Wednesday, May 2, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግርና የአንድ አድርገን ዘገባዎች

Click here to read in PDF
አንድ አድርገን የተባለው የማኅበረ ቅድሳን ብሎግ በማኅበሩ “ግልገል ካድሬዎች” የሚዘጋጅ  ብሎግ ነው። ማኅበርዋ በተለመደው እናንተ ባትኖሩ ቤተክርስቲያን ትጠፋለች የሚለው አታላይና ስሜት ቀስቃሽ “ወንጌሏ” ቀልባቸውን ሰልባ ለሥራ ያነሳሳቻቸው ሕጻናተ አእምሮ አባላትዋ የማኅበረ ቅዱሳን ስውሩም ግልጹም አመራሮች የሚያዙባትና እንቅስቃሴዋን በንቃት እየተከታተሉ ከማኅበሩ የመረጃ ክፍል የሚገኙ መረጃዎችን እንደ ወረደ በግልብ ስሜት ባልታረመ ብዕር ተጽፈው የሚቀርቡባት ስድ ብሎግ ስትሆን የአጻጻፍ ስልትዋና የቋንቋ አጠቃቀምዋ ከማህበሩ ሌሎች ብሎጎች ለየት ያለ ነው።

ጸሀፊዎቹ “ሕጻናት” ስለሆኑ በአፃፃፍ ስልታቸው በማስመሰል እንኳ ሊደብቁት የሚገባቸውን ከማኅበሩ ጋር ያለቸውን ግንኙነት ለመደበቅ አልተቻላቸውም። ሕጻን መች ይደብቃል። ለማህበራቸው ማኅበረ ቅዱሳን ያላቸው አመለካካት ከጭፍን ፍቅር የመነጨና በተለይ ማኅበሩ የተወቀሰ ዕለት እሳት እንደበዛበት ሽሮ በቶሎ የሚገነፍል ነው። 

ማኅበረ ቅዱሳን ከመንግስት ጋር ያለውን የአቋም ልዩነት እንደነ ደጀ ሰላምና ገብርሄር አጠይሞ ሣይሆን በግልጽ አቋሙን የሚያሳውቅበት አንድ አድርገን፣ በውስጣቸው ያለውን ፓለቲካዊ ማንነት በግልፅ እንዲታይ ጥረት የሚያደርጉበት አንድ አርገን፣ ከዚህ ማንነታቸው በመነሳትም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሕፃን በሆነው አእምሮአቸው ለመውቀስ ሞክረዋል ሲጀምሩም እንዲህ ነበር ያሉት። 

“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምክር ቤቱ አባላት በተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተው ነበር ፤ ስለ ሀይማኖት አክራሪነት ላይ በተነሳው ጥያቄ ላይ በተነሳ ጥያቄ ላይ ውሀቢዝምን ካስረዱ በኋላ አንዳንድ የዚህ አይዲዎሎጂ ተከታይ የሆኑ ሰዎችን ‹‹የማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ›› በማለት መስለዋቸዋል ፤ ይህ ምን ማለት ነው? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተረዱት ማህበረ ቅዱሳን የሀይማኖት አክራሪነት የሚያራምድ ማህበር አድርገው ነው የሚያስቡት ፤ ሰው ሀይማኖቱን ሲጠብቅ እንዴት አክራሪ ይባላል? ፤ ከአባቶች የተረከቡትን እምነታቸውን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ስራ ቢሰሩ እንዴት የሀይማኖት አክራሪዎች ሊባሉ ይችላሉ ? ፤ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የእውቀት ማነስ ከሌለብዎ በስተቀር ይህን ማለት ባልቻሉ ነበር ፤ እኔ በበኩሌ ወሀቢዝም የሚለውን አይዲዎሎጂ በመሰረቱ የገባዎት ራሱ አይመስለኝም ፤ አለማወቅ ሀጥያት አይደለም ነገር ግን አለማወቅን እንደ እውቀት ቆጥሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ በምክር ቤቱ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም ፤”

በመጀመሪያ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስረዱት ስለወሀቢዝም ሳይሆን ስለሠለፊያ ነው። የሠለፊያ አባላት በቅርብ እንኳ በግብጽ ምርጫ እንዳይወዳደሩ ታግደዋል። ቀጥተኛ አላማቸው በከፍተኛ የአክራሪነት ስሜት ተነሳስተው ሙስሊም ባልሆነ ሌላ ህዝብ ላይና በጠቅላላው በሙስሊሙም ማኅበረሰብ ላይ አምላክህን የምታገኘው እኛ ባልንህ መሰረት ነው። ከዚያ ውጭ ሌላው መንገድ ወደ ሞት ስለሚያደርስ እኛ ቀድመን እናስወገድህ የሚል አይነት ነው። ከዚህ አንፃር እስኪ ማህበረ ቅዱሳንን እንመዝነው።

ማኅበረ ቅዱሳን በጎንደር በደብረማርቆስና በደብረ ብርሃን በፕሮቴስታንቶች ላይ፣ በሐረር፣ በመቀሌ፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በጎንደር በአዋሳና በሌሎችም ከተሞች “ተሀድሶ” ብሎ በጠመዳቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ያደረሰውን የድብደባና የሕይወት ማጥፋት ወንጀሎች ለማስተባባል የመጣለትን የሚናገረውና ማመዛዘን የማይችለው ሕጻነ አእምሮው አንድ አድርገን አቅም ያለው አይመስለንም። ስለደብረ ብርሀኑ ዘግናኝ ወንጀል በተለይ ነጭ ለባሹ ማንያዘዋል በግልጽና በጀብደኝነት ስሜት ምን እንዳደረገ እዚያው ቢሮዋችሁ ሊነግራችሁ ይችላል። ጥያቄውን ከፈለጋችሁ ሥላሴ ኮሌጅ እንዴት ገባህ? ብላችሁ መጀመር ትችላላችሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበረ ቅዱሳንን አክራሪ ያሉት አንድ አድርገን እንዳለው ሃይማኖቱን ስለጠበቀ አይደለም። በሀይማኖትና በሃይማኖተኛነት ስም ሌሎችን ስለሚገድል ስለሚያሳድድና በግልጽ ኢትዮጵያን በመሰለ ግማሽ የሚሆነው ህዝብዋ ኦርቶዶክሳዊ ባልሆነባት አገር ስለመንግስታዊ ሀይማኖት አስፈላጊነት አጥብቆ ስለሚሰብክና ለዚህም እንደሚታገል ስለሚገልጽ ነው። ሀይማኖት ጠባቂነት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው በማስተማርና መኖር ነው እንጂ ሰይፍ መዞና ድንጋይ ጨብጦ “ጉዳዩ የክር ጉዳይ ነው ለሃይማኖቴ እገላለሁ” ማለት አይደለም። ይህ አክራሪነት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን “የጥምቀት ተመላሽ” የሚላቸውን ወጣቶች ያደራጃቸው ስለሃይማኖት  እንዲያሳድዱ፣ እንዲደበድቡና እንዲገድሉ እንጂ ከሱስ ተላቀው ህብረተሰቡን ከማወክ ነፃ ወጥተው እንደ መጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲኖሩ ለማድረግ አይደለም። ለነገሩ ከጥምቀት ሲመለሱ ሰክረውና “ጨርቅ ሆነው” ነው። ብዙ ወጣቶችን በከተራ እና በጥምቀት ዕለት እንዲህ ሆነው ማየት ተለመደ ነው። ይህም የማቅ ውጤት ነው። እርሱ የመለመላቸው ለአሸባሪ ተግባሩ እንጂ የእነርሱ ሕይወት በቃለ ወንጌል ተለውጦ ለራሳቸው መዳን እንዲሆንላቸው፣ ለቤተ ክርስቲያናቸውም ተስፋ እንዲሆኑ አይደለም። ስለዚህ እንደተሰበከላቸው አሸባሪነታቸውን በተክለ ሐይማኖት፣ በዑራኤል፣ በእግዚአብሄር አብና በሚካኤል በተግባር አስመስክረዋል።

ቢያንስ ዑራኤልና ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ያሉ የቤተክርስቲያን ልጆችን ለመደብደብ የሚሯሯጡት ልጆች ምንም አይነት መንፈሳዊነት የሌላቸው እና አሁንም ከሱስና ከነውር ስራዎች ያልተላቀቁ መሆናቸውን እናውቃለን። ማኅበረ ቅዱሳንም የሚፈልገው ሕይወታቸውን ሳይሆን ጉልበታቸውን ስለሆነ ልጆቹን እያስተማራቸው ያለው ቤተክርስቲያንን በጉልበታቸው እንዲጠብቁ እንጂ ሕይወታቸውን ለክርስቶስ እንዲሰጡ ስላልሆነ በልጆቹ ህይወት ምንም መንፈሳዊ ለውጥ ማየት አልተቻለም። ልጆቹም ሰው በደበደቡ ቁጥር ቤተክርስቲያንን ያገለገሉ እየመሰላቸው እየተደባደቡ ይኖራሉ። አንድ አድርገን ይህ ከቶ ምን ይሆን? የእናንተ አእምሮ እንደሚተረጉመው ከአባቶች የተቀበሉትን ሃይማኖት ለልጆች ማውረስ ትሉ ይሆናል እኮ?
ጠቅላይ ሚኒስትሩን የእውቀት ማነስ አለብዎት ሲል በድፍረት የተሳደበው አንድ አድርገን እውቀት እንዴት እንዳነሳቸው ያስረዳን ከእርስዎ በላይ አውቃለሁ በማለት ነው። ጉድጓድ ውስጥ ያለች እንቁራሪት የሰማዩ ስፋት በጉድጓዱ አፍ ልክ ይመስላታል!! አሉ። ይደንቃል! ምን እየፃፋችሁ እንደሆነ እንኳ ያልገባችሁ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን በእውቀት ማነስ መተቸታችሁ ያስገርማል። ለእናንተ ዕውቀት ማለት ያችው ማህበራችሁ በመቁኑን እየሰፈረች የምትሰጣችሁ “መረጃ” ነች። ለእናንተ እውነት ማለት ማህበራችሁ የሚያደርገውና እንደ በጎ ምግባር የሚያወራው ክፉ ሥራው ብቻ ነው። ዕውቀትን በተመለከተ እንኳን በእናንተ በተረት አባቶቻችሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዕውቀት አይታሙም። 

“ማህበሩን ለማያውቀው ሰው እንዲህ ነው ብሎ ለንግግር ማጣፈጫዎ መጠቀምዎ ተገቢ አይደለም ፤ ከበታችዎ ያሉት ሰዎች እውነቱን ሳይሆን መስማት የሚፈልጉትን ነገር ነው የሚግርዎት ፤ ከወራት በፊት ሳያስቡ የሚናገሩት አቦይ ስብሀት ‹‹ማህበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ ነው ›› በማለት ከአንድ የሀገር ሽማግሌ ሊጠበቅ የማይችል ንግግር በአደባባይ ተናገሩ ፤ እኔ በበኩሌ እርጅና ሊሆን ይችላል በማለት አልፌዋለሁ ፤ ሰው ሲያረጅ ወደ ህጻንነት ይመለሳል ይባላል ፤ ይህ ነገር እውነት መሆኑን የዛኔ ነው ያየሁት ? በዚህ አጋጣሚ ጭንቅላት ያለው ሁሉ አያስብም የሚል ጥቅስ በልጅነቴ አንብቤ ነበር  ፤ ለካንስ እውነት መሆኑ የገባኝ ዘንድሮ ነው ፤ ያኛው የትግል አጋርዎ በቅርቡ በውጭ ሚዲያ ሀገራችንን የማይመጥን አሳፋሪ ቃለ መጠይቅ ያደረገው አቶ ታምራት ላይኔ ፓትርያርክ ሸኝቶ ፓትርያርክ ሲያመጣልን ፤ አቦይ ስብሀት ደግሞ መደራጀቱ ያላማራቸው ማህበረ ቅዱሳን ላይ የቃላት ጦርነት ይከፍቱ ጀመር ፤ ቤተክርስትኒቷ ጌታ በወንጌል ‹‹ አይችሉሽም››ተብላለች ፡፡”

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለማህበሩ የተናገሩት ለንግግር ማጣፈጫነት አይደለም። የጽዋ ማህበራችሁ የመንግስትም የቤተክርስቲያንም ሸክምና ችግር ስለሆነ ነው እንጂ። ደግሞስ የትኛው ጨውነታቸሁ ነው ለንግግር ማጣፈጫነት እንድታገለግሉ የሚያደርጋችሁ? እናንተ እኮ ጣዕም የለሽ አልጫዎች ናችሁ። ከበታች ያሉ ሰዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እውነቱን ቢነግሯቸው ኖሮማ እስካሁንም ማህበሩ በትክክለኛ ቦታው ላይ ተቀምጦ በተገኘ ነበር። ይህንንም እሳቸው የተረዱት አልፈው በሚወጡ ነገሮች ነው። የእናንተ የአሸበሪነት ልክ እኮ ከደርብ በላይ ነው። ሞልቶ ከፈሰሰው ያወቁትን እውነት ነገሩን እንጂ እናንተማ እንድ ቀንም እንኳን እንድትኖሩ የማያሰነብት ግፍና የህዝብ ደም ያለባችሁ ናችሁ።
አቦይ ስብሀት “ማህበረ ቅዱሳን የቤተከህነት ዕዳ ነው” ብለው መናገራቸውን የማንነትህ መገለጫ የሆኑ ተራና ተልካሻ ቃላትን ተጠቅመህ ወቅሰሃቸዋል። እግረ መንገድህንም የስድብ ሊቅነትህን በጥቅስ ለማስደገፍ ሞክረሀል። እኛ በበኩላችን ከአቦይ ስብሀት ከሰማናቸው ቁም ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው ይህ ንግግራቸው ነው እንላለን። ማቅን ለመግለጥ ጥሩ ቃል ቸግሮን ነበር አሳቸውም “የቤተክህነት ዕዳ ነው” ብለው በዐጭር ቃል በሙላት ገልጸውታል። በዚህ እናመሰግናቸዋለን። ማቅ የቤተክህነት ዕዳ ለመሆኑ የሲኖዶስ ስብሰባ ሲደርስ የስብሰባውን አቅጣጫ ለማስቀየርና እርሱ በሚፈለግው መንገድ ለመንዳት አመራሮቹ የሚያደርጉትን ዕንቅልፍ አልባ ሩጫ በግልጥ ያስረዳል። 

አቦይ ስብሀትን ለመንካት ማህበረ ቅዱሳን “መደራጀቱ ያላማራቸው ማህበረ ቅዱሳን ላይ የቃላት ጦርነት ይከፍቱ ጀመር” ብለሀል። መደራጀት ለምን? የቤተክርስቲያን ልጆችን ለማሳደድ? ፓትርያርክን ለማውረድ? የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ? መልስ ይኖርህ ይሆን? አይመስለኝም። ይህንን የአቦይ ስብሃት ንግግር ለማርከስ በማሰብ ባለቤትና ማሰሪያ አንቀጽ ባልተስማማበት አረፍተ ነገርቤተክርስትኒቷ ጌታ በወንጌል ‹‹ አይችሉሽም›› ተብላለች ፡፡”ብለሀል። ችግራችሁ ይሄ ነው። በቤተክርስቲያንና በማህበራችሁ መካከል ያለውን ልዩነት አታውቁም ለእናንተ ቤተክርስቲያን ማለት 20 አመት ያልሞላው የጽዋ ማህበር ነው። ኦርቶዶክሳዊነት ማህበረ ቅዱሳን መሆን ነው። መናፍቅነትም ማህበሩን መቃወም ነው። ከዚህ ያለፈ አመለካከት የላችሁም። ይሄ ጠባብ አመለካከታችሁ ነው፣ ሰውን ያህል ክቡር ፍጡር እንኳ ለመግደል የሚያስጨክናችሁ። እንዲህ ያለው ሀሳብ ነው ሰለፊያ ያሰኛችሁ። ሰው ስታሳድዱ ክርስትናን የኖራችሁት ይመስላችኋል። ስትገድሉ የማህበራችሁን ህልውና ያስቀጠላችሁ ይመስላችኋል። ያደረባችሁ የአጋንንት መንፈስ የቤተክርስቲያንን ህልውና አሳጥቶ ማህበራችሁን ቤተክርስቲያንን አድርጎ ያሣያችኋል። በዚህ ማንነት ታውራችሁ ህዝቡን “ከኛ የተሻለ መሪ አታገኝም። አባቶችን አትስማ ቤተክርስቲያንን አትስማ። እኛን ብቻ ስማ” ትላላችሁ። ይህን አስተሳሰባችሁን መቃወም ክርስቲያናዊ ግዴታ ስለሆነ ዝም ልንላችሁ አልቻልንም። ልብ ካላችሁ ልብ በሉ። 

በማህበራችሁና በቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ልዩነት ተረዱ። ምን እንደሚያገናኛቸው እወቁ። ምን እንደሚለያቸውም ጠንቅቃችሁ ተረዱ። ለእናት ቤተክርስቲያን ቅድሚያ ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ ለእውነት ወገን የምትሆኑበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
                                                              ይቀጥላል

25 comments:

  1. እንዲህ ያለውን ማስተዋል ይባርክልን

    ReplyDelete
    Replies
    1. የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 12:9 ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።

      10 ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል። አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፥ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።

      11 እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።

      12 ስለዚህ፥ ሰማይና በውስጡ የምታድሩ ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፥ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።

      13 ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።

      የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ13:4 ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም። አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።

      5 ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።

      6 እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።

      7 ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።

      Delete
  2. በጣም ጥሩ የሆነ ጽሁፍ ነው። ሀሳባችሁን ብደግፈውም ባልደግፈውም አመክኖአችሁ የሚደንቅ ነው። የምትቃወሙትን ነገር እንዲህ በምክንያት ስትቃወሙ ጥሩ ነው። እኔ በበኩሌ አፃፃፋችሁ ደስ ብሎኝ ነው ያነበብኩት።

    ReplyDelete
  3. andeaderegen melse Yemesetet akem kalehe mokere eseti. aeme endelelehe ahun bedenb awkenal. down with mk.

    ReplyDelete
  4. you guy are such lier no one can believe you whatever you guys saying about MK. you guys just wasting your time no matter what the out come MK is not like you guy involved in their own interest. they are doing what is best for our church in many ways. look out what they have done for while you guys trying to manipulate our church for your interest. i hope you can post this comment

    ReplyDelete
  5. I dont belong to any party i am chrstian! Just to let you know, we dont need any analysis from anybody, i think we heared it wit our own ears when we were being compared! Yafe welemeta bekebe ayetashime yebale yele, maybe an appology might make it upto us! there is no better insults for chrstians than this! Such a shame you try to cover things up! God bless you and my you be helped to reflect only truth!

    ReplyDelete
  6. i read the article in andadergen but i didn't see it just like this. really good job. you open our eyes to see things in different angle.

    ReplyDelete
  7. You are edits and raven wolves on the closing of sheep. don't say we are orthodox. Don't mislead the people by saying we are orthodox say that we are Protestant and go to there.....
    damn you

    ReplyDelete
  8. AWIQENACHIHUAL tehadisowoch nachihu. long live for MK

    ReplyDelete
    Replies
    1. yetesafew eko yihew new. mk yemikaweme hulu lenantef tahadeso newe. maferiyawoche

      Delete
    2. yihe mahebre yeagnente mahebere newe hasabun yemigeltew kediyabilos gar new. metefiyawen yakerbew abo

      Delete
  9. useless article!

    ReplyDelete
  10. yehanen yasdibe afe kamane yetesate yehone?

    ReplyDelete
  11. አስቂኝ ነዉ::
    ማህበረ ቅዱሳንን በግድ ነፍሰ ገዳይ ማህበር ለማድረግ የተሞከረበት:: አልገባችሁም እንጂ አንባቢ እውነቱን ይመረምራል::የምትሉትን ሁሉ የሚሰማ የለም:: ማህበሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር አባላት አሉት
    ትኩስ ወይም በራድ የሆኑ በተለያዬ መስክ ቤተክርስቲያናቸዉን የሚያገለግሉ
    አንድ አድርገን ከነዚህ ዉስጥ ምን አልባት አንዱ ሊሆን ይችላል
    መናፍቃንንና አላዉያን ነገስታትን በቤተክርስቲያኑ ላይ ሲነሱ የሚቆጭና የበኩሉን ለማድረግ የሚጥር
    አንተ እንደምትለዉ ሳይሆን ቤተክርስቲያን አንድም ክርስቲያን ቢሆን ቤተክርስቲያን እንኩን ይህንን ያህል ክርስቲያኖች ያሉበት ማህበር
    አትሳሳት ማህበሩን መንካት ማለት የቤተክርስቲያን የሆነዉን መንካት ማለት ነዉ
    አትጠራጠር ደግሞ አንድ አድርገንን ስምን መላዕክት ያወጣዋል ይባላል እግዚአበሔር ዋጋዉን አያሳጣዉም

    ReplyDelete
    Replies
    1. ገኑን በድንጋይ ደብዳቢ፣
      እውር ፈረስ ጋላቢ፣
      ትልቅ ትንሹን ተሳዳቢ፣
      የዳቢሎስ አጃቢ፣
      ማቅ ማጂራት መችው ሰድቦ ለሰዳቢ፣
      ባለ ውቃቢ ነው ድቤ ደብዳቢ፣
      ባለጌ የእናቱን ቀሚስ ገላቢ::

      Delete
  12. Yidires Le Deje Selam Azegagoch ( D Efirem-D Alula-Kesis Yared Wzet...)Minew Deje Selamn Ke Esat radio -Esat radion Ke Dejes Selam magenaget min Yibalal?Min Gingunet Alachew ? Esat Radio sile Waldiba Zegebe malet Min malet new ?Esatm Deje Selam Yetebalew Blogg Sile Waldiba Zegebe eyalu magenaget lemin asfelege ?Ene Ye Mahibere Kidusan Abal neg Deje Selam melkam neger neberat ahun gin Zare ginguneta kepoletikega Gar kehone Nege Degimo Kemenafikan gar yitebaberal malet new ?
    Deje Selam yepoletikan neger lerasachew tewlachew- yehayimanot timihirt akirbu- lemenafikanu mels azegagu-tehadison asafiru Mahibere Kidusann Ashebar-Akirari yasbalew Deje Selam & Ahat Tewahedo & And adirgen -Gebir Her nachew yasblal yesewn sim eyanesu masadedi -ye chirchin Melkam neger alemasayet -yesewn Kibir menkat-
    Kahinatun Ato malet -Papasun mawared-sebakiwin zemariwn masaded lemehonu Dr Kesis Mesfin Kinetachew tagede tebale Gin Yikedsalu endet hone ?yeman kinet sihon new wigzet yemiseraw ?
    Aba Sereken -D Begashawn- Kesis Getachew Donn Ato yemalet mebtu yemanew ?

    ReplyDelete
  13. Hahahahahaha yedabilose melektegnoch awukenbachihual alamachihun befetsum ayisakalachihum menem enkuan memenu lemashber betemokerum ewuntw gen ewunte nate eshi mahaberun mesadeb yikren semunm meterateh deferet enedhon letawukew yigebahal chifen amerohen egziabeher yabraleh

    ReplyDelete
  14. Deje Selam 65.000 birr ke Waldiba Gedam tesereke bilo zegboal lemehonu waldiba gedam new enj bank bet nebere malet new ?yasazinal keawerahu ayiker bilo yamaymesil neger memezigeb yasafiral waldiba gedam new yeminorutim menagoch nachew genzeb yelachewm Ehilim aybelabetm Fetenaw keken wede ken alemakomu yigermal degimom mewashet leman yitsekmal 65.000 birr ketewsedem semonu yegesegesew keteme lihon yichlal 65.000 birr Mewesedun atsartachihu aswkun

    ReplyDelete
  15. እኔ ምለው የዐውደ ምህረት ብሎግ የተሀድሶ ነው? የሙስሊም ነው? የካቶሊክ ወይስ ከ1950ዎቹ በፊት የነበረ የህብረተሰብ ክፍል? ይገርማል እስቲ ይታያችሁ ለጠ/ሚ/ሩ መልስ ለምን ተሰጠ ብሎ እንዲህ መንጨርጨር የመሪዎችን ቃል እንደፈጣሪ ቃል መየትኮ በ1950ቹየነበረ አስተሳሰብ ነው ዎይም የካቶሊኮች ዶግማ ነው ምክንያቱም እነሱ የሮማው ፖፕ ፍጹም የማይሳሳት የክርስቶስ እንደራሴ ብለው ስለሚያምኑ ነው::

    ReplyDelete
  16. you are make very big mistake about MK because yopu do not about MK.

    ReplyDelete
  17. I used to be able to find good info from your articles.
    Have a look at my web blog - Takeielts.Com

    ReplyDelete
  18. Everything said was very reasonable. However, what about this?
    suppose you added a little content? I mean, I don't wish to tell you how to run your blog, however suppose you added something to possibly grab people's attention?

    I mean "የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግርና የአንድ አድርገን ዘገባዎች" is kinda plain.
    You might glance at Yahoo's home page and note how they create post headlines to get viewers interested. You might add a related video or a picture or two to grab people interested about what you've written.

    Just my opinion, it would bring your posts a little bit more interesting.
    Feel free to surf my weblog ; fastloans

    ReplyDelete
  19. I have been browsing on-line more than three hours lately, but I by no means discovered any fascinating
    article like yours. It's pretty value enough for me. In my view, if all web owners and bloggers made excellent content material as you probably did, the web shall be a lot more helpful than ever before.
    Here is my web site :: Http://goldentime.ru

    ReplyDelete
  20. Right here is the perfect site for anybody who wants to understand this topic.

    You understand so much its almost hard to argue
    with you (not that I personally will need to…HaHa).
    You certainly put a fresh spin on a topic that's been discussed for years. Wonderful stuff, just wonderful!
    Also visit my weblog : Instant Cash Loans

    ReplyDelete
  21. Good day I am so thrilled I found your website, I really found you by mistake, while I was looking on Digg for something else,
    Nonetheless I am here now and would just like to say cheers for a tremendous post
    and a all round interesting blog (I also love the theme/design), I don't have time to read it all at the minute but I have book-marked it and also included your RSS feeds, so when I have time I will be back to read a great deal more, Please do keep up the fantastic job.
    Also see my website > Aktivix.Org

    ReplyDelete