Monday, May 28, 2012

እውን “ማኅበረ ቅዱሳን” (ሰለፊያ) እየተዘጋ አይደለምን???

Click here to read in PDF
አንዳንድ የዚህ ክፉ ነብሰ በላ የሆነ ድርጅት አመራሮችና አባለት “አባሠረቀንና አቡነ ጳውሎስን ብንገድል መንግስተ ሰማያት መግባታችን አይቀርም እንጸድቃለንም። በዚህ አንጠየቅም” እያሉ ሲያወሩ ስንሰማ ግራ እየገባን ይህ ከምን የመጣ አመለካከት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈውን አስተሳሰብ እንዲህ በድፍረት የሚናገሩት ለምንድን ነው እያልን ለአመታት የቆየን ቢሆንም በስተመጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የሚሉት ለምን እንደሆነ በግልጽ ነግረውናል። እኛም ነገሩ ገብቶን ሰው በመግደል ገነት እንደሚወርሱ የሚያምኑ ሰለፊዎች መሆናቸውን አረጋግጠን ከየትኛው መጽሐፍ ይህን ትምህርት እንዳገኙት አውቀናል። ከማቅ ሰዎች ጋር በሀሳብና በአመለካከት ብቻ የተለያየን መሰሎን የነበረ ቢሆንም በምንመራበት መጽሐፍም ቢሆን ልዩነት እንዳለን አውቀናል።
ከዚህ እውነት በመነሳት “ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” እንዲሉ በግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የታዩ ክስተቶችን የተመለከተ ትንታኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው የፖለቲካ ድርጅት ለአለፉት ሁለት አሥርት አመታት በቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ሆነ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳስነበብናችሁ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የታቀፈውና በዲያቢሎስ መንፈስ የሚመራው ማቅን ለመሆኑ ማን መሠረተው? እነማንስ ስም ሰጡት የሚለውን እውነታ ስንመለከት ‹‹ማቅ›› የተሀድሶ ኮሚቴ ይባሉ በነበሩ የደርግ ደጋፊ አባላት የተመሠረተ ሲሆን ይኽ የጥፋት መልዕክተኛ ዘር ግንዱ እነኮሎኔል አጥናፉ አባተ ካቋቋሙት ”ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ” ይነሳል። ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን አባቱ መሆኑ ነው። ይኽ አባቱ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማፍረስ እና በውስጥዋም ሥርዐት አልበኝነት በማንገስ ቤተ ክርስቲያን ደካማ እንድትሆን ለደርግ ያገለገለ ነው። የእኛ ጊዜዋ ማቅ አገልግሎት ሁለት መልክ አለው - የሞተውን ሥርዐት ለመመለስ እና የየግል ጥቅማቸውን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም ነው፡፡

”ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል” እንደሚባለው ይኽ ጊዜጣዊ የተሀድሶ ጉባኤ የመንደረተኝነቱን ቂም ለማርካት ሲል ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ፓትርያርክዋን በገመድ አሳንቆ ያስገደለ የሠይጣን መልእክተኛ ነው። እንኩዋን የቤተ ክርስቲያኒቱን አደረጃጀት ሊያድስ ቀርቶ የዕሪያ መፈንጫ አድርጓት አረፈው። የያኔው የጊዜያዊ ተሀድሶ ጉባኤ አባላት ግማሹም በሹመት ግማሹም በሞት ሲበታተኑ ያደረገው ቀለማቸውን ለውጠው ”ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል ሥያሜ የደርግ ወታደሮችን ሰብስቦ(አዲሱ ማቅ የተመሰረተው በደርግ ወታደሮች አማካኝነት እንደሆነ ማኅበርዋ አትክድም)ወራሹን ማደራጀት ነበር። ቤተ ክርስቲያኒቱን ተጠልሎ የወደቀ ሥርዐት ለማስመለስ ስለነበረ አባቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉልላት እየናደ ሲደልቅ ቆይቶ ልጁ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እንደሌሊት ሌባ መሠረትዋን እንዲሰረስር ክህነት ሰጥቶ ባረከና አደራጀው።
”የአዛኝ ቅቤ አንጓች” እንዲሉ ለገዳማት ልማት ያሰበ በመምሰል የገዳመት ጉብኝት እያዘጋጀ ሀብት አካበተ፣ ንዋየ ቅድሳትን ዘረፈ፣ አስዘረፈ፣ ገዳማትን አስደፈረ፣ አንዳንድ ገዳማትን መርጦ ለ ”ትንቢት ተናጋሪ ባህታውያን ማሠልጠኛነት” አደራጀና በከተሞች ማሰማራት ጀምሮ ነበረ። ”ከጳጳሱ ምእመኑ -ቄሱ” እንዲሉ አባቱ ጊዚያዊ የተሀድሶ ጉባኤ ያተራመሰውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተክቶ እንደ ብፁዕ አቡነ መርሀ ክርስቶስ (የቤተ ክርስቲያኒቱ መዝገበ ሃይማኖት በመባል የሚታወቁትን)፣ መጋቤ ብሉይ ሠይፈ ሥላሴ ያሉትን ሳይቀር ተሀድሶ ናቸው በማለት ስም ከማጥፋት አልፎ እስከማስወገዝ የደረሰ የዐይነ ደረቆች ቡድን ነው።  የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር ለመጨበጥ አንዳንድ ጳጳሳትን በገንዘብ በመደለል፣ አንዳንዶችን ደግሞ በስነ ምግባር ጉድለታቸው ካርድ እመዝዛለሁ እያለ በማስፈራራት የሕይዎት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ቢሆንም እሰከ መሰዋት ድረስ የማሉለትን ሥልጣን የዚህን እኩይ ማኅበር ዓላማ ለማስፈጸም ሳያፍሩ ተሰለፉ። አስቀጥሎም የቅዱስ ሲኖዶስን የስብሰባ አጀንዳ የሚወስን፣ ማን ኤጲሲ ቆጶስ ሆኖ እንደሚሾም መመሪያ ቢጤ ሰጭ ሆኖ ተኮፈሰ።
ማቅ ሆይ መንገድሽ የጥፋት ነው፣ አንቺ ብቻሽን ብትጠፊ ባልከፋ ግን ሊቃውንትዋን በማሳደድ፣ ቀኖነዋን በማራከስ ቤተ ክርሰስቲንን ጤና አትንሺ ያሉትን የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበራት ለክርስቶስ አገልግሎት ሳይሆን ለሷ እንዲያጎበድዱ፣ ይህን ያልተቀበሉትን በተቧደኗቸው ጳጳሳት ተራዳኢነት ማስወገዝ፣ ቤተክርስቲያኒቱ ደቀ መዛሙርትን ለመፍራት ያቋቋመቻቸውን መንፈሳዊ ኮሌጆች የመናፍቃን መፈልፈያ ስለሆኑ ይወገዙ (ይዘጉ ለማለት ነው) እያለ ሲፉዋልል የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ” ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም” ቢልም አፍ በማዘጋት ጊዜና ገንዘብ እንዲባክን፣ በየመንፈሳዊ ኮሌጆች ያሉ ደቀ መዛሙርት እንዲተራመሱ በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሁከት አውድማ አድርጓታል፡፡
ማህበሩ ስያሜውን ያገኘው በቅዱስ ፓትሪያርኩ የሁል ጊዜ ጠላትነት የሚታወቁትን፣ እና ገዥውን ፓርቲ በሰሜን አሜሪካ ባንዲራ በመያዝ ሲቃወሙ የነበሩት፣ አሁንም በምዕመናንና በመንግስት ትልቅ መቃቃርና ደም መፋሰስን እያበረታቱ ባሉት በሄዱበት ሰላም በማይቆያቸው አሁንም አዋሳን ከማቅ ጋር በመሆን እያመሱ በሚገኙት አቡነ ገብርኤል አማካኝነት ማህበረ ቅዱሳን የሚል ስያሜውን አገኘ፡፡

የማኅበሩ ስውር አላማዎች፣
1.     በቤተመንግስትም ይሁን በቤተክህነቱ የአፄው አሠራሮች እንደገና መመለስና  መሳፋንታዊ አገዛዝን ዳግሞ ለመመለስ የሚደረግ  ተግባር ነው፡፡
2.    ከፍተኛ ደረጃ ጥረት እየተደረገበት ያለውን የቤተክርስቲያን አንድነት እንዳይሳካና ተግባራው እንቅስቃሴው ላይ ተግዳሮት በማብዛት ቤተክርስቲያን አንድ እንዳትሆን ማድረግ፡፡ ይኸውም በውጭ ያሉ ሲኖዶስ አባላት ‹‹የጎንደርና የጎጃም ተወላጆች›› ናቸው ሲሉ በአገር ውስጥ ያለውን ሲኖዶስ  ደግሞ ‹‹የትግራይ ተወላጅ›› ናቸው፡፡ በሚል የሁለቱ ሲኖዶስ አባላት አንድነት የሚፈጥረው ውህደት የሚያመጣውን የቤተክርስቲያን አንድነትና ሀገራዊ ስሜት ተጽዕኖ በመፍራት ለአጼው መንግስት በግጭት መካከል ቦታ ለማመቻቸት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡
ይህንን ለማስፈጸም ማኅበሩ ከመጀመሪያው ጀምሮ የሚጠቀምባቸው በአንድ አስተሳሰብ ዙሪያ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳትን መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተነሱ ጳጳሳት ብንመለከት፤
1. ብፁዕ አቡነ ይስሀቅ በሕይወት የሌሉ
2. ብፀዕ አቡነ ቀውስጦስ
3. ብፀዕ አቡነ ገብርኤል
4. ብፀዕ አቡነ ቄርሎስ
5. ብፀዕ አቡነ ሕዝቅኤል
6. ብፀዕ አቡነ ፊሊጶስ
7. ብፀዕ አቡነ ኤልያስ እና ሎችም ሲሆኑ

ከሊቃውንተ ቤተክርስቲናን፣

1. ሊቀ ጉባኤ አበራ
2. መ.ሰላም ዳኛቸው
3. ሊ.ካህናት ክንፈገብርኤል አልታዬና
4. ሊ.ካህናት ብርሃኑ ገ/አማኑኤል ናቸው፡፡

3.    ማህበሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመንፈሳዊ ጉባኤ ስም በመግባት መንግስት እያሰለጠናቸው ያለውን ሃገር ተረካቢ ወጠት ምሁራን የገዥውን ፓርቲ አስከፊነት በመግለጽ በሚሰማሩባቸው የሙያ መስኮች ሁሉ ሥውር የማኅበሩን ዓላማ ማስፈጸም እንዲችሉ ማዘጋጀት፤ከቀበሌ እስከ ከፍተኛ የመንግስት መዋቅር የሚገኙት የማህበሩ አባላት የተሰጣቸውን የስራ ድርሻ ቸል በማለት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የማህበሩን ጽንሰ ሐሳብ በማስረጽ ከፍተኛ ሃገራዊ ኪሳራ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡
አንዳንዶች የማኅበሩ ቀደምት አመራር በሃገር ውስጥ ያላቸውን ተልዕኮ ካጠናቀቁና መንግስት እንቅስቃሴያቸውን መከታተል መጀመሩን ሲያውቁ የሃይማኖት ካባቸውን በማውለቅ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘውን ሕልመኛ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ቡድን መቀላቀላቸው
 ከአመራሮች በጥቂቶች፤
ሀ. አቶ በላቸው ወርቁ፣ የማኅበሩ ሰብሳቢ የነበሩ፣ ባለው መንግስት የፓርላማ ፀኃፊ ደረጃ የደረሱ (ብዙ የመንግስት መረጃዎች አሉኝ እያሉ በሰ/አሜሪካ ቅስቀሳ የሚያደርጉ)፣ በአሁኑም ሰዓት የማኅበሩ የአሜሪካ ሰብሳቢ የሆኑ ከአ.አ.ዩ በአማርኛ የመጀመሪ ዲግሪ ያላቸውና የሸዋ ተወላጅ
ለ. አቶ ኤፍሬም እሸቴ የሚባሉ ከዚህ በፊት የማኅበሩ ጋዜጣ አዘጋጅ የነበሩ፣ በሰሜን አሜሪካ ኦነግ ነኝ በማለት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው የማኅበሩ የአሜሪካ ፀሀፊ በመሆኑ $2500 እየተከፈላቸው dejeselam, ahati tewahido እና andadirgen የሚባሉትን blogs ላይ ከፍተኛ የሆነ propaganda በመፍጠር መንግስትንም ሆነ ቤተክርስቲያንን ለመበጥበጥ ዋና ሁነው የሚንቀሳቀሱና የጠቅላይ ሚኒስቴሩን በቀዳሚነት የተቃወሙ ሰለፊያ ሲሆኑ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከኮተቤ በአማርኛ አግኝተዋል፡፡
3ኛ/ አቶ ብርሃኑ ጎበና፣ በአሁኑ ሰዓት የጠየቁት የኦነግነት  ፖለቲካ ጥገኝነት አልሳካ ብሎቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሲሆኑ፤ እኝሁ በመጀመሪያዎቹ አመታት የማኅበሩ ዋና ተቃዋሚ የነበሩና አሁን ተቀላቅለው ከማህበሩ ከላይ ለተገለጹት ብሎጎች( dejeselam, ahati tewahido እና andadirgen)  ተባባሪ ፀኃፊ በመሆን የሚያገለግሉ  ሲሆኑ ከአ.አ.ዩ. የኬሚስትሪ ዲግሪ ያላቸው ሰለፊያ መምህር ናቸው፡፡
4ኛ/ ዶ/ር መስፍን ተገኝ የህክምና ዲግሪ ከጎንደር ኮሌጅ ተመርቁው፣ በሙያቸው ካሣዩት ድክመት የተነሣ የህክምና ፈቃዳቸው በመንግስት በመወሰዱ፣ በአቡነ ቄርሎስ (በአገራቸው ሰው) አማካኝነት በልማት ኮሚሽን ተቀጥረው የነበረ ቢሆንም፣ በዚሁ መ/ቤት ባሳዩት የሥራ ድክመት የተባረሩ ሲሆን፣ በሰሜን አሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት ግንቦት ሰባት ነኝ ብለው ጠይቀው የሚኖሩ ሲሆን በአሣዩት ከቤተክርስቲያን ሥርዓት የወጣ(“ተሀድሶ” እንበለው ይሆን? ያውም ቁልቁል) እንቅስቃሴ (ከትዳር በኋላ ክህነት መቀበላቸው) እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ በቤተክርስቲያኒቱ  የተወገዙና  ግለሰብ ሲሆን ይህንንም ውግዘት ሲኖዶስ አጽንቶታል፡፡
5ኛ/ አቶ ደጀኔ ሸፈራው (Denver) እና አቶ ያሬድ ገብረመድህን የሚባሉ ግለሰቦችና የሰሜን ሸዋ ተወላጆች በሰሜን አሜሪካ ምንም አይነት የቤተክርስቲያንም ይሁን የዘመናዊ ትምህርት የሌላቸው ሲሆኑ በተለይ ያሬድ ገብረመድህን 12ኛ ክፍል ሳይጨርስ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲገባ ማኅበሩ ፎርጅድ ሰርቶለት በዲፕሎማ እንዲመረቅ ተደርጎል፡፡ ይህ ሰው አሁን አቶ ማንያዘዋል የሚባሉ የማህበሩ ጉዳይ አስፈጻሚ እያደረጉት እንዳለው ሁሉ በቤተ ክህነትና በማኅበሩ እንዲሁም በመንፈሳዊ ኮሌጅ ሰላይ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በዳንኤል ክብረት አማካኝነት ከማኅበሩ ተባረው አንድ አግብታ የፈታች ምዕመን አግብተው  ወደ አሜሪካ በመዝለቅ ቄስ ነኝ በሚል ለሚያደርጉት ያልተገባ እንቅስቃሴ ባሉበት ስቴት ከፍተኛ ተቃውሞ እና ክስ ተመስርቶባቸው ሊቋቋሙት ባለመቻላቸው ሚስታቸውን ወደ ሎሳንጀለስ ልከዋል፡፡ እርሳቸውም በቅርብ ወደ ሎሳንጀለስ እንደሚጓዙ ተገልጦአል። ስለሆነም ተመሳሳይ ተቃውሞ በLA ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡
በአጠቃላይ የማኅበሩ ሥራ አመራሮች በከፍተኛ የሞራል ዝቅጠት ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ ከመመስረታቸው ጊዜ ጀምሮ በተሃድሶአዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኙ ቀደምት አባላት የሚያውቁትና በፖሊስና ርምጃው የኢቲቪ ፕሮግራም የቀረበ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ለምሳሌ፡-
1ኛ እንደ አፋኒንና ፊንሀስ በቤተ እግዚአብሔር የምእመናትን ክብረ ንጽህና በመግፈፍ የሚታወቁት በዋናነት አባይነህ ካሴ፣ በላቸው ወርቁ፣ ኤፍሬም እሸቴ፣ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም፣ እሸቱ ወ/አገኝ፣ ባያብል ሙላቱና ያሬድ ገ/መድህን ናቸው፡፡ ከመረጃ ጋር በቅርብ እናወጣዋለን፡፡
በዚህም ምክንያት ከማኅበሩ አዝነው ከተሰናበቱት አባላት መካከል ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል መድኃኒት ዘዋለ (የመለከት መጽሄት አዘጋጅ የነበረች)፣ ዳግማዊት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ፈትለወርቅና ፋሲካ የሚባሉ የህግ ምሩቃን የማኅበሩ ቀደምት አመራር አባላት፣ ቅድስት የምትባል የህግ ባለሙያ (የአባይነህ ካሴ ሚስት)፣ ስመኝ የሞትባል ቀደምት አመራር በአሁኑ ሰዓት የፍትህ ሚኒስተር ባለስልጣን እንዲሁም ብዙ ንፁሀን ልጃገረዶች ከማኅበሩ ተለይተዋል፡፡ ማኅበሩም የሃይማኖት ካባውን እንዲያወልቅ በትግል ላይ ይገኛሉ፡፡
2. ሌላው በአባላቱ ላይ የተፈጠረው መፈራረስ ምንጩ የማኅበሩ የሥራ አስፈጻሚ አባላት የፖለቲካ ልዩነት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
ሀ. የኢህአዲግ ከፍተኛ አመራር ነን በሚል  ጳጳሳትንና ሊቃውንትን እንዲሁም የማኅበሩን አባላት የሚያስፈራሩና ኢህአዲግነታቸውን የሚወዱት ሰው ከማስፈራራያነት ያለፈ እንደልሆነ ግን በግልጽ የሚታወቅ እና ለገዢው ፓርቲ አለን የሚሉዋት ይቺው የአላማ ፍቅራቸውም ብትሆን ለመንግስት ከፍተኛ ጥላቻ ካላቸው የማኅበሩ አባላት ጋር የማታስማማቸው
-  አቶ ካሣሁን ኃ/ማርያም (መንገዶች ባለስልጣን)
                                                -   አቶ ባያብል ሙላቱ( ኮንስትራክሽን ባንክ
                                                    ባለስልጣን)
የማኅበሩ አመራር አባላት በዋናነት             - አቶ ሳምሶን ገብሬ (ደህንነት ቢሮ)
-  አቶ ደስታ በርሄ (ጠበቃ)
-  አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም

ለ. የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊነት በሚል ደግሞ የሚታገሉ ዋና አባላት
-   በላቸው ወርቁ አሜሪካ ኦነግ
-   ኤፍሬም እሸቴ አሜሪካ ኦነግ
-   ያሬድ ገ/መድኅን አሜሪካ ግንቦት 7
-   ብርሃኑ ጎበና አሜሪካ ኦነግ
-   መስፍን ነጋሽ (አዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረ)
-   ማንያዘዋል ከአዲስ አበባ
-   እርገተ ቃል (አትላንታ)
-   ነጻነት ተስፋዬ(ዕንቁ መጽሔትና ኢቢኤስ ቲቪ ላይ የሚተላለፈው የአኮቴት ፕሮግራም አዘጋጅ)
-   ታደሰ ወርቁ(እንቁ መጽሔት የስምዓ ጽድቅ ዋና አዘጋጅና የአንድአድርገን ብሎግ ጸሀፊ)
ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ማኅበሩን በከፍተኛ አመራር ይመሩ ከነበሩ አባላት መካከል ብዙዎቹ በፈቃዳቸው ማኅበሩን በመልቀቅ ለቅድስት ቤተክርስቲያናቸው አንድነትና ሉዐላዊት እየታገሉ ይገኛሉ፡፡ ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል፡
Ø ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
Ø ወ/ሮ መድኃኒት ዘዋስ
Ø ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ
Ø ዲ/ን ቸሬ አበባ
Ø መስፍን ነጋሽ (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ)
Ø ቀሲስ ተስፋ እንዳለ
Ø ዲ/ን ደረጀ ጅማ
Ø ፈትለወርቅ፣
Ø ፋሲካ፣ ቅድስትና ስመኝ የሚባሉ የህግ ባለሙያ ሴቶች እና ሌሎች አባላት ያሉበት ሲሆን አንዳንዶች በማህበሩ ውስጥ ያሉ አባላትንና አመራር አባላትን በቅርብ ሁሉንም መረጃ ስላገኘንው እናወጣዋለን የወጡበትን ምክንያት ጭምር ትንታኔ በመስጠት እንገልጸዋለን፡፡

ከማህበሩ አመራር አባልነት የወጡና ማኅበሩን ለቅቀው የሚታገሉበትን መንገድ እያጠኑ ያሉ
Ø ዲ/ን ዳንኤል ክብረት(ከአዲስ አበባው ማቅ ጋር ሙሉ በሙሉ ግንኙነት ያቆመ ሲሆን አሜሪካ ባሉ ጓደኞቹ በእነ ኤፍሬምና ብርሃኑ ግፊት አሜሪካ ካለው የማኅበረ ቅዱሳን ክንፍ ጋር የሚሰራ )
Ø ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ(መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ መማሩ የጠፋበትን ማስተዋል የመለሰለትና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማኅበሩ ጋር ሆኖ ባጠፋቸው ጥፋቶች እጅግ በመጸጸት ብቸኝነትና ትካዜ የሚያበዛ)

የማኅበሩ ስትራቴጅዎች

1.     በቤተክርስቲያኖች ሁሉም ተቋማት ውስጥ አባላትን በማስገባት/በማስቀጠር ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የማህበሩን ዓላማ ማስረጽ፡፡ ለምሳሌ፡-
·        ጠቅላይ ቤተክህነት
·        አህጉረ ስብከት
·        ልማት ኮሚሽን
·        መንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
·        ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
2.    በከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ የቤተክርስቲያን አባላት ለማኅበሩ እኩይ ተግባራት ማዘጋጀት፤
3.    በሰ/ት/ቤቶች ውስጥ ተለጣፊ ማኅበራትን በመፍጠር በቀጥታ አመራር ከማኅበሩ እንዲቀበሉ በማድረግ የማኅበሩን አኩይ ተግባር እንዲሳካ ብጥብጥ መፍጠር፤
4.    በስብከተ ወንጌል ስም ‹‹ፀረ-ተሃድሶ›› ጥምረት በሚል አንዳንድ ሲሞናዊ የገንዘብ አገልጋዮችን በገንዘብ በመደለል የእኩይ ተልኮአቸው አስፈጻሚ ማድረግ
5.    ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን እንረዳለን በሚል ሰበብ የዋህ መነኮሳትንና የአብነት መምህራንን በማግባባት የአላማቸው ማስፈጸሚያ አካላት ማድረግ፤
ምሳሌ፡- የዋልድባ ገዳም መነኮሳት
        ከመምህራን መጋቢ ሀዲስ እሸቱ
6.    የአንዳንድ ጳጳሳትን የስነ ምግባር ጉድለት እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም የአላማቸው ማስፈፀሚያ አካላት ማድረግ፡፡
ምሳሌ፡-
ሀ. አቡነ አብርሃም (ሰብለ የምትባል ሚስት ያላቸው)፡፡ ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው፣ የቅባት ሃይማኖት አራማጅ የሆኑና የማኅበሩ የአሜሪካ ብሎግ ጽሑፍ ማዘጋጃ እንዲሁም ሀ/ስብከት ጽ/ቤት የሰጣቸው፣ ግንቦት 7 በማጠናከር በአሜሪካ የሚታወቁ ሲሆን በሲኤምሲ እና በአስኮ ፎቅ ቤቶች ያላቸው መጽሐፍ ቅዱስ አንብበው የማያውቁ እስኪመስሉ ድረስ በፍጹም ጥላቻ የተሞሉ፣ ሰለፊያ አስፋፊና የጉድ ሙዳይ የሆኑ ጳጳስ ናቸው፡፡
ለ. አቡነ ሳሙኤል፡- ከዚህ በፊት የጳጳሱ ቅሌት በሚል መጽሐፍ የልብ ወዳጃቸው በነበረ ሰው በሚገባ የተገለጹና የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን ተገን በማድረግ የጨለማው ንጉስ ከሚባለው ማንያዘዋል ጋር በመሆኑ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን የሚያምሱ ፕትርክና ናፋቂ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ናቸው፡፡
ሐ. አቡነ ሉቃስ፡- የደርግ ኢአፓ አባል የነበሩ፣ ምንም አይነት እምነት ሳይኖራቸው ለጵጵስና  የተሾሙ፣ በአሁኑ ሰዓት ሐዋሳ ያለው ቤታቸው ለማኅበሩ አከራይተው የሚጠቀሙ፣ የአቡነ በርተለሜዎስ ሠራተኛን ወሽመው በፍርድ ቤተ ተከሰው የነበረ ሥራ አስኪያጅ የነበሩ፣ በአሁኑ ሰዓት ለሐዋሳው ብጥብጥ ዋና ተጠያቂ የሰለፊ ደጋፊ ናቸው፡፡
በቀጣይ የሁሉንም መረጃ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
የማኅበሩ ወቅታዊ ሁኔታ
1.     የማኅበሩ እኩይ አላማ እና ተግባር በቤተ መንግስት አመራር አባላት ጭምር ታውቆ በይፋ በፖርላማ ተገልጾል፡፡ መንግስትም በቀበሌና በወረዳ ደረጃ የማኅበሩን እኩይ አላማ ገልጾአል፡፡ ምዕመናንም በቂ ግንዛቤ አግኝተዋል፡፡
2.    በማኅበሩ የአገረ ውስጥም ይሁን የውጭ አገር ተባባሪ የነበሩ አባላትና ድርጅቶች ተለይተው ታውቀዋል፡፡ የተወሰኑ አካላት ላይም እርምጃ ተወስዶአል፡፡
ሀ. ስብከተ ወንጌል፤ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ ከም/መምሪያ ኃላፊነት ተወግደዋል፡፡
ለ. ሰንበት ት/ቤት መምሪያ፡- አባ ህሩይ ወንድይፍራው የተባሉ የመምሪያ ኃላፊ ተወግደዋል፡፡
ሐ. የገዳማት መምሪያ፡- ንቡረዕድ ገብረ ማርያም ከኃላፊነታቸው ተወግደዋል፡፡
መ. በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሰራተኛ የነበሩ 18 የማኅበሩ እኩይ ተግባር አስፈጻሚዎች ተሠናብተዋል፡፡ ምሳሌ አቶ ማንያዘዋል የተባሉት የማኅበሩ ካድሬ ሲሆን ይህ ጉዳይ እንደሚቀጥል ተገልጾአል፡፡
3.    የጳጳሳት ያልተገባ የገንዘብ ዝርፊያ፣ ጥቅመኛነትና እንዲሁም የፖለቲካ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት እንዲጠና ኮሚቴ ተቋቋሞል፡፡ ይሀ ጉዳይ አገራዊም ሆነ ቤተክርስቲያናዊ ፋይዳ ስላለው መንግስትም ሆነ ምዕመናንና በቅርብ ክትትል ላይ ናቸው፡፡
4.    ማኅበሩ በሁሉም የቤተክርስቲያን ተቋማት ጣልቃ እየገባ የሚያደርጋቸው እኩይ ተግባራት እንዲያቆም ለጊዜው (እስኪፈርስ) እንደ አንድ መምሪያ እንዲቀሳቀስ ተደርጎል፡፡ የዚህ አንድምታ፡-
ሀ. ማኅበሩ በሰ/ት/ቤት ሥም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ያቆማል፡፡
ለ. በአዲስ የስብከተ ወንጌል መመሪያ መሠረት በየትኛውም ቦታ የፈለገውን ፖለቲካዊ ጉባኤ ማድረግ አይችልም
ሐ. ማኅበሩ በገዳማት፣ አብነት ት/ቤቶችና ሰበካ ጉባኤ ነክ ጉዳዮች ያለው እንቅስቃሴና ገንዘብ ማካበት ያቆማል፡፡
መ. የማኅበሩ አመራር እንደሌሎች መምሪያዎች በቅዱስ ፓትርያርኩ ይሾማሉ፡፡ ይሻራሉ፡፡
ሠ. ማኅበሩ ሀብቱን ኦዲት ያስደርጋል፡፡ወጭውን በፋይናንስ ህግ መሠረት በቤተክርስቲያን በኩል ብቻ ያደርጋል፡፡ በሁሉም አካውንቱ ላይ ብፁዕ ሥራ አስኪያጅ ፈራሚ ይሆናሉ፡፡ እንደ ሁሉም መምሪያዎች ማለት ነው፡፡
ረ. ጥገኝነት አገልግሎት ያቆማል፡፡ በውጭ ሀገርም ምንም አይነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስለሌሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ይዘጋሉ፡፡
ሰ. በሐምሌ የማኅበራት ጥናት መሠረት የሚወስነው የመጨረሻ ውሳኔ በማኅበሩ ላይ ይወስናል፡፡ በቀጣይ ዝርዝር መረጃዎች ጋር እንልካለን፤
ታዲያ ይህ ሆኖ እያለ ሰሞኑን ለምን ማኅበሩ እና የማኅበሩ ልሳናት ጮቤ ረገጡ፡፡ ምክንያቱ ይህ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው በአሁኑ ሰዓት ነፃ የHIV/AIDS ህክምና/ እድሜ ማርዘሚያ ተጠቃሚ ነው፡፡ ART (የእድሜ ማራዘሚያ) መውሰድ ማለት ግን ከቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ መላቀቅ አለመሆኑን የሕክምና ሊቃውንት ያረጋግጣሉ፡፡ በተመሣሣይ መንገድ ለማኅበሩ ሰሞኑን በአቡነ ገሪማ አማካኝነት የተደረገው የዕድሜ  ማራዘሚያ አንድምታው፤ በሥነ ስርዓት የማኅበሩን ንብረት የቤተክርስቲያን ለማድረግ የሚያመቻች ሂደት እንጂ ሰለፊያ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለማስፋፋት አለመሆኑ በሁሉም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች ግንዛቤ ተፈጥሮል፡፡ አባቶቻችን ሲተርቱ ላይቀርልሽ አመድ አትላሽ ይላሉ። ማቅ መፍረሷ የማይቀር ነገር ነው።
ይቀጥላል፡፡

8 comments:

  1. enantew metedaderia denb awttachu arefachut eko aye maferiawech ergmanachu tsidk endemisten alawekachumine

    ReplyDelete
  2. Very thrush analysis

    ReplyDelete
  3. ለአቡነ ገብርኤል ሊቀ ጳጳስ

    ማኅበር ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሊሰጥ ይቻላል ያሉት ሊጸጸቱና ንሥሓ ሊገቡ የሚገባቸው አቡን

    ጸረ ሃይማኖት የሆነውና የሶሻሊዝም ሃይማኖት ተከታይ የነበረው ደረግ አኢወማ አንድ የወጣት ማኅበር ብቻ ሆኖ በኢትዮጵያ እንዲኖር ማድረጉ የታወቀ ነው፡፡ የደርግ አመለካከት ግን ለምን እንደበርና ምን አይነት ውጤት እንደመጣ የሚያውቁት ይመስለኛል፡፡ በመጀመሪያ አንድ የወጣት ማኅበር ብሎ ያወጀው ሁሉም ወጣት የእሱን መመሪያ እንዲከተል፣ ሁሉም ኮሙኒስት እንዲሆን፣ ሁሉም በአንድ ወጥ መመሪያ እንዲራመድ፣ በየመንደሩ የወጣት ማኅበር እያለ መዋጮና አባል እየሰበሰበ የደርግን የፖለቲካ መርህ እንዳይቃወም፣ አንዳንዱም ሃይመኖተኛ እንዳይሆን፣ ከኢሠፓ ውጭ ሌላ ፓርቲ እንዳይፈጠር፣ ሌላ ጎጥ (በደርግ ቋንቋ)፣ እንዳይፈጠር፣ መላ ሀገሪቱን አብዮተኛ ለማድረግ ነው፡፡ ደርግ ግን ይህን ያደረገው በጦር መሣሪያ አፈ ሙዝ በግድያና በአፈና ነው፡፡ ሌሎች ሲደራጁ እያሠረና እገረፈ ሁሉንም ወደ አኢወማ ይከት ነበር፡፡

    ለመሆኑ እርስዎ ቤተ ክርስቲያንን ከደርግ ጋር ያመሳሰሉት በምን ምክንያት ነው፡፡ እኛ ደርግ አይደለንም ያሉት ምንን መሠረት አድርገው ነው፡፡ በአንዲት (አሐቲ፣ ዋሕድ፣ ውሒድ) ጉባኤ (ማኅበር)፣ የክርስቶስ አካል እናምናለን ያሉት ሠለሥቱ ምዕት ደርጎች ናቸው፡፡ አንድ እምነት፣ (አማኞች የሚሰባሰቡባት)፣ አንዲት ጥምቀት (ሰንዓዊ ፍጡራን ወደ አሚን የሚመጡባት)፣ አንድ እግዚአብሔር ሁሉም የሚያምኑት ብሎ ያለው ሐዋርያ ደርግ ነው፡፡ ሐዋርያት የሰበሰቧት፣ የሚሰበስቧት አንዲት ማኅበር ያሉት አባቶች እኮ የሚሰበሰቡት ምእመናን ሰብሳቢዎቹ ሐዋርያት ጳጳሳት እናንተ ናችሁ ከዚህ ቃል እንዴት ነው የምትወጡት፣ ማኅበረ ቅዱሳን ምንድን ነው ደባል ኪራይ ሰብሳቢ በምእመናን መካከል ገብቶ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር የሚያውክ አሸባሪ ቡድን ነው፡፡ በማንኛውም የኦርቶዶክስ የዶግማና የቀኖና ሥርዓት ውስጥ ቦታ የሌለው መዋጮ እና አባል ሰብሳቢ ቡድን ነው፡፡ እስከ አሁን የሰበሰበው እና የሠራ እኮ ቤተ ክርስያኗ በመዋቅሯ ልትሠው የሚገባትን ሥራ በማዳከም ለራሱ ቀዳዳ የፈጠረ ቡድን ነው፡፡ አሁን በኮሚቴ ተመርጣችኋል የማኅበሩን አወቃቀርና አደረጃጀት ስትመለከቱ ታዲያ ይሄማ ራሱ ቤተ ክህነት አይደለም እንዴ (መቼ ነው የገለጣችሁት) እንደምትሉ ፍጹም አንጠራጠርም፡፡ እናንተ በሲኖዶስ በበጎ አድራጎት እንዲሠራ ያላችሁት ማኅበር ለስንት ሰው ደመወዝ እንሚከፍል ታዩታላችሁ፣ በወጣቶች ሰንበት ትምህርት ቤት ይሁን ያላችሁ ማኅበር በስንት አባት ጡረተኞች ይመራ እንደነበር ታዩታላችሁ ያን ጊዜ ለካ ግጭቱ የመነጨው ከዚህ ነው ትላላችሁ፡፡ (አእምሮአችሁን በተለመደ…. ሁኔታ ካልተሸበበ)፡፡ ለማንኛውም ሠለሥቱ ምዕትንና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ደርጎች በማለትዎት ንሥሓ ይግቡ፡፡ እኛ ግን ለርስዎና ለመሰሎችዎት እንዲሁም ሌላ ማኅበር ለሚሉ ማቆች ይብላኝላቸው እንጅ በማትከፋፈል አንዲት የክርስቶስ አካል በሆነች ሐዋርያት (እውነተኞች ጳጳሳት) በአንድነት በሰበሰብዋትና በሚሰበስብዋት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡፡ በቡድንም አንከፋፈልም፡፡

    አቡነ ገብርኤል፡ በጣም ከምናከብቸውና በውስጥና በውጭ ትምህርታቸው ባልተጨብረበሩ የትምህርት ማስረጃዎች ብፁዕ ወቅዱስን ይመስላሉ ብለን ከምናውቃቸው አባቶች አንዱ አቡነ ገብርኤል ናቸው፡፡ ነገር ግን እርስና መሰሎችዎ የቡድን ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን የቤተ ክርስቲያኗን ዓላማ ትታችሁ ማሳዎች የሚያጠፉ፣ ሀብቷን በመዋጮና በልመና ለሚመዘብሩ፣ አባላቷን በሌላ መተዳደሪያ የሌላ ቡድን አባል ለሚያደርጉ፣ ለትናንሽ ቀበሮዎችን እና የዲያብሎስ (የዓለም) ዘር አረሞች ዘብ ቆማችኋል፡፡ ይቅር ይበላችሁ፡፡

    አቡነ ገብርኤል በቅዳሴ ማርያም ማኅበረ ምእመናን ወይም ቅዱሳን ማለት ቤተ ክርስቲያን በትልቁ በትንሹ (አጥቢያ) ናት፣ ማህበረ መነኰሳት ማለት ረሱት እንጅ ገዳም ነው፣ ማኅበረ ሰማእታት ማለት መካነ ሰማዕታት በሰማይ ያለች የሰማእታት ማረፊያ ነው፣ ማኅበረ መላእክት ማለት የሁሉም መላእክት አንድ ማኅበር ነው በመላእክት ውስጥ ሌላ የመላእክት ማኅበር የለም፡፡ ሠራዊት ደግሞ የተልእኮ ሥምሪት ነው እንደ መምሪያ፡፡ ገባዎች አባታችን.. ፡፡ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አሁን ማን ይሙት ከርስዎ የበለጠ የቡድኖችንና የማኅበሮችን ከፍተኛ ጉዳት ማን ሊያውቅ ይችላል፡፡ አዋሳ ከመጡ ጀምሮ እንኳን ማኅበረ ቅዱሳን እንደ አንድ ቡድን፣ በአካባቢው በተዋቀሩ የልማትና የስብከተ ወንጌል ኮሚቴዎች ላይ ያደረገው እና ለበርካታ የዋህ ምእመናን ከቤተ ክርስያን ለመውጣት ምክንያት የሆነው እርስዋ እንደአባትነት፣ እንደ ምሁር፣ እንደ ዕድሜ ባለ ጸጋ፣ መፍታት ያልቻሉት ችግር ለምን ተከሰተ፣ የቤተ ክርስያን ዓላማ ሁሉም በአንድ ልብ እንዲሆን፣ የክርስቶስ ዓላማ ሁሉም የርሱ አካል እንዲሆን አካሉ የሆኑ ምእመናን በልዩ ልዩ ማኅበራትና መሰል ቡድኖች እንዲከፋፈሉ የምታደርጉ ዓለም አቀፍ የቴዎሎጅ ወንጀለኞች ናቸሁ፡፡

    እመኑን የማቅ ገመና ሲጋለጥ ከማን ጋር ነበርን ብላችሁ ታፍራላችሁ፡፡

    ReplyDelete
  4. ማቅ በሃያ ዓመቱ ክርስቲያን የሆነበትን (ክርስትና የተነሳበትን) ከንዑስ ክርስትና ወደ ክርስትና የመጣበትን ሃያኛ ዓመት በቅርቡ ያከብራል፡፡ ለዚህም የመረጥንለት ርዕስ

    ማቅ በሃያ ዓመቱ ተጠመቀ ወደ ቤተ ክህነት ወደ ቤተ ክርስያንም ገባ ወይም ሊገባ ነው

    እስከ ዛሬ የምናውቀው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ ቤተ ክርስቲያን ያገባል በሰበካ ጉባኤ አስመዝግቦ የቤተ ክርስያን አካል ያደርጋል ሲባል ሲኖዶስ ለራሴ መተዳደሪያ ሰጠቶኛል ዐሥራት በኩራት እንደሰበስብ ፈቅዶልኛል በማለት ወጣቶቹን የማቅ አባል፣ ሀብታቸውን ወደ ማቅ ባንክ፣ ሃይመኖታቸውን የማቅ ሃይማኖት፣ ሥርዓታቸውን የማቅ ሥርዓት በማድረግ ስብሰባው በየሆቴሉ፣ በየአዳረሹ፣ ገንዘቡን በየ አባላቱ ኪስ፣ የራሳቸው መዝሙር፣ የራሳቸው ዩኒፎርም፣ የራሳቸው አርማ፣ የራሳቸው መተዳደሪያ በመያዝ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሆነው ነበር፡፡

    አሁን ግን በሃያ ዓመቱ ወደ ቤተ ክህነት ሊገባ ነው መሰል ምናልባት እምቢ ካላለ በቀር አሁንም ያላመሁ አባላት ስላሉ፡፡

    ለዚህ ከፍተኛ ስኬት የሐዋርያነት ሥራ ለሠራችሁ ለእነ አባ ሠረቀ፣ ለማኅበራት ጉዳይ አጥኒ ቡድን እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ማቅን ከሐጢአትና፣ ከኑፋቄ፣ ከዝርፊያና ከአሸባሪነት አውጥታችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለመለሳችሁ፡፡ ልትመሰገኑ ይገባል እንላለን፡፡

    እስኪ ምእመናን ማቅ በሃያ ዓመቱ የንዑሰ ክርስቲያን ጉዞው ምን ሠራ እንዴት አሳለፈው፣ በሚለው ጉዳይ እየተወያየን ማቅን እንኳን ደህና መጣህ እንበለው፣ ሰብሰብ ብለን እስከ አሁን ከሰበሰቡት ወይም ከዘረፉት ገንዘብ ከወጭ ቀሪ ሰንት አስገባችሁ፣ ወደ ማኅበር መዝገብ ከሰበሰባችሁት ዓባል ስንቱን ለክርስቶስ አመጣችሁ እንበላቸው፡፡

    ግጥም እነሆ ለማቆች ሃያኛ ዓመት

    ወንዙ ወርዶ ወርዶ
    ሲሔድ ገደል ንዶ
    ደንጋይ ጋር ተጋጨ
    እያሙለጨለጨ
    ቀጠለ እያፏጨ
    ዛፉንም ገንድሶ
    ሜዳውንም አርሶ
    ገስግሶ ገስግሶ
    ስንቱን አተራምሶ
    ይደርሳል ከባሕር
    ከዚያ ላይሻገር
    ማቅ የሚሉት ቡድን
    ቢጽ ሐሳዊ ሰይጣን
    ስንቱን ሰው አታሎ
    የሰው ክብር አቃሎ
    የዋሁን ደልሎ
    የሰው ሥራ ሟጦ
    የስንቱን ኪስ ልጦ
    ስንቱን በቃል ወግቶ
    የስንቱን ቤት ፈቶ
    መቆሚያው ሊገታ
    የማታ የማታ
    ሊገባነው መሰል
    ከባሕሩ ወለል
    ሊካፈል ከማዕድ
    ከአቅሌስያ አጸድ

    ReplyDelete
  5. ግጥም እነሆ ለማቆች ሃያኛ ዓመት

    ወንዙ ወርዶ ወርዶ
    ሲሔድ ገደል ንዶ
    ደንጋይ ጋር ተጋጨ
    እያሙለጨለጨ
    ቀጠለ እያፏጨ
    ዛፉንም ገንድሶ
    ሜዳውንም አርሶ
    ገስግሶ ገስግሶ
    ስንቱን አተራምሶ
    ይደርሳል ከባሕር
    ከዚያ ላይሻገር
    ማቅ የሚሉት ቡድን
    ቢጽ ሐሳዊ ሰይጣን
    ስንቱን ሰው አታሎ
    የሰው ክብር አቃሎ
    የዋሁን ደልሎ
    የሰው ሥራ ሟጦ
    የስንቱን ኪስ ልጦ
    ስንቱን በቃል ወግቶ
    የስንቱን ቤት ፈቶ
    መቆሚያው ሊገታ
    የማታ የማታ
    ሊገባነው መሰል
    ከባሕሩ ወለል
    ሊካፈል ከማዕድ
    ከአቅሌስያ አጸድ

    ReplyDelete
  6. aeimro bis hulu...comeback to your sense!

    ReplyDelete
  7. ማቅ በተለይ ሀዋሳ ላይ በፈፀመው የአሸባሪነት ተግባሩ በተለዬ ሁኔታ ንስሃ መግባትና መጠመቅ አለበት፡፡ ማቅ አሸባሪው አልቃይዳ ከቤተክርስቲያናችን ላይ እጅህን አንሳ፡፡ ተነቅቶብሃል፡፡

    ReplyDelete
  8. leboch nachu lemayegebaw tsafu egna yegabanal

    ReplyDelete