Monday, July 2, 2012

የሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርትን አስመረቀ።

Click here toread in PDF
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ባለፈው ቅዳሜ ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት ደቀ መዛሙርቱን አስመረቀ። የኮሌጁ ተማሪዎች በቤተክርስቲያን ትምህርት ባላቸው ጥልቅ እውቀት የሚታወቁ ሲሆን ኮሌጁ ባላቸው እውቀት ላይ የወንጌልን እውቀት በመጨመር አውነተኛ የወንጌል አገልጋዮች የሚወጡበት ኮሌጅ ነው። በምረቃው ዕለት የኮሌጁን ዲን አቡነ ያሬድን ጨምሮ አቡነ ገሪማ እና ሌሎችም ብጹአን ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን በምረቃው ዕለት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ያሰሙት ቅዱስ ፓትርያርኩ ጆሮ ገብ የሆነና ጠቃሚ ምክር ለተማሪዎቹ ሰጥተዋል።
ቅዱስነታቸው በንግግራቸው የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ስለቤተክርስቲያን ሥርዓት በተናገሩት ንግግር “…ቤተክርስቲያን የራስዋ ስርዓት አላት። ለድቁናው ለቅስናው ለቁምስናው ለጵጵስናው ሁሉ ለስልጣነ ክህነቶችዋ ኃላፊነቶችዋ ሁሉ እራሱን በቻለ ሥርዓት ከአባቶች በተሰራ ሥርዓት እስካሁኑ ትውልድ ድረስ የደረሰ ነው። እና ቤተክርስቲያኒቱ በነበራት እንዲህ አይነት ወጥ የሆነ ነገር ያልተለመደ ነገር ዛሬ በቤተክርስቲያናችን እየታየ ነው። ዝም ብሎ ከሜዳ ተነስቶ ቀሲስ እከሌ ምናምን እየተባባሉ ቤተክርስቲያንን በውጭ ሃይል ለመግፋትና በግዳጅ አቅጣጫውን እንድትስት ለማድረግ የሚታገሉ አሉ። ነጻ የሆነን ሕዝብ እንደዚህ ማድረግ አይቻልም።” በማለት አንዳንድ ክህነት በግድ በማለት የክብር ድቁናና ቅስና የወሰዱ ሰዎችን ክህነት አቀባበላቸው የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ያልጠበቀ እና ሌላ አጀንዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል። በመቀጠልም
  “አብዛኛዎቹ ሌሎች አለማት በባርነት ቀንበር የነበሩ ናቸው። ነጻ እምነት ያልነበራቸው የፖለቲካና የተለያየ ነገር ተጽእኖ ያለው የወንጌል አገልግሎት የደረሳቸው ወይም የክርሰቶስን ልደት ሞትና ትንሳኤ በርቀት የሰሙ ከዘመናት በኋላ ወንጌል የደረሳቸው ናቸው። በመንፈስ ቅዱስ የተቃኙ ሰዎች በጻፉት ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ብቸኛዋ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር የምትዘረጋ ተብላ በእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል የተቀመጠች አገር ናት አገራችን። በነጻነት ታሪካችንም ቢሆን ምድሪቱን የረገጡ ነበሩ። ታሪክ እንደሚያሳየን ምድሪቱን የረገጡ ለዘመናት ነበሩ ግን በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተረጋግተው አልተራመዱም። ስለዚህ ትውልዱ ነጻ ሆኖ የኖረ ትውልድ ነው። ነጻ ሆኖ የሆነ ህዝብ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ነጻ የሆነን ህዝብ ዝም ብሎ መጥቶ የሆነ ነገር ላሸክምህ ማለት አይቻልም። ነጻነቱን ያውቃልና ደግሞም ከሜዳ ተነስቶ የሌላውን መብት የሌላውን ሥርዓት ማፈን አይቻልም።” በማለት እነ ብጥብጥና ጠብ ወዴት ነህን ነቅፈዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ በሀገሪቱ ስለነበረው ሊኖር ስለሚገባው ልበ ሰፊነትም
“ማንም የፈለገውን ሊያመልክ የፈለገውን ሊከተል ይችላል። ይሔ እግዚአብሔርም የሰጠው የህሊና ነጻነት ነው። የሰውየውም ሰብዓዊ መብት ነው። ግን የራሳችንን እምነት ጠብቀን ከማንም ጋር በሰላም መኖር እንችላለን። ይህንን እውነት ነው ማስተዋል የሚገባን። ኢትዮጵያ እኮ በእምነት የማይመስሉዋትን ሰዎች የተቀበለች አገር ናት። እንኳን ከሚመስለው የራሱ ከሆነ ህዝብ ጋራ በሰላም መኖር ሊያቅተው ይቅርና በእምነት የማይመስሉዋቸው ሰዎች ሂዱ ወደ ሀበሻ ህዝብ ወደ ሀበሻ ምድር እዛ ሰላማዊ የሆነ ህዝብ አለ። ሰላማዊ የሆነ መንግስት አለ እነርሱ ጋር መጠለያ ታገኛላችሁ ተብሎ በእምነት የማይመስሉን ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መጥተው ተጠልለዋል። ለሌሎች እንኳ የሚተርፍ ማንነት ነበረን እንኳን ለራሳችን ቀርቶ እንደዚህ አይነት ነው ታሪካችን ይሄን ታሪክ ግን በተለያየ መልኩ የሚያጎድፉ ሰዎች አሉ። እነዚህን ሰዎች ቀለል አድርገነወ አናያቸውም።” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተመራቂ ደቀ መዛሙርትን በተመለከተ “…ከዚህ በኋላ መምህራን ናችሁ አገልጋዮች ናችሁ። እንግዲህ እኛ ወዳለንበት እንኳን ደህና መጣችሁ። አብረን ሁሉን እንቀበላለን። ፈተናውንም አብረን እንቀበላለን። ተመርቃችኋል እንኳን ደስ አላችሁ ልላችሁ አልፈልግም። ምክንያቱም ወደ ደስታ አይደለም የመጣችሁት። ወደዚህች አለም ልትሔዱ ነው ክርስቶስን ወደአልተቀበለች አለም። ክርስቶስ እንደተናገረው አለሙ ተኩላ ነው እንደ በግ በተኩላዎች መሃል ልትላኩ ነው።ስለዚህ የተለያየ መከራና ትግል ወዳለበት እንቆቅልሽ ወዳለበት አለም ልትገቡ ነው። ወደ ትግል መድረክ ነው የመጣችሁት። ብዙ አገልግሎት ወደ ሚፈልገው ትውልድ፤ ስለዚህ ኃላፊነት አለ፤ መገፋት አለ፤ ፈተና አለ፤ መከራ አለ፤ ተቀባይነት ማጣት አለ።
 ክብርና ስልጣን አይደለም የሚጠብቃችሁ ዕዳ ነው የሚጠብቃችሁ። ስለዚህ እንኳን ደስ አላችሁ አይደለም የምላችሁ እግዚአብሔር ያስችላችሁ ትከሻችሁን ያስፋው ነው የምላችሁ…” በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል።
በተለምዶ በሀገራችን ገጠሪቱ ክፍል ጽንፍ የሚጨነግፋባቸው ሴቶች ሾተላይ መታቸው ይባላል። እንደ ጽንስ አጨንጋፊው ሾተላይ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን በእናታቸው በቤተክርሰቲያን ጉያ ያሉ ደቀ መዛሙርትን ለማጨንገፍ ተስፋቸውን ለማጨለም ያደረገው ሙከራ ሳይሳካለት ቀርቷል። የዘወትር ተግባራቸው ማሳደድና ማጨንገፍ የሆነው የማኅበረ ቅዱሳን ቅጥረኞች በተለመደው መረጃ አልባ የስለላ መዋቅራቸው እና በተለመደው የክስ አንቀጻቸው ከዚህ በፊት በዚህና በሌሎች ኮሌጆች እንዳደረጉት ዘንድሮም በርካታ ደቀ መዛሙርትን ለማባረር ያሰፈሰፉ ቢሆንም በኮሌጁ አስተዳደር አስተዋይነት ከወሬ ባልዘለለው ነገር ከዚህ በፊት እንደነበረው ደቀ መዛሙርት እንዳይጠቁ በማድረግ ካለፈው ስህተት መማር የቻሉቱ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ባለስልጣናት ባደረጉት ከፍተኛ ማጣራትና ጥረት ከመጨንገፍ አምልጠው ብዙ ደቀ መዛሙርት ለመመረቅ በቅተዋል። ማኅበሩ ከዚህ በፊት ያደርግ እንደነበረው በሆነ ባልሆነው ተነስቶ የቤተክርሰቲያን ልጆችን የሚያባርርበት መንገድ ከዚህ በኋላ በነበረበት ሁኔታ እንደማይቀጥል ያሳየ ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል። በቅድስት ስላሴ ኮሌጅም ሆነ በዚህ የሆነው ነገር ይህን እውነት ያስረገጠ ነው።
ታሪክ ራሱን ላይደግም ቤተክርሰቲያን ልጆችዋን ላታጣ ለረዥም ዘመናት በጉያዋ ተደብቀው የቤተክረስቲያን ልጆችን ላልለፉባቸውን ላልደከሙባቸው ሌሎች ቤተ እምነቶች አሳልፎ መስጠት ሳይፈልጉ ማባረር በግልጽ አንተ እንደዚህ ነህ በማለት በእግዚአብሔርና በሰውየው ብቻ የሚታወቀውን የእምነት ጉዳይ በሰው ልብ ገብቶ የመመዘን ያህል ባለ ድፍረት ለመመዘን እየተንቀሳቀሰ ያለው ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ በኋለም የሚያደርገው ውጊያ እንደማይሰምርበት ያሳየ የምርቃት ፕሮግራም ነበረ።

5 comments:

  1. menfes yakebelachihu tsihuf new.awo menfes!

    ReplyDelete
  2. አቤት እናቴ ድሮ ደስ ሲላት ለነገሩ ዛሬ ቅቤ እየተፈራ ነውና በመጠኑ ማድረግ አይከፋም ብፁዕ ፓትርያርኩ ያስተላለፉት መልዕክት አንጀት አርስ ነው እንዲህ ዓይነት አባቶች ባይኖሩልን ጉድ ነበር የሚገርመው እኮ በእምነት የማይመስሉአትን ሰዎች የተቀበለች ይህች ቤ/ክ ዛሬ ልጆችዋን እየገፋች ወደ ሌሎች የእምነት ድርጅቶች እየሸኘች ነው ቢባል ማን ያምናል????እንዲህ ታሪክ የሚሰሩልን አባቶችን እግዚአብሔር እድሜያቸውን ያስረዝምልን!!ቢቻልማ የእርሳቸውን ሙሉ ንግግር አትማችሁ ብታወጡልን ትልቅ ደስታ ነበር::በርቱ ተበራቱ!ለእነዚያ ምሩቃን ከመናፍቁ ማህበረ ቅዱሳን የሰወራቸው አምላክ ከጭንገፋው የታደጋቸው ጌታ እንኳን አስደሰታችሁ በሉልን!መልእክቴ ይድረሳቸው ከ 2ኛ ጢሞቲዎስ ምዕ 2:1 እስከ 4 ያለውን ያንብቡልኝ!!አደራቸውን የተቀበሉት ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ወይም ከአቡነ ጳውሎስ መስሎአቸው እንዳይታለሉ ከጌታ መንፈስ ቅዱስ እንጂ!ገና በወንጌል የሚታረስ የሀገራችን ምድር ብዙ ነው ዳር ድንበሩ ድረስ ተጓዙሳይቀድሙን እንቅደም!
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  3. ......እንደው ይቅርታ ‹የሰዋስወ ብርሃን ኮሌጅ አይደለም አደራ የሰጣችሁ ለማለት ነው›መልእክቴ ለቅድስት ሥላሴም ምሩቃን ይሁንልኝ!
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  4. በእውነት ቤ/ክንን ለማገልገል ከሆነ ደስ ይላል፤የተቀበሉት አደራ ለፍትፍት አይደለም፤
    ከ12ቱ ሐዋርያት ከክርስቶስ ጉባኤ ይሁዳ እንክርዳድ ተገኝቷል፤ስለዚህ ማንጠሪያ መንሹ በእሱ በባለቤቱ እጅ ስላለ ጠንቀቅ ነው፡፡

    ReplyDelete