Wednesday, May 23, 2012

ሲኖዶሱ የሚመራው በማን ነው? በፓትርያርኩ ወይስ?


Click here to read in PDF
የሰሞኑ የሲኖዶስ ስብሰባን ሂደት ላየ ሊለው የሚችለው ብዙ ነገር ይኖረዋል። በተለይ በስብሰባ ላይ በተነሳ ሀሳብ ሁሉ ላይ ከውጭ ካለው አየር ምክር የሚሹ አንዳንድ ጳጳሳት አካላቸውን ሲኖዶሱ ላይ አድርገው ልባቸው ማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ ውስጥ አስቀምጠው በማቅ ሳንባ ነው የሚተነፍሱት፤ የሚተነፍሱበት አየር ደግሞ በልዩ ሁኔታ ማንያዘዋል በሚል ኬሚስት የተሰራ ነው። ይህ ታዋቂ ኬሚስት የሚቀምመው ነገር የሚባል ኬሚካል ሲሆን በመጀመሪያ የሚሞክረውም አባ ሳሙኤል የሚባሉ ባለመንታ ችግር ጳጳስ ላይ ነው። እሳቸው ላይ በትክክል እንደሰራ ሲያውቅ እሳቸውን አስጨብጦ በእለቱ በየሚተነፍሱት አየር ለሚያጥራቸው ሌሎች ጳጳሳት ይልከዋል።
ከዛማ ገበርዲኑን ለብሶ ቤተ ክህነት ግቢ ላይ መዞር ነው። ከዛ ጋሻ ጃግሬዎቹ ሲከቡት የዛሬ አጀንዳ ይህ ይህ ነው የሚወሰነውም ይሔ ነው እያለ ራሱን በመንፈስ ቅዱስ ቦታ አስቀምጦ ያወራል። ማታ ላይም የኮሌጁ ምሩቃን ቢሮ ላይ መብራት አጥፍቶና መጋረጃ ጋርዶ ሰው የሌለ አስመስሎ ይቀመጣል እንዲህ እንደሚያድርግ የሚያውቁ የኮሌጁ ተማሪዎች ታድያ ማንያዘዋል የሚባል የሌሊት ሰይጣን አለ ብለው “በመፍራት” ወደ ምሩቃኑ ቢሮ አካባቢ አይሄዱም። 

 ይህ ሰው ታድያ መሸት ሲል ሶስት ወይም አራት ሰዓት ላይ በአባ ሳሙኤል ስልክ ጥሪ መሰረት ወደ አባ ሳሙኤል ሄዶ ስብሰባው እንዴት ነበር? ብሎ ይጠይቃል። ታድያ አባ ሳሙኤልም በተለመደው ጀብደኛ ባህሪያቸው እንዲህ ተብሎ እንዲህ ተደርጎ እንዲህ ተወሰነ ብለው ይነግሩታል። አጅሬም 6ሰዓት ወይም 7 ሰዓት ላይ ወጥቶ ይሄዳል። አንዳንዴም እዛው ያድራል። ያደረም ቀን ወጥቶ የሄደም ቀን ተማሪ ያየዋል። ተማሪ ለጥናት ማታን ይመርጣልና ሹክክ ብሎ ከአባ ሳሙኤል ቤት ሲወጣ ያዩታል። ቀን ለደጀ ሰላም ብሎ አስቀድሞ ያዘጋጀውን ሪፓርት ያወጣና እሳቸው ካሉት ጋር ያስተያየዋል። የሚሻሻል ካለ አሻሽሎ ቅመም መጨመር ካለበትም ጨምሮ ደጀ ሰላም ላይ ፖስት እንዲደረግ ለአሉላ ይልካል። አንዳንዴም ለአሉላ በስልክ ይነግረውና እሱ የራሱን ቅመም ጨምሮ ያመጣዋል። ታድያ ይህ ሁሉ ቅንጅት እያለ ደጀ ሰላም እውነት የማታወራው ብሎ ለሚጠይቅ ጠያቂ እንዲህ የሚል መልስ እንሰጠዋለን። ብዙ ጊዜ ደጀ ሰላም የተሳሳተ ዘገባ የምታወጣው በሶስት ዋና ዋና  ምክናቶች ነው።
የመጀመሪያው በአባ ሳሙኤል ሪፖርት አሰጣጥ ስህተት ነው። ሁለተኛው ደግሞ በማንያዘዋል ስህተት ነው። ሶስተኛው ደግሞ በአላማ ነው።
ማንያዘዋል ስብሰባውን እሱ እንደሚመራው እሱ እንደሚወያይበት እሱ እንደወሰነው አድርጎ ሲያስብ ኩራት ይሰማውና ለራሱ በመስታወት ፊት ቆሞ እህሳ ፓትርያርክ ማንያዘዋል እንዴት ነህ? ይለዋል። እራሱን እንደፓትርያርክ ስለሚያስብም በኔ ላይ ተደረቡብኝ ብሎ የሚያስባቸውን ቅዱስ ፓትርያርኩን አምርሮ ይጠላል። በእሱ ፊት ወዳጄ ብሎ የሚጠራቸውን ሰዎች ሁሉ የወዳጅነት መስፈርት አንድን የግድ ማሟላት አለባቸው። እርሱም ፓትርያርኩን መጥላት ነው። አንዳንድ ወገኖች ማንያዘዋል ለምንድን ነው ነጭ ልብስ መልበስ የሚወደው? ብለው ይጠይቃሉ። ታድያ መላሾች ሲመልሱ አንዳንዶቹ ቅኖች ፈሪሳዊ ስለሆነ ነው ይላሉ ሌሎች ደግሞ ላደገበት አካባቢ ያለውን ፍቅር በአለባበስ ለመግለጽ ነው ይላሉ ውስጠ ሚስጢሩን የሚያውቁ ደግሞ በጓዳ በሚሰራው ስራ ፓትርያርኩ እኔ ነኝ ብሎ ስለሚያምን የፓትርያርክነት ህልሙን ያሳካ ስለሚመስለው ነው ይላሉ። ፓትርያርክነት ህልሙ ስለሆነ ህልመያርክ እንበለው ይሆን?

No comments:

Post a Comment