Thursday, May 24, 2012

የሲኖዶሱ ስብሰባ ተጠናቀቀ

Click here to read in PDF
በልዩ ልዩ ድራማዎች የታጀበውና በስድብና በከፍተኛ የጥላቻ ስሜት የታጀበው የሲኖዶሱ ስብሰባ በትናንትናው ዕለት ተጠናቀቀ። የመዝጊያው ንግግር ራሱ ራሱን የቻለ ድራማ ተስተናግዶበታል።

በትናንትናው ጠዋት ውሎ የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ እንደገና ያነጋገረ ሲሆን መተዳደሪያ ደንቡ እስኪሻሻል እስከ ጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ብቻ ከሰንበት ማደራጃው ተለይቶ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ሥር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል። አዳዲስ ጳጳሳት እስኪሾሙ ድረስም አቡነ ገብርኤል ቦረናን አቡነ ዮሴፍ ጅጅጋን ደርበው እንዲሰሩ ተወስኗል። አቡነ ሳሙኤል ከልማትና ክርስቲናዊ ኮሚሽን በተጨማሪ ትንሳኤ ዘጉባኤንና የቤተክህነት ቤቶችን ያስተዳድሩ የሚል ሀሳብ ቢቀርብም ገጠሩን እንኳ አይተውት ኣያውቁ ቦረና ቢሄዱ ምናለ? የሚል ሀሳብ በመቅረቡ ሁሉ ቀርቶ በልማትና ክርስቲያናዊ መምሪያ ብቻ እንዲያስተዳድሩ ተወስኗል።
የመዝጊያው ሥነ ሥርዓት አዲስ ድራማ ያስተናገደ ሲሆን ጋዜጠኞች ከተጠሩ በኃላ የሚነበበው ጽሁፍ እኛ ያዘጋጀነው ነው ብለው እነ አባ አብርሃም ከማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ አስጽፈው ያመጡት መግለጫ እንዲነበብ በመፈለጋቸው መግለጫው ለሰዓታት ተጓቷል። ተጽፎ  የመጣው መግለጫ የማኅበሯን ጽድቅ የሚዘረዝርና ማኅበርዋ ለሀገርም ለቤተክርስቲያንምም ተቃሚ ስለሆነች ማንም ሊቃወማት አይችልም። የሚል ይዘት ያለው እግረ መንገድም መንግስትን ለመጎንተል ያለመ ነበር። ቅዱስነታቸው ግን በሲኖዶስ ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ ስለአጠቃላይ የስብሰባው ሂደት ነው እንጂ ስለ አንድ ማኅበር አልዘግብም በማለታቸው መግለጫው የዘገየ ሲሆን በመጨረሻም መግለጫው ተሻስሎ እርሱን አንብበዋል።
 የዘንድሮው የሲኖዶስ ስብሰባ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ መንፈስ ቅዱስ የራቀው በስድብና በእርግማን የታጀለ በጳጳሳት መካከል የነበረውን መከባበር ያጠፋ እንደነበር ታውቋል። በሲኖዶስ ስብሰባ ጳጳሳት ለመጀመሪያ ጊዜ አንተ አንተ ተባብለው የተነጋገሩ ሲሆን በተለይም ዘንድሮን የማያልፉ ይመስል በነገርና በአመጽ ልባቸው ተደፍኖ የነበረው የአባ አብርሃም ሁኔታ ግን እንኳን ጳጳስ በእንዲህ ያለ ጉባኤ ቢታደም ዱርዬ እንኳ የማያደርገውን ሥርዓት አልበኝነት አሳይተዋል ተብሏል። ጳጳሳትን አንተ እያሉ መሳደባቸውንም ደጀ ሰላም አድንቃና ተደንቃ አቡነ ፋኑኤልንከእኔና ከአንተ…” አሉ በማለት ዘግባልናለች።
ውግዘት የሚመለከታቸውን ትተን ውግዘት የማይመለከታቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች በተመለከተ አባ አብርሃም  ሁለት ተልዕኮ ይዘው ተንቀሳቅሰዋል። የመጀመሪያው ማቅ የሰጠቻቸው ተልዕኮ ሲሆን እስዋም ሆን ብላ ቤተክርስቲያኒቱን አንፈልግም ብለው የራቁትን ወገኖች ቀላቅላ ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያሉትን ወገኖች ማስመታት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የግላቸው ሲሆን እሳቸው የቅባት ሃይማኖት ተከታይ በመሆናቸው ማንኛውም የተዋህዶ አማኝ መናፍቅ ነው ስለሚሉ ከልባቸው የሚያምኑበትን የተዋኅዶ ልጆችን “ምንፍቅና” ማውገዝ በማንኛውም መንገድ ቢሆን ለውጥ ስለሌለው በመካከል ተደባልቀው የተጨመሩት ግለሰቦችና የማኅበራት ንጹህ መሆን አለመሆን ሳያስጨንቃቸው ይወገዙ ሲሉ ተደምጠዋል። የሚያሳዝነው የተዋኅዶ ልጆች ሆነው ሳለ ሰውየውን ተከትለው እስር ስር ሲሉ የነበሩት ሌሎች ጳጳሳት ጉዳይ ነው።
በዚህ የሲኖዶሱ ስብሰባ ከመቸውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ በርካታ ጳጳሳት ስብሰባውን አቋርጠው የሄዱ መሆናቸውም ታውቋል። የአብኛዎቹም ምክንያት ስድብና እርግማንን እያዳመጥን መቀመጥ እንችልም የሚል ሲሆን እንዲያውም አንደኛው አባት መከባበርና መግባባት እንዲሁም መፈራራት የነበረበት የአባቶቼ ዘመን ናፈቀኝ ምነው ይሔንን ጉድ ሳላይ በተጠራሁ ኑሮ ሲሉ ተደምጠዋል። እንዲህ ያለ በግልጽ መንፈስ ቅዱስ ከራቀው ጉባኤ መታደም በራሱ የኃጢአቴ ቅጣት ነው። ሲሉም አክለዋል።
በርግጥም ጉባኤው መንፈስ ቅዱስ ራቀው እንደነበር ግልጽ ነው። እግዚአብሔርን ሰምቶ እግዚአብሔር የፈቀደው ይሁን ብሎ ለስብሰባ ከመግባት ይልቅ አድማ መትቶ እና ሴራ ሸርቦ እኔ ያልኩት ካልሆነ ጉባኤው ይታመሳል የሚሉ አባቶች ያሉበት ስብስብ መንፈስ ቅዱስ ከራቀው ከሚለው ውጭ ሌላ ምን መገለጫ ይኖረዋል? በጉባኤው ላይ ተገኝተው በሀሳቦች ላይ ተዋያይተውና እዛው ጉባኤው ላይ መወሰን እያቃታቸው ውሳኔውን ሆን ብለው ከማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች እስኪማከሩበት ድረስ የሚያዘገዩ አባቶች የመንፈስ ቅዱስን ምሪት የሚጠብቁና የሚያምኑ ማለትስ ይቻላልን?
በቀደሙት አባቶች ይደረግ የነበረው የሲኖዶስ ስብሰባ ተጀምሮ እስኪያልቅ ደረስ በስብሰባው ላይ የሰው ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ሀሳብ ብቻ እንዲፈጸም ከውጭ ሰው ጋር ያለመገናኘት አካሄድን ትተው ተጠሪነታቸውን ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለማቅ አድርገው ጠቅላላውን የስብሰባውን አካሄድ ለማቅ ሪፖርት እያቀረቡና ቤተክርስቲያን ከሰጠቻቸው ደረጃ ወርደው ከማህበሩ ሰዎች መመሪያ እየተቀበሉ ወደ ስብሰባ የሚሄዱ አባቶችን ስንመለከት ቤተክርስቲያን ምን ያህል ለሰማያውዊም አምላክ ሰማያዊ ሀሳብ መገዛት ፈተና የሆነባት ዘመን ላይ መሆንዋን እንገነዘባለን።

3 comments:

  1. wod yegziabher lejoch ye ethiopia orthodox tewahido betecrstiyan wordet kejemere 20 amet molla .mahbere kidusan ejun arzimo endefelge yemiyankesakeswo sinodos menfes kidus yimerawal belen anamenem.yesbsebawo wotet yemiyasayew papasat teblew yetekemetuten abatoch yemenfesawi ena sgawi bislet manes sihon wedefitm benzihu abatoch amerar wedeteshale menfesawi ena economiyawi edget letshager endematchel gebtognalselzih lebetecrstiyanitu nesa mewotat 1 yih nekersa mahber kechankawa lay mewored alebet 2 yetshomut abatoch lekrstos adera tamagnoch honew le hezb ena lehager yemitekmu wosanewochen kemanm teseno woch hone liwosenu yigebal 3 sinodosu kidesena yegodelachew tera papasat yemolubet selhone bekenona bete chrstiyan mesert lileyu woyme degmo niseha ligebu yasfelgal ; erasun yalgeza ye egziabheren bet liyastedader aychilm.

    ReplyDelete
  2. በጣም ደስ የሚለው ነገር እምነትን ከልብ አውጥቶ የሚወስድ ማንም የለም። ተወገዙ አልተወገዙ ምንም ትርጉም
    አይሰጥም። ምክንያቱም ለእውነተኛ ክርስቲያኖች እንዲህ ተበሎ ተፅፉአልና፤ በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ክፉውን
    ሁሉ በውሸት ቢናገሩባችሁ፣ መከራም ቢያበዙባችሁ፣ የምታምኑትን ታውቃላችሁና እንዲሁም እኔ ዓለሙን ሁሉ
    አሸንፌዋለሁና አይዙአችሁ፣ በመከራም ደስ ይብላችሁ እስከ መጨረሻው የፀና እርሱ ይድናል ብሎ ጌታችን አምላካችን
    መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ አስጠንቅቆናልና ከምንም አንቆጥረውም። ድሮም እኮ ማቅ የግብር አባቱን
    የዲያቢሎስን ሥራ ለመስራት ነው የሚሩሩጠው ይህ እኮ የታወቀ ነው። ነገር ግን ድሉ የኛ የተገፋነው ክርስቲያኖች ነው።

    ማቅና ግብረአበሮቹ እንኩአን አሁን ጌታችንንም ሰቅለው ሲሳለቁና በትዕቢት ተወጥረው ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው። ታዲያ
    ማቅ ያልገባሽ ነገር ቢኖር ድሉ ማታ ነው ድሉ ሲባል ሰምተሻል አይደል\ የኛ ጌታ እኮ የአሸናፊዎች አሸናፊ ነው።
    እንኩአን በክርስትናቸው የበሰሉትን ወንድሞቻችን ቀርቶ ገና ወተት የሚመገቡ በክርስትና ያልበሰሉትን እንኩአን ከእጁ
    ማንም ፈልቅቆ ሊያወጣቸው አይችልም። አሜን። ማፈሪያው ማቅ ኪ...ኪ....ኪ.................

    ReplyDelete
    Replies
    1. I pray for you all the time!May 28, 2012 at 2:13 AM

      for all of tehadisos whose heart is aching by enemies of your precious lord, listen to me: i was praying to lord about you all. lord replied:" when everybody seems to be away from you, i come very closer to you all.now it is a time i stood up to collect my final harvest. you are my loyal servants. remember that i am God almighty, i am not just a man. so, do i forget what you received due to my holly name? think what was happening in the church history. no one comes to me without will of my Father.you are mine. mk is not mine. because it is my Father's will. you are receiving these all troubles because it is your heavenly Father's will to have a history similar to your lord." my brothers i just cried when i recognised this message. finally lord said" avoid insulting and violent speech at all. you all were like mk before i came down from heaven. surely not better. so did i concentrate on information collection and establishing accusations? no. to whom do you expose somebody's secrets for every body is corrupted minded i just went to the poor and preached God's saving news. do the same thing now. i will give you unexpected victory soon. now i am very nearest to you than any time else. i want you all to suffer only because you are mine, not by violation of earthly law. even i dare to order you to love mk and their fathers . the only way you win is by my love.your teaching of my word is very important to me rather. i am changing the lives of many people. you may not know how many people nurturing. you will know by the time i give you reward in my kingdom. only pray and preach the gospel vigoriously, i will give you endless victory" yibarki!yikadisi! selamun yisti!fitun yabrali!

      Delete