Friday, May 11, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን አቡነ ጳውሎስን ከሥልጣን ለማውረድ ታጥቆ ተነስቷል

Click here to read in PDF
  • በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ስም ደብዳቤም አሰራጭቷል
ሰሞኑን እየገጠመው ካለው ችግርና ፓትርያርኩም በውሳኔዎች ላይ ቆራጥ እየሆኑ በመምጣታቸው የእሳቸው ስልጣን ላይ መቆየት ለህልውናዬ ያሰጋኛል ብሎ በማሰቡ ማኅበረ ቅዱሳን እሳቸውንን የማውረድ ዘመቻ ውስጥ ውስጡን ጀምሯል፡፡ በተለይም በጠ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ስም “የዳኛ ያለህ! ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዳኝነት ይታይላት” በሚል ርዕስ ያሰራጨው ጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የደረሰ ሲሆን ይህንኑ እንደ ግብአት ተጠቅመው አጀንዳ ለማስያዝና ቅዱስነታቸውንን የማውረድ ሴራ እንዲሸርቡ የተመከሩ ጳጳሳት እንዳሉ ይነገራል፡፡

ምንም እንኳ የጽሁፉ ምንጭ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ናቸው ቢባልም ጹሁፉ ግን ከማኅበረ ቅዱሳን እንደወጣ እና አብዛኛው የጠ/ቤተ ክህነት ሠራተኞችችም ጽሁፉ መጻፉን እንኳን እንደማያውቁ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ በጠ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ስም ካሰራጨው ጽሁፍ በተጨማሪ በቆዩትና አዳዲስ እየከፈታቸው ባሉ ብሎጎች ሀሳቡን እያንሸራሸረ የሚገኝ ሲሆን ይህም የታቀደው ተሳክቶ ፓትርያርኩ ቢነሱ ሕዝቡ ግር እንዳይለው ግንዛቤ መፍጠሪያ መንገድ መሆኑም ታውቋል፡፡

 በአንዳንድ ብሎጎችም ቅዱስነታቸውን “እናሸንፋቸውና // ሰላም ታግኝ” በማለት ይፋ የስልጣን ማፈናቀል ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ብሎጎቹ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ስም ከተጻፋ ደብዳቤ ጋር በይዘትም በቅርጽም ተመሳሳይ የሆነ ጽሁፍ የለቀቁ ሲሆን ልዩነቱ ብሎጎቹ ላይ ያለው ጽሁፍ በግል አስተያየት ስም የተጻፉ መሆናቸው ነው፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች ጽሁፉን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ጻፉት ከማለት አልፎ የት  ተሰባስበው እና ምን ተነጋግረው ለዚህ ውሳኔ እንደደረሱ ለማብራራት አልሞከሩም፡፡ ምክንያቱም ጽሁፉ መፃፉን በማያውቁ የቤተ ክህነት ሰራተኞች ስም የጻፈው ማቅ ነውና፡፡ በዚህ ደብዳቤና በሌሎች የቅስቀሳ መንገድም ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት አሳስቶና አነሳስቶ የሲኖዶሱን ጉባኤ የረብሻ መድረክ ለማድረግና በግርግሩም ፓትርያርኩን ለማንሳት የታሰበና የታቀደበት ሲሆን በብዙዎች ዘንድ የማቅ የሞት ሽረት ትግል የሚታይበት የሲኖዶስ ስብሰባ ነው እየተባለ ነው፡፡

2 comments:

  1. Melkam newa tadya. Minew yesachew shumet kelay aydelem ende? Tadya kelay kehone min aschenekachihu? Chuchewoch nachihu!

    ReplyDelete
  2. Abune Paulos is best leader in the church. Death to mk who is enemy of EOTC and Ethiopia. Abune Paulos have made great progress in the basic development of church which including to built school, college, clean water, Theological college and all others from zero intial. Before him our church was simpley the home of Neghtegna and Zergena. I wish him all the best and long live that including to our hero fathers Aune Fanuel, Abune Markos, Aba Serke, Megabe Hadis Begashawo and Aba Zelebanose.

    ReplyDelete