መንገድ አንዱ ህጋዊ መዋቅሮችን አክብሮ መንቀሳቀስ መቻሉ ነው፡፡ ያለ ሕጋዊ መዋቅር ህግ እና እውነት የበላይነት ይዘው መቀጠል የማይችሉ መሆናቸው እውነት ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ህግ የት እንዳለ የሚያስታውሰው ሌሎችን ለመምቻ የሚጠቅመው ከሆነ ብቻ ነው፡፡ የማኅበሩን ፍላጎት ለማስጠበቅ  ግን እስካዋጣው ድረስ በህጋዊ አሰራር እሱም ካላዋጣ የወንጀል ድርጊቶችን ጨምሮ የትኛውንም ህገ ወጥ አካሄድ ለመጠቀም ወደ ኋላ የማይል ድርጅት መሆኑን እስካሁን ያሉት ተሞክሮዎቹ ያስረዳሉ፡፡  

8 comments:

  1. endihe new yehen kefu mahebere mewetere mengest bezhe betekehenet beza. abo tolo adeb aseyezulenema

    ReplyDelete
  2. MK has a right to do what he want. Because MK is the real son of Orthodox church !!!!!!!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. shame on you. this attitude put u in jail and push you to hell. you need to think about respect that is what the true orthodox church sons do.

      Delete
  3. እውነተኛ ስራ ሰርቶ መኖር የአንድ መንፈሳዊ ሰው ተግባር ነው። እግዚአብሐር እራሱ እውነት ነውና። የማቅ የአመጻ ልጆች ዛሬም ከሁከትና ከብጥብጥ መንገድ የማይመለሱ ናቸው። ግን በህግ ማቆም ይቻላል። ለዚህ ምስክሩ ስራው ነው። የአድስ አበባ ሀገረ ስብከት ከልብ እናመሰግናለን ቆራጥ አቋም በመውሰዳቸው።መፍራት እግዚአብሔርን በቻ ነው። የማቅ ስም ማጥፋት እየተፈራ ብዙ ዘመናት ተቆጥሮዋል ።ሁሉ ነገር ገደብ አለው።

    ReplyDelete
  4. it is really a shame to mk. they need to think to change their attitude

    ReplyDelete
  5. ታዲያ ምን ይስሩ እነርሱ እኮ ሁሉንም ናቸው ሀገረ ስብከቱ እነርሱ መንበረፓትርያርኩ እነሱ መንግስት እነርሱ ማንን ይፈራሉ?እነርሱ ብቻ ልክ ሌላው ሁሉ ውሸተኛ ነው እንደውም ዓለም ሁሉ ከእነርሱ በስተቀር ውሸተኛ ነውና ለዚህ መፍትሄው ልክ እንደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እየተከታተሉ ቀንድ ቀንዳቸውን ማለት ነው:እንጂ!ኧረ ሌላው እነዚያ ይህንን የእነርሱን ደብዳቤ አይተው በየሀገረ ስብከቱ የተቀመጡት እነርሱው ራሳቸው ካልሆኑ ወይም በማቅ ገንዘብ የተገዙ ካልሆኑ እንዴት ሀገረ ስብከቱ ሳይፈቅድ ደብዳቤ ሳይልክ በማቅ ደብዳቤ ስብሰባ ይጠራል?ጠርቶ ከሆነ ነው::ለምን መቃብራቸውን ያፋጥናሉ ሞት እኮ ሞተዋል የሞቱት እኮ መንበረ ፓትርያርክ ጽሕፈት ቤት ያልተስማማበትን ማሳመን ሲያቅታቸው ተሐድሶ እያሉ ስም በማጥፋት በጥፋት ጋዜጣቸው ላይ ያወጡትን ማየት ነው!ይህንንማ በየክልሉስ እየሰበሰቡ የሲኖዶስ ውሳኔ እያሉ ማስፈራሪያ እኮ ካደረጉት ቆይተዋልና ይህንን የተዋረድ ጥሰት ካሁኑ ካላስቆሟቸው ነገ አልሞትኩም ብለው ሊነሱ ይችላሉ!!
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  6. Mk is not son of orthodox.why, mk was dose so many bad thing in the name of church, without anything mk is against of the right and good spiritual peoples. mk used a lot of money to control the church leaders. that so bad way. Orthodox church children are lovers and doing good things. not destroying and against true christian names. as the word of God we must be good and lover our enemy. If you not obey word of the truth God, something is wrong with the Mk. members.

    ReplyDelete
  7. one thing I would like to ask, who is the step son to ortodoxe. Mk is the son of the devel. Aloways they create problems in the church, in the country. their goal is not the church, their goal is Politics, poor saycolge. Know I think this is the time for them. Let us wait and see what is ging on in the near future. SELIFEWOCH< GODOCHE.

    ReplyDelete