Monday, May 7, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ከገቡበት አጣብቂኝ ለመውጣት ወደፓትርያርኩ ቢሮ እግር አብዝተዋል

  •     የማቅ ተከፋዩ አባ ኅሩይ ማኅተም ይዘው ተሰውረው ሰነበቱ
የማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ አመራሮች ሰሞኑን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጽ/ቤት ወጣ ገባ ማለት ይዘዋል። ምንጮቻችን እንደጠቆሙት የማቅ አመራሮች የሚመላለሱበባቸው ሁለት ዋነኛ ጉዳዮች አሉዋቸው። የመጀመሪያው ከአባ ሠረቀ ብርሃን ጋር በዋናነት ያጣላቸውና “ሂሳባችሁን አስመርምሩ። ያላችሁን የገንዘብ ዝርዝር አሳውቁ። ገንዘብ አጠቃቀማችሁ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው ይሁን።” የሚለው አጀንዳ እንደገና ስለተቀሰቀሰ እሱ “አይሁን አይደረግብን” ለማለትና የቅዱስነታቸውን ልብ ለማራራት ነው። ሁለተኛውና ዋነኛው ደግሞ ቅዱስነታቸው የማህበሩ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጣቸው የግብር ስም ከሰለፊያ ዝቅ ያለ እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ፓትርያርኩ መንገድ እንዲያዘጋጁላቸው ለመጠየቅ ነው።
ሁልጊዜም “ለእውነትና በእውነት” እሰራለሁ የሚል ድርጅት ሊያስደነግጠው የማይገባ “ሂሳባችሁን አሳውቁ፤ አጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሴያችሁን ኦዲት አስደርጉ” የሚለው ጥያቄ የማህበሩን አመራሮች ለምን እንደሚያስደነግጣቸውና ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚደፍረውን ሰው ሁሉ ደግሞ “ተሐድሶ” እያሉ ለመጥራት እንደሚያስቸኩላቸው ብዙዎችን ግራ እያጋባ ነው። እውነት በቀኝም አዩዋት በግራ፣ በፊት ለፊትም አዩዋት በጀርባ፣ አዙረውም አዩዋት ገልብጠው ያው እውነት ናት። ስለዚህ “እውነትን ይዣለሁ” የሚል ሁሉ ምንም ነገር አያስፈራውም። ሂሳብህን ኦዲት ላድርግ የሚል የበላይ አካል ሲመጣማ “የአሠራሬን ትክክለኛነትና እውነተኝነት ለማረጋገጥ የምችልበት መንገድ አገኘሁ ብሎ” በደስታ ነው የሚቀበለው።
ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ጥያቄ አጥብቆ ለምን ይፈራዋል? በግልጥ እንደታወቀው ማኅበሩ እንደ ጣልያን ማፍያ ዓላማውን ለማሳካት ሁለት ዓይነት መንገድ ይጠቀማል። የመጀመሪያው ሕጋዊ መንገድ ሲሆን በዚህ መንገድ ብዙም አይራመድም። አሠራሩ በአብዛኛው ሕጋዊነት ስለሚጎድለውና በብርሃን ከመመላለስ ይልቅ በጨለማ መሄድን ስለሚመርጥ በፍጥነት ከዚህ መንገድ ወጥቶ ወደ ዋናው መጓዣው ወደ ሕገ ወጥ መንገድ ይገባል። ማንኛውንም ነገር እንደ ክርስቲያን “የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ይሳካል” ብሎ ሳይሆን “እኔ ከፈለኩት መሳካት አለበት” በሚል እምነት የሚንቀሳቀስ ድርጅት ስለሆነ ሀሳቡን ለማሳካት ሕጋዊው መንገድ አላዋጣ ሲለው ሕገ ወጡን መንገድ አጥብቆ ይከተላል። ይህም ጉቦ በመስጠት፣ ቁልፍ ቦታ ላይ አሉ የተባሉ ሰዎችን ከቦታቸው እስኪነሱ ድረስ ቋሚ ተከፋይ በማድረግና ዓላማው በሁለቱ መንገድ እንደማይሳካ ሲገባው ደግሞ ዱርዬ በገንዘብ ገዝቶ በማስፈራራት ሀሳቡን ለማስፈጸም የሚፈልግ ማፍያ ድርጅት ነው። ይህ አካሄድ ታዲያ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ስለሆነ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት ከሰፈነ ያሰበውን ማሳካት አይችልም። ስለዚህ ይህ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚቀርብለትን የተቀደሰ ሐሳብ እያመከነ ጥያቄውን የሚያነሳበትን ሰው መርዞ በመያዝ ከቦታው እንዲነሣ እስከማድረግ የደረሰ እርምጃ በአመፅ መንገድ ከመውሰድ ወደኋላ አይልም። እንቅልፍም አይወስደውም። በአባ ሠረቀ ላይ የተከፈተባቸው የስም ማጥፋት ሥራ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው።
ይህ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሰራር ተፈጻሚ እንዳይሆን የሚፈለግበት ሌላም ምክንያት አለ። የማህበሩ አመራር (ስውሩም ግልጹም) አባላትና አንዳንድ ለተንኮል ሥራ የሚፋጠኑ “ትጉህ” አገልጋዮቹ ለእንቅስቃሴያቸው መሳካት የሚያስፈልገውን ገንዘብና ለአንዳንዶቹ ከመሰረታዊ ፍልጎት አልፎ ኑሮ መደጎሚያ እንዲሆን በህገ ወጥ መንገድ ከማህበሩ የሚወጣውን ገንዘብ ግልጽነት ያለው አሰራር ስለሚያስቀርባቸው የሚያስፈልገውን ሁሉ ዋጋ መክፈል የህልውና ጥያቄ ስለሚሆንባቸውም ነው።
ታዲያ ሰሞኑን በአቡነ ገሪማ ፊርማ የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃው ይህን ጉዳይ መልሶ እንዲያንቀሳቅስ ሲጠየቅ፤ አሜሪካ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በፍቅረ ንዋይ የሚታሙትና በቅርቡ ከስጦታና ከእጅ መንሻ ገንዘብ ተላቀው የማኅበሩ ቋሚ ተከፋይ ወደ መሆን የተሸጋገሩት አባ ኅሩይ ጉዳዩን ለማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ አመራሮች ሹክ ይላሉ። የማህበሩ አመራር አባላትም ይህ “እንቅልፍ የሚነሳ” ጉዳይ ካሉበት ቦታ አሰባስቦአቸው ወደ ቅዱስነታቸው በመግባት “ይህ አይሁንብን አይደረግብን” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። ቅዱስነታቸውም የሁሉም አባት እንደመሆናቸው በሚያጽናና ቃል ጉዳዩን መልሰው እንደሚያዩት ሲነግሩዋቸው ደስታው አላስቀምጥ ብሎአቸው ምክንያት ሲፈልጉ፣ ከተቀበሩ ሁለት ሳምንታት ያለፋቸውን የቅዱስነታቸውን ወንድም ሞት እንደጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው የእዝን እራት እናበላንን ብለው እራት አብልተው ነገሩን አብስለነዋል ብለው ሁለተኛ ጉዳያቸውን ደግሞ እንዴት እንደሚያሳኩት በማሰላሰል ይሄዳሉ።
ቅዱስነታቸውም ነገሩን ሲያስቡት ኦዲት የመደረጉና ሂሳብ የማሳወቁ ክፋት ስላልታያቸው ደብዳቤው እንዲወጣ ያዛሉ። ይህን ትዕዛዝ የሰሙት አባ ኅሩይ ከመዝገብ ቤት ማህተም ተቀብለው (በትክክለኛው አገላላጽ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው በመስረቅ) ከግቢው ወጥተው ይጠፋሉ። ይህ እንደታወቀም ማህተሙ ሌላ ወንጀል እንዳይፈጸምበት በሚል ለፖሊስ ተነግሮ ፍለጋ ተጀመረ። ፖሊስ እንደሚፈልጋቸው የተረዱት አባ ኅሩይም አመሻሽ ላይ የጠፋሁት አቡነ ገሪማ ስላዘዙኝ አዝኜ ነው በማለት ማኅተሙን መለሱ።
ለመሆኑ ግን የብፁዕ አቡነ ገሪማ ሥልጣን አባ ኅሩይን ለማዘዝ ያንሳልን? ሌሎች ስልጣንና ኃላፊነታቸው ሣይጨመሩ የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ መሆን አንድ የሰንበት ማደራጃ ኃላፊ አልታዘዝም የሚለው ስልጣን ነው ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ ለአባ ኅሩይና ለመካሪዎቻቸው እንተወዋለን?
ሁለተኛውና በእጅጉ ይፈልጉት የነበረው ጠቅላይ ሚኒስቲሩን የማግኘት ጉዳይ ለጊዜው ስለአልተሳካ “ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ ቢሆንም በበዓለ ሃምሳ (ጰራቅሊጦስ) ይዘነው የነበረው ጾም ጸሎት አልተሳካም።” በማለት ቁዘማ ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
አንዳንድ ወገኖች ከመንግሥት የተሻለ ሥራ እየሰራን ስለሆነ ነው መንግስት ጠምዶ የያዘን (አንድ አድርገን ሚያዚያ 17 ፤ 2004 ዓ.ም፤ መንግስት ለምን ‹‹ማህበረ ቅዱሳንን›› ጥምድ አድርጎ ያዘው?) በማለት በብሎጎቻቸው እየጻፉ ስለሆነ ለምን አሁን የገጠማቸውን ችግር ለመፍታት እራሳቸውን ባዩበት መነጽር ልክ አይሞክሩም እያሉ ይገኛሉ። ይኸውም “ካንተ የተሻለ ስራ እየሰራን ስለሆነ ይህን አለአግባብ የሠጠኸንን ስም በአስቸኳይ እንድታስተካክል እንደራደር አለበለዚህ ለአንድ ዓመት እጃችንን አጣጥፈን የምንመለከትህ ይሆናል ቢሉ መንግሥት ፈርቶና ደንግጦ በአስቸኳይ እሺ ይላል የምን በቅዱስነታቸው በኩል እየሄዱ መንገድ ማርዘም ነው” ሲሉ የማህበሩን አመራሮች  በስላቅ እየተቿቸው ይገኛሉ።

13 comments:

  1. kmnegwesete Ytsale sertnal. alu yedenkal tinese koyetew dekmo kpawlos yetsale meshas sefenal wengelun tewote yelunal

    ReplyDelete
  2. Mahibere Kidusan keEgziabher gar newna minim neger ayasferawm. atidikemu. Nufakeachihun silemiyagalitibachihu new hulachihum atimidachihu yeyazachihut. degimo alamachihu mechem ayisakam. enanite yediyablos lijoch nachihuna.

    ReplyDelete
  3. ዉሾች ይጮሃሉ ግመሎች መንገዳቸዉን ይጉአዛሉ!!! አንተ ለፍልፍ ሥራ ስለሌለህ ነዉ! ሥራ ያለዉ ሥራዉን ይሠራል!

    ReplyDelete
    Replies
    1. አይ ሞኞ ውሻ እኮ የሚጮኸው ስራ የሰራ መስሎት ነው፡፡የልከስክስ ውሻ ጥርቅምማ ማቅ ነው፡፡ መሽቶ እስኪነጋ የምትጮሁባቸውን ብሎጎችማ አትረሱዋቸው፡፡

      Delete
  4. weregna mechey yehon asamagn mereja yemtaqerbut

    ReplyDelete
  5. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  6. to add more you are typically untie EOTC rule which traded in its name and eat its injera and bread by doing wrong things as your brain and heart more over the Holy God knows very well.

    ReplyDelete
  7. Enante tekulawoch esti yibkachu rasachun mermeru.
    sew eyetazebachu enji eyesemachu aydelem.
    LONG LIVE M/K!

    ReplyDelete
  8. MK'N SEYETANINA ENANTE NEGER SERI SELHONACHU KEMENGISTACHEN ENA KE KIDIUS ABATCHEN LEMATALAT YEMITTIRU ZEWTIR LERASCHHU ENA LEHODACHU YEDERACHU BEMEHON MELKAM YEHON HULU YEMAYWATILACHU NACHU. DUROS KEDAMILOS ENA KETKTAYOCH MIN YETABKAL ENDIHUN KEYHUDA.

    ReplyDelete
  9. ሕገ ወጥ ሕግ አስከባሪዎች
    ሚያዝያ 24/2004 ዓ.ም.

    ከሰሞኑ ለሰሚ የሚያሳፍር፤ አንድ ጉዳይ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተፈጽሟል፡፡ ጉዳዩን በአንክሮ ለተመለከተው በእጅጉ ያሳስባል፡፡ የሰላ አንደበት ይዘው ያልኾኑትን ነን በማለት የሌላቸውን ሥልጣንና ዕውቀት እንዳላቸው በማስመሰል ደግ አባቶችን የሚያታልሉ፤ ከቤተ ክርስቲያን ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን የሚያስቀድሙ ወረበሎች አሉ፡፡ እነዚህ ጆቢራዎች በደጋግ አባቶቻችን አእጋር ሥር እየተርመሰመሱ፤ ዕውቀት መንፈሳዊ ሳያቋርጥ የሚያፈሰውን የእናት ቤተ ክርስቲያን ጡት እየጠቡ አድገውና ጐልምሰው ሊያገለግሉ በተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከል እየተሹለከለኩ ተንኮላቸውን ያለድካም ለመፈጸም ሲኳትኑ ይታያሉ፡፡ ከሰሞኑ የሰማነው ግብዝነትን ከአላዋቂነት ጋር አስተባብሮ የያዘ ከንቱ ተግባር፤ እነዚሀን መሰሪዎች አበው በበሰለ አመራራቸው ለይተው በመጠረቅ ከጉያቸው የሚያባርሩበት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም በዕውቀት ሚዛን መዝነው ማኔ ቴቄል ፋሬስ ብለው ለይተው የሚጥሉበት ሰዓት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መድረሱን የሚያመለክት ነው፡፡ ጊዜ ለሚሰጠው እንጂ ለማይሰጠው ጉዳይ መዘግየት ጉዳቱ ለራስ ነውና፡፡

    ጉዳዩ በማኅበረ ቅዱሳን እንቅስቃሴ ጥቅማቸው የተነካ ወይም የሚነካ በመሰላቸው ሰዎች ተቀነባብሮ የነበረ ሴራ ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ማኅበሩ በአባቶች መመሪያና ምክር እንዲሁም ጸሎት እየታገዘ የነበረ አገልግሎቱን በተጠናከረ መንገድ ቀጥሎ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ከሕግና ትእዛዝ ፍጹም እንደወጣ አድርገው በማቅረብ በአገልግሎቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያመጣ ደብዳቤ ተፈርሞ እንዲበተን ለማድረግ ያደረጉት ከንቱ ሙከራ ነው፡፡ ግለሰቦቹ ይህንን እኩይ፣ በእግዚአብሔርና በሰው ሕግጋት የሚያስጠይቅ ተግባር ለማሳካት ያላደረጉት ጥረት ለአባቶችም ያልቀባጠሩት ማሳመኛ የሚመስል ነገር የለም፡፡ የእኩይ ተግባራቸው መነሻ ያደረጉት ለማኅበሩ እንዲደርስ ያሉትን ማሩን የሚያመር ወተቱን የሚያጠቁር የክስ ደብዳቤ ማርቀቅ ነው፡፡ ለደብዳቤው ርዕሰ ጉዳይነት የመረጡት ዐረፍተ ነገር «ለሕግ የበላይነት ሥልጣን ታዛዥ ሆኖ አለመገኘትን በሚመለከት ይሆናል» የሚል የአማርኛ ሰዋስው ሀሁን ያላለፈ በዚህም የጆቢራዎቹን ማንነት የገለጠ ያልተሟላ ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይነት የታሠረው ከንቱ ደብዳቤ በወግ ባልተጻፈ፤ ርዝመታቸው በትልልቅ አናቅጽ ማሠሪያ የተገታ ከሳሽ ዐረፍተ ነገሮች ታጅሏል፡፡ የደብዳቤው ፍሬ ሐሳብ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ፊርማ በጸደቀ ደንብ የተቋቋመው፤ በደንቡም ብቻ ሳይኾን በየዕለቱ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዐን አበው ተግሣጽ፣ ምክርና መመሪያ እየታገዘ አገልግሎቱን እየፈጸመ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያኗ ማእከላዊ አስተዳደር ቁጥጥር ውጪ ነው፤ በዚህም የሚሰጠውን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ አልኾነም የሚል ነው፡፡ ደብዳቤው ይኽንኑ እንቢተኝነት ለመቀልበስ በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደርና በማኅበሩ መካከል «በዕለት፣ በሳምንት፣ በወርና በዓመት ያልተገደበ የመጻጻፍ ተግባር» ሲካሔድ እንደቆየ ያትታል፡፡ ደብዳቤ መጻጻፉ አሁንም «ከመቼውም ጊዜ ጐልቶ የታየበት ወቅት» እንደኾነም ያስረግጣል፡፡ ይህም የማኅበሩን «የበላይ ተጠሪ የሆነውን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያን» ለወቀሳ የዳረገ መኾኑን ይጠቅስና፤ ማኅበሩ በዚህ ተግባሩ የመምሪያውንም ኾነ የቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ አስተዳደር ህልውና እየተፈታተነ እንደኾነ በሬ ወለደ አሉባልታውን ይነዛል

    ReplyDelete
  10. Woregnache!!!!!!

    ReplyDelete
  11. weye gude min yesanela yehe yeagannete menfese yadrebete mahebere eko betebeten

    ReplyDelete
  12. yehe aremene mahebere bezu yasebal gin keegziabehere gar ayesakletem

    ReplyDelete