Sunday, May 20, 2012

የ“ኢሳት” የዜና ማእከል እና “የማህበረ ቅዱሳን ጊዜያዊ ጋብቻ!

Click here to read in PDF
ሙሉውን የጽሑፉን ይዘት ከማንበብዎ በፊት÷
1.     ጸሐፊው በጽሑፋቸው ውስጥ የጠቀሱትን የዜና ማዕከል “ማህበረ ቅዱሳን” በመባል ስለሚታወቀው መንፈሳዊ ካባ ያጠለቀ ጸረ ቤተ-ክርስቲያን ጸረ ሀገርና ጸረ ትውልድ ማኅበርን በተደጋጋሚ ሽፋን በመስጠት ጽድቁን በዜና መልክም ሆነ በሐተታ ተጠቃሹ የዜና ማዕከል ለአድማጮች ያቀረባቸውን ፍጹም ሚዛኑን የሳተና የተንጋደደ ዘገባን ብቻ በማስመልከት ያነጣጠረ ለመሆኑ÷ 
2.    አሁንም በጽሑፉ ውስጥ የተካተቱ ማናቸውም ሂሶችና ጥያቄዎች “ማህበረ ቅዱሳን” በማስመልከት እጃቸውን የጨመሩ የክፍሉ ሰራተኞች/ግለሰቦች/ እንጅ የመደብሩ ባለደረባዎችን በመላ የማያጠቃልል ለመሆኑ÷ 
3.    የጸሐፊው ዓላማም ሆነ የጽሑፉ ግብ በማጣመም ሌላ አንድምታ በመስጠትም “በኢሳት” የመጣ በዓይኔ ብሌን” በማለት አካኪ ዘራፍ የሚልም ስለማይታጣ  “ኢሳት” “ማህበረ ቅዱሳንን” በተመለከተም ሆነ “ደጀ-ሰላም” በመባል የሚታወቀውበኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያንና በተከታዮችዋ ላይ ሁከትን ለመፍጠር ታጥቆ የተነሳ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን’) በአንድ ራስ ላይ ተደራቢ ምላስ/ልሳን ሆኖ የበቀለ ድረ ገጽ ዋቢ እያደረገ የሚዘግባቸው ዘገባዎችና የሚያቀርባቸው ማናቸውም ዓይነት ሀተታዎች ፍጹም ከእውነት የራቁና ነጭ ሐሰት መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በወንጀል የሚያስጠይቅ ስራ እየሰራ ለመሆኑ÷ 
4.    በተጨማሪም “ኢሳት” ጭራሽ “የማህበረ ቅዱሳን” ልሳን አስኪያስመስልበት ድረስ እየሄደበት ያለውን አካሄድ ማለት ነፍሰ ገዳይን የመታደግ ስራ ትክክል አለመሆኑ ለማሳየት ምንም በማያሻማ ግልጽ በሆነ አማርኛ የቀረበ ጽሁፍ ለመሆኑ÷ 
5.    በመጨረሻም “ለኢሳት” ለብቻ ተብሎ የሚታለፍ እውነት አለመኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንደበት የሚወጣ ቃል የሰውን ልብ ከማሸፈት በላይ ህይወትም ይቀጫልና በተለይ የጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤቶችና ሰላባዎች ሊሆኑ የሚችሉ/የምንችል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን እምነት ተከታዮችና ምእመን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ይህን ጽሑፍ ሊዘጋጅ ግድ ብለዋል። ደግሞም ሰው ይከበራል እንጅ ስጋ ለባሽ ሆኖ የሚፈራ፣ አምልኮም የሚገባው አንድ ስንኳ አለመኖሩን በሚያምን ልብ ተጻፈ። ጽሑፉ ልዩነትን የሚያሳይ እንጂ የክስ ደብዳቤም ሆነ የስሞታ ማመልከቻም አይደልም።
ከሰርጎ ገቦች የተነሳ በኢ/ኦ/ተ/ቤተ/ያን አስተዳደራዊ ማእከል ላይ ስለተፈጥረውና ስላለው ችግር በማስመልከት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት ዜናዎችን በማቅረብና ሰፊ ሐተታዎችን በመስጠት ይታወቃል። ይህ መቀመጫውን ሆላንድ አምስተርዳም ያደረገ እንዲሁም በአሜሪካን ክፍለ ግዛት ዋሽንግተን ዲሲ በመሆን ከሚያሰራጫቸው ሀገራዊ ዜናዎች በብዙዎቻችን ዘንድ የታወቀ ለመሆኑ አልጠራጠርም። ስለ መረጃው ማእከል ከማንም የተለየ የጠለቀ ቅርበትም ሆነ ስለ ጣቢያው የተሻለ እውቀት ባይኖረኝም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሚኖረኝ የጊዜ ክፍተት አልፎ አልፎ አድማጭ ነኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድ ሃሳብ የበላይነት ከሚንጸባረቅበት ብቸኛ መንግስታዊ የዜና ማሰራጫ ተገላግሎ አማራጭ እድል በማግኘቱም ደስታዬ ወሰን የለውም። ታድያ ይህ መቀመጫውን በምእራቡ ዓለም ያደረገ “ኢሳት” በመባል የሚታወቀው የዜና ማእከል በብዙ የአገልግሎት ዘርፎቹ ሁሉንም የሚያስማማና ሁሉንም ያቀፈ ስራዎቹን ውሃ የሚቸልስ ስራዎችን ሲያቀርብ አንዴ፣ ሁለቴና በተደጋጋሚ መፈፀሙ በተለይ ለጉዳዩ ቅርበት ባላቸው የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ልጆችና ባለ አደራዎች ዓይን ሲታይ ነገሩ በቀላሉ የማይታለፍ ሆኖ በመገኘቱ ለመተራረምና እርስ በርስ ለመማማር ለማስታወሻም ያክል አንድ ማለቱ አስገዳጅ ሆኖ ተገኝቷል።
የነገሩ ስር ተጠቃሹ የዜና ማዕከል ኢ/ት/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመለከተ ለሚያስተላልፋቸው/ለአድማጭ የሚያደርሳቸው/ በምስል የተቀረጹ ዘገባዎች በዋናነት “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀው ሰምዓ ሐሰት መካነ ድር እንደ ዋቢ መጠቀሙ አንዱ ነው። በነገራችን ላይ የዜና ማእከሉ እንደ አንድ የመረጃ ማሰራጫ ማዕከል ሚዛኑን በጠበቀ ሁሉንም በሚያንጽ መልኩ ዘገባዎችን ማቅረብ ሲገባው “ባለቤትነቱ በውል የማይታወቅ” የሰፈርተኞች አሉባልታ ማስተጋባት ምን ይሉት የሞያ ሃላፊነትና ግዴታ ነው ለማለት እንጅ “ኢሳት” ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመለከተ ለምን  ይዘግባል መዘገብ አይገባውም እየተባለ አይደለም ያለው። “ኢሳት” ድምጽ ሆኖ ካልዘገበ ሌላ ማን ይዘግብ!
የመረጃ ማእከሉ ነፃና ገለልተኛ ነኝ ሲል አላማው  የዘራውን እያጨደ ስለሚገኘው፣ በብዙዎች ደም ተጠያቂ የሆነው፣ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ጥንታውያንና ታሪካዊያን ቅርሶችዋ በማውደምና በመዝረፍም አቻ የማይገኝለት ሕጋዊ ሽፍታ፣ የሰው ለውጥና ዕድገት ደም የሚያስቀምጣቸው፣ ለሀገርና ለወገን ኪሳራ የሆነውን ትውልድ የሚፈለፍል ቆፍቁፎም የሚያሳድግ፣ እነሱ ያልተካፈሉበት ስራ ሁሉ ለመኮነንና ለማፍረስ የማይቀደሙ፣ የእግዚአብሔር እጅ የከበደችበት፣ በሞት አፋፍ ላይ ስለሚገኘው የሰው እባብ ስለ “ማህበረ ቅዱሳን” ጽድቅ መዘገብና ሽንጥን ገትሮ መከራከር ከሆነ÷
  • ዋጋ በከፈልኩበት!
  • እንደ ፌስታል እየተንጠለጠልኩ ወደ እስር በተወረወርኩበት፣
  • ዜግነታዊ መብቴን ተግፎ ከትምህርት ገበታዬ በተፈናቀልኩበት፣
  • በተወልድኩባት እትብቴም ተቆርጦ በተቀበረባትና በገዛ ሀገሬ በተገፋሁበት፣
  • በተዋረድኩበት፣
  • በተንገላሁበት፣
  •  በተደበደብኩበት፣
  • በተረገጥኩበት፣
  • በቆሳሰልኩበት፣
  •  አባት እንደሌለው በስደት ምድር ቁምስቅሌን ባየሁበት፣
  • በኬንያ ጎዳናዎች በወደቅኩበትና በተጣልኩበት፣
  • ወላጅ አባትእናቴ ወንድም እህቶቼ በትልቁም እናት ሀገሬ ጥዬ ለግዞት ህይወት በተዳረኩበት አጀንዳ ላይ እውነት የማይዋጥለትና ሲነገረውም ጆሮውን የሚያሳክከው ምንስ ቢሆን ማንም ሙሉጌታ ተኝቶ ያድራል ማለት ሲበዛ የዋህነት ነው። ደካማ መስዬ የታየሁት ግለሰብ ሆነ ድርጅትም ቢኖር መፅሐፍ ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሽ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል እንዲል ጥጉ እንዲሁ ነው።የተደገፍኩትም እንደ ሸምባቆ የሚሰበረው ከሁኔታዎች ጋር የሚለዋወጠውን ሰው ሳይሆን ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ/የሚያደርግ/፣ ሰማያትን በብልሃት የሠራ፣ ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፣ ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፣ ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፣ በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፣ ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራታላላቅ ነገሥታትን የመታ፣ ለባሪያው ለእስራኤል ርስት የሆነውን እግዚአብሔርን ነው።
እንግዲህ ይህ የመረጃ ማእከል ከተቋቋመበት ዓላማ በማፈንገጥ በተለይ “ማህበረ ቅዱሳን” በተመለከተ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በተደጋጋሚ ሽፋን በመስጠት የሚያስተላልፋቸው ዘገባዎች ፍፁም ከእውነት የራቀ፣ ጭብጥ የሌለው፣ተጠያቂነት በማይንፀባረቅበት፣ ሃላፊነት የጎደለበትና ሲበዛም የጋዜጠኝነት የሞያ ስነምግባር በሚያጎድፍ መልክ የቀረበ ለመሆኑ ልብ ብሎ ላስተዋለ ሰው ምንም አያጠያይቅም። ቁርጡ “ኢሳት” ለእኔ ለተገፊው ግለሰብ ስለ ሰላቢው ማህበር “ማህበረ ቅዱሳን” እንዲነግረኝ አይጠበቅበትም። (ደጀ ሰላምን በተመለከተ በሚቀጥለው ጽሑፌ እመለስበታለሁ)
ይህ በዋናነት “በኢሳት” ዜና ዘጋቢዎችና አንባቢዎች ሰፈር ዋቢ እየተደረገ የሚጠቀሰው መካነ ድር ፀሐፊው ማን ነው? ለዜናዎቹና ዘገባዎቹ ሐላፊነት የሚወስድ ግለስብም ሆነ ድርጅትስ ማን ነው? ለሚለው እጅግ ቀላል ጥያቄ “የኢሳት” ባልደረቦች በተለይ ማህበሩን በተመልከተ ጊዜያቸውን ሰውተው ብዙና ጥቂት የሚሉትን ለእነዚህ መሰል ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ይዘው እንደሚመጡ ተስፋ አደርጋለሁ። የሌሎቹን ባላውቅ እንደነ አበበ ገላውና ልጅ ተክሌ የመሳሰሉ በውጭ ዓለም የከፍተኛ ተቋማት ያለፉ ግለሰቦች የሚገኙበት ቤት አንዴት ነው እንዲህ ያለ ነገር በተደጋጋሚ ሊከሰት የሚችለው? ተጨማሪ ጥያቄ ነው (ስለማውቀው ተናገርኩ እንጅ ሌሎቹ አልተማሩም እያልኩ አይደለም)። ማንስ ይዘግበው ማንም የተገኘውን የማቅረብ መብት አለን ከተባለ ደግሞ ከዚህ በኋላ ሙግቱ ሞያ ነክ መሆኑ ነው። ያገኘኸውን ማግበስበስስ ተገቢ ነው ወይ ባይም ነኝ? ከሆነ ደግሞ የሌላውን ወገን ድምፅስ ለምን አይሰማም? ነፃ የመረጃ ማዕከል ተብሎ የሚነገርለት ፍትሃዊና ሚዛናዊ መሆን አይጠበቅበት? አንድ የመረጃ ማእከል የህዝብ አይንና ጆሮ ነው ሲባልስ የማን ጥቅም ማዕከል አድርጎ ሲሰራ ነው? የሕዝብና የሀገር ወይስ የጥቂት አማፅያንን?
እዚህ ላይ ቀለል ያለ ነገር ግን በቀላሉ የማይታለፍ ሞያዊ/101 ጥያቄ ማንሳት እወዳለሁ። ይኸውም ይቅር አንድ በተቋም መልክ የተደራጀና በምእራቡ የዓለማችን ክፍል መቀመጫው ያደረገ ቀርቶ ሃላፊነት ወስዶ ለሚሰራዎች ስራዎች አንድ በዋቢም ሆነ በምንጭ ደረጃ ለመጠቀም ቢያንስ ቢያንስ ቀዳሚው የመረጃ አካል ለሚያቀርባቸው ዘገባዎች በሕግ ሃላፊነት የሚወስድህጋዊነቱ የተረጋጋጠለትየሪፖርቱ ፀሐፊም ሆነ የዘገባው አጠናካሪ አካል በውል የሚታወቅሓላፊነት የሚወስድዓላማውና ግቡ በግልፅ የሚታወቅተአማኝነት ያለው መሆኑን ሳይረጋገጥ እንዲሁ እገሌ እንዳለው ተብሎ ዜና ማለትስ የማን ንቀት ነው? ታማኝ ምንጮች እንደዘገቡት፣ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት፣ ሮይተር እንደዘገበው ማለቱ አይበቃም? አንድ በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ያለፈ ሰው ይቅር እንዲሁ ያደገውን የጋዜጠኝነትን መሰረታዊ ስልጠና የወሰደ ሰው ይህን መሰረታዊና አንኳር ስነ-ምግባር እንዴት ይስተዋል? በመረጃ የሚያምን ተብሎ የተነገረለት “የቃሊቲው መንግስት” የሚለውን መጽሐፍ የፃፈ ሰው ባለበት (መጽሐፉ ደርሶኝ እያነበብኩት ሰላለሁ ነው) እንዴት ነው እንዲህ ያለ ጉልህ የሆነ ስህተት የዜና ማሰራጫ ማእከሉ ሁነኛ መታወቂያ ሊሆን የሚችለው?
እንግዲህ በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ የኢሳት ባልደረቦች ለማህበሩ እየዋሉት ያሉትን ውለታና እያደረጉት ያሉት ቅምጥል ህጻን ልጅ የማባበል ያክልም እሽሩሩ ማለቱ “ማህበረ ቅዱሳን” መሞቴ አይቀር አጥፍቼ ልጥፋ በማለት ፀሐይ ሳለ በቀን የታወሩት አባላቶቹ አሰልፎ ሊፈጥረው የሚችለውን ግርግር ወደ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ሊያደርስ ይችላል ተብሎ ገና ለገና ከወዲህ ታምኖበትም እንደሆነ በዚህ አጋጣሚ ግምቱ ከቅዠት የማያልፍ ትልቅ ስህተት መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ። ማህበሩም እንደሆነ የሚይዘው የሚጨብጠው በማጣት የተቃዋሚዎች ደጋፊ ስለሆንኩ ነው፣ ለቤተ-ክርስቲያን ስለቆምኩ ነው፣ በዚህ ስለመጣሁና በዛም ስለወጣሁነው፣ የሚለውም አጥቶ ብረት ስለዋጥኩ ነው ቢል ከተዘረጋች የጽድቅ እጅ የሚያተርፈው አንዳች ሃይል የለም። አሜን!!
ቁርጣችንን እንወቅ። አይደለም የጥቂቶች ጩኸትና ሁካታ ስድስት ቢሊዮን ሕዝብ ሰልፍ ወጥቶ አይሆንም! ቢል የእግዚአብሔርን እጅ አይመለስም አይከለክልምም።  ታድያ በማወቅም ባለማወቅም ቢሆን በዚህ ሰልፍ መኸል የሚገባ ማንኛውም አካል ቢኖር በግብፅ ምድር የተገለጠውን መልአክ ሰለባ መሆኑን ሳይዘነጋ ያድርገው።
ለማጠቃለል ያክል የጸሐፍትና ፈሪሳውያን ገጽታ በከፊል ላውሳችሁ እወዳለሁ እነዚህ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ በነበረበት ዘመን በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ መፈራት፣ ተቀባይነት ያላቸውና የላቀ የክብር ስፍራም የሚሰጣቸው ሰዎች ሲሆኑ በተመሳሳይ ትልቅ ትምክህትም የነበራቸው ሰዎች ነበሩ። በጥቂቱ የተመለከትን እንደሆነ  ኢየሱስ የመጣበት ዓላማ በሚያከናውንበት/እውነቱን በሚያስተምርበት ወቅት የአይሁድ ስርዓትና ወግ፣ በሙሴ ሕገ ኦሪት ላይ ያነጣጠረ በአጠቃላይ ብሉያት መፃሕፍትን በተመለከተ ቃል ከአፉ ያወጣ እንደሆነ እኛ ጋር ሳይደርስ ሕዝቡ ራሱ እንደተራበ አውሬ ቦጫጭቆ ይገድለዋል፣ ይውጠዋል በማለት ይታበዩና የልብ ልብ ይሰማቸው ስለነበር በዋለበት እየተገኙ ኢየሱስን ለማሳጣትና በወጥመዳችው ውስጥም ለማስገባት  ያላደረጉት ጥረት አልነበረም።
በተጨማሪም የእነዚህ አፅራረ ፅድቅ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ትልቁ መታመኛቸው ሕዝብ እኛ ያልነው ይሰማል ከእኛ እውቅና ውጭ ምንም የሚፈጠር ተአምር የለም አይኖርም! የሚል ፈሊጥም ስለነበራቸው ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ደረታቸውን ገልብጠውና ምላሳቸውን አስረዝመው ለመዘባበት ተችሎአቸው እንደነበር ከቅዱሳት መፃህፍት ለመረዳት ይቻላል። ኢየሱስ ይህን እያወቀ በሕዝብ ፊት የተቃወማቸው እንደሆነ ግን ሊገጥመው የሚችለውን አደጋ ወደ ጆሮው ጠጋ በማለት ትሰማለህ ከእሳት ጋር አትጫወት! እንደማለት ይፎክሩበትም እንደነበር የታወቀ ነው። በተመሳሳይ “የማህበረ ቅዱሳን” ጉዳይም ሆነ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ጊዜያዊ አለመረጋጋት “ደጀ-ሰላም” በመባል የሚታወቀው ጋጠ ወጥ መካነ ድር ዋቢ በማድረግ እንዲሁ “ነጩን አጥቁረን ማሩንም አምርረን ሲፊ ጊዜም ሰጥተን ደግመን ደጋግመን ያሻን ብንዘግብ እስቲ በእኛ ላይ/በጣቢያው/ ላይ አፉን የሚከፍትም ሆነ ጣቱን የሚሰድ ማን ሱሪ የታጠቀ ወንድ ነው” በሚል አንድምታ ከሆነ በእውነቱ ነገር መጪው ሰፊ ጊዜ ሱሪ የታጠቀ ማን እንደሆነ ፍርዱ ለሕዝቡ የምንተው ይሆናል በማለት ለዛሬ ጽሑፌን በምስጋና ልቋጭ።
ከጽሑፉ እውነተኛነትና ቀጥተኛነት የተነሳ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ/በብዕር ስም በጹሑፉ አዘጋጅ ላይ ለሚሰነዘረው ማንኛውም ዓይነት የዓይን ቅንድብ ማነቃነቅ የማይቻለውን ዘለፋና መሰረተ ቢስ አሉባልታ ጨምሮ ደቀ- መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥምና ሊመጣ ያለውን ልክና ገደብ ያለው ሁሉ እንደ አመጣጡ በጸጋ እንደሚቀበሉ ሲገልፁ በአክብሮት ነው። በዚህና ተጓዳኝ በሆኑ ርእሰ ጉዳዮች ጸሀፊው በየትኛውም መድረክ ሃሳባቸውንና ተሞክሮአቸውን ለማካፈል ለሚቀርብላቸው ጥሪ ዝግጅነታቸውን እየገለጹ አስቀድመውም ለማመስገን ይወዳሉ።
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
United States of America

7 comments:

  1. wedaje kesedeb wechi yemtawekew yelem malet new.
    kezih yelek merejahen awtana enemeneh . betekekel
    metsaf kedus yemtaneb kehone bianes esti yerasehen tsehuf degemeh anebew.dekameh sayehon metefateh yaschenekegnale.

    ReplyDelete
  2. One of ESAT Journalist he looks like terrerist which called him self Abebe Gelawo he tried to attack Our Global Leader Prime minester Melese in G-8 MEETING. This indicates that esat is terror media including to mk dejselam web. stationed by USA soil. After his trial he was arrested by American police so that we now understood mk and ESAT are flop side of coin.

    ReplyDelete
  3. betam tiru meglecha newu Muluye, berta sayawquachew
    kehonem masawequ tiru newu. Getam, hone ewnetegna
    kere stiyanoch hulu kegoneh nenena. This is the time to know about mk(ye-Aden Genetu ebab) mehonun hulum endiyawq elalehu. Medehanialem kante gar newu.

    ReplyDelete
  4. Awde Mihiret sinodosu abeka malet new ?Mr Enkobahiry tenestewal Abba Hiruy Temelsewal yetebalew tikikil new ?Ahun Min Ajenda kere yibalal ?Abba Zelibanos -ABba Gebre wold _ Kesis ergete kal YEtebalut mahibere kidusan Abune Fanueiln asnestew endimetsu ke America bizu Genzeb tesebisibo Hedew neber lesinodosu kerbew Asiredu Malet New ? Ahun Abune Fanueil Tenestewal Yemil Were Tesemtal ewnet Newy ? zirzir Hasabun FEtsen BElu

    ReplyDelete
  5. mk.endenant eyedelem.enanet keseytan wegen setehon mk degmo ke.....b/c serachehu yegeltacheal.

    ReplyDelete
  6. ዛፍ ከፍሬው ይታወቃል መልካም ዛፍ መቸም ክፉ ፍሬ አያፈራም ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬ አያፈራም እንዲሁም መቸም ከሰይጣን ተከታዮች መልካም ነገር ሲመለከቱ አያስችላቸውም ስለዚህ ወንድሜ ላንተ 2ኛ የሚሰቀልልህ አምላክ የለምና ከጥፋትህትመለስ ዘንድ በጌታ ስም እለምንሃለሁ

    ReplyDelete
  7. የምህረት አምላክ ምህረት ይላክልህ

    ReplyDelete