Friday, May 11, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ አባ ሠረቀ ብርሃንና ዲ/ን በጋሻውንን የኃይማኖት ህጸጽ የለባቸውም ተሃድሶ መናፍቃንም አይደሉም አለ

Click here to read in PDF
በትናንትነው ዕለት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የጀመረው ከጥቅምቱ ስብሰባ ወደ ግንቦት የተዘዋወሩ ጉዳዮችንን በመመልከት ሲሆን የመጀመሪያ አጀንዳውም ሊቃውንት ጉባኤው “የሐይማኖት ህጸጽ” አለባቸው ተብለው ስለ ቀረቡ ወገኖች አጣርቶ የደረሰበትን እንዲያቀርብ ማድረግና ውሳኔ መስጠት ነበር። በዚህም መሰረት ማቅ ይወገዙ ይከሰሱልኝ ሲል ካቀረባቸው ሰዎች መካከል የአባ ሠረቀ ብርሃን እና የዲ/ን በጋሻው ጉዳይ ታይቶ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ይህ ውሳኔ ለማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ ውድቀት እንደሆነ ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ። 

አባ ሰረቀ በነበሩበት የሰንበት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊነት ሕግን ማስከበር ግዴታቸው ስለሆነ ማኅበሩ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ሊያሟላ የሚገባቸውንን መስፈርቶች አሟልቶ ሊፈጽም የሚገባቸውን ግዴታዎች ፈጽሞ በሕጋዊነት ይንቀሳቀስ ማለታቸው “የኑፋቄ መጨረሻ” ነው ብሎ ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳ በተለያየ መንገድ ሲዘራባቸው የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ አንገት ደፍቷል። ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ በኋላ የአባ ሰረቀ ክኅነት እንደተያዘ በማስመሰል አባላቱ አምደኞች በሆኑባቸው እና ድርጎ ቀማሽ በሆኑ ጋዜጦችና በብሎጎቹ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ሊቃውንት ጉባኤው በተሻለ ጥንቃቄ ነገሮችን ተመልክቶ የሚወራባቸው ወሬ ሁሉ ፍሬ ከርስኪ መሆኑን አሳይቷል። ይህ ውሳኔ ለአባ ሠረቀ ብርሃን ትልቅ ድል መሆኑም የሚታይ እውነት ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዲ/ን በጋሻውንን ከሚቃወምበትና መናፍቅ እያለ ስሙን ማጥፋት የጀመረበት ምክንያቶች ሦስት ሲሆኑ እነርሱም ከአቡነ ጳውሎስ ጋር መታረቁ፣ ማኅበሩን በስህተቶቹ አደባባይ ላይ መውቀሱ እና በካሴት ሽያጭ ደግሞ የአንበሳውን ድርሻ ወውሰዱ ናቸው።

ከአቡነ ጳውሎስ ጋር በታረቀ ጊዜ “ገዝግዘን ገዝግዘን ልንጥላቸው በነበረ ጊዜ ከእሳቸው ጋር ታርቆ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎቹን ለእሳቸው ያለው አስተያየት ወደ መልካም እንዲለወጥ አድርጓል። ይህም ለፓትርያርኩ ተጨማሪ ጥንካሬን ሰጥቷል። በማለት ገና የማጥላላት ዘመቻውን ከመጀመራቸው በፊት በንዴት ሲናገሩ የተሰሙት አንዳንድ የአመራር አባሎች ይህ ንግግራቸው በወቅቱ በቅርብ በሚያውቁዋቸው ሰዎች ዘንድ ለከፍተኛ ትዝብት ዳርጓቸው እንደነበር አይዘነጋም።

 ከዚህም ጋር ተያይዞ ማቅ ችግር በሚፈጥርባቸው ነገሮች ላይ መናገር መጀመሩ በማህበሩ በተሃድሶነት ለመወገዝ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንዳለው ደግሞ በጋሻው ማኅበሩን መንቀፉ “ተሀድሶ” ተብሎ የተነከሰበት ጥርስ እንዲጠብቅ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል። ዲ/ን ዳንኤል ባለፈው አመት በለቀቀው ጽሁፉ ስለ ዲ/ን በጋሻው እንዲህ ብሎ ነበር “ዲያቆን በጋሻው ማስተማር የጀመረው መቼ ነው? ማኅበሩ በነዲያቆን በጋሻው ላይ ሃሳብ ዛሬ መሠንዘር ለምን ጀመረ? በጋሻው ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም። በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ስለ ተናገረ ነው። ከዚህ በፊት ምንም ያልተናገረው ማኅበር ስሙ ሲነሳ ቤተክርስቲያን ተነካች ብሎ ተነሣ።” ይህ የዳንኤል ውስጥ አወቅ ጽሁፍ ማኅበሩ እንዴት ባለ ውድቀት ውስጥ እንዳለ እና እኔን የተቃመወና ስህተቴን የነገረኝ ሁሉ የቤተክርስቲያን ጠላት ተሃድሶ መናፍቅ ነው በሚል አባዜ እንደሚመራ ያሳየ እና የበጋሻው ችግር ሃይማኖታዊ አለመሆኑን ያሳወቀ ነበር። (በነገራችን ላይ ዲ/ን ዳንኤል ከማኅበሩ ጋር የገባው ውዝግብ በይቅርታ ሳይፈታ አንድ ሳምንት እንኳ ቢዘገይ ኖሮ በዘሪሁን ሙላቱ አማካኝነት ዕንቁ መጽሔት ላይ እንዲወጣ የተዘጋጀ ጽሁፍ ነበር። እርቁ የዘሪሁን ተሳዳቢ ብዕር ያጠቆረውን ወረቀት ማረፊያ አሳጥቶታል።)

 ከዚህ ጋር ተያይዞ ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ የዲ/ን በጋሻው የስብከት ሲዲዎች በከፍተኛ ቁጥር መሸጣቸው የማኅበሩን ሲዲዎች ከገበያ ውጭ በማድረጉ ማቅ በሚመራበት የቢዝነስ ሕግ ደግሞ “ተቀናቃኝህን እና ገበያ ላይ ፍርሀት የሆነብህን ሰው ማንኛውንም መንገድ ተጠቅመህ አስወግድ” የሚል በመሆኑ በጋሻውን ከገበያ ለማስወጣት  “ተሃድሶ መናፍቅ” የሚል ዘመቻውንን በተጠናከረ መንገድ ለመጀመር አስችሎታል። 

ማቅ በተለያየ መንገድ ሊያጠፋ ሚፈልገውን ሰው ሁሉ ህዝቡን በቀላሉ ለማሳመን በሚረዳው “ታድሰዋል  መንፍቀዋል” በሚል መንገድ ከሶ ስለሚያጠቃ ምንም እንኳ አባ ሠረቀ እና ዲ/ን በጋሻው ከእነርሱ ጋር ያልተግባቡበት መንገድ የተለያየ ቢሆንም የከሰሱዋቸው ግን በአንድ ስም “ተሀድሶ መናፍቅ” ብለው ነው።
የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ማኅበረ ቅዱሳን አካሄዱን እንዲፈትሽና እኔን ያልተቀበለ ሁሉ መናፍቅ ነው ከሚያሰኝ አባዜው በቶሎ ሳይመሽበት ነጻ እንዲወጣ አቅጣጫ ጠቋሚ መሆኑም ተመልክቷል።  

7 comments:

  1. If this is true, it will be one of the best things the Synod has done ever. Congrats for those who have been victims of organized attacks but finally the truth is revealed. God is always stands with truth...Take the previous temptation as enjoyable event...Wow for those who have been engulfed in false accusations and defamatory actions...God will ask them to pay the price...

    ReplyDelete
    Replies
    1. Begashaw beka yehone FENDATA new Enje ye-hamanot cheger yalebt ayemselghm gene Chirstan aymselm beka Doreye negre new

      Delete
  2. ሲኖዶሳችን መልካም ሥራ እየሠራ ነው። እናመሰግናለን ማቅ የቆጡ የባጡን ቢቀባጥር ማን ይሰመዋል፡ማቅ ጥሩ ነጋዴና ጎጠኛ ፖለቲካኛ ነው፡ ስውርና ለአባላቱ ሳይቀር ግልጽ ያልሆነ ሴራ ያለው ድርጅት ነው፡ የክርስትና ካባ ለብሶ በሃይማኖት ተሸብቦ ወስጣዊ መርዙን እሚረጭ ክፉ መንፈስ ነው። ቆሞስ አብ ሰረቀም ሆኑ ዲያቆን በጋሸው ድሮም መናፍቅ ሆነው አይደለም። ማቅን ሥርዓት ያዝ ስላሉት ብቻና በሕዝብ ፊት ያላቸውን አድናቆት ለመጣስ ነበር። አሁንም ማቅ ከዚህ ይማር ንስሐ ይግባ።

    ReplyDelete
  3. ቅዱስ ሲኖዶስ የአባቶቻችን ጉባኤ እጅግ እናመሰግናለን ማቅን በሀፍረት አከናንቦ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አባ ሰረቀንና ዲ/በጋሸውን ነጻ ናቸው ማለቱን ስሰማ ተደሰትኩ አውደ ምህረት ትዊተርንም እናመሰግናለን።

    ReplyDelete
  4. Awde Mihiret Kidus Sinodos Abba Serek & D Begashaw Menafi Ayidelum Ale bemalet 05 11 2012 zegebachihu Negeru Gena mehonun degimo zare zegebachihu yetun enmen ? Ahunim Teketatilachihu beyedekikaw yetewsenewn asawkun Sewm yemtazebew neger yinoral Mahibere Kidusan Sile waldiba yezegebachihutin Amitu Bilo Mr Enkobahiriy Tseyekeg bilo Kefitotal tenadwal Ahunim Selamaw Self lemewtsat yifelgal

    ReplyDelete
  5. senodos sayhon yeh yegezeabher tat new maheber kdusan ayhud ayelachew taot amelaki yekrestosen sem yemeyanesawen eyasadedu new yaleut. wongel gen ayetaserem agelagaun leyangelatu yechelau. geta ena yegetan sera yemeseru gen yasenefalu. Egeziabeher tewagi new semum Egezabeher new. segemere menafek malet betekiresteyan endasetemarechen beselasi sosetsenetena andenet yemayamin malet new enesugen sew yeseraw sereat aletekeberem belew sewen hulu menafek eyalu ye'egezabeheren heseb yametatalu. maheber kedusan yemibalut neseha kalegebu ena ye'eteyobeya betekreseteyan kaletefwosech bezu mekesefet gean bezehech hager yemetal. hesebum geta balemawek yesekayal. ye'kirestos sem setera ke'diyabilos yelek yemidenegetuten mahber kedesan nen bayoch geta yasebachew. lehesebum geta yeraralet. lesenodosemu eskemecheresashaw ke'ewenet ga endikomu geta yeredachew.
    yetemarek amelake abewen.

    ReplyDelete
  6. Betam Des Yilal Egziyabher Yimesgen Neger Ine Begil Abasereken Ahukachewalehu Betam Tiru sehu nache Yehu Deg le orthodox Tiru Amelekaket yalache nachehu GIN AHUDE MIRET YEMIBALEHU WEB SITE LEMINDINEHU MEHABEREKIDUSANIN METECHET YEMIFELIGEHU? Mahiber Kidusal Lebetekiristyanachin Betam Asfelagi Yehone Mahiber Nehu LOG LIVE for Mhberekidusan Alamachehu Yetsena be wore Sayihon besira Yebetekirstiyan Yekurt Lijoch Mehonachehun Yasmesekeru Mechem DIYABILOS AYITEGNAM ina Kidus Sira Yemiserutin Ketint Gemiro Ayihodim Diyabilos be tsom betselot Bemasoged Mehabiere Kidusan Yiketilal Diabilos Iyawora Yinoral Mahiberekidusan Iyetegadele Kidus Sirahun Yiketilal ABETU AMILAKACHIN WEY Le BETIH DEFAKENA YEMILUTN ABERTACHEHU TELATACHEHUN BEHIGRCHEHU SIR INDODK ADRGILIN AMEN

    ReplyDelete