Sunday, July 22, 2012

ለማኅበረ ቅዱሳን ፍርሀት የሆነው ጉባኤ አርድዕት በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ታወቀ።

Gubae ardiet: Click Here To Read In PDF
  • ሊቀ ሥዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ መኪና አልተቀማም
  • ጉባኤ አርድእት ስብሰባ እንዳይሰበሰብ አልታገደም
  • መንግስት ለማኅበረ ቅዱሳን የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ማንም አልሰማም በማለት ወደ ጉባኤ አርድዕት ለማዞር ሞክረዋል
(ሐምሌ 15 2004 ዓ.ም.፣ ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com)የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች በተለመደው ዋሾ ባህሪያቸው ያልሆነውን ሆነ እያሉ መዘገብን ቀጥለውበታል፡፡ ስለጉባኤ አርድዕት በመፈራረቅ በሰሩት ዜናም ገና በመደራጀት ላይ ያለውን ጉባኤ ተፈረካከሰ ተልፈሰፈሰ ሄደ ተመለሰ እያሉ የጅል ምኞታቸውን ይነግሩን ይዘዋል፡፡ ሊቀ ሥዩማን ሃይለጊዮርጊስም በጠቅላይ ቤተክህነቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ፊርማ መኪናው ስለተበላሸ ቅያሪ መኪና እንዲሰጠው የትብብር ደብዳቤ እንደተፃፈለት እያወቁ  ደብዳቤውን ከኛ በቀር ማንም አያገኘውም በማለት ተበላሽቶ ወደ ጋራዥ የገባውን መኪና ተቀማ በማለት ዘግበዋል፡፡
እነዚህ የማኅበሩ የውሸት ቃል አቀባይ የሆኑ ደጀ ሰላምና አንድ አድርገን የተባሉት ብሎጎች በጉዳዩ ላይ እርስ በእርሳቸው እንኳ መስማማት አቅቷቸዋል። ዋሽቶ ስምምነት የት አለና?። ደጀ ሰላም ሀይለጊዮርጊስ መኪና የተቀማው በአቡነ ጳውሎስ ትዕዛዝ ነው ብላ ጀምራ ወደ ታች ወደ ወረድ ሲባል ደግሞ በምክትል ስራ አስኪያጁ በተስፋዬ ነው በማለት ራስዋን ተጣልታ ዘግባለች። አንድ አድርገን ደግሞ በምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ነው ትላለች።
እውነታው ግን ሌላ ነው በምክትል ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ፊርማ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው የሃይለጊዮርጊስ መኪና በብልሽት መቆምዋን እና እንዲያውም ተለዋጭ መኪና እንዲፈለግለት ልማትና ክርስቲያናዊ መምሪያን የሚጠይቅ ነው።


ደብዳቤውን በግልጽ ማየት እንደሚቻለው መኪናው በብለሽት ምክንያት መቆምዋን እየገለጸና እና ተለዋጭ መኪና ይፈልግ ተብሎ ሳለ እነ ውሸት ስንቁ ግን ተቀማ ብለው መጻፋቸው ሊያገኙት የፈለጉትን ተራ ውዥንብር የመፍጠር ትርፍ አላማው ምን እንደሆነ ያሳውቅባቸዋል።
እንደዚሁም ደጀ ሰላም
“..ባለፈው ሳምንት፣ ሰኔ 26 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጠቅላላ አገልግሎት ሓላፊ ሊቀ ኅሩያን ዓለም እሸት ገብረ ጻድቅ ተፈርሞ በአድራሻ ለጥበቃ አገልግሎት ክፍል የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው÷ ራሱን “ጉባኤ አርድእት” በሚል የሚጠራው ቡድን ከቅዱስ ሲኖዶስ ይኹን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተሰጠው አንዳችም ዕውቅና የለውም፤ የጉባኤው አስተባባሪዎች በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ በውል ተለይቶ ላልታወቀና ላልተፈቀደ ዓላማ በኅቡእ መሰብሰባቸው ሕገ ወጥነት በመኾኑ የትኛውንም አዳራሽ ይኹን ቢሮ ለስብሰባ መጠቀም አይችሉም፤ የጥበቃ አገልግሎት ክፍሉም ይህንኑ ተከታትሎ እንዲያስፈጽም ትእዛዝ ተሰጥቶታል፡፡በማለት የዘገበችው ዘገባ ሙሉ በሙሉ ውሸት እንደሆነ እና በደብዳቤው ላይ ስለጉባኤ አርድዕት የሚያወራው ነገር እንደሌለ የሰኔ 26ቱ የሊቀ ኅሩያን አለም እሸት ደብዳቤ ያስረዳል።

ደብዳቤውን በግልጽ ማየት እንደሚቻለው “በቅዱሳን ፓትሪያርኮች ማረፊያ ህንጻ ማንም እንዳይገባ እና እንዳይሰበሰብ” የሚያግድ እንጂ ስለ ጉባኤ አርድእት የሚያነሳው ነገር የለውም። ግን የማቅ ብሎጎች ደብዳቤውን ጠምዝዘው እና አቅጣጫ አስቀይረው ያልተጻፈበትን ነገር እንደተጻፈ አድርገው ማስነበባቸው እንዲህ እውነቱ ሲወጣ ትዝብት ላይ ከመውደቅ አያድናቸውም።
ደጋግመን እንደዘገብነው ውሸት የማኅበረ ቅዱሳን ተፈጥሮ ነው፡፡ ሀሳበ ሰንካላው ማኅበር በፊቱ የሚቆም ሌላ ማኅበር ካለ የጥፋት ማኅበር መሆኑ ጎልቶ እንደሚወጣ ስላወቀ የነገር ቀንዱን አሹሎ ያገኘውን ካልወጋሁ እያለ እያስቸገረ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ገና በሀሳብ ደረጃ ያለ ማኅበርን የፈራውና ያርበተበተው ተደራጅቶ ስራ ቢጀምር የሚያመጣበትን ኪሳራ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ለሁላችንም ሳንጠይቀው ስለጉባኤ አርድዕት ያስተዋወቀን እና የጉባኤውን መመስረት ማኅበረ ቅዱሳን ከጠበቀው በተለየ መልኩ በርካታ የቤተክርስቲያን ልጆች በናፍቆት እነዲጠብቁት ያደረጋቸው ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡
ስለ ጉባኤ አርድእት በተዘጋጀው እና ስለጉባኤው የሚተነትነው ጹሁፍ እንደሚያስረዳው የጉባኤው አላማ
 “… የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፣ ይህም አንድነትዋ በሃይማኖት፣ በቀኖናና በሥርዓት፣ በሕግ፣ በመዋቅር፣ በአስተዳደር፣ በአሠራርና በአመራር አንድነት የሚገለጥ ነው ብለን ስለምናምን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚያጠናክር ሁለንተናዊ አስተዋፅኦ ለማድረግ አንድነት የበለጠ ጠቃሚ ነው ብለን ይህችን መንፈሳዊት ኅብረት ፈጥረናል፡፡” የሚል ነው፡፡ ይህንን አላማ ሰይጣን ካልሆነ ማን ሊቃወመው ይችላል? ሥራ ሳይጀምር አካሄዱ ሳይታወቅ እንዲሁ ብቻ ከማኅበረ ቅዱሳን ቁጥጥር ውጭ ነው ብሎ መርበትበት መደንገጥና ኡኡታ ማሰማት ምንድን ነው? ይህ ራሱ ማኅበሩ በስራው መተማመን እንደሌለው እና ሌላ ማኅበርም ከመጣ ያለ ብዙ ድካም ከማቅ የተሻለ ሥራ እንደሚሰራ የሚያሳይ ነው፡፡
መበለጥን ቀድሞ ለመከላከል ካልሆነ እንቅስቃሴ ሳይጀመር ይህን ያህል መደናበር ምን ማለት ነው? ሕዝቡን በስራ ሳይሆን በሽብር እኔ ከሌለሁ ዋጋ የለህም በማለት እራስን በእግዚአብሔር ቦታ አስቀምጦ ያለአቅም በመንጠራራት ከማሸበር ይልቅ አቅምንና ቦታን አውቆ የተሻለ ነገር ለማድረግ መሞከሩ የተሻለ ነው፡፡
ሌላው አስቂኝ ዘገባቸው ጉባኤ አርድእትን መንግስት ተቃውሞታል የሚለው ነው። እንዲያውም መንግስት ሐምሌ 3 ቀን የማኅበሩን አመራሮች ጠርቶ ባናገራቸው ጊዜ ያላቸው የተገላቢጦሹን ነው። መሰባሰብ እና መደራጀት መብት እንደሆነ የማንንም ሕገ መንግስታዊ መብት ማፈን እንደማይችሉ ማንም ተነስቶ ይህን እና ያን ማድረግ እችላለሁ ብሎ የሰዎችን የመደራጀት መብት ማፈን እንደማይችል እና ይሄ አካሄዳቸው ራሱ ጸረ ሕገ መንግስት መሆኑን እንደተገለጠላቸው የሚታወቅ ነው፡፡
የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ከባድ ስለሆነ፣  የመንግስትን ማስጠንቀቂያ ለማስተባበል እና አቅጣጫ ለማስቀየር ከጠፋን አይቀር ሁሉንም ይዘን እንጥፋ በሚል መሯሯጥ መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ጉባኤ አርድእት ግን ስራውን እንዳላቆመ እንዲያውም አካሄዱ እየተጠናከረ መምጣቱ ግልጽ ነው። ይህም ስላስደነገጣቸው አባላቱ ተከፋፈሉ ተገነጠሉ እያሉ ወሬ ማስወራትን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል።
ጉባኤ አርድዕት አሁንም ከማቅ የሚደርስበት ውርጅብኝ እንዳለ ሆኖ የታቀደለትን ወጥመድ እየሰባበረ ጉዞውን መቀጠሉ ታውቋል። አሁን ያለበት እንቅስቃሴ በጣም ጥሩ እንደሆነ እና እንዲያውም የአባልነት ጥያቄውን ብዛት ከጠበቀው በላይ እንደሆነ በአጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናትና በሃገረ ስብከቶች የጉባኤ አርድዕት አባል ለመሆን እንደሚፈልጉ እና ቤተክርስታንን ካሁን በኋላ እነደ ማቅ ላለ የቀን ጅብ አሳልፈው መስጠት እንደማይፈልጉ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ታዋቂ ሰባኪያን እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ ሰዎች የጉባኤ አርድዕት አባላት እየሆኑ መምጣታቸው ታውቋል።
ማህበሩ የጉባኤው አደረጃጀት ስላስፈራው ወደ ታች ወርዶ አባላትን ማሳተፍ እንዳይጀምር ህዝብን ለማስደንገጥና ሲል በስምአ ጽድቅ ጋዜጣው እና በብሎጎቹ ጉባኤውን የተጠጋህ ወየውልህ የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ እየሞከረ ይገኛል።
እስካሁን ደረስ ባለው አደረጃጀት እንደ ጉባኤ አርድዕት አባቶቻችንን እንርዳ ብሎ የተነሳ ስብስብ የለም እነ ማኅበረ ቅዱሳን የጳጳሳትን ስራ ወስደው በእነርሱ ላይ እንደ ጳጳስ እየሆኑ ያልናችሁን ፈጽሙ ማለት እንጂ እንርዳችሁ የሚል አካሄድ የላቸውም። ጉባኤ አርድእት ግን ተልዕኮ እናሳካ እናንተን አንርዳ የሚል አካሄድ ነው ያለው። ይህንን አካሄድ ማንም ለቤተክርሰቲያን ቅን ልቦና ያለው ሰው የማይቃወመው ነው።  ማኅበረ ቅዱሳን ሀሳቡን በሀሳብ ደረጃ እያለ መቃመሙ እና ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ማድረጉ ማኅበሩ  ቤተክርስቲያንን በሞኖፖል የመቆጣጣር ህልሙን እና ከክርስቶስ ባሪያነት ለይቶ የሀሳቡ ባሪያ ለማድረግ የሚያደርገው ሩጫ አካል መሆኑ ግልጽ ነው።
         

6 comments:

  1. tiru new ewnetun endenaweke metarachehu yasemesegenachuwal

    ReplyDelete
  2. Ayi Efrem Eshete ena Mesfin Tegegne????????? Yih Eko Mefitihe ayidelem... meftihew menfesawinet new????? Geta mastewal yistachihuuuuuuuuuuuuu

    ReplyDelete
  3. Wonderful!This is the truth.Gubaeardeet is moving forward to serve the will of God and His Church. Ato Eskindir wants the car.when it is repaired. The car was to be given to Aba Serekebirhan, head of training and education department. But,Ato is better than a monk for the Church that is lead by the Two Atos, Eskindir and Tesfaye. Anyway, May God save His Church from these two Mafyias.

    ReplyDelete
  4. ማህበረ ቅዱሳን ውሸታም ናቸው፡፡አውደ ምህረት እባካችሁን ማ/ቅዱሳን የሚነዛውን ውሸት ተከታትላችሁ አጋልጡልን፡፡

    ReplyDelete
  5. What does "በቅዱሳን ፓትሪያርኮች ማረፊያ ህንጻ ማንም እንዳይገባ እና እንዳይሰበሰብ" mean then?

    ReplyDelete
  6. You accuse MK of falsehoods. And where are the evidence you have for all your accusations in this "crappy" article? So, who is spreading falsehoods? Just insults ans accusations over and over and over and over..............again...with out any "meaningful" work... don't you get tired...what a waste..

    Egziabher Libona yistachihu.... I know u wouldn't bend even if you see our Lord and Savior Jesus Christ standing in front of u ... what a sad bunch... just burning with so much hate and vengeance .... not good

    Markos from AA

    ReplyDelete