Monday, May 14, 2012

በትናንትናው ዕለት በአቡነ አብርሃም ቤት ልዩ ስብሰባ ተካሄደ

Click here to rear in PDF
  • የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ እና የአቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ መነሳት አጀንዳዎች ነበሩ፡፡
በትናንትናው ዕለት አቡነ አብርሃም ቤት እስከ ምሽቱ የዘለቀ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን ስብሰባውም ሁለት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል፡፡ የመጀመሪያው በዛሬው ዕለት በቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያ አጀንዳ የሆነውና አብዛኛዎቹን ጳጳሳት ያለልዩነት በአንድ ጎራ ላይ ያቆመው የዜና ቤተክርስቲን ጋዜጣ ዘገባ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሲኖዶሱ በአጀንዳነት አለመያዙ አቡነ አብርሃምንና ማኅበረ ቅዱሳንን እጅግ በጣም ያበሳጨው የአሜሪካ አኅጉረ ስብከት ጉዳይ እንደገና ወደ አጀንዳ የሚገባባት መንገድን ማመቻቸት ነው፡፡ 

የቅዳሜው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ባልጠበቁት መንገድ የሄደባቸው ማኅበረ ቅዱሳንና እና እንደ ሮብዓም “በልጅ” ምክር ተሳስተው “እርስዎ ካልፈለጉ ሌላ ሰብሰቢ መርጠን መቀጠል እንችላለን” ብለው ሲናገሩ በአቡነ ሙሴ እንደ ልጅ “ተው!! እንዲህ አይባልም” ተብለው የተገሰጹት አቡነ አብርሃም ከዚህ አጋጣሚ ሊገኝ የሚችለው ትርፍ ምንድር ነው? ብለው አስበውና መክረው ይሄን አጀንዳ በማብሰልና ስር በመስደድ ሰበብ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የዜና ቤተክርስቲያንን ጋዜጣ አዘጋጆች በዛሬው ዕለት ሲኖዶስ ስብሳባ ላይ ሲቀርቡ ምን ምን ጥያቄ እንጠይቃቸው? በሚለው ዙሪያ ሰፊ ጊዜ ወስደው የመከሩ ሲሆን ለቀጣዩ መወያያ በር ለማመቻቸትም የማቅ ሰዎች እዚህ አሳብ ላይ ደጋግመው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ሊቃነ ጳጳሳቱ “በነፃው ፕሬስ ጋዜጦች እንሰደብ እንጂ እንዴት በራሳችን ጋዜጣ እንሰደባለን?” በማለት እጅግ በጣም የተቆጡ ሲሆን አብዛኛዎቹ ዜናውንን ካነበቡበትና ከሰሙበት ከቅዳሜ ዕለት ስሜት ምንም ያልበረዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህ በአይነቱ ልዩ በሆነው አጀንዳ የጋዜጣው አዘጋጅና ምክትል አዘጋጅ ምን መልስ ይሰጡ ይሆን? ጳጳሳቱስ ይህ ስሜታቸው በርዶ ወይስ በቁጣና በብስጭት ያናግሩዋቸው ይሆን የሚለው ትኩረት የሚስብ ሆኗል፡፡ 

በዚህ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ባመቻቹት የአቡነ አብርሃም ቤት ስብሰባ ለምን የእናንተ አጀንዳ ብቻ የእኛም አጀንዳ ይታይልን እንጂ በማለት  “ርስት ጉልቴ” ብለው አስበዋትና ለዘላለም ሊያስተዳድሩዋት የፈለጉት የአሜሪካው አኅጉረ ስብከት አጀንዳ አለመሆን ያንገበገባቸው አቡነ አብርሃም እና “አኁጉረ ስብከቱን የተደላደለ ዙፋኔና የገቢ ምንጬ አደርገዋለሁ” ብሎ አስቦ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካው ጉዳይ አጀንዳ ስለሚሆንበትና አቡነ ፋኑኤል ስለሚነሱበት መንገድ መምከራቸው ተነግሮዋል፡፡

የሮብዓምን መንገድ የመረጡትና ምክር ከሚያሳሳስቱ “ልጆች” ጋር ጊዜያቸውን የሚያጠፉት አቡነ አብርሃም የሚናገሩት ንግግር ሁሉ እውቀትና ማስተዋል የጎደለው እና ለእሳቱ የጭድ አቀባይነት ሚና ያለው ነው፡፡ የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ዘገባ ከሚያካትታቸው ጳጳሳት መከከል እኚህ አቡነ አብርሃም የሚገኙበት ሲሆን ስብሰባው የተካሄደበት የግል መኖሪያ ቤታቸው የፈሰሰበት ገንዘብ እንኳን የጳጳስንን የኢንቨስተርንም አቅም የሚፈትን ከመሆኑ አንጻር አንዱ ተጠቃሽ ማስረጃም ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

እስከ ዛሬ ድረስ የቅዳሜን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለመዘገብ ያልደፈሩት የማቅ ብሎጎች እና አመራር አባለት በአቡነ አብርሃም በኩል አስነግረውት የነበረው ሰብሳቢ የመቀየር ምኞታቸው በአቡነ ሙሴ ተግሳጽ በቶሎ ስለተኮላሸ እና ስለአልተሳካ እንዲሁም የዜና ቤተክርስቲን ጋዜጣ ሰበር አጀንዳ ሆኖ መገኘት ከጣለባቸው ድንጋጤና ብስጭት በቅጡ እንዳላገገሙ የታወቀ ሲሆን የጋዜጣው አጀንዳ መሆን ሊፈጥርላቸው የሚችል ሌላ ዕድልም ካለ ለመጠቀም የትናንቱን ስብሰባ ማዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡  

4 comments:

  1. kkkk sbsebaw lay neberachihu ende? Endiawum ajendawn enante sathonu atkerum yazegajachihut aydel? Kkkk...

    ReplyDelete
  2. wey gude min yesalal enante? negeru kepoletikam base eko!

    ReplyDelete
  3. ሰለ ሮብዓም ለማታውቁ


    መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 12፤
    1
    እስራኤል ሁሉ ያነግሡት ዘንድ ወደ ሴኬም መጥተው ነበርና ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ።

    2
    እንዲህም ሆነ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን በሰማ ጊዜ፥ እርሱም ከንጉሡ ከሰሎሞን ፊት ኰብልሎ በግብጽ ተቀምጦ ነበርና፥ በግብጽም ሳለ ልከው ጠርተውት ነበርና

    3
    ኢዮርብዓምና የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ መጥተው ለሮብዓም።

    4
    አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቃልልልን እኛም እንገዛልሃለን ብለው ተናገሩት።

    5
    እርሱም፦ ሂዱ፥ በሦስተኛውም ቀን ወደ እኔ ተመለሱ አላቸው። ሕዝቡም ሄዱ።

    6
    ንጉሡም ሮብዓም። ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ።

    7
    እርሱም፦ ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸውም፥ መልሰህም በገርነት ብትናገራቸው፥ በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል ብለው ተናገሩት።

    8
    እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ።

    9
    እርሱም፦ አባትህ የጫኑብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? አላቸው።

    10
    ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች። አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ። ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች።

    11
    አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችኋል፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችኋል፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ በላቸው ብለው ተናገሩት።

    12
    ንጉሡም። በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ ብሎ እንደ ተናገረ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ።

    13
    ንጉሡም ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ለሕዝቡ ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው።

    14
    እንደ ብላቴኖችም ምክር። አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ ብሎ ተናገራቸው።

    15
    እግዚአብሔርም በሴሎናዊው በአኪያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ነገር እንዲያጸና ከእግዚአብሔር ዘንድ ተመድቦ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።

    16
    እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ። በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ ዳዊት ሆይ፥ አሁን ቤትህን ተመልከት ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደ ድንኳኖቻቸው ሄዱ።

    ReplyDelete
  4. teru new ega Yehulum information yasfelegenal ewnetun rasachen enmezenalen. eskahun yande wegen becha information eyeseman tetalen neber. ena merega kamageget ansare bertu belenal

    ReplyDelete