Sunday, May 27, 2012

አባ ሳሙኤልና ሚጡ


መቼም በዚህ ወር ቤተክርስቲያናችን ያላስተናገደቸው ጉድ የለም። አባቶቻችን በቁም ነገር ያሳልፉታል ብለን የገመትነው ስብሰባ ገና ከመነሻው በጋዜጣ መንፈሳዊ ሰዎች ነን እያላችሁ ለሁሉ ሞተናል በሚል ሥርዓት ውስጥ አልፋችሁ ስታበቁ ለምን ሀብት ታከማቻላችሁ? ለምን አትከባበሩም እንደ መንፈሳዊ ሰው አንዱ አንዱን መሸከም ለምን ይከብደዋል? በአባቶቻችን ዘንድ ያልነበረ በእናንተ እንዴት ተከሰተ? ደሞ መጽሐፍ አገራችሁ በሰማይ ነው ሲል እናንተ አረ የለም በአሜሪካ ነው እያላችሁ ዜግነትን ታከማቻላችሁ ተው እንዲህ ያለውን ነገር!! ሥርዓት አፍርሳችሁ ሀብት ታከማቻላችሁ ሀብት ለቤተክርስቲያን ማውረስ ሲገባችሁ ለሥጋ ዘመድ ታወርሳላች!! ግድ የለም አባቶቼ ንስሐ ግቡ የሚያዋጣው እሱ ነው ተባልን ብለው ጣራ እየቧጠጡ ንዴት አስክሯቸው በማኅበርዋ አጋፋሪነት የጋዜጣው አዘጋጆች ካልተወገዙ እያሉ አራት ቀን ሙሉ ስለጋዜጣ ያወሩባት ተዓምረኛ ወር ነች።
ደግሞም እንዲሁ  በዚህ ወር ማኅበሯ ራስዋን ከፍ ከፍ አድርጋ እንደ ሳጥናኤል ወደ ላይ ቀና ብላ እያየች ከኔ በላይ ሌላ አለ እንዴ? እያለች መጠየቅ ጀመረች ወር ናት። ይኸው በቤተክርስቲያኒቱን ነገስኩባት እኮ መሻቴ ተፈጸመ እንግዲህ ራስ ሆንኩዋት እያለች በውስኪ ጠርሙስ በኩል ራስዋን ማየት የጀመረችበት ወርም ነው። እንደሚታወቀው በውስኪ ጠርሙስ በኩል የሚታይ ነገር አቅልን አሳጥቶ ራስን አስቶ ከመስመር የማስወጣት አባዜ እንዳለሁ በልምምድም በተሞክሮም የሚበልጡን የማኅበሯ ሰዎች አይስቱትም። እኛማ እንዲህ ያለው ነገር የማይነካካን የእኛም ሆነ የቤተክርስቲያን ራስ ማን እንደሆነ አሳምረን የምናውቅ እና እሱን የምናከብር ነን። ጌታ በክብሩ ሲመጡበት ምን እንደሚያደርግ በቅርቡ ያሳየናል።
ሌላው እነዚህ አባቶች “ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ከእርሱ” ነው የሚለውን አምላካዊ ቃል አንብበው ስለማያውቁ ሳያፍሩና ሳይፈሩ “እንዴ ሆሆይ እንዴት ያለው ደፋር ቢሆን ነው? ዋናችን ኢየሱስ ነው እኮ ነው ያለው? አረ እንዲህ ያለውን ነገር ሳንሰማ ብንሞት ይሻለን ነበር። ኢየሱስ ዋና ነው ይላል እንዴ? ይወገዝልን!!” እያሉ ከሌሎቻችን ተሰውራ ለእነርሱ እና ለልጆቻቸው የማቅ አባላት ተሰውራ በተገለጸች ልዩ ሃይማኖት አማካኝነት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዋና ነው ማለት ከሁሉ የከፋ “ምንፍቅና” ነው በማለት አወገዝን ያሉባት ወር ነች።
ዋናቸው እሱ የዘላለሙ ንጉስ እርሱ የሰላሙ አለቃ እርሱ ብቸኛው መጽናኛችን እርሱ የአለሙ ሁሉ አስገኝ ካልሆነላቸው ማን ሊሆንላቸው ነው? ብለን እጅግ አዝነን ሳለን “…ይወገዙልን!! የምን ጠርቶ ማናገር ነው የምን አቋም መጠየቅ ማኅበረ ቅዱሳን ያለውን አምኖ ማውገዝ ነው። አለቀ ደቀቀ።” ከሚሉት ጳጳሳት መካከል አቡነ ሳሙኤል ኢየሱስ ክርሰቶስን ዋና ማለት ምንፍቅና ነው ያሉበትን ምክንያት ደረስንበት።
መቼም እኚህ ሰው ተዋረዱ ሲላቸው የሚኖሩት በስላሴ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ከተማሪ ጋር ነው። ተሜ እንኳን ነገር ፈልጎት መጥቶ እንዲሁም አሽትቶ የመድረስ ባህሪ ያለው ነው። እናማ  በአባ ሳሙኤል መዝገብ ዋና ተደርጋ የምትወሰደው ሚጡ እስዋም ከሰውየው ጋር መራራቅዋ ጨንቋት ባልተጠበቀ ሰዓት ከች ትላለች። ልክ እስዋ ስትገባ አትመጣም ተብሎ ሌላ ባለድርሻ ቀድማ መግባትዋን ያየ ተሜ ምን ይፈጠር ይሆን እያለ ከኋላ ከኋላ ቀስ ኣለ መከተል ይጀምራል። ተማሪዎች በሚያሳዩዋት ፊት ደስተኛ ያልሆነችው ሚጡም ለወትሮው ስልክ ደውላ በር እንዲከፈት የምታዘው ገና የኮሌጁ መግቢያ በር አካባቢ ስትደርስ ነው። ያን ቀን ታድያ ስትደውል ስልክ አልነሳ በማለቱ መናደድ ጀመረች።
የጳጳሱ መኖሪያ ጋር እስክትደርስ ድረስም ደጋግማ ብትደውልም ስልክ አልነሳ አላት። ልክ በር አካባቢ ስትደርስም ከኋላ ሲከተል የነበረው ተሜ በድንገት የሁለቱም እግር ጫማ ይፈታበትና በትክክለኛ አገላለጽ ይፈታውና ለማሰር ጎንበስ ይላል ክፋቱ ደግሞ ጫማው አልታሰር ብሎ የሰው ጉድ ያሳየዋል። ሚጡ በር ላይ ስትደርስ በሩን በኃይል መደብደብ ጀመረች የሚከፍት የለም። ጠጋ ብላ በመስኮት ስታይ ሌላ አዲስ ሴት ቀድማ ስፍራ መያዝዋን አወቀች። ያኔማ አበደች። በሩን በእግርዋ እየደበደበች “ክፈት” እያለች መጮህ ጀመረች  “ክፈት … ጳጳስ ክፈት ብዬሀለሁ ክፈት” እያለች በሩን በእግርዋ መደብደብ ጀመረች። ያኔ ታድያ በስብሰባ ደርቆ የነበረ ገላቸው እንዲታሽላቸው ሚጡ እስክትመጣ አላስችል ብሎዋቸው ሌላ ያስገቡት አባ ሳሙኤል በር ሳለ መስኮት ከፍተው አይናቸውን እያሻሹ ምንም እንዳልተፈጠረ ምንድን ነው? ይላሉ። በብስጭት እየተንተከተከች ያለችው ሚጡ ገና መስኮት ሲከፍቱ በጥፊ ትላቸውና “በሩን ክፈት” ብላ ጮኸች። ያኔ ነገሩ ያላማራቸው አባ ሳሙኤልም መስኮቱን ቶሎ ይዘጉና ወደ ዘበኞች ደውለው ድረሱልኝ አሉ። ዘበኞቹም መጥተው ችግርሽን ተረድተነዋል በሚል ስሜት እያባባሉ ከግቢ አስወጡዋት።
እኛም ከሁሉ ከሁሉ ዋናችን ኢየሱስ ነው የሚለው ቃል እንዴት ሰውን ያስወግዛል ብለን አዝነን የነበረን ሰዎች ይኼን ስንሰማ ሀዘናችን ለቆን እውነታቸው ነው ማለት ጀምረናል። እነ ሚጡ ዋና የሆኑባቸው ጳጳሳት የኢየሱስ ክርስቶስ ዋና መባል ቢያበሳጫቸው እውነት ነው ብለን “ተቀብለናቸዋል”። የመከረ ጋዜጣ ይወገዝ ያሉ “ቅዱሳን” አባቶች ጢፊ እያጣጣሙ መቀመጣቸው ገርሞን ችግራቸውን ለመረዳት ሞክረናል። አቡነ መርሃ እንዳራቸው ሲሉዋቸው የነበሩ “መነኮሳት” ሁሉ እሳቸው ሲሞቱ ጳጳስ ሆነው መጽሀፍ ለማንበብ ጊዜ የሚነሳ ፍቅር ውስጥ ወድቀው መኪናም እየገዙ፣ ቤትም በጋራ ስም እየገዙ፣ ካፌም እየከፈቱ፣ ቤት እንዲያስተዳድሩ ለዋኖቻቸው እየሰጡ በህልምም በእውንም ፊታቸው ላይ ድቅን እያሉ ሰላም የሚነሱዋቸው ዋኖቻቸው ሳሉ እንዴት ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና ይባላል?
እውነታቸውን ነው!! እንዲህ ያለውን ሀሳቤም አላማዬም ዋናዬም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የሚለውን ሁሉ “እያወገዙ” እንደ እነርሱ ዋናቸው ገንዘብና ሴት የሆኑላቸውንና ኢየሱስ ክርሰቶስ ከተወለደ ከሁለት ሺህ ዓመት በኃላ እንኳን መወለዱን ያልሰሙትንና ኦሪታዊያኑን የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን እያሉ ይቀጥሉ። አፈርኩብሽ እንዳልል ከአንቺ ማንነት አንጻር ሀፍረት ራሱ ያፍራል አሉ። አይ አባቶቻችን!!


6 comments:

  1. እኛማ እንዲህ ያለው ነገር የማይነካካን የእኛም ሆነ የቤተክርስቲያን ራስ ማን እንደሆነ አሳምረን የምናውቅ እና እሱን የምናከብር ነን!!!!!kikikikiki.......asafari menafikan!!!!ye diabilos telalakiwoch!!!min min ????iski lelam chewanetachihun giletu1!!!!

    ReplyDelete
  2. Yemayerebu dedeboch nachu afehen kefetena manenethen lengerhe bado ersonch nachu!!!!!

    ReplyDelete
  3. ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
    እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።
    ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።
    ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
    ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።
    እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
    ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።
    ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤
    በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።

    ReplyDelete
  4. tell us more about this people. they are not servants of God

    ReplyDelete
  5. Gud Sayesema....E/R Amlak yeqer yebelachew. Be ewnet aferku aferku Egzioooooooooooo!

    ReplyDelete
  6. እኔ የምለው ጳጳሳቱ ሁሉ በሽተኛ ናቸው እኮ አታውቁም እንዴ አውደ ምህረቶች ምነው ወጣ ብላችሁ ሌላመ ብታዩ ስለ አቡነ ኤፍሬምስ ምናለ ብትጽፉ የቢሮ ሰራተኛው 85 ፐርሰንቱ ዘመዳቸው ነው ሲያስነጥሱ ልቡን የሚይዝ እሳቸው እንቅፋት ሲመታቸው የእሱ ጥፍር የሚላጥ ከቢሮ የብዙ ዓመት የቤተ ክርስቲያንን ቅን አገልጋይ በግፍ አባረው በጥንቆላ የሚታወቅ ሀገረ እንትፍ ያለውን የሚያቀርቡ በ97 ዓመታቸው 1885 ቤተ ክርስቲያን የሚመሩ አሁን ደግሞ ይብስ ተብሎ ለዚያን የሚያክል ሀገረ ስብከት ፀሐፊ የእህታቸውን ልጅና ሰማይ ብልጭ ቢል በስመ አብን የማያውቅ ከዚህ በፊት የሒሳብ ሹም በመሆን በስውር ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ሲያገለግል የነበረውን አቶ ፈቃደ ደመሳን ዋና ፀሐፊ ያደረጉ ባለፈው ወር በሀገረ ስብከቱ የተደረገውን ታላቅ ጉባኤ የተሐድሶ መፈንጫ ሆነ ብለው ያኮረፉ በጋሻው ወለንጪቲ ሰበከ ሲባሉ አጎራባቹ ምንጃር ነው ሀገረ ስብከቴ እዳይመጣ ብለው በጋሻውን እንዳይቀበሉ ብቻ ለማውገዝ ምንጃር ድረስ የሄዱ የማቅ የአባልነት ደብተር ያላቸውና በየወሩ የአባልነት ክፍያ የሚከፍሉ አረ ስንቱ ይወራል ምነው ህዝብስ ቢድን እናንተስ ብትዘግቡ

    ReplyDelete