Friday, May 25, 2012

ማን ይሆን እውነተኛ? “ለማህበረ ቅዱሳን” የተሰጠ ምላሽ:

Click here to read in PDF
(ውንድማችን ዲ/ን ሙሉጌታ ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን ለመሆንዋ “ልሳነ ሌዋታን “ደጀ ሰላም” የማን ናት?” በሚል ርዕስ በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ጽሁፍ በዚህ ድረ ገጽ ማውጣቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ የማቅ ሰዎች ስንሸፍነው የነበረው እውነት ተገለጸ በማለት ድንጋጤና ፍርሀት በተቀላቀለበት መልኩ የእኛ አይደለም በማለት እየተሯሯጡ ይገኛሉ። ማኅበርዋ አርቃ ሳትመትር በብሎጉ ላይ ያወጣችው ጽሁፍ የሚያስከትልባትን ችግር ውላ አድራ መገንዘብ በመቻሏ ጽሁፉን ለመሰረዝ ብትሞክርም ጎግል ግን እውነትን መግለጽ ስለማይቸግረውና አንዴ ተጭኖ የነበረ ነገር ሲወጣ/ሲሰረዝ ምን እንደ ተደረገ የሚገልጽበት መንገድ ስላለው የማኅበረ ቅዱሳንን የእኛ አይደለም ጫጫታ ሊያግዝ አልቻለም። የማቅ ሰዎችም ዋናውን ማረጋገጫ ትተው በተጨማሪ ማስረጃነት የቀረቡ ጹሁፎችን ለመቃወም ሞክረዋል። ቀድሞ ሲጠየቅ ይኸው ብሎ ከተፍ ያደርገው የነበረውን     ጽሁፍ ሲሰረዝ ደግሞ ተሰረዘ ማለቱ አናዷችሁ ጎግልን በተሀድሶነት ሳትጠረጥሩትም አልቀራችሁ? ሲል የሚጠይቀው ዲ/ን ሙሉጌታም የእኛ አይደለም የሚል የካፈርኩ አይመልሰኝ ጫጫታችሁን ከቀጠላችሁ የእናንተ እንደሆነ አብራርቼ ልግለጽላችሁ ብሎ ይሄን ድንቅ ጽሁፍ ጽፏል።)
የሀገሬ ሰው ቅጥፈት የለመደች እጅ ከንስሃ ይልቅ ለዓመጽ ቅርብ ነች። እንዲል ይህ ነፍሰ ገዳይ ሳለ ራሱን “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት የሚጠራ ድርጅት ስሙ የማይጠራ አጋንንት የነገሰበት “የጎበዝ” ስብስብ በስህተት ላይ ስህተት፣ በውሸት ላይ ውሸት፣ በአመጽ ላይ አመጽ መስራትና መደጋገም ሁነኛ መታወቂያው ለመሆኑ ማናችንም አንስተውም። ይህን መሰሉ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን”) መሰሪ ድርጊት በማጋለጥ ረገድም ጸሐፊው “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀው የሽብርና የሁከት ማእከል መካነ ድር “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑና ማህበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያንና አገልጋዮችን በተቀናጀ መልኩ ማተረማመስ እንዲሁም ማሳደድ  እየተያያዘው ሲመጣ የቀድሞ ስራዎቹ(ባለቤትነቱን የሚመሰክሩና የሚያረጋግጡ) ከስፍራው በመንቀል የእኔ አይደለም በማለት እስከ መካድ ደርሷል። በዚህም ሳይመለስ የሚያቀኝ የለም በሚል የሞኝ ፈሊጥም እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ያለውንና የሌለውን አቅም በመጠቀም ከወትሮ በበለጠ ሁኔታ ሰማያዊትና ቅድስት በሆነችው ቤ/ያን ላይ ሽብርንና ሁከትን በመዝራት ረገድ እየገፋበት እንደሚገኝ በመግለጽ ከጥቂት ቀናት በፊት የሚከተለው ጽሁፍ ለንባብ መብቃቱ ይታወሳል።

“ይህ የሚመለከቱት መረጃ “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀውን ድረ-ገጽ/ብሎግ ሲጀመር ማኅበሩ የራሱ እንደሆነ በይፋ በድህረ ገጹ የገለጸበት/ያስተዋወቀበት በእንግሊዝኛ የድረ-ገጹ የመጀመሪያ የጽሑፉ “ሊንክ” ነበር። በተለይ deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html- የሚለውን ጽፈው ለመጎልጎል የሞከሩ እንደሆነ “ጭራሽ ከስፍራው ተነቅለዋል” የሚል መልስ ነው የሚያገኙ ለምን? ማኅበሩ ስራዬ ብሎ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንን መዋጋትና ማፍረስ ብሎም ቅድስት ቤተ-ክርስቲያንና የአባቶችን ክብር በሚነካ መልኩ ከአንድ በኢትዮጵያዊ ባህልና ወግ ያደገ ፍጡር በማይጠበቅ ልቅነትና ዋልጌነትን በእጅጉ አይለው በሚታዩበት ሁኔታ ማዋረድና ማንቋሸሽ እየተያያዛው ሲመጣ ጽሑፉን ከስፍራው በመንቀል የእኔ አይደለም እስከ ማለት ደርሷል።ድያ  ይህን ቁልጭ ያለውን በማያሻማ አገላለጽና በግልጽ መረጃ/ሰነድ የተደገፈውን ሐቅ ሽምጥጥ አድርጎ ለመካድ የማቅ ሰዎች የሆነውና ያልሆነውን ያልተባለና ያልተጠየቁትም ለመቀባጠር እንቅልፍ አጥተው ሰንብተዋል። በዚህ አጋጣሚ“… ምላሽ” በማለት የቀረበውን የቅጥፈት ስራ ሳይውል ሳያድር በኢ-ሜይል አድራሻዬን የላክህልኝ ወዳጄ መ/ም ደመላው እጅግ አድርጌ ላመሰግንህ እወዳለሁ።

ውድ አንባቢ! “ልሳነ ሌዋታን “ደጀ ሰላም” የማን ናት!” በሚል ርዕስ የቀረበውን እውነት ለማዳፈን ደጀ ሰላምየማ/ቅዱሳን ናት? በሚልኢትዮፕያን ሪቪውላይ ለተስተናገደው ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ” በሚል በመካነ ድሩ በኩል “አይደለም! ሐሰት ነው የተሃድሶዎች ውንጀላ ነው” ሲል ሀፍረት ሳይሰማቸው ዳግም ለማደናገር ቃጥቷቸዋል። ታድያ ዲ/ን ሙሉጌታ ለቃላቸው እማኝ በዋናነት በማስረጃነት ያቀረቡትን “ሊንክ” (deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-) ተጭነው እውነቱ እንዲያረጋግጡ በተጠየቀው ጥያቄ መሰረት ነው ምላሹ የተሰጠው ወይስ ሃሳባቸውንና ሐተታቸውን “ደጀ ሰላም” “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ እንደ ተጨማሪ መረጃ በተጻፉ ማስረጃዎች ላይ?

        መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” መሆኑን የሚገልጽና የሚያሳይ ማህበረ ቅዱሳን “ደጀ ሰላም” መካነ ድር የእኔ ነው ሲል በመጻፍ ራሱ ያስተዋወቀበትን በጸሐፊው ለመረጃ የቀረበውን ሊንክ የት ገባ? ለምንስ መልስ ሳይሰጥበት ተዘለለ? መካነ ድሩ “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆኑ በማያሻማ መልኩ የሚያሳይ ተብሎ በብቸኛነት ማስረጃ የቀረበው እኮ(deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-)የሚለው ነው? ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ይሉት እንዲህ ያለውን ነው።

እንግዲህ ጎግልም “የተሃድሶ” ነው! ካልተባለ በስተቀር ከላይ ያለውን ሊንክ ቢሰጡት  የሚሰጥዎች ምላሽ የሚያረጋግጠው ሐቅ ይህ ነው። “ደጀ ሰላም” የምትባለውን ልሳነ ሌዋታን የግብረ እከዩ ድርጅት “የማህበረ ቅዱሳን” ለመሆንዋ የሚከተለውን “ሊንክ” ጎግል በሚባለው ገጽ ላይ አስፍረው ይጨቁኑትና እውነቱን ይለዩ። “(deje-selam.blogspot.com/…/Ethiopia-mahberekidusan-eotc-past.html-)


                     
ጎግል የዋዛ አይደለም! የተባለው/የቀረበው ማስረጃ ሐሰት ወይንም ደግሞ የፈጠራ ቢሆን ኖሮ ከፍ ሲል ከላይ ከነምስሉ “ይቅርታ! የፈለጉትን ገጽ በብሎጉ/በስፍራው ላይ የለም/አልተገኘም!” ባላለ ነበር። እንደውም ከዚህ በፊት ተጭኖ ያልነበረ እና ጭራሽ የሌለ ነገር የጠየቁት እንደሆነ ይሉኝታ በሌለው ሁኔታ እንደሚከተለው ነበር የሚመልስሎት:
Your search - - did not match any documents.
Suggestions:
·         Make sure all words are spelled correctly.
·         Try different keywords.
·         Try more general keywords.ተግባባን? እንግዲህ አሁን በአንድ ድምጽ “የሊንኩ” ጽሑፍ የት ገባ? በማለት ጥያቄአችን ለእውቀት አልባው ጽንፈኛ ድርጅት “ለማህበረ ቅዱሳን” እናቅርብ።

ጥብቅ ማሳሰቢያ

Ø ደጀ ሰላምየማ/ቅዱሳን ናት በሚልኢትዮጵያን ሪቪውላይ ለተስተናገደ ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ” የሚለውን ድረ ገጹ እንደማንኛውም የነፃ ሃሳብ ማንሸራሸሪያ አስተናገደ እንጅ የጽሑፉ ባለቤት አይደለም። መጠሪያ ስሙ በሰማችሁና ባያችሁት ቁጥር ጠበል እንደገባ ስይጣን የሚያስበረግጋችሁ፣ የሚያጮኸችሁና የሚያስደነግጣችሁ የቀድሞ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?” መጽሐፍ ጸሐፊ “ደጀ-ሰላም” የማን ናት?” ሲል ለጻፈው ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ ማለትን ትታችሁ የሊማሊሞ መንገድ ምን አስኬዳችሁ? ደግሞስ ሌሎች በርካታ ጽሑፉን ያስተናገዱ ድረ ገጾችን ትታችሁ ወደ ኢትዮፕያን ሪቪውየዘለላችሁት ምን ዓይነት መልዕክት ለማስተላለፍ ነው? 

Ø ተሐድሶዎቹ ይኼንን ራሳቸው ስድብ ማጠናከሪያነት ተጠቀሙበት” ላላችሁት የተጻፈው በአንድ ሰው! ጻሐፊውም ከልጅነት እስከ እውቀት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ያን ትምህርትና ስርዓተ ቤ/ያን በሚገባ ያደጉና የተፈተኑ እንዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታቸውና በመልካም ስነምግባራቸው የተፈተኑ ቀደም ሲል የስነ መለኮት ሊቅና ፈላስፋ ከሆኑትና ከብጹዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ እግር ስር ትምህርተ ሃይማኖትን የቀጸለና ያጠና በመቀጠልም በሁለቱ የነገረ መልኮት ተቋሞች ማለትም በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅና አባ ሰላማ ካሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ በሚገባ ትምህርቱን የተከታተለ “ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን? የሚለውን መጽሐፍ በመጻፉ ለዓመታት ከለፋበት ት/ቤት ታግዶ ለስደት ህይወት የተዳረገ ወጣት ጸሐፊና መምህረ ወንጌል በዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል የተጻፈ ነው። ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው ወደ ተሃድሶ ጎራ የተመደቡ? በነገራችን ላይ “ማህበረ ቅዱሳን” የሚስጨንቅ ግለሰብ ሁሉ “ተሃድሶ” ማለትም ሲያንስ ነው።በድጋሜ ልሳነ ሌዋታን “ደጀ ሰላም” የነፍሰ ገዳዩ ማህበር “የማህበረ ቅዱሳን” ናት!


በክፉው ላይ እንዳልተኛ አንቃኝ!

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

1 comment:

  1. እሰይ ... ! ምን አቃጠላችሁ? ማኅበረ ቅዱሳን ደጀሰላም የእርሱ ብትሆን የሚያስፈራው ነገር የለም ግን በጣም ትገርማላችሁ። እኛ እኮ ደጀ ሰላምን ከምሥረታ ጀምሮ ስንከታተል ቆይተናል። ያልተጻፈ ማንበባችሁ ምናልባትም ለማኅበሩ ያላችሁን ጥላቻ እንዳላችሁ ከማሳበቁም በላይ ልንገራችሁና መርሐክርስቶስ ማለት ዋነኛ የተሐድሶ አንቀሳቃሽ እንደነበሩ ሙሉጌታን ብቻ ሳይሆን እነ ግርማ በቀለን ያጣመሙ እና በምግባርም ደረጃ በ4 ኪሎ አስፓልት ላይ ለውዝ እየቃሙ የሚንከላወሱ ቅልጥ ያሉ መናፍቅ ናቸው እንጂ እናንተ እንደዘገባችሁት እንከን የማይወጣላቸው ሊቅ አልነበሩም። ማፈሪያ ሁላ!

    ReplyDelete