Sunday, May 13, 2012

(ርእሰ አንቀጽ)የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርቲያን ሲጋለጥ

Click here to read in PDF
(በትናንትናው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰበር ያስተናገደው አጀንዳ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የተጻፈ ርዕሰ አንቀጽን የተመለከተ ነው። ርዕሰ አንቀጹ ለምን አወያየ የሚለው በብዙዎች ዘንድ መወያያ ስለሆነ ርዕስ አንቀጹን እንዳለ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ)
 ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት፣ የካህናትና የምእመናን ድምር ውጤት ናት፤ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ባልን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ማለታችን ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ብለን በጥቅሉ በምንናገርበትም ጊዜ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ማለታችን ነው፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ አካላት የተካተቱባት ቤተ ክርስቲያን አንዲት ተቋም ስለሆነችም ማኅበር ተብላ ትጠራለች፤ ራሷ ማኅበር ስለሆነችም ከዝክርና ከሰንበቴ ማኅበር በስተቀር በተቋም የተደራጀ ሌላ ማኅበር አያስፈልጋትም፡፡
ሆኖም ቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ የተሰኘ የመተዳደሪ ደንብ አውጥታ በሰበካ ጉባኤ ከመደራጀቷ በፊት የእርሷ ወኪልና ደጋፊ በመሆን ድምፅ የሚያሰሙላት አንድ አንድ የወጣት መንፈሳወውያን ማኅበራት እንደነበሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በሰበካ ጉባኤ ከተደራጀች ወዲህ ግን ሕገ ልቡና እስከ ሕገ ኦሪት፤ ሕገ ኦሪትም እስከ ሕገ ወንጌል መዳረሻ ሆነው ወይም አገልግሎት ሰጥተው አንዳለፉ ሁሉ እነሱም አልፈዋል፡፡ ይህም ማለት በቃለ ዓዋዲው የመተዳደሪያ ደንብ በየድርሻቸው ተካትተዋል ማለት እንጅ ጨርሰው ወድመዋል ማለት አይደለም፡፡
ቤተ ክርስቲያን የምትመራበትና የምትተዳደርበት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ዌም ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ሕገ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት በቅዱሳን ሐዋርያት የተደነገገ ሕግ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚመሩትና የሚተዳደሩት በዚሁ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አካል እንደመሆኗ መጠን የምትመራውና የምትተዳደረው ወይም የምትዳኘው ከፍ ሲል በሕገ ቤተ ክርስቲያን፤ ዝቅ ሲል በቃለ ዓዋዲ የመተዳደሪያ ደንብ ነው፡፡

ይሁን እንጂ በ1991 ዓ.ም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹‹የብላጊ ዝናም ከላም ቀንድ ይለያል›› እንዲሉ ከሦስቱ አካላት አንዱን አካል ለይቶ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ምቾት ወይም መብት እንጂ የቤተ ክስቲያንን ምቾት ዌም መብት ሙሉ በሙሉ የጠበቀ አይደለም፡፡ አልፎ ተርፎም የቤተ ክርስቲያኒቱን ርእሰ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን መብት የሚጋፋ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የእርስበርስ መለያየትን እንጂ አንድነትን፤ ጠብ ክርክርን ወይም ሁከትን እንጂ ሰላምን፤ ጥፋትን እንጂ ልማትን ሊያመጣ አልቻለም፡፡
ለምሳሌ ያህል በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በአድላዊነት ከተደነገጉት ጥቂቶችን መጥቀስ ቢያስፈልግ በሐተታዊ መግለጫው እንደተገለጸው ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነጻ ምግብ፣ ነጻ ቤት፣ ነጻ ሕክምና አላቸው፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ካህናትና ለሠራተኞቹ ግን የላቸውም፡፡ እንደዚያም ሆኖ አንዳንደ ጳጳሳት በእግዚአብሔር ገንዘብ የግል ቪላ እየገነቡ ያከራያሉ፤ ቤተ ክርስቲያን ለሐዋርያዊ አገልግሎት ገዝታ ከሰጠቻቸው መኪናዎች ሌላ እንደዓለማዊ ሰው ለአባት የማይገቡ እጅግ ዘመናዊ የሆኑና ከፍተና ዋጋ ያላቸው መኪናዎችን በቤተ ክርስቲያን ስም በሚያገኙት ገንዘብ በግል እየገዙ ሲያሽከረክሩ ይስተዋላሉ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የተሠሩ ቤቶችንም እየሸጡ ለግል ጥቅማቸው ያውላሉ፤ በየአድባራቱ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ለሚፈጸመው ሕገ ወጥ ብልጽግና በር የከፈቱትም እንዲህ ዓይነቶቹ አባቶች ናቸው፡፡ ሐናንያን ሰጲራ ከዚህ የበለተ ሌላ ምን አደረጉ? በቫት ተይዘው የታሰሩት ባለሀብቶችስ ከዚህ ሌላ ምን ፈጸሙ?
እንዲሁም ጳጳሳቱ ለራሳቸው ብቻ በሚመች ሁኔታ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በደነገጉት መሠረት የየሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያች ሲፈልጉ ይሾሟቸዋል፤ ሳይፈልጉ በሾሟቸው ማግስት እንደ ቤት ሠራተኛ ያለ ፍትሐ ያባርሯቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር የጡረታ ሕግ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ካህናትና በሠራተኞቿ ዘንድ የተከበረ ነው፤ ጳጳሳቱ ጡረታ የሚወጡት ግን ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በሚለዩበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ጳጳሳት ዕድሜ ልክ ያከማቹትን የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት መልሰው ለቤተ ክርስቲያን ማውረስ ሲገባቸው የሚያወርሱት ለቤተሰብ ነው፡፡
ከዚህም ሌላ በጳጳሳት ምርጫ ጊዜ የካህናትና የምእመናን ተሳትፎ የለም፤ እንደ ስም ኦን ቀሬናዊ ቆሞሳቱን ከመንገድ እየጎተቱ ለጵጵስና የሚመርጧቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብቻ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ምርጫው ብቃትና ጥራት ስለሌለው ከሢመተ ጵጵስና በኋላ በአንድ አንድ ብፁዓን አባቶች ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ ዓላማዊ የሆኑ አሳፋሪና ድርጊቶች እየተከሰቱ ነው፡፡ በቀድሞው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ግን በጳጳሳት ምርጫ የካህናትና የምእመናን ተሳትፎ ነበረበት፤ ይህም በመሆኑ የቀድሞቹ ጳጳሳት በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ምንም ዓይነት እንከን ስለአልነበራቸው የራሳቸውንም ሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር አስጠብቀው ነው ያለፉት፡፡
በአሁኑ ሕገ ቤተ ክርስቲያን እጅግ አስገራሚና አስደናቂ የሆነው አዲስ ጉዳይ ደግሞ ጥንታውያኑ ግብፃውያን ‹‹ኢትዮጵያውያን ከአዋቂዎቻቸው ጳጳሳትን አይሹሙ›› በማለት በሥርዋጽ ያስገቡት ቃል ከተሻረ ከዘመናት በኋላ ሙሉ ኢትዮጵያዊ ሳይጠፋ ግማሽ ዜግነት ያለፈው ኢትዮጵያዊ ወይም የውጪ ዜጋ ጳጳስ ሆኖ እንዲሾም በራሳችን አባቶች ዛሬ መደንገጉ ነው፡፡ በዚህ ክፍተት ሳይሆን አይቀርም ጥቂት ጳጳሳትም በአገሪቱ በሌለ ሕግና ከመንፈሳውያን አባቶች በማይጠበቅ ሁኔታ የውጭ ዜግነት አግኝተው አንድ እግራቸውን ኢትዮጵያ፣ አንድ እግራቸውን አሜካሪ አድርገው የሚኖሩት፡፡
ከሁሉም በላይ ‹‹ጳጳሳቱ ፓትርያርኩ የሁላቸውም የበላይ ስለሆነ እንደንጉሥ ይፍረት፤ እንደአባት ይውደዱት፣ እንደ እግዚአብሔርም ይመኑት›› ተብሎ በዲድስቅልያ በአንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 27 የተደነገገው ተሸሮ በአንዳንድ ተጨባጭ ችግሮች ምክንያት ጳጳሳቱና ኤጲስ ቆጶሳቱ በተሾሙባቸው ሀገሮች ውስጥ የሚሠሩትን ሥራና የሚሰጡትን ትእዛዝ ፓትርያርኩ ይመለከታል፣ ይመረምራል፤ እነሱም ማናቸውንም የማይገባ ሥራ ሲሠሩ ቢገኙ ይለውጣቸው (ያዛውራቸው)፣ እርሱ ለሁሉም የበላይ ነውና፣ ወይም አባታቸው ነውና፣ እነሱም ልጆቹ ናቸውና›› ተብሎ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 39 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጳሳቱን ከአንዱ ሀገረ ስብከት ወደ ሌላው ሀገረ ስብከት በሚያዛውሩበት ጊዜ ጳጳሳቱ ‹‹አንዛወርም፣ አሻፈረን›› በማለት ሽቅብ መልስ ይሰጣሉ፡፡
ከዚህም አልፈው በነጻ ፕሬሶች ውዝግብ በመፍጠር የራሳቸውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገበና ያጋልጣሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆነው ወጣት ትውልድም ተቀናንቶና አንጃ ለይቶ በሆነ ባልሆነው በነጻው ፕሬስ መወዛገብ የጀመረው ከእነዚሁ አባቶች ተምሮ ነው፡፡ ይህም ማለት ፓትርያርኩ ከሕግ በላይ የፈለገውን ያድርግ ማለት ግን አይደለም፡፡
ለዚህ ሁሉ ክፍተት መነሻውና ለአባቶች ገበና መጋለጥም ዋና ምክንያት ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ስለሆነ ከቤተ ክርስቲያናችን ዕድገት አንጻር ዓለም አቀፋዊ ይዘት ሊኖረውም ስለሚገባ ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም፣ ለአባቶችም ክብር ሲባል በ1991 ዓ.ም የወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲሻሻልና እንዲታረም በቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል፡፡ ውሳኔውም ከአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ማለፍ እንደሌለበት ዜና ቤተ ክርስቲያን ሳይጠቁም አያልፍም፡፡

4 comments:

  1. ርእሰ አንቀጹን ስላቀረባችሁልን አመስግኛለሁ፡፡ ግን ማነው የጻፈው መልእክቱ ሁሉንም አካል የሚነካ ነው፡፡
    ለምሳሌ፡
    “…ቤተ ክርስቲያን አንዲት ተቋም ስለሆነችም ማኅበር ተብላ ትጠራለች፤ራሷ ማኅበር ስለሆነችም ከዝክርና ከሰንበቴ ማኅበር በስተቀር በተቋም የተደራጀ ሌላ ማኅበር አያስፈልጋትም”፡ ...
    የሚለው እነ ማኅበረ ቅዱሳንን አታስፈልጉም ለማለት ይመስላል፡፡

    “…በ1991 ዓ.ም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹‹የብላጊ ዝናም ከላም ቀንድ ይለያል›› እንዲሉ ከሦስቱ አካላት አንዱን አካል ለይቶ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ምቾት ወይም መብት እንጂ የቤተ ክስቲያንን ምቾት ዌም መብት ሙሉ በሙሉ የጠበቀ አይደለም፡፡” ....ይሄኛው ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የሲኖዶስ አባላትን ብቻ ተጠቃሚ ያደረገ ስለመሆኑ ይናገራል፡፡

    “…ሕገ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት በቅዱሳን ሐዋርያት የተደነገገ ሕግ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚመሩትና የሚተዳደሩት በዚሁ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አካል እንደመሆኗ መጠን የምትመራውና የምትተዳደረው ወይም የምትዳኘው ከፍ ሲል በሕገ ቤተ ክርስቲያን፤ ዝቅ ሲል በቃለ ዓዋዲ የመተዳደሪያ ደንብ ነው፡፡”.... ይሄ ደግሞ ቤ/ክኗ ራሷ ብቻዋን ባለህግ እንደሆነችና ሌሎቹን መቀላቀል እንዳለባት ይመክራል፡፡ አሪፍ የእንቀላቀል መልእክት ናት የሚሰማ ካለ፡፡

    “..ጥቂት ጳጳሳትም በአገሪቱ በሌለ ሕግና ከመንፈሳውያን አባቶች በማይጠበቅ ሁኔታ የውጭ ዜግነት አግኝተው አንድ እግራቸውን ኢትዮጵያ፣ አንድ እግራቸውን አሜካሪ አድርገው የሚኖሩት፡፡” ይቺ ደግሞ እነ አባ ፋኑኤልን ትነካለች፡፡ አባ ፋኑኤል አሁኑኑ ጵጵስናቸውን ሊነጠቁ!

    ታዲያ ማነው ያልተነካ? ምእመንና አባ ጳውሎስ ብቻ~:: ዘይገርም ርእሰ አንቀጽ

    ReplyDelete
  2. Corruption is an extermely hurts and damaged directley in our poor church, people and gov. Also it is unethical and illegal in religious society. Holy synod should be stop immidately that use church money for private use. Let see one example I read from this blog one of false father he called him self aba ABRHAM, built multi million Birr VILLA in Addis Ababa, my question is clear and concise how and where the source of this money came from? Infact, it church money Aba Abrham to built his current villa will be save money the next 600 years on his current income unless imposible. So, his villa ,auto, and other income will be controle by anti corruption official otherwise waste of time to much talk. He stole money from here in USA too. Shame on Aba PAULOS HOW CAN HE SIT WITH SUCH KIND OF CORRUPTED BISHOP.

    ReplyDelete
  3. Yeha hethbe bethu yawkal men albat yehn yemtesefut melekt yemanenem leb ayashefetem kenant gon yemikomewem menem merega yemayagegew sew new atdekemu betekrestyan ye Ortodoxawyan nech enant ena gulbetegaw papas tasaferalachehu

    ReplyDelete
  4. Villa bet yalachew -Begenzeb Yekeberu -Zemenaw Mekina yalachew yetewsenu Nachew 1 Abba Kale Tsidik( Abune Abirham ) 2 Abba Tekeste ( Abune Samueil) 3 Abba Gebre tinsae ( Abune Entsos )4 Abba Melaku ( Abune Fanueil )5 Abune Diyoskoros 6 Abune Daneil 7 Abune Gebreil 8 Abune tsimotewos 8 Abune Kewsitsos- 9Abune Matiyas 10 Abune Epifanyos Tewdadar yelachewm neger Gin Minm malet aymeslegm Serkew Kehone Masrega Mekireb Alebet Keman -Keyet-Meche mebal alebet Genzeb silalachew bicha menekef yelebachewm Kehizib netsikew sayihon beteleyaye mikinyat sew yiredachewal Ye Katolik Papas Heger yemigeza habit alachew Ortodoks tewahedo yediha bicha mesebsebiya yadergat manew ? enkanm keberu Menfik Kemehon yeteshale new

    ReplyDelete