Tuesday, May 8, 2012

አባትነት በገንዘብና በፖለቲካ ሲፈተን

Click here to read in PDF
  • አቡነ አብርሃም በማቅ ተላላኪነታቸው ገፍተውበታል
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምእመናን ተለምኖ በተገኘ ገንዘብ የተገዛውን የዲ.. እና አካባቢው መንበረ ጵጵስና /ቤት እንዲያስረክቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወሰነ። ማኅበረ ቅዱሳን እያለ ራሱን በሚጠራው ድርጅት አቀንቃኝነታቸው የሚታወቁት ወጣቱ ጳጳስ አቡነ አብርሃም በአሜሪካ በተለያየ ስቴቶች በተካሄዱ ጉባዔያት አማካይነት ከምእመናን በተሰበሰበ የአሜሪካ ዶላር 265 000.00 የተገዛው መንበረ ጵጵስና በራሳቸው እና በወሮ. ሀረገወይን ስም ለምን ለማዛወር እንደፈለጉ ባይታወቅም መንበረ ጵጵስናው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ንብረት መሆኑ እየታወቀ አላስረክብም ማለታቸው በዘመናዊ አነጋገርየመርካቶ ቁጩዐይነት ቢሆንም የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት እንዲያውቁት ተደርጎ በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ከዚህ በታች አባሪ በሆነው ደብዳቤ መታዘዛቸውን ቤተ ክርስቲያን ገለጸች።


መቼም መስከራም ሳይጠባእንደሚባለው የዋሽንግተንና አካባቢዋ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስናውን በሥርዐት እንዲያስረክቡ በተደጋጋሚ ቢጽፍላቸውም አሻፈረኝ ብለው መንበረ ጵጵስናውን ለማኅበረ ቅዱሳን /ቤት (ደጀ ሰላምና አሃቲ ተዋህዶ ብሎግ ማዘጋጃ) አከራይተው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ታውቁዋል። አኒህ ጳጳስ እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ከመርካቶው ራጉኤል ቤተ ክርሰቲያን ባካበቱት (በዘረፉት ቢባልም ሥራቸው ነውና ራሳቸው ይፈሩ!) ገንዘብ ሲ.ኤም.. አጠገብ ፎቅ ቤታቸውን ሠርተው ሳያፍሩ ያስመረቁ ሲሆን፣ በቅርቡም በባንክ ሂሣብ የተጠራቀመውን ከዲ.ሲ ከወሰዱት የሀገረ ስብከቱ ገንዘብ እና አቶ አሥራት ከሚባል (የጎጃሙ ባለአውሊ) የተቸራቸውን ብር 400 000.00
በመጨመር ሁለት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ልዩ ላንድ ክሩዘር ገዝተው -መንፈሳዊ የሆኑ ተግባራትን እያከናወኑበት ይገኛሉ።

 ምንም እንኳ የህዝቡን ልብ ባያገኙትም መንበረ ጵጵስናውንን ርስት ጉለት አድርገን እንይዘዋለን ብለው የነበረው የማቅ አመራሮች ለእውነትና ለወንጌል የቆሙት አቡነ ፋኑኤል በቦታው መሾማቸው ከፍተኛ ነውጥ ያስነሳል በማለት ከፍተኛ የሆነ የሽብር ቅስቀሳ ቢያደርጉም ሀሳባቸውንን ተቀብሎ “የአጥፍቶ መጥፋት” እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ የሆነ ሰለፊ በአሜሪካ ባሉ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ምዕመናን ዘንድ ባለማግኘታቸው በቂ ሥራ አልሰራንምም ብለው ዶክትሬቱ አሜሪካን አገር ሲደርስ አፈር በላሰበትና የክብር “ቅስናው” ደግሞ አለአግባብ ሲዘባርቅ በተገፈፈበትና ከጎጋ ምዕመንነት ተነስቶ በአንድ ጊዜ በአቡነ አብርሃም ፈቃድ “የቤተክርስቲያንን አስተዳዳሪ በሆነው” ጨዋው አቶ መስፍን መሪነት ቤንዚን እንዳለቀበት መኪና ቢንተፋተፍምም ውጤት ሳያስገኝለት ቀርቶዋል።

ይህ የማቅና የአቡነ አብርሃም ሴራ በእግዚአብሔር ፈቃድና በምዕመኑ አስተዋይነት ከከሸፈ በኃላ የቅዱስ ሲኖዶስን ስልጣን ቸል በማለት የሀገረ ስብከቱን ጽህፈት ቤት አንመልስም ማህተምም አናስረክብምም በማለት ከአሜሪካ ርስተ ጉልታቸው ላለመነቀል በጥፍራቸውምም በጥርሳቸውምም እየቧጠጡ ይገኛሉ።
አቡነ አብርሃምም ህመማቸውንን አርፈው እንዳያስታምሙ ሰላማቸውንን የሚያቃውስ ስጋዊ ትግል እያደረጉ መሆናቸው በታዛቢዎች ዘንድ የተጠሩበትን መንፈሳዊ አደራ የዘነጉ አባት አስብሎዋቸዋል።

ያዳቆነ ሠይጣን ሳያቀስ አይለቅምእንደሚባለው አቡነ አብርሃም አዋሳን ትኩረታቸው በማድረግ ለመዛወር የድጋፍ ድምጽ እያሰባሰቡ ነው ይባላል። የአዋሳ ሕዝበ ክርስቲያን እምነቱን ለመዝባሪ አሳልፎ እንደማይሰጥ በተደጋጋሚ ያረጋገጠ ነውና ሙከራቸው ፋይዳ እንደማይኖረው ተስፋ እናደርጋለን፣ በሌላ በኩል ማኅበረ ቅዱሳን በአዋሳ የፈጠረውን ችግር እየታወቀ አባ አብርሃም በጥቅም ለቆሙለት ማኅበረ ቅዱሳን አዋሳ ላይ ርስቱን ሊያስመልሱለት ቃል የገቡ ይመስላል፣ ግንሞኞ ሆይገደሉን ሳታይእንደሚባለው በዚህ አካሄዳቸው ከማን ጋር እንደሚላተሙ አዙረው ማሰብ አልቻሉም ማለት ነው - ገንዘብ ያውራል ይባል የለ!

ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያንን ተጠልሎ ምእመናንን እየከፋፈለ የፖለቲካ መሣሪያ እስከማድረግ የሚያደርገው ተልእኮ እንዲቀጥል ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አቅርቤ አቡነ ፋኑኤልን አስነሳለሁ በማለት ገንዘብና ተወካይ ላኩልኝ ባሉት መሠረት ገንዘቡም መልእክተኞችም (ከአሜሪካ አባ ዘሊባኖስና አባ ገብረ ወልድ) መጥተው አባ አብርሃም ቤት በሰሞኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጳጳሳትን ለመከፋፈል በዱለታ ላይ ይገኛሉ፣ ለተቀደሰ አገልግሎት ሊውል የሚገባውን ገንዘብና ጊዜ ጳጳሳትን ለመደለል እያባከኑት የሚገኙት አባ አብርሃም ዲያብሎስን በመወከል የአድማ ምንጭ ሆነዋል። ምንም ቢሆን በቤተ ክርስቲያናችን የእምነት ትምህርትና ክህነት በገንዘብ አይሸጥም፣ ለአድማ ተግባርም አይውልም። አባ አብርሃም ግን የማኅበረ ቅዱሳንን የአድማ ተልዕኮ ለማጠናከርና የገንዘብ ምንጫቸው እንዳይደርቅባቸው፡ - አሜሪካ ከገቡ በኃላ እንደ ካንጋሮ እጅ አጥራ “በተማሩበት” ትምህርት አላሰራ ያለች ዲግሪያቸውን ጥለው ቤተክርስቲያን ጥላ ውስጥ ተወሽቀው በክብር “ክህነታቸው” ቤተክርስቲያንን የእንጀራ ገመዳቸው ያደረጉትንን  

  1. ዶር. መስፍን የሚባለውን ምእመን ለቴነሲ ኪዳነምህረት አለቃ፣
  2. ብርሃኑ ጎበና ለሜሪላንድና ፔንሲልቫንያ ኪዳነ ምህረት አለቃ፣
  3. ቀሲስ ያሬድ /መድኅን ለኦሃዮ ገብርኤል አለቃ፣
  4. አቶ በላቸው ወርቁ (ፓርላማ የነበረና ጥገኝነት ጠይቆ የሚኖር) ለኒውዮርክ ኪዳነ ምህረት አለቃ፣
  5. አቶ ገብረ ወልድ (ድሮ አባ የነበሩ ግን ከተለያዩ ሴቶች ልጆች ያፈሩ) ዳላስ አጠገብ ለሚገኘው ለቨርጂኒያ ራጉኤል አለቃ አድርገው በመሾም ከአባቶችዋ አንዱ ነኝ የሚሉዋትን ቤተ ክርስቲያናቸውን አዋርደዋል፤ ሀገረ ስብከቱንም የፖለቲካ መናቆሪያ አድርገዋል። ይኽ እንግዲህ መንግሥት ለረጅም ጊዜ በትእግስት ይዞት የነበረውን የሰለፊያንን ጉዳይ በሳቸው ሀገረ ስብከት እንዲጠናከር ሲያደርጉ የት ላይ ለመቆም ፈልገው እንደሆነ ከወዲሁ ሊታይና ሃይ ሊባሉ ይገባል።

እንግዲህ አባ አብርሃም ዋሽንግተን በቆዩበት ጊዜ የግል ሥራቸውን ሲያሳድዱ መደበኛ ሥራቸው የተጎዳ መሆኑ፣ አብያተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል ሙያው የሌላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሥልጣነ ክህነት እየሰጡ በመሾም ትርምሱን ለማጠናከር እንደሞከሩ ከአሠሪያቸው /ቤት በተጻፈላቸው ደብዳቤ ላይ ተጠቅሱዋል። ይች ቤተ ክርስቲያን እንደአባ አብርሃም ያሉ አባቶች የሚመሩዋት ከሆነ ከሀገርም አደጋ ነውና ቅዱስ ሲኖዶስም ምእመናንም ሊታገሉዋቸው ይገባል።

ቀደም ሲል ዳንኤል ክብረት “አቡነ አብርሃምንን እንደማውቃቸው” ብሎ በብሎጉ እስከ ዛሬ ድረስ ተስሎ የማያውቅ የስዕል ደብተር እስከ አሁን ድረስ ላልተፈጠሩት “አቡነ አብርሃም” ለሚባሉ ገጸ ባህሪ በመሳል በሕይወት ያሉት አቡነ አብርሃም ለማቅ የሰሩትን ውለታ “በውዳሴ” ለመመለስ መሞከሩ ይታወቃል።
ዳንኤልና አቡነ አብርሃም በተመሳሳይ ነውር የሚታወቁ ከመሆናቸው አንጻር እና አቡነ አብርሃም በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሾሙዋቸው ሰዎች የማቅ ክፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ለተገነዘበ ሰው ዳንኤል ለአባ አብርሃም ያቀረበላቸው “የውዳሴ” ገጸ በረከት “ሲያንሳቸው” ነው ያሰኛል።

 ጳጳሱ በምንኩስና ሕይወታቸው የሚታወቁበት በርካታ ነውር ጠገግ ሕይወት ስላላቸው ይህ እንዳይገለጥባቸው በማኅበረ ቅዱሳን እቅፍ ውስጥ መደበቅ አማራጭ የሌለው ጉዳይ አድርገው የወሰዱትና ለዚህም በታማኝነት መንቀሳቀስ ግዴታዬ ነው ብለው ቢያምኑም በአደባባይ የተሰራን ነውር ግን ከዚህ ብሎግ አዘጋጆች ጀምሮ በርካታ ሰዎች የሚያውቁት መሆኑን መገንዘብ አለመቻላቸው አሳዛኝና እርሳቸውንም አደጋ ላይ የሚጥል ነው። ሰሞኑን እንቅልፍ አጥተውና ከፍተኛ ገንዘብ እየረጩ እየደከሙበት ያለውን የማኅበረ ቅዱሳንን አጀንዳ ረቡዕ በሚጀመረው የሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ የማስፈጸም ትግል እሳቸውን እራሳቸውን የት ያደርሳቸው ይሆን የሚለው ጥያቄ በጉጉት ምላሽ የሚጠብቅ ሆኗል። ተንኮላቸውንን የአመጽ አካሄዳቸውንን ካላቆሙ በማኅብረ ቅዱሳን ጉያ ሊደብቁት የሚደክሙበትን ነውር በቅርቡ ይፋ መሆኑ እንደማይቀር ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።

እግዚአብሔር ለአባ አብርሃም ልብ እንዲሰጣቸው፣ ጤናቸውንም እንዲመልስላቸው እንጸልይላቸዋለን።

                               ከታዛቢ

12 comments:

  1. እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው!

    ReplyDelete
  2. Abune Abriham Wey Gud ? Minew / Ahuns yibekawtal Ke Ragueil gezeb Keaba Meshe Bekentu Genzeb-ke HIV Genzeb Ke America Genzeb -CMC menorya bet -Asko Menorya bet -Bete Kihinet Gibi Menorya bet Yibekal leman New Hulum yalfal tamami honewl Ke Abune Fanueil Gar yitareku Yetetsekesewn nibret Asirekibu Betesebiwotn beselam yasadigu neger mefelfel yikirbiwot yawardal

    ReplyDelete
  3. i think this man is a puppet. the real problem is mk. we need remove them from our church.

    ReplyDelete
  4. Abba Zelbanos -Aba Gebrewold- kesis ergete kal nachew Addis Abeba yemetsut melkam abatochi nachew abune fanueiln lemasnesat Abune Abirham tsertewachew new lecinodos yasredalu teblo yitsebekal American Hager letewekayochuna le Abune Abirham Kebad Genzeb tesebsiboal Ahunim Abune Fanueilm honu Abune Abirham Abune Gebreil Ayasfelgum Kesis Asteraye yetenagerut tikikil new

    ReplyDelete
  5. Ere zendros egzeo yemiyaseg new. Babatoch beza zrefiya. Egzeabher endet yeker lil new. betam yasaznal. Lzh hulu mekenyatoch ande ande memnanochem chmre selehonu liyasbubt yegebal.

    ReplyDelete
  6. budawoch wero beloch---

    ReplyDelete
  7. Ere mindin naw zendiro min inet seytan naw yegebaw kiritina mesedadeb hone malet naw?

    ReplyDelete
  8. we orthodox people know Abune Abreham !! Ende enante binasib enkuan Betekiristianachin ye hatiyatin dikam titagesalech !! Enkuan talakun abbatachinin tewu ena enante tehadisowochinim lebizu amet tagisalech ! Ye hayimanot hitsest yalebachewun tekluawoch ke betekiristian lematsidat sibal yefelegutin biyatefu minim anikawemim (Ersachewum ayadergutim enji).Le mezrefima ke abune paulos ena ke tehadisowoch belay man betekiristianachinin zerefena !!!

    ReplyDelete
  9. መጋረጃ ለመትከል፣ ዕቃ ለማሰናዳት ሲነሡ ጳጳስ መሆናቸው ትዝ አይላቸውም፡፡ አገልግሎቱ እንጂ፡፡የአቡነ አብርሃም ድፍረት ከአቋም ጋር ነው፡፡ አዲስ አበባ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጥተው እያለ በፓትርያርኩ እግድ የትም ቤተ ክርስቲያን እንዳያስቀድሱ፣ በኋላም ከሀገር እንዳይወጡ ብዙ ጫና ነበረባቸው፡፡ ከዚህም ሌላ እርሳቸው የሚያውቁት ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን «የፓትርያርኩን ስም ካልጠራችሁ ከእናንተ ጋር ኅብረት የለኝም» የሚለው አቋማቸው አልተቀየረም፡፡ ሲፋጅ በማንኪያ፣ ሲበርድ በእጅ እንደሚሉት እንዳንዳንዶቹ ጊዜ እና ሁኔታ አይተው ቢለዋወጡ ኖሮ ተለዋዋጮቹ ያገኙትን ሁለት ሀገረ ስብከት አያጡትም ነበር፡፡አቋም አቋም ነው፡፡ በችግሮች እና በሁኔታዎች አይለወጥም፡፡ አቋም የሌለው ሃይማኖት ሊኖረው አይችልም፡፡ ከአሥር አብያተ ክርስቲያናት በላይ በእናት ቤተ ክርስቲያን ስም እንዲጠቃለሉ ያደረጉት በዚህ አቋማቸው ነበር፡፡ «ከሕዝብ ከሚጣሉ ይህንን አቋምዎን ይተውት» ሲባሉ «ከእግዚአብሔር ከመጣላት ከሕዝብ መጣላት ይሻላል» ይሉ ነበር፡፡ በአሜሪካን ሀገር ታላላቅ ሥራዎች እየሠሩ የሚገኙ ሦስት ታላላቅ ማኅበራት አሉ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን፣ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና ማኅበረ በዓለ ወልድ፡፡ በተለይም የኋለኞቹ ሁለቱ በራሳቸው መዋቅር ነበር የሚጓዙት፡፡ እነዚህን ማኅበራት ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መሥመር ለማስገባት ከወጣቶቹ ጋር በመከራከር፣ በማሳመን እና አብረውም በመሥራት ያደረጉትን ተጋድሎ ሳስበው አቋም እና ሃይማኖት ያለው አባት ካገኘ ወጣቱ የት ሊደርስ እንደሚችል ይታወሰኛል፡፡በተገኘው አማራጭ ሁሉ እየተጓዙ በጉባኤያቸው ላይ ይገኛሉ፡፡ መሥመር ያልያዘ መስሎ በተሰማቸው ነገር ሁሉ ሃሳብ ይሰጣሉ፡፡ ጉባኤያቱ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ የመውጫ መንገድ ያመለክታሉ፡፡ ራሳቸውን እንደ አንድ ተሰብሳቢ ቆጥረው ይከራከራሉ፣ እንደ አባት ይመክራሉ፣ እንደ ወንድም ያበረታታሉ፡፡ትዝ ይለኛል የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ሲቋቋም እርሳቸው የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ዴንቨር ተደርጎ በነበረው የሰንበት ት/ቤቶች ጉባኤ ላይ የወጣቱ መንገድ ምን መሆን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ሁላችን እንፈራው የነበረውን አቋም ሠነዘሩ፡፡ ክርክር ተፈጠረ፡፡ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነው መጓዝ እንዳለባቸው በድፍረት ተከራከሩ፡፡ ከጉባኤው መልስ በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ቀስቃሽነት የተሰባሰቡ ወጣቶች የአቡነ አብርሃምን ሃሳብ ይዘው ተነሡ፡፡ በተለይም ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እያሉ ከፍተኛው ችግራቸው ማረፊያ ነበር፡፡ ይህ ነበር ወጣቶቹን ያንገበገባቸው፡፡ አባቶቻችን በልመና ቤት አያርፉም፡፡ መንበረ ጵጵስና ያስፈልጋቸዋል አሉ፡፡ ሌላም ችግር ነበር፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ እና በአካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የተሠራ ቤተ ክርስቲያን አልነበረም፡፡ በዚህም ምክንያት ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚቀድሱበት ቤተ መቅደስ አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹም ፖለቲካውን ፈርተው እንዳይመጡብን ብለው ወስነው ነበር፡፡ ይህንን የወጣቶች ሃሳብ ሲሰሙ አቡነ አብርሃም ከኒውዮርክ ወደ ዲሲ በአውቶቡስ መጡ፡፡ በወይዘሮ ሐረገ ወይን ቤት ከወጣቶቹ ጋር ውይይት አደረጉበት፡፡ መቼም ወጣት የያዘው ነገር ኃይል እንጂ አቋም ለማግኘት ጊዜ ይፈጅበታል፡፡ ወጣቶቹ በልዩ ልዩ ሃሳብ ሲላጉ ከኒውዮርክ በአውቶቡስ እየተመላለሱ መክረዋል፣ አስተምረዋል፣ አሠርተዋልም፡፡ ጉባኤያት በተደረጉ ቁጥር ሳይሰለቹ ይገኙ ነበር፡፡ በአንድ በኩል ከገለልተኞች፣ በሌላም በኩል ከስደተኞች፣ ሲብስ ደግሞ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ነን ከሚሉ ዘረኞች የደረሰባቸውን ጫና ሁሉ ተቋቁመው በስም ብቻ የነበረውን ሀገረ ስብከት በሕግ እንዲቋቋም፣ መንበረ ጵጵስና እና የመንበረ ጵጵስና ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረው አድርገዋል፡፡ከኒውዮርክ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመጡ በኋላ አናጺ ሆነው መንበር እየሠሩ፤ እንደ ልብስ ሰፊ መጋረጃ እያዘጋጁ፣ እንደ አካውንታት ሂሳብ እየሠሩ፣ እንደ ፕሮግራም መሪ ገንዘብ እንዲዋጣ እያደረጉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል፡፡ የአሜሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች ጳጳሳትን ሲፈትሹ ክብር በሚነካ ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን የፈታሾች ሥርዓት አልበኛነት ሊታገሡት ባለመቻላቸው የአንድ ቀን መንገድ ያህል በመኪና እየተጓዙ ነው አያሌ ሥራዎችን ያከናወኑት፡፡አቡነ አብርሃም ከዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ወደ ሐረር እንዲዛወሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢኖርበትም ዋናው ምክንያት ግን የአቋም ሰው መሆናቸው ነው፡፡ የአበው ሊቃነ ጳጳሳት በር ሲደበደብ እና፣ አቡነ ሳሙኤል ከሥርዓት ውጭ ሲታገዱ «ይህ ከሥርዓት ውጭ ነው መታረም አለበት» ብለዋል በድፍረት፡፡ ተሐድሶ የለም የሚል ደብዳቤ ከመንበረ ፓትርያርኩ ሲደርሳቸው «ተሐድሶማ አለ፤ በዓይናችንም አይተነዋል» ብለው ነው በአደባባይ የተናገሩት፡፡ ከሀገረ ስብከት በላይ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ሲቋቋም ከማንም ቀድመው ነው ስሕተት ነው ያሉት፡፡ በመጨረሻም «የሲኖዶሱን ውሳኔ ባልስማማበትም አክብሬ ወደ ታዘዝኩበት እሄዳለሁ» ያሉትም የአቋም ሰው በመሆናቸው ነው፡፡አሜሪካ አቡነ አብርሃምን አጣች እንጂ አቡነ አብርሃም አሜሪካን አያጧትም፡፡ ለአንድ ሐዋርያ ሀገሩ ሁሉም ነው፡፡ ምናልባትም ሰው ካልሄደ አይመሰገንምና ከእርሳቸው በኋላ የሚመጣው ሰው እርሳቸውን የሚያስመሰግን ይሆናል፡፡ «ትሻልን ሰድጄ.....» አይደል የሚባለው፡፡አሁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት ሊቀለበስ ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ከአቡነ አብርሃም ይልቅ ከባዱ ቀጣይ ዕዳ ያለው በሲኖዶሱ እጅ ነው፡፡ አቡነ አብርሃምማ ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደውም ሥራ ይሠራሉ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. ki ki ki ki ki sakubachu

      Delete
    2. ምነው ሀገረ ስብከቱን በራሳቸውና በወ/ሮ ሀረገ ወይን ስም ማስመዝገባቸውን አልተናገርክም?

      Delete
  10. ዶር. መስፍን የሚባለውን ምእመ, minew lelochu gentiles nachew malet new? Kahinus amagn adyidelem ende!

    ReplyDelete