Monday, May 21, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ለተጻፈበት ደብዳቤ የሰጠው ምላሽ ሲገመገም

Click here to read in PDF
ሌባ እናት ልጇን አታምነውም ይባላል፡፡ ይህቺ እናት ልጇን ለማመን የተቸገረችው ልጁ የእጅ አመል ኖሮበት (እየሰረቀ) ያስቸገረ ሆኖ ሳይሆን እርሷ ያለባት ችግር ሁሉም ሰው እንዳለበት ሆኖ ሲለሚሰማት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንም እንዲሁ እርሱ ሕገ ወጥነት በሙላት በውስጡ ስላለ ሌላው የሚያደርገው ነገር በሙሉ ሕጋዊ ያልሆነ መስሎ ይታየዋል፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ምክንያት የሆነው ግንቦት 7/ 2004 . ማኅበሩ በድረ ገጹ ያለቀቀው መልእክት ነው፡፡ ይህ ጽሑፍ ገና ከርዕሱ በሕገ ወጦች በጨለማ የተዘጋጀው ደብዳቤ ተበተነ የሚለው ጽሁፍ በውስጡ የያዘውን ሐሳብ አለፍ አለፍ ብለን ስንመረምረው ሌባዋን እናትና አመኔታን ያጣውን ልጅ እንድናስታውስ ያደርገናል፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ማእከላዊ አስተዳደር ተገዥ ካለመሆን አልፎ የተቋሙን ሕልውና ወደ መፈታተን እንደ ደረሰ በማተት የሚከስ ደብዳቤ ለሕግ ተገዢ ባልሆኑ ግለሰቦች በጨለማ ተረቅቆ በመምሪያው ሓላፊ እንዲፈረም ተደርጎ ሊወጣ እንደ ነበር፤ ነገር ግን በመምሪያው ሓላፊው በቆሞስ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ መታገዱን ገልጸን ነበር የሚለውን መግቢያው ያደረገው የማኅበሩ መልእክት ያለስሜ ስም ተሰጠኝ በሚል ብሶት ሮሮውን ለማስማት ጥረት እያደረገ ያለ አስመስሎታል፡፡

መግቢያው ሊያደርጉት እንደሞከሩት በማኅበሩ ላይ የተጻፈው ደብዳቤ ‹‹የሚከስ›› ደብዳቤውን ያዘጋጁት ጸሐፊዎች ደግሞ ለሕግ ተገዢ ያልሆኑ ሆነው የተጻፈበት ወቅትም ብርሃን ያልነበረበትን ለውንብድና የተመረጠ ሰዓት ነው ለማለት በማሰብ ጨለማ መሆኑን አስፍረዋል፡፡
በማኅበሩ የተባሉት ነገሮች በሙሉ በራሱ በማኅበሩ ለዘመናት ሲተገበሩ የነበሩ በመሆናቸው ማለትም የክስ ወረቀቶችን ይዞ በመሮጥ እውቅናን ያተረፈ፣ ለሕግ ተገዢ ባለመሆኑ በመንግስት ባልስልጣናትም በኩል ተደጋጋሚ ተግሳጽ የቀረበበት፣ በብርሃን ሊሰራቸው የማይችላቸውን ክፋቶች በጨለማ በመስራት ‹‹የተመሰገነ›› ስለሆነ ‹‹የእምዬን እከክ ለአብዬ ልክክ›› እንደሚባለው የራሱን ወደሰው እየለጠፈ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
በመቀጠል የሰፈረው ግልጽ ባልሆነ ሁኔታፍጹም ሕገ ወጥ ድርጊት በሕጋዊዋና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መፈጸም የለበትም፤ ይቁምያሉትን የመመሪያ ሓላፊ አስተዳደሩ ከቦታቸው አንሥቷል የሚለው ነው፡፡ ለመሆኑ በወቅቱ የመምሪያ ሐላፊ የነበሩት አባ ኅሩይ ሕገ ወጥን ሲቃወሙ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ነው ከኃላፊነታቸው የተነሱት? ኧረ ለመሆኑ እናንተ ህገወጥነትን የምትከላከሉት ከህግ ውጪ በሆነ አካሄድ መሆኑ የሚያበቃው መቼ ይሆን? የህገወጥ ድርጊት ተቃዋሚ ናቸው ያላችኋቸው አባ ኅሩይ ለሕጋዊ ስራ ማስኬጃ ተብሎ የተሰጣቸውን ማኅተም እንደግል ንብረታቸው ይዘው ለቀናት መሰወር ሕጋዊነቱ የቱ ጋር ይሆን? እናንተ ‹‹ሕጋዊ›› የምትሉትን መንገድ ለመሄድ በሕጋዊነት እንዳታደርጉት የከለከላችሁ ማን ይሆን? ይህስ ወንጀለኛነታችሁ እስከመቼ አብሯችሁ ይዘልቅ ይሆን?
አባ ኅሩይን በተመለከተ በመቀጠል የሰፈረው የመምሪያ ሓላፊው ቆሞስ አባ ኅሩይ ባላጠፉት ጥፋት ተከሰው ከቦታው መነሣታቸውን በመቃወም ማኅበሩ ጽፎት ስለነበረው ደብዳቤ ነው፡፡ በማቅ መስፈርት መሰረት ጥፋት የሚበላው ነገር ምን ይሆን? አባ ሕሩይ የፈጸሙት እኮ ከጥፋትም አልፎ ወንጀል ነው፡፡ ለተወከሉበት ስልጣን ሳይሆን በገንዘብ ለገዛችው ማኅበር ለማገልገል መነሳታቸውስ ቢሆን ከእግዚአብሔር መንግስት ባያጎላቸውም ከምድራዊ ስልጣን ቢያንሸራትታቸው ምን ይደንቅ ይሆን? ብዙ ጊዜ እንደሚባለው ጥፋት ያልሆነው ነገር በማቅ መነጽር መመልከት ብቻ እንደሆነ በሌላ አማርኛ እየነገራችሁን ይሆን እንዴ?
አሁንም ከአባ ኅሩይ ጋር በተያያዘ የማኅበሩን አመራር አካላት እየሰበሰቡ መመሪያ ሲሰጡ፣ ማኅበሩም መመሪያዎችን እየተቀበለ ወደ ተግባር ሲለውጥ ቆይቷል የሚል ቃል ሰፍሮ አንብበናል፡፡ የማኅበሩ አመራር አካላትና (ስውሩ አመራር ይሁን ፊት ለፊት ያለው ግልጽ ባይሆንም) አባ ኅሩይ ተሰባስበሰው በጋራ የጸደቀው ወደተግባር ይቀየር ነበር በሚለው ሐሳብ ላይ ተቃውሞ የለንም፡፡ ነገር ግን እርሳቸው ሰብስበው መመሪያ እየሰጡ ማኅበሩ እየተቀበለ የሚለው ቦታ እንዲቀያየር እንጠይቃለን፡፡
አባ ኅሩይ ናቸው መመሪያ ሰጪ ወይስ ማኅበሩ የሚለውን ሊያሳየን የሚችለው አንድ በግልጽ የተከናወነ ድርጊት ብቻ ማንሳቱ ምናልባት ምን ለማለት እንደፈለግን ግልጽ ያደርግልን ይሆናል፡፡ አምነውበት ተቀብለው ከፈረሙበት በኋላ ሁለት ቀናትን አሳልፈው በመምጣት ደብዳቤውን ስላላመንኩበት አይወጣም በማለት ከመዝገብ ቤት ክብ ማህተም ነጥቀው ተሰውረው ነበር። በወቅቱ ከማህበረ ቅዱሳን ጸሀፊ ከዲ/ ሙሉጌታ ሀይለ ማርያም ባገኙት ምክር መልካም ነገር መስሏቸው አደረጉ። የማደራጃ መምሪያው ሠራተኞች ግን በወቅቱ እጅግ ተገርመው ጉዳዩን ይከታተሉ ነበር። ማህተሙ በተነጠቀበት ጊዜ / ሙሉጌታ ሀይለ ማርያም በማደራጃ መምሪያው መኪና ከአባ ህሩይ ጋር ቢሮ ገብቶ ሲያበረታታ ነበር። አባ ኅሩይ በዚህ ጊዜ ነው የማህበሩ ቀኝ እጅ መሆናቸው በጥርጥር ውስጥ የገባው።  ይህ ጽሑፍ የተገኘው ከማደረጃ መመሪያው (አባ ሕሩይ ቀደም ሲል ሲመሩት ከነበረው) መሆኑ ሰውየው በማን ይመሩ እንደነበረ የተሻለ ግልጽ ያደርገዋል፡፡
ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ደብዳቤውን በወቅቱ በተገለጠው ሁኔታ በማርቀቅ፣ እንዲፈረምና እንዲሠራጭ የሞት ሽረት ትግል ሲያደርጉ ከነበሩት ግለሰቦች አንዱ የሆኑትን መምህር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተን ሾሟል፡፡መምህር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተ ለረጅም ዓመታት የታገሉለትን ማኅበሩን የማደናቀፍ እኲይ ተግባር የሚለውን ሐሳብ የተመለከተ ሰው ቀጣዩ የማኅበሩ ዒላማ ማን እንደሆነ ነቢይ መሆን ሳያስፈልገው መተንበይ ይችላል፡፡ ለምንድን ነው የማኅበሩ ዒላማ በመምህር ዕንቁ ባህርይ ላይ የሚሆነው? ማኅበሩን የማደንቀፍ እኩይ ተግባር የሚባለውስ ምንድን ነው?  
ለእነዚህ ጥያቄዎች ሊኖር የሚችለው መልስ አንድ ብቻ ነው፡- ሕጋዊ ሁኑ የሚል፡፡ ማኅበሩ የተጠየቀው አንድ ግልጽ ጥያቄ ነው ይህ ጥያቄ ዛሬ በመምህር ዕንቁ ባህርይ የተነሳ ሳይሆን ከዓመታት በፊት ጀምሮ ማኅበሩ ሲወተበትበት የነበረ ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄውም ለአንድ ሕጋዊ ነኝና ሕጋዊን አሰራር ተከትዬ ነው የምሰራው ለሚል ማኅበር የሚያስደስት እንጂ ሜዳው ጠበበኝ የሚያስብል አልነበረም፡፡
ይህን ሁሉ ነገር ያመጣው የደብዳቤው መልእክት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቃለ አዋዲውን እንዲሁም በማኅበሩ ውስጠ ደንብ የተቀመጠውን መብትና ግዴታ አውቃችሁ ተንቀሳቀሱ የሚል ነው፡፡ ይህ ማለት ቤተ ክርስቲያኒቱ በፈቀደችላችሁ መስመር ላይ ብቻ ተራመዱ እንደማለት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ነገር ደግሞ ያለእኔ ማን አለ ለሚል ማኅበር ከባድ ራስ ምታት ነው፡፡ ይህን ሐሳብ የሚያራምዱም ሰዎች ራስ ምታት ፈጣሪዎች ናቸውና ቤተ ክርስቲያን አፍራሽ የሚል ቅጽል እየተጨመረላቸው ስፍራ እንዲለቁ ጥረት ይደረጋል፡፡ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው ማኅበሩ ለቅዱስ ሲኖዶስ በጻፈው ደብዳቤ መጨረሻ ስለመምህር ዕንቁ ባህሪ የተጻፈው የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማደናቀፍ ከተንቀሳቀሱት ሕገወጦች ውስጥ አንዱ የሆነው በሚል ነው፡፡
እኔ ሕጋዊ ነኝ ሕገወጡ ሌላው ነው ለሚል ማኅበር ሕጋዊነትህን አሳይ የሚል መልእክት (ደብዳቤ) ሲደርሰው በኩራት ይሄው ማለት ምነው ተሳነው? በዚህስ ፈንታ ይህን ጥያቄ ይዘው የሚመጡትን ሰዎች ሕገወጦች ናቸው ማለቱ ለምን ይሆን?            

No comments:

Post a Comment