Monday, May 7, 2012

ሰበር ዜና:የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊ የነበሩት አባ ኅሩይ ከሥልጣናቸው ተነሱ

Click here to read in PDF
አቀርቅሮ ወጊውና የማቅ ቀኝ እጅ መሆናቸውን በይፋ ያረጋገጡት የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊ የነበሩት አባ ኅሩይ ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ በምትካቸውም መምህር ዕንቁባህሪ ተተክተዋል፡፡  እጅግ በሆነ መሰሪ አቀራረብ የሰንበት ማደራጃውን ሚስጢር ለማኅበረ ቅዱሳን አሳልፈው እየሰጡ ቤተክርስቲያንና ማደራጃውን ወደ ማቅ አቅጣጫ እየመሩ የነበሩት አባ ኅሩይ መነሳታቸው ለእውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች እጅግ አስደሳች ዜናና የጸሎታቸውምም ምላሽ ነው፡፡
ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ በድብቅ የማቅ ተላላኪ በመሆን የሰንበት ማደራጃውን አሰራር በሙሉ ለማቅ ለማስረከብ ተዘጋጅተው የነበሩት አባ ኅሩይ ከዚህ በፊት አብረውኝ የሚሰሩ ሰዎች ሁሉ በስራዬ ላይ እንቅፋት ስለሆኑ ይነሱልኝ ብለው ጠይቀው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ጥያቄያቸው ምላሽ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ በቦታው ላይ የሚተኩት ሰዎች በማቅ በኩል ተዘጋጅቶላቸው ነበር፡፡ 

እኝህ ሰው እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ዜግነት እስተቀበሉባት አሜሪካ ድረስ መፍቀሬ ንዋይነታቸው በእጅጉ የታወቀ ስለነበር በሰንበት ማደራጀው ላይ በተሙ ጊዜ፤ ሹመታቸው ብዙዎችን የቤተክርስቲያን ልጆች አሳዝኖ  ነበር፡፡ የሰውየውን የባህሪ ክፍተት አሜሪካ ባሉ ባልደረቦቻቸው የሰሙት የማቅ አመራር አባላት አባ ኅሩይ አዲስ አበባ በገቡ ጊዜ በቀላሉ በማግኘትና የንዋይ ፍቅራቸውን በማርካት ከጎናቸው እንዲቆሙ አድርገዋቸዋል፡፡ ከዛም ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በቅርቡ እንኳ ማቅን በሚመለከት የአሰራርን ግልጽነት ለማስረጽ የሚረዳ ደብዳቤ እንደይወጣ ማህተም ይዞ እስከመሰወር የደረሰ አሳፋሪ ድርጊት የፈጸሙ ሰው ናቸው፡፡ ከዛ ጊዜም በኋላ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ ሲሆን ከሰዎች ጋር ያላቸውም ግንኙነት በስልክ ብቻ የተወሰነ ነበር፡፡ የእለት ዕለት የስራ ዕንቅስቃሴ የሚያስፈልገው የማደራጃ መምሪያው የስራ ገበታ ክፍት ስለሆነና የሰውየውም አካሄድ አደገኛ በመሆኑ መነሳታቸው አስፈላጊ ሆኗል፡፡
አባ ኅሩይ ቦታ የተሾሙት መምህር ዕንቁባህሪ ሲሆኑ እሳቸውም ከዚህ ቀደም በመምሪያው ኃላፊነት የሰሩና እስካሁንም ድረስ ደግሞ በምክትል ኃላፊነት የቆዩ ሰው ናቸው፡፡ ለመምህር እንቁባህሪም የሹመቱ ደብዳቤ የደረሳቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡


9 comments:

  1. Elelelelele des sil

    ReplyDelete
    Replies
    1. Chche yemin elilita new. Ere mafer yigebahal.

      Delete
  2. Aba Hiru Enkan Tenesu Mejemeryam Mekemets Yemigebachew Sew Alneberu Mahibere Kidusan Aba Hiryin Bemigeba yawkachewal Ke Pawlos Menfesaw Kolej- Kenaziret wilntcit Giyorgis-America Bosten Mikaeil-Kansas Kidane Mihiret -Kaliforniya Gebreil Bemin endetebareru Mahibere Kidusan Yawkal wedefit enzerezirewalen Letalku memirya lihonu ayichilum Gize Anurenlet new Delala Bihonu Yawatsachewal Addis Abeba Kemetsu jemiro Keman Gar endeminoru enawkalen gin legizew yikoyen Ahun Aba Hiruy Yet Temedebu ?Abune Markos Behager sew Hisab Genzeb Kekefelk Papas asdergihalehu Maletachewn tesfa koretu malet new yasazinal

    ReplyDelete
  3. this is good news for our church. this person is not a loyal and a trusted one i know him very well in america.

    ReplyDelete
  4. Kelkelo shilecha shilecha kelkelo

    ReplyDelete
  5. ሰበር ዜና: http://www.bbc.co.uk/news/world-south-asia-17981323

    ReplyDelete
  6. Dear Sir, don’t know this person and I don’t know what is all about his position. But I know mk here in America I think and believe that they are not religious person at all. The all are purely motivated and engaged in politics. If he is with them it is good to our church to replace him in someone who has better vision than mk have.

    ReplyDelete
  7. እርሱ እግዚአብሔር ነው የወደደውን ያድርግ ይላል መጽሐፍ ቅዱስእርሱ እግዚአብሔር ነው የወደደውን ያድርግ ይላል መጽሐፍ ቅዱስ

    ReplyDelete
  8. Pls check the link:

    http://eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=976:2012-05-04-09-25-45&catid=1:-&Itemid=18

    This is Why aba Hiruy is fired.

    ReplyDelete